YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ባንክ የዘረፉት ተከሳሾች የ12 እና 13 አመት ፅኑ እስራት ተወሰነባቸው።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሪከርድ ያልቀረበበትና የቤተስብ አስተዳዳሪ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ በማህበራዊ አገልግሎት የሰጠ መሆኑን በቅጣት ማቅለያ በመያዝ 1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ከ6 ወር 2ኛ ተከሳሽ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በማለት ወስኗል፡፡

ዝርዝሩ👇👇👇


https://telegra.ph/BankRobing-12-05
ግብረሰዶም የፈጸመዉ ወጣት በ15 አመት ፅኑ በእስራት ተቀጣ ፡፡

ተከሳሽ ክብሮም ገ/ኪዳን የተባለ የ22 ዓመት ታዳጊ ወጣት ለአካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል በመፈጸሙ በዐቃቤ ህግ ተከሶ ክርክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ተከሰሹ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 631/1/ለ/ ሥር የተደነገገዉን ተላልፎ በታዳጊዉ ላይ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል፡፡ ወጣቱ ግንቦት 21 ቀን 2011ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12፡30 ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ሎቄ ምስራቅ ተብሎ ከሚጠራዉ ስፍራ የ 9 ዓመት ህፃን የሆነዉን የግል ተበዳይ ቤተሰቦቹ ዳቦ እንዲገዛ ሲልኩት ተከሳሹ ህጻኑን ዳቦ ቤት ዉስጥ አስገብቶ በመድፈር ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት የየካ ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ህግ በማስረጃ አረጋግጦ ክሱን መስርቶበታል፡፡ተከሳሹ ፈፅሞታል ተብሎ የተከሰሰበትን ዝርዝር ምክንያት በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ረዳት ኢንስፔክተር እቴነሽ ወዳጆ ተነቦለት የግል ተበዳዩን ህጻን በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ዳቦ ሊገዛ በመጣበት ጊዜና ቦታ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሜበታለሁ ፡፡ ጥፋተኛ ነኝ በፈጸምኩትም ወንጀል ጸጸት ተሰምቶኛል በማለት የእምነት ክህደት ቃሉን ለመርማሪ ፖሊስ ሰጥቷል፡፡ጉዳዩን የተከታተለዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽ ወንጀሉን ያመነ በመሆኑና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ተመልክቶ የጥፋተኝነት ብይንም ሰጥቷል፡፡በዚህም መሰረት ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ባስቻለዉ ችሎት ተከሳሹን በ15ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

Via Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa
በብልፅግና ፓርቲ ውህደት ተስማምተው ከፈረሙ ስምንቱ ፓርቲዎች መካከል እስካአሁን ለመክሰም ያመለከተው አንድ ፓርቲ ብቻ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡

ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል ከወሰኑት ሶስቱ የኢህአዴግ አባል እና አምስቱ እህት ድርጅቶች መካከል እስካአሁን ራሱን ማክሰሙን ለምርጫ ቦርድ ያስታወቀው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ብቻ መሆኑን የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል፡፡

ግንባር ለመፍጠር፣ለመዋሃድ ወይም ደግሞ ለመቀናጀት የሚደረጉ ስብሰባዎች ሲኖሩ ቦርዱ በመድረኮቹ ላይ እንዲገኝ ቢያንስ ከ30 (ሠላሳ) ቀናት በፊት ጥሪ ሊደርሰው እንደሚገባ አዲሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ይደነግጋል፡፡

ምርጫ ቦርድ ከእነዚህ ጉባኤዎች ውስጥ አራቱን እንደታደመ የህዝብ ግኝኙነት አመካሪዋ ያነሳሉ፡፡ሀገሪቷን ለ28 አመታት ሲመራ የነበረው ኢሕአዴግ ከስሞ የመዋሃዱ ነገር ከግንባሩ መስራች ህወሓትና ከመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ግልፅ ተቃውሞ እንደተነሳበት አይዘነጋም፡፡

ምንጭ:አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ግምታዊ ዋጋው ከ28,386,000 ብር በላይ የሚሆን #አደንዛዥ_ዕፅ_በቁጥጥር ስር ዋለ
ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ዕፁ የተያዘው በጉምሩክ ኢንተለጀንስ ሰራተኞች እና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች አማካኝነት በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ አለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ነዉ፡፡

እፁን ሲያዘዋዉሩ የተገኙት፡-

1ኛ. ኖምዛሞ ግላዲየስ ቦዛ ዜግነት ደቡብ አፍሪካዊት የፓስፖርት ቁጥር A08864208
መነሻዋ ከ ደቡብ አፍሪካ መዳረሻዋ ወደ ህንድ ደልሂ ስታዘዋውር ይዛ የተገኘችው 7.4
ኪግ ኮኬይን።

2ተኛ. አንቲቃ ሱለይማን ቂዚ አባሶባ ዜግነት አዘር ባጃን የፖስፖርት ቁጥር CO 2722082 ጠዋት ከሞስኮ አ/አ የመጣች እና ሆቴል አርፋ ተመልሳ ወደ ባንኮክ ልትወጣ ስትል 4 ኪግ ኮኬይን ይዛ በቁጥጥር ሰር ውላለች።

በዕለቱ በድምሩ 11.4 ኪ.ግ ኮኬይን ተያዟል።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስአበባ ነፃ የውሻ ክትባት እየተሰጠ ነው፡፡ክትባቱ ባለቤት አልባ ውሾችን ጨምሮ ለ19,000 ውሾች የሚዳረስ ሲሆን ከትናንት በስቲያ የተጀመረና እስከ ነገ አርብ ምሽት የሚቆይ ነው ተብሏል።

ምንጭ: ሸገር ኤፍ ኤም
@YeneTube @FikerAssefa
ህውኃት - መቐለ

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በመቐለ ከተማ ፌደራል ስርዓቱንና ህገ-መንግሥቱን መጠበቅ በሚል በተካሄደው የውይይት መድረክ ጥቂት የማይባሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጥሪውን ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ከእነዚህ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ነው፡፡ የፓርቲው የወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ አቶ አዲሱ ቡላላ ህውሐት ከዚህ በፊት የፌደራል ስርዓቱን በስርዓት ሲመራ ስላልነበር ዛሬ የፌደራል ስርዓቱ ተቆርቋሪ ነኝ ማለቱ የሚታመን አይደለም ይላሉ፡፡

በተመሳሳይ ጥሪውን ውድቅ ያደረገው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ነው፡፡ የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ቡላላ ደግሞ ከዚህ በፊት እኛን ሲያሳድድ ከነበረ ሃይል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን አይችልም ብለው ከመድረኩ ቀርተዋል፡፡

በትግራይ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጥሪው ስላልተደረገላቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡
በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የአረና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ጥሪ እንዳልተደረገላቸው ለቢቢሲ ሬድዮ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከትግራይ ክልል የተገኙት ሁለት ፓርቲዎች ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

ህውሐት የፌደራል ስርዓቱና የህገ-መንግሥቱ ጠባቂ ነኝ የሚለው ሌሎች ላይ ጫና ለማሳደር እንደሆነም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:- አሐዱ ሬዲዮ
@Yenetube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራት ክፍለ ከተሞች በ132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ሊገነቡ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ት አለም አሰፋ እንደገለጹት በከተማዋ የመናፈሻ ፓርኮች ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ ይገኛል፡፡በቅርቡም የከተማው ካቢኔ ከባለሃብቶች ጋር በመሆን የተሟላና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከሉ መዝናኛ ያላቸው ፓርኮች እንዲሰራባቸው መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህም የከተማዋን አረንጓዴነት ያጠናክራሉ የተባሉ እና ለነዋሪዎቿ የመዝናኛ አማራጭ ያሰፋሉ የተባሉ በአራት ክፍለ ከተሞች በሚገኑ 132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ግንባታ ለማካሄድ የመሬት ልየታ ስራ መሰራቱን ወ/ት አለም አሰፋ ተናግረዋል፡፡የሚገነቡት የመናፈሻ ፓርኮች በመንግስት እና ከግል አልሚዎች ጋር በትብብር የሚለሙ ሲሆን ለበርካታ ሴቶች እና ወጣች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ኮሚሽነሯ አስረድተዋል፡፡በተያያዘም በከተማዋ በክረምት ወራት ከተተከሉት ችግኞች መካከል ከ81 በመቶው በላይ መጽደቃቻን ኮሚሽነር ወ/ት አለም አሰፋ አስታውቀዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በክረምት ወራት እና በአረንጓዴ አሻራ ቀን ከ3.53 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ:የከተማ መስተዳድሩ ፕ/ሴ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ማለዳ የላዳ ታክሲ በመንገድ ፅዳት ላይ የነበረች የ40 ዓመት ሴት ገጭቶ መግደሉ ተሰማ፡፡

አደጋው የደረሰው በቦሌ ክፍለ ከተማ ደሳለኝ ሆቴል አካባቢ ማለዳ 12 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሰምተናል፡፡የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚዲያ ዘርፍ ሀላፊው ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለሸገር እንደተናገሩት በመንገድ ፅዳት ላይ እያለች በላዳ ታክሲ ተገጭታ ሕይወቷ ያለፈው ሴት የሁለት ልጆች እናት ናት ብለዋል፡፡የላዳ ታክሲው አሽከርካሪ የመኪናው የኋላ መስታወት ተሰብሮ እንደወጣና በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
"የኢንተርኔት መቋረጥ ዛሬ የተከሰተው በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረ ጥቃትን ለመከላከል በ INSA በተወሰደ እርምጃ ምክንያት ነው"--- የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ የነገሩኝ

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የዐረብ ፓርላማ በሕዳሴ ግድብ ላይ የያዘውን የተሳሳተ አቋም እንዲያስተካክል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አሳስበዋል። አዲስ ስታንዳርድ አየሁት ባለው ደብዳቤ፣ የዐረብ ፓርላማ በናይል ወንዝ አጠቃቀም ግብጽን ብቻ አሸናፊ ከሚያደርገው አቋሙ እንዲታቀብ አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ አሳስበዋል። የፓርላማው ውሳኔ የካርቱሙን የሦስትዮሽ የጋራ መርሆዎች ስምምነት ይጻረራል። በጥቅምት 30ው ውሳኔው የዐረብ ፓርላማ ግብጽ እና ሱዳን በወንዙ ውሃ ላይ ላላቸው ታሪካዊ እና ሕጋዊ መብት ጥብቅና እንደሚቆም መግለጹ ይታወሳል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ ችያለው ብሏ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፡፡

የፋይናንስ ተቋሞችን የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኔትወርኩን ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች ለማቋረጥ ተገድዶ እንደነበር የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ተመሳሳይ ችግሮችን ለማክሸፍ ኤጀንሲው ከኢትዮ ቴልኮም ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ ኢቲቪ ያነጋገራቸው የኢትዮ ቴሌኮም ኮምዩኒኬሽን ዋና ኦፊሰር ወይዘሮ ጨረር አክሊሉ የኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት የተቋረጠው በአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ኢንሳ በወሰደው እርምጃ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ኢንተርኔት የሚቋረጠው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በቅድሚያ እንዲያውቁት ከተደረገ በኋላ ቢሆንም ዛሬ የተቋረጠው የሀገር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር በማገጠሙ ነው ብለዋል፡፡ ለተፈጠረው የኢንተርኔት መቋረጥም ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል ብለዋል፡፡በኤጀንሲ ውስጥ ኢትዮ ሰርት የሚባል የፋይናንስ ተቋማትን ለ24 ሰዓት የሚከታተል እና አዲስ ጥቃቶች ሲቃጡ የመከላከል ተግባር ያለው ክፍል መኖሩን ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ክፍል ጥቃቱ ሳይደርስ መከላከል መቻሉን ኢንጅነር ወርቁ ተናግረዋል። ስራው ብዙ ጊዜ የተለመደውና የኔትወርክ ለውጥ የሚደረገው ብዙ ሰው ኢንተርኔት በማይጠቀምበት ሰአት ምሽት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ላይ የተፈጠረው አስቸኳይ ስለነበር ቀን ላይ እርምጃው መወሰዱን ተጠቁሟል፡፡ ጥቃቱ ከየት እንደተሰነዘረ ዝርዝር ጉዳዮችን እየተመለከቱ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ከተማና በዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች በቅርቡ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 156 ግለሰቦች ለሕግ መቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በግጭቱ ምክንያት የ43 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

ምንጭ:ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ኖቤል ሽልማትን ሲቀበሉ ጋዜጠኞች ጥያቄ የሚያቀርቡበት ፕሮግራም እንደማይኖር የኖቤል ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ ዐቢይ ፕሮግራሙ ላይ እንደማይቀርቡ ለኮሚቴው አሳውቀዋል- ብለዋል የኖርዌይ ዜና ምንጮች፡፡ ከሽልማቱ በኋላ ኖርዌያዊያን ሕጻናት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎችም ዝግጁ አይደሉም፡፡ የተሸላሚው አቋም ለአሠራሩ ችግር እንደፈጠረበት ኮሚቴው ገልጧል ተብሏል፡፡ የሽልማት ስነ ሥርዓቱ በመጭው ማክሰኞ በኖርዌይ ኦስሎ ይካሄዳል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድኃኒት ቅመማ አገልግሎት ጀመረ!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድኃኒት ቅመማ አገልግሎቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት ጥቅምት 25/2012 ዓ.ም በይፋ ጀምሯል፡፡ በፕሮግራሙ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሲሳይ ይፍሩ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡አቶ ያዕቆብ ሰማን ፣በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳሬክተር፣ የመድሀኒት ቅመማ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መጀመሩ የመድሀኒቶችን ሁኔታ በቅርብ ክትትል ለማጥናትና የመድሀኒት ግዥ ወጭን ለመቀነስ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየሠራ ለሚገኘው የመድሀኒት ቅመማ ከፍተኛ ክብርና እውቅና ከመስጠት ባለፈ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

-የዩንቨርስቲው ህ/ግ/ዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን የፊታችን ማክሰኞ ይቀበላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን የፊታችን ማክሰኞ በኖርዌይ ኦስሎ በመገኘት እንደሚቀበሉ ታውቋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነው ባለፈው መስከረም ወር መመረጣቸው ይታወሳል።ዶ/ር ዐቢይ በኖርዌይ ቆይታቸው በኖቤል መርሃ-ግብሩ ዋና ዋና ሁነቶች ላይ ብቻ እንደሚሳተፉ እና ሁሉን ለማዳረስ በአገር ቤት የሚጠብቋቸው አስቸኳይ ስራዎች እንደማይፈቅዱላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢለኔ ስዩም ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
ከትላንት ማምሻውን ጀምሮ የእርድ በሬዎች በተለመደው መጠን እየገባለት አለመሆኑን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለፀ፡፡

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃለፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል እንደገለፁት ከሆነ ድርጅቱ ከ700 በላይ የቁም ከብቶች የእርድ አገልግሎት ለመስጠት ቢዘጋጅም 200 የቁም ከብቶች ብቻ ወደ ድርጅቱ መምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡የእንስሳቱ ቁጥር የቀነሰበትን ምክንያት በቃል አልተነገረኝም ያሉት አቶ አታክልቲ ጉዳዩን ለማጣራት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሉካንዳ ቤቶች ማኅበር ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ እንደገለፁት የሉካንዳ ቤቶች አድማ አድርገዋል ስለተባለው ጉዳይ እንደማያውቁ ገልፀው ፤ በሉካንዳ ቤቶች ላይ መንግሥት እንዱከፍሉ ባስቀመጠው የገቢ ግብር ቅሬታ አድሮባቸው እንደነበር እና ቅሬታቸውንም ለተለያዩ ተቋማት ሲያቀርቡ መቆየታቸን አስታውቀዋል፡፡ነገር ግን በተቋማቱ አመርቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ ሉካንዳ ቤቶቹ ወደ አድማ ሳይገቡ እንዳልቀረ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በገብረ ጉራቻ ከተማ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አራት የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አባላት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ትናንት (ሃሙስ) ምሽት 2፡30 ገደማ በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገብረ ጉራቻ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ ደንደዓ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱ የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪ አካላትን ለመግደል ያለመ መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ የግድያ ሙከራው ኢላማ ከነበሩት መካከል የኩዩ ወረዳ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ሳጅን አዱኛ ደቀባ እና አብረዋቸው የነበሩ ሌላ የወረዳው ፖሊስ አባል እንደሚገኙበት አስተዳዳሪው ይናገራሉ።

ጥቃቱ የተፈጸመው የፖሊስ አባላቱ እራት በልተው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ እየገቡ ሳለ እንደነበር የሚናገሩት የኩዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ፤ በፖሊስ አባላቱ ላይ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ያስረዳሉ።"ዋና ሳጅን አዱኛ እግራቸውን ነው የተመቱት። አብሯቸው የነበረው የፖሊስ አባል ደግሞ እጁን ነው የተመታው" የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ የተኩስ ድምጽ ሰምተው ወደ በስፍራው የተገኙ ሌሎች ሁለት የቀበሌ ሚሊሻዎች ላይም ተኩስ ተከፍቶ ጉዳት ደርሶባቸዋል" በማለት ትናንት ምሽት በገብረ ጉራቻ ከተማ የተፈጠረውን ክስተት ያስረዳሉ። አቶ ደረጄ በአራቱም የጸጥታ አስከባሪ አካላት ላይ የደረሰው ጉዳት ለህይወት የሚያስጋ አለመሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ ሶስቱ እግራቸው ላይ አንዱ ደግሞ እጁ ላይ ጉዳት ማጋጠሙን አስረድተዋል።

"ሁለቱ በከተማችን በሚገኘው ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ለተጨማሪ ህክምና ወደ አዲስ አበባ ተልከዋል" ብለዋል። በኩዩ ወረዳ ጸጥታ አከባሪዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።የቀድሞ የወረዳው ፖሊስ ኃላፊ ጨምሮ ሁለት የፖሊስ አባላት ከወራት በፊት በታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።

በተጨማሪም በወረዳው ቆላማ ቀበሌ ውስጥ ሁለት የቀበሌ ሚሊሻዎች ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ተገድለው እንደነበር አስተዳዳሪው ያስታውሳሉ። የኩዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጉት "በቀድሞ የኦነግ ጦር ስር የነበሩ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን" ነው።ትናንት ጥቃት ያደረሱት ታጣቂዎች ተከታትሎ መያዝ አለመቻሉትን የተናገሩት አስተዳዳሪው ፖሊስ የግድያ ሙከራውን እየመረመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ኢትዮጵያን ለማዳን» በሚል ዓላማ ባንድ ያበሩ ኢትዮጵያዉያን ለስድስት ወራት በሚስጥር ያደረጉትን ዉይይት ባለፈዉ ሮብ አጠናቀቁ።በተከታታይ በተደረገዉ ዉይይት የምክር ቤት እንደራሴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የተለያዩ መስኮች ባለሙያዎች፣ ነጋዴዎችና የመብት ተሟጋቾች ባጠቃላይ 50 ሰዎች ተካፍለዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa