YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ለወንዶች!!!!
የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን
RJ FASHION
ለውድ ደንበኞቹ ጥራት ያላቸውን የወንዶች ብራንድ እና አዲስ Style
➡️ሹራቦች
➡️ጃኬቶች
➡️ቱታዎች
➡️ጫማዎችን
በቅናሽ ዋጋ አቅርበናል:
ሾው ሩም አድራሻ:
ገርጂ መብራት ሀይል (ዊዝደም ህንፃ ፊት ለፊት)
ስልክ:-+251900628132
:-011-6296465
የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለውን ሊነክ በመጫን ያገኙናል
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
1ሺህ 400 ቶን ዲዲቲ እና 20 ቶን ነባር የትራንስፎርመር ዘይት ከአገር ውጭ ለማስወገድ እየሰራ መሆኑን የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በሀገር ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘውንና የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ኬሚካል ለማስወገድ እስከ አምስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስወጣ ገልጿል።በኮሚሽኑ የደረቅና አደገኛ ቆሻሻ ህግ ተከባሪነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ገመቹ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ አገር ውስጥ የሚገቡትም ሆኑ አገር ውስጥ የሚመረቱ ኬሚካሎች በብዛት ተከማችተውና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው አልፎ ህጋዊ አስወጋጅ ተቋም ባለመኖሩ ሳይወገዱ ቆይተዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
እነ አቶ ልደቱ ምርጫ ቦርድን እንከሳለን አሉ!

ኢዴፓን በሃይል ተነጥቀናል ያሉት እነ አቶ ልደቱ አያሌው ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ መፍትሔ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ምርጫ ቦርድን በህግ ለመጠየቅ መዘጋጀቸውን አስታውቀዋል፡፡ከአንድ ወር በፊት የብሔራዊ ም/ቤት ስብሰባ አድርገው አዳዲስ አመራሮች መርጠው ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ህልውና እንዲያረጋግጥላቸው ጠይቀው የነበረ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ያስረዱት ፕሬዚዳንቱ አቶ አዳነ ታደሠ ቦርዱ ምንም አይነት ምላሽ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለምናቀርበው ጥያቄም ቦርዱም ዝምታን መርጧል ብለዋል፡፡“አሁንም ኢዴፓ በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ ጉልህ ሚና እንዳይጫወት ስውር ደባ እየፈፀመበት ነው የሚሉት አቶ አዳነ በፓርቲው ጉዳይ ቦርዱ ለመወሰን ለምን እንደተቸገረ አልገባንም ብለዋል፡፡

ችግሩ የተፈጠረው እንዴት ነው? ችግሩ ያለው ማን ጋር ነው? የሚሉትን ለይቶ ለማወቅ ሲባል አምስቱም የምርጫ ቦርድ አባላት በጋራ እንዲያነጋግሯቸው ህዳር 17/2012 በደብዳቤ መጠየቁንም አቶ አዳነ አስረድተዋል፡፡አምስቱም የቦርዱ አባላት ባሉበት ነው በኢዴፓ ጉዳይ ከእንግዲህ መወያየት የምንፈልገው ያሉት አቶ አዳነ ለዚህ ጥያቄያችን ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ በቀጥታ ቦርዱ ላይ በፍ/ቤት ክስ እንመሠርታለን ብለዋል፡፡“በዋናነነት በኢዜማ የተወሰዱ ጽ/ቤቶቻችን እንዲመለሱ፣ ማህተማችን እንዲመለስ የቦርዱ ውሣኔ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ አዳነ ቦርዱ በተደጋጋሚ ኢዴፓ አልፈረሰም የሚል መግለጫ መስጠቱንና ካልፈረሰ ለባለቤቶቹ መመለስ እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡ይህን አቤቱታቸውንም በተመሳሳይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በደብዳቤ ማቅረባቸውንም አቶ አዳነ ተናግረዋል፡፡

Via Addis Admas
@YeneTube @FikerAssefa
ብራዚል ተዋናይ ሌዎናርዶ ዲካፓሪዮ አማዞን ጫካ እንዲቃጠል አድርጓል ስትል ከሳለች!

የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ ተዋናይ ሌዎናርዶ ዲካፕሪዮ የአማዞን ጫካ እሣት እንዲለብስ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ሲሉ ወቀሱ።ፕሬዝደንቱ ተዋናይ ይህንን ስለማድረጉ ምንም ዓይነት ማስረጃ ባይሰጡም አማዞን ጫካ ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሲወቅሱ የመጀመሪያቸው አይደለም።ሰደድ እሣቱን ያስነሱት የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የፈለጉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ናቸው ያለው የብራዚል መንግሥት የጠረጠራቸውን በርካታ ሰዎች አሥሯል።ለአማዞን ጫካ መልሶ መቋቋም 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባው ሌዎናርዶ የፕሬዝደንቱን ወቀሳ አስተባብሏል።

አራት በጎ ፈቃደኛ የሰደድ እሣት ተከላካዮች በብራዚል መንግሥት መታሠራቸውን ተከትሎ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የቦልሶናሮ መንግሥትን እየወረፉ ይገኛሉ።ኢ-መንግሥታዊ ድርጅቶች እና የመብት ተሟጋቾች የብራዚል መንግሥት ድርጊት ፖለቲካዊና ተፈጥሮ ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችን ለመፈታተን ያሰበ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰማሉ።ባለፈው ነሐሴ የሰደድ እሣት ሰለባ የሆነው የብራዚሉ አማዞን ጫካ ጉዳይ ብዙዎችን ያስጨነቀ ሆኗል።

ፕሬዝደንቱ ባለፈው አርብ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ነው ወቀሳቸውን የሰነዘሩት። «ሌዎናርዶ ዲካፕሪዮ የሚሉት ሰውዬ ጥሩ ይመስላል አይደል? ገንዘብ ሰጥቶ አማዞንን የሚያነድ።» «እነዚህ ኤንጂኦ ተብየዎች ምንድነው የሚሠሩት? ጫካውን ያቃጥላሉ ከዚያ ፎቶ ያነሳሉ፤ ቪድዮ ይቀርፃሉ። ዎርልድ ዋይልድላይፍ ፈንድ [WWF] ለምሳሌ ከዲካፕሪዮ ጋር ነው የሚሠራው፤ እሱም 500 ሸህ ዶላር እርዳታ አድርጓል።በተፈጥሮ ጥበቃ ለተሰማሩ ድርጅቶች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው ዲካፕሪዮ፤ ምንም እንኳ አማዞን ጫካ ውስጥ የሚሠሩ ድርጅቶች እርዳታ ቢሹም እኔ እርዳታ አላደረግኩም ሲል ወቀሳውን አስተባብሏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን መካከል እንደ አዲስ የተጀመረው ድርድር ነገ ካይሮ ይካሄዳል።በድርድሩም የሶስቱ ሀገራት የውሃና መስኖ ልማት ሚንስትሮች እንደሚገኙ AAWSA የተባለው የግብፅ ሚዲያ ዘግቧል።ባለፈው ወር አሜሪካ ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ በአራት ዙር ድርድር ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል። የመጀመሪያው ዙር አዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን ይህ ሁለተኛው የድርድሩ አካል ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከወላይታ የሀገር ሽማግሌዎች እና የዞኑ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።ጠ/ሚው በማህበራዊ ሚድያ ገፃቸው ውይይቱ ፍሬያማ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሃጌ ጌኢንጎብ ማሸነፋቸው ተሰማ!!

የናሚቢያው ፕሬዚዳንት ሃጌ ጌኢንጎብ ረቡዕ ዕለት በተካሄደው ምርጫ በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ፕሬዚዳንቱ ምርጫውን ያሸነፉት 56.3 በመቶ ድምፅ በማግኘት ሲሆን የቅርብ ተፎካካሪያቸው ፓንዱሌኒ ኢቱላ 29.4 በመቶ ድምፅ ማግኘታቸው ተነግሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
የኢህአዴግ ውህደት የፊርማ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው!

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢህአዴግ እና ኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የስምንቱ ፖርቲዎች ሊቀመናብርት ተገኝተዋል። ሚንስትሮችም በእንግድነት ታድመዋል።

Via:-EBC
@Yenetube @Fikerassefa
😍ለጫማ አድናቂዎች😍
ለወንድም ለሴትም ሚሆኑ አዳዲስ ጫማዎችን እነሆ ብለናል::

💥ማስታወሻ:ተደራሽነታችን በአዲስ አበባ እንዲሁም ሁሉንም የክልል ከተምችን ያካትታል
🎯አድራሻ:-ገርጂ መብራት ሀይል ዊዝደም ህንፃ ፊት
ስልክ:-0900628132
0116296465
በቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉን👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
#አስደሳች ዜና ለሞባይል መለዋወጫ ሱቆች
በስክሪን ኘሮቴክተር መሰቃየት ቀረ
አንዴ ገዝተው እስከ ሁል ጊዜ ከጥሩ ትርፍ ጋር ለሁሉም አይነት ስልክ የሚያገለግል።

በ 12000 ብር ብቻ

አሁኑኑ በ 0911522626
0953120011

ይደውሉ። ወይም በ @natyendex መልእክት ያስቀምጡ።

For more @natcomputers
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የብልፅግና ፓርቲን የተቀላቀሉ ድርጅቶች የስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢህአዴግ እና ኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የስምንቱ ፖርቲዎች ሊቀመናብርት ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባረጉት ንግግር ብልጽግና በእውነት እና በእውቀት ላይ ተመስርቶ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሻግራታል ብለዋል።

@Yenetube @FikerAssefa
ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ #ጃዋር_መሀመድ ድጋፋቸውን እና #ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል።

ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ ጃዋር መሀመድ ድጋፋቸውን እና ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል። ጃዋር መሀመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች እና በአውሮፓ ሀገራት እየተዟዟረ ከደጋፊዎቹ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። ዛሬ በኑርንበርግ ከተማ ድጋፋቸውን ለመግለፅ አደባባይ የወጡት ኢትዮጵያውያን የኦነግን ጨምሮ የሌሎች ክልሎችን ባንዲራዎችም ይዘው ተስተውሏል።

ተቃውሟቸውን ለማሰማት የከተማዋ ባቡር ጣቢያ አካባቢ የወጡት ደግሞ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ያለውን ባንዲራ ይዘው ነበር። ተቃዋሚዎች በቅርቡ ጃዋር መሀመድ መንግሥት ጠባቂዎቼን ሊያነሳብኝ ነው የሚል መልዕክት ለደጋፊዎቹ ማስተላለፉን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሞቱ 86 ሰዎችም የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት አድርገዋል። ጃዋርም ለፍርድ ይቅረብ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ክልል የመሆን ጥያቄ ካቀረበው የዎላይታ ዞን ባለሥልጣናት እና የማህበረሰቡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቢ፤ የሰላም ምኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የሐይማኖት መሪዎች ጭምር ተገኝተዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር «ፍሬያማ ውይይት አድርገናል» ብለዋል።

በውይይቱ የተሳተፈው እና የላጋ የተባለው የዎላይታ ወጣቶች ማኅበራዊ ንቅናቄ መሥራቾች አንዱ የሆነ አሸናፊ ከበደ «ዎላይታ ራሱን ችሎ ክልል ከመሆን ሌሎች አማራጮች ይኖራሉ አይኖሩም? የሚሉ ጉዳዮች እና ሌሎች ተያያዥ አማራጭ የሆኑ ጉዳዮች ምንድናቸው? እዚያ ላይ እንወያይ» ማለታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል።

ተሳታፊዎች «የአስራ አምስት ሚሊዮን የዎላይታ ሕዝብ አቋም እና ፍላጎት ህገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት የዎላይታ ሕዝብ ራሱን ችሎ በራሱ ክልል የመሆን አማራጭ ተወዳዳሪ እና አቻ የለውም» የሚል ምላሽ ለጠቅላይ ምኒስትሩ እንደሰጡ አሸናፊለዶይቼ ቬለ አስረድቷል።

የዎላይታ ዞን ክልል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ በመጪው ታኅሳስ አስር ቀን አንድ አመት ይሞላዋል። ለጥያቄው መልስ ለማግኘት ከታኅሳስ አስር በፊት የሕዝበ ውሳኔ የሚካሔድበት ቀን እንዲታወቅ እንደሚፈልጉ አሸናፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል።

የዎላይታ ዞን የዴሞክራሲ ተቋማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የኮምዩንኬሽን ኃላፊ አቶ አለማየሁ አፈወርቅ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም በይፋ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት አሁንም ግፊት እየተደረገ ነው።

የደቡብ ክልል ምክር ቤቱ የዎላይታ ዞን ያቀረበውን ጥያቄ ለመመለስ «መወሰን የማይችል ከሆነ አመት ከሞላ በኋላ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሔዶ አንዳንድ ሥራዎችን ለመስራት በዞኑ ምክር ቤት እንደ ይግባኝ የተዋቀረ ኮሚቴ አለ።

ከዚያ በዘለለ ማሟላት ያለበትን አሟልቶ ነው የሔደው። አሁን ደግሞ ደኢሕዴን ወደ ብልፅግና ፓርቲ ተቀላቅለናል። በጠቅላላ ጉባኤ ተወስኗል። ብልፅግና እንደ ሀገር አንድን ብሔረሰብ መወከል የሚችል፤ ማሳተፍ የሚችል ነው ብለን እናምናለን።

የዎላይታም ጥያቄ በብልፅግና የማይመለስበት ምክንያት የለም ብለን እናምናለን» ሲሉ አቶ አለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የብልፅግና ፓርቲ ስምምነቱን የፈፀሙ ድርጅቶች ሊቀ መናብርት ፊርማ።
@Yenetube @Fikerassefa
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ላይን በመጪው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ያቀናሉ። ከርዕሰ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋሳቂ ማኅማት ይገናኛሉ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው!

በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ ኤችአይቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ገለፀ።ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራና ቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በኤችአይቪ ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።


https://telegra.ph/AIDS-12-02
በሲዳማ ክልል የፓርቲው ቅርንጫፍ እንደሚከፈት አስታወቁ የዞኑ አስተዳዳሪ ገለፁ።

የብልጽግና ፓርቲ እየተበራከቱ የመጡ የህዝብ ፍላጎቶችን መመለስ በሚያስፈልግበት ወቅት የተወለደ ፓርቲ መሆኑን የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ፡፡ የሲዳማ የክልልነት ሂደት ሲጠናቀቅም በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እንደሚከፈት አስታውቀዋል፡፡ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ የህዝብ ፍላጎቶች ታይተዋል፤ ጥያቄዎችም ተነስተዋል፡፡ ይህን ሊመልስ የሚችል ቁመና ያለው ፓርቲ አስፈላጊ እንደመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ ወቅቱ የፈጠረው ፓርቲ መሆኑ እሙን ነው፡፡የብልጽግና ፓርቲን በመመስረት ሂደትም የሲዳማ ተወላጅ የደኢህዴን አባላት ተሳታፊና የውሳኔው አካል እንደመሆናቸው የሲዳማ የክልልነት ሂደት ሲጠናቀቅ በፓርቲው ሕገ ደንብ መሰረት የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በክልሉ ይኖራል፡፡

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
Center for Advancement of Rights and Democracy(CARD) አሳሳቢ የጥላቻ ገለጻዎች በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በቅርቡ ጀዋር መሃመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከደጋፊዎቹ ጋር ውይይት ሊያደርግ ባቀናባቸው ከተሞች መንፀባረቁን ታዝቦ ይህንን መግለጫ (መልዕክት) አስተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa