YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ የሚያስችለውን ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ። የንቅናቄው ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳስታወቁት ንቅናቄው የውህደት ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይና ልዩ ጠቅላላ ጉባኤው ነው። ጉባኤው ውህደቱን ለመቀላቀል የሚያስችለውን ውሳኔ ያሳለፈው በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም፣ በህገ ደንብ እና መመሪያ ላይ ከጉባኤው አባላት ጋር ከተወያየ በኋላ መሆኑን አቶ ሞገስ ጨምረው ገልጸዋል።

Via:- DW
@Yenetube @FikerAssefa
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ትምህርት ለ15 ቀናት እንዲቋረጥ መወሰኑ ተሰማ፡፡

ከሰሞኑ አለመረጋጋት ተከስቶባቸው ከነበሩት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሆነው ዩኒቨርሲቲው ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ተማሪዎች በተለያዩ ውይይቶች ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይ መክሮ ነው ተብሏል፡፡በዚህም ከኅዳር 17/2012 ጀምሮ ለ15 ቀናት ማስተማሩን በማቋረጥ በ15ቱ ቀናት ዩኒቨርሲቲው መፈታት አለባቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ችግሮች እንዲፈታ ሴኔቱ ውሳኔ ማሳለፉን አሐዱ ቴሌቪዥን ያገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴርም ይህንኑ ለአሐዱ አረጋጧል፡፡በ15ቱ ቀናት ውስጥ በግቢው ለሚቆዩት ተማሪዎች የምግብና መኝታ አገልግሎት እንደማይቋረጥ በመጠቆም፤ ለ15 ቀናት ተማሪዎች በፈቃዳቸው ከዩኒቨርሲቲው ለእረፍት መሄድ ከፈለጉ ቅፅ ሞልተው መውጣት እንደሚችሉም ተወስኗል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለተኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ህዳር 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም አስቻለው እንደገለጹት ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሂዳል፡፡የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በሁሉም ተቋማት የእቅድ ግምገማ አድርገው ጥንካሬ እና ድክመታቸውን በእቅዳቸው ሊሰሩ የሚችሉ ግቦች ላይ ተፈራርመው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡በዚህም መሰረት በ41 ተቋማት ላይ የሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ለተቋማቱ ደረጃ ሰጥቷል፡፡በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ ከነገ ከህዳር 19-20 ቀን 2012 ዓ.ም በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ተደጋጋሚ የህዝብ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን አራት ተቋማት ትምህርት ቢሮ ፣ቤቶች እና ኮንስራክሽን ቢሮ ፤የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ እንደሚያቀርቡ አቶ አዲስአለም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ: የከተማ መስተዳድሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
#አስደሳች ዜና ለሞባይል መለዋወጫ ሱቆች
በስክሪን ኘሮቴክተር መሰቃየት ቀረ
አንዴ ገዝተው እስከ ሁል ጊዜ ከጥሩ ትርፍ ጋር ለሁሉም አይነት ስልክ የሚያገለግል።

በ 12000 ብር ብቻ

አሁኑኑ በ 0911522626
0953120011

ይደውሉ። ወይም በ @natyendex መልእክት ያስቀምጡ።

For more @natcomputers
Forwarded from YeneTube
ለወንዶች!!!!
የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን
RJ FASHION
ለውድ ደንበኞቹ ጥራት ያላቸውን የወንዶች ብራንድ እና አዲስ Style
➡️ሹራቦች
➡️ጃኬቶች
➡️ቱታዎች
➡️ጫማዎችን
በቅናሽ ዋጋ አቅርበናል:
ሾው ሩም አድራሻ:
ገርጂ መብራት ሀይል (ዊዝደም ህንፃ ፊት ለፊት)
ስልክ:-+251900628132
:-011-6296465
የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለውን ሊነክ በመጫን ያገኙናል
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
🎊አስደሳች ዜና 🎊
📲በ 09 13 29 17 35 ይደውሉ
👉🏾ቢንቢ እና በረሮ አላስተኛ ብሎዎታል
የህፃን ልጅዎን ሰውነት እያበላሸ አስጨንቆዎታል?
👉🏾ሰላም የሚሰጡ እና መኝታ ክፍልዎን ውበት የሚያላብሱ የአልጋ መጋረጃዎች አስመጥተናል የሰላም እንቅልፍ ይተኙ::
👉🏾ለመኖርያ ቤት, ለሆቴሎች,ለገሰት ሀዉስ በብዛት ለሚወስዱ በቅናሽ እናቀርባለን።
👉🏽ለነብሰ ጡር, ለአራስ እና ቢንቢ/ዝንብ/ትንኝ ለሚበዛበት አካባቢ የመጀመርያ ምርጫዎ!!!
👉🏽ግድግዳውን ሳይበሱ መሬቱን ሳይቆፍሩ በራሱ መቆም የሚችል ነው
👉🏽ቢቆሽሽ አውርዶ ማጠብ የሚቻል
🏢 ወኪሎች
✔️መቀሌ
✔️ባህርዳር
✔️ጅማ
✔️ድሬዳዋ
✔️ሃረር
✔️ጂጂጋ
👍🏼 አዲስ ኣበባ :- ቦሌ መዳንያሃለም ከሽገር ህንፃ ፊት ለፊት
ሱቃችን ከእሁድ እስከ እሁድ ክፋት ነዉ
🚚 አሁኑኑ ይደውሉልን ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን::
ዋጋ-3800ብር
📲 በ 0913291735 ይደውሉልን🛒
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለ6 ግለሰቦች የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ

በዚህም መሰረት፡-

1. አቶ ፍቃዱ ተሰማ ፡-የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ

2. አቶ አዲሱ አረጋ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የማህበራዊ ሴክትር አስተባባሪ

3. ወ/ር ጫልቱ ሳኒ የበምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የኢኮኖሚ ሴክተር አስተባባሪ

4. አቶ ካሳሁን ጎፌ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ሀላፊ

5. አቶ ሳዳት ነሻ በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ሀላፊ

6. አቶ አበራ ወርቁ በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል።

ምንጭ:OBN
@YeneTube @FikerAssefa
86 ሺ 9መቶ ሀሰተኛ ገንዘብ ወደ ባንክ ለማስገባት የሞከሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሳት ወረዳ ኦሎንጭቲ ከተማ 86 ሺህ 9 መቶ ባለ መቶ ኖት ሐሰተኛ ገንዘብ (forged) ወደ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለማስገባት ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገለጸ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሁለት ሆነዉ ሐሰተኛ ገንዘቡን ወደ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለማስገባት ስሉ ህብረተሰቡ ለአካባቢዉ ፖሊስ ባደረሰዉ ጥቆማ ከሐሰተኛ ገንዘቡ ጋር መያዛቸዉን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር አስቻለዉ አለሙ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ሁለቱንም ግለሰቦች በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያካሄደባቸዉ መሆኑን በመግለፅ በአቋራጭ ለመበልፀግ ከምንቀሳቀሱ ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ህብረተሰቡ መጠንቀቅ አለበት ብለዋል፡፡ህገ ወጥ ገንዘብ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ለመከላከል ሁሉም አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ አለበት ስሉም ኮማንደር አስቻለዉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

Via ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን/Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
የ2012 የወንዶች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር የውድድር ፕሮግራሞችን በስፓርት ቻናላችን ላይ ለቀናል። @Yenesport ላይ ሙሉውን መመልከት ይችላሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
(ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው መማክርት ጉባኤ (Senate) የተላለፉ ውሳኔዎች)

እንደሚታወቀው በዩኒቨርሲቲያችን በደረሰው የፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ተቋርጦ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
የዩኒቨርሲቲያችን መማክርት ጉባኤ (senate) ሀዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ተማሪዎች ዓርብ ህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ትምህርት ገበታቸው በመመለስ ትምህርት እንዲጀምሩ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች የመማር ማስተማር ሥራ የተጀመረ ቢሆንም አሁንም እስከ ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2012 በትምህርት ገበታቸው ላይ ያልተገኙ ተማሪዎች መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንንም በመረዳት የዩኒቨርሲቲው መማክርት ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም በድጋሚ ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን ዉሳኔዎች ወስኗል፡፡

- በአሁኑ ጊዜ የዩኒቨርሲቲዉን ሰላም ለማስጠበቅ ከዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ፤ ከድሬዳዋ አስተዳደር፤ አካባቢዉ ማህበረሰብ ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እየተሰራ ያለዉ አመርቂ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡፡


ተጨማሪ⬇️
https://telegra.ph/Yenetube-11-29
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ተበተነ!

ፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ከምርጫ ቦርድ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ውይይት በተፈጠረ አለመግባባት ተበተነ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የስነምግባር አዋጅ መፅደቁ ይታወሳል። የፀደቀው አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ለማድረግ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ቢሰባሰቡም መግባባት ላይ ባለመድረሳቸው ውይይቱ ተበትኗል።

Via:- አሐዱ ሬድዮ
@Yenetube @FikerAssefa
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎት በእነ ክንፈ ዳኝው የክስ መዝገብ ላይ እንዲከራከሩ ብይን ሰጠ፡፡

በነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኝው የክስ መዝገብ በአዳማ እርሻ ኢንጅነሪነግ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከትራክተሮችና የትራክተር አካላት ግዥ ጋር በተያያዘ በፈጸሙት የሙስና ወንጀል የቀረቡባቸውን 7 ክሶች እንዲከላከሉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጠ፡፡ተከሳሾች በብረታብረትና ኢንጅነሪነግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) ስር የሚገኘውን የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንጅነሪነግ ኢንዱስትሪ፤ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ትራክተርና የትራክተር አካላት ግዥ ሲፈጽሙ በህግና በተቋሙ የግዥ መመሪያ መሰረት መፈጸም ሲገባቸው፤ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ከህጋዊ አሰራር ውጭ ከተለያዩ የውጭ ሐገር ኩባንያዎችና የኩባንያዎቹ ወኪል ከሆኑት ኢትዮጵያውያን ደላሎች ጋር በጥቅም በመመሳጠር እንዲሁም ግዠዎች ከኢንዱስትሪው ፍላጎት ውጭ በቀጥታ በኃላፊዎች ተጽዕኖ እንዲፈጽሙ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

በመሆኑም በአጠቃላይ ከ 7 የውጭ ሀገር ኩባንያዎች ከ14,000(ከአስራ አራት ሺ) በላይ ትራክተሮችን እና የትራክተር አካላትን 181,076,621 የአሜሪካ ዶላር 43,385,173.8 ዩሮ ወጭ በማድረግ ህገ-ወጥ ግዥ መፈጸማቸውን በዚህም ምክኒያት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አለአግባብ እንዲባክን አድርገዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ የተገዙት ትራክተሮች የጥራትና የቴክኒክ ችግር ያሉባቸው በመሆናቸው ከ6,000 በላይ ትራክተሮች ገዥ አጥተው በኢንዱስትሪው ግቢ ውስጥ ተከማችተው በፀሀይና በዝናብ እንዲበላሹ በመደረጉ በመንግሰት ላይ አሁን ባለው ደረጃ ወደ 300,000,000 ብር አካባቢ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን እንዲሁም በግዥ ሂደት የተሳተፉ የውጭ ሀገር ኩባንያዎች እና ሌሎችም ከፍተኛ ጥቅም እንዲያገኙ ማድረጋቸውን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ዐቃቤ ህግ 23 የሰው ምስክሮችን ፣19 የሰነድ ማስረጃዎችን ፣የኢሜል መልዕክት ልውውጦችን እንዲሁም የፎቶ ግራፍ ማስረጃዎችን በክስ መዝገብ ላይ አካቶ አቅርቧል፡፡ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ሁሉንም ተከሳሾች የቀረቡባቸውን ክሶች እንዲከላከሉ በማለት በ12/03/2012 ዓ.ም ብይን ሰጥቷል፡፡በዚህም መሰረት ተከሳሾች አሉኝ የሚሏቸውን የመከላከያ ማስረጃዎች ከጥር 4/2012 ዓ.ም ጀምሮ አቅርበው ለፍርድ ቤቱ እንዲያሰሙ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

Via Federal Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa
ሲዳማ ለደቡብ ክልል ሀዋሳ ላይ ለፈሰሰው ሀብት በብር ካሳ ይከፍላል ።

የደቡብ ክልል መስተዳደር ሀዋሳን ነቅሎ ሲወጣ በህዝብ ምርጫ ክልል የሆነው ሲዳማ ሀዋሳ ላይ ደቡብ ክልል ለመሰረተ ልማት ግንባታዎችና ለሕንፃዎች ያፈሰሰውን ሀብት መቼ እንደሆነ ባይታወቅም መክፈሉ አይቀርም መባሉን የሲዳማ ዞን የህዝብ ግንኙነት ክፍል #ሰራተኞች በመልክት #አሳውቀዉኛል ሲል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት በማህበራዊ ሚድያ ገፁ አስፍሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
ሱዳን የኢጋድ ሊቀ መንበር ሆና ተመረጠች።

ሱዳን የኢጋድን ሊቀ መንበርነት ቦታ ከኢትዮጵያ ተረክባለች፡፡

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ አስታውቋል፡፡
@Yenetube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሶስት የመንግስት የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከትናንት ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት የመንግስት የስራ ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት መሰጠቱን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት

⚡️አቶ አህመድ ቱሣ - የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር።

⚡️ዶክተር አለሙ ስሜ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ።

⚡️አቶ አወሉ አብዲ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

@Yenetube @Fikerassefa