YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሀዘን መግለጫ!

*************

በዩኒቨርሲቲያችን የሜድካል ላቦራቶሪ ትምህርት ክፍል የክሊኒካል ኬሚስትሪ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪያችን የነበረችው ኦብሲ ነጋሳ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየች ዩነቨርሲቲዉ የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለመላ ቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ጅማ ዩነቨርሲቲ!

Ibsa Gaddaa
************

Barattuu Digirii 2ffaa Kilinikaal Keemistirii kan turte Obsii Nagaasaa du'aan addunyaa kana irraa boqochuusheetti Yuunivarsiitiin jimmaa gadda itti dhagahame ibsaa maatiifi firoottan ishee hundaaf jajjabina hawwa.

Via:- Yunivarsitii Jimmaa
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ዛሬ ኅዳር 17/2012 ጠዋት ላይ 25 ተማሪዎች እና 5 አስተማሪዎች ላይ በተፈጠረው የጤና ዕክል ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች የተወሰዱ ተማሪዎች ከሁለት ተማሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ፍርህይወት አዳል ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

የ5እና የ7ኛ ክፍል የሚማሩ በተማሪዎቹ እና በአስተማሪዎቹ ላይ የማሳል፣ ማስመለስ፣ ብርድብርድ የማለት እንዲሁም እራሳቸውን የመሳት ምልክት መታየቱን ገልጸዋል።

በትምህርት ቤቱ በሚሰጠው የምግብ አገልግሎት 700 ተማሪዎች የሚመገቡ ሲሆን ነገር ግን 25 ተማሪዎች ብቻ መታመማቸው ታውቋል።

የጤና ዕክል ካጋጠማቸው አንዱ የሆነው ተማሪ ፉአድ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፀው ጠዋት ለቁርስ የተመገቡት ዳቦ በማር ሲሆን ከተመገቡ በኋላ ሕመም እንደጀመራቸው አስታውቋል በቦታው የተገኙት አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሞያዎች ተማሪዎች ጠዋት የተመገቡት ምግብ ለምርመራ ናሙና መውሰዳቸውን የገለፁ ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በአሁን ሰዓት ከኹለት ተማሪዎች ውጭ ሁሉም ተማሪዎች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ለቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን ፍርህይወት አዳል ገልጸዋል።

Via:- አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መንግሥት እያደገ የመጣውን የምግብ ዘይት ፍላጎት ለማርካት የፓልም ዘይት አስመጪዎችን በእጥፍ ማሳደጉን ፎርቹን ዘግቧል።በዚህም መሠረት እያንዳንዳቸው አስመጪዎች በየወሩ ቢያንስ 2 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ማስመጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) መሪዎች ከሱማሊያዋ ጁባላንድ ራስ ገዝ ባለሥልጣናት ጋር በኬንያ ናይሮቢ መክረዋል፡፡ በውይይቱ አዲሱ የኦብነግ ሊቀመንበር አብድራህማን መሃዲ እና የጁባላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ማዶቤ መገኘታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የውይይቱ አጀንዳ በዝርዝር አልታወቅም፡፡ ማዶቤ የኦጋዴን ጎሳ ተወላጅ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያና ኬንያ ጁባላንድ ራስ ገዝ ላይ የተለያየ አቋም ያራምዳሉ፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታቸውን ምስል ከአንገት በታች በታዋቂው የፊልም ተዋናይ ሲልቬስተር ስታሎን(ራምቦ) ጋር በፎቶሾፕ በማገናኘት በትዊተር ገፃቸው መልቀቃቸው የማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ሆኗል። ስለ ጉዳዩ ፎክስ ኒውስ እንዳለው በዲሞክራቶች ሲቀርባቸው የነበረው ክስ ዛሬ የሚሰማበት ቀን በመሆኑ የፖለቲካው ከባድ ሚዛን ሻምፒዮን መሆኔን እወቁልኝ ለማለት ፈልገው ነው ይህን አስቂኝ ምስል የለቀቁት።😊

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ጋር መከሩ!

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡በኪጋሊ ከተካሄደው የአለም አቀፉ የስርአተ ጾታ ጉባኤ ጎን ለጎን ውይይት ያደረጉት መሪዎቹ ሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰላም ሚንስቴር የፖሊስ ዶክትሪን (ገዥ መመሪያ) አርቅቋል፡፡ ረቂቁ ላይ ሚንስቴሩ ዛሬ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበራት ጋር እንደተወያየበት የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ዶክትሪኑ የተረቀቀው በፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ የፖሊስ ተቋም ለማቋቋም፣ የፌደራል-ክልል እና የፖሊስ-ሲቪል ሕዝብ ግንኙነትን ለማሻሻል ነው ተብሏል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዳቦን በተመጣጣኝ ዋጋና በብዛት ለማቅረብ ታስቦ እየተገነባ ያለው የዳቦ ፋብሪካ ከጥር ወር በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ።

በውጭ ምንዛሬ እጥረት እስከ አሁን የስንዴ ግብይት አለመፈጸሙ ተግዳሮት መሆኑም ተጠቅሷል።በሆራይዘን ፕላንቴሽን የዕቅድ ቢዝነስ ዴቨሎፕ መንትና የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ ለአዲስ ዘመን እንዳስረዱት፣ ከቅርብ ወራት በፊት ግንባታው የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በቀን 18 ሰዓታትን በመስራት ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቋል። በቀጣይ ወራትም የማሽን ተከላና ቀላል ሥራዎች ይከናወናሉ።

ማሽኑ በመጓጓዝ ላይ ያለ ሲሆን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሥፍራው ይደርሳልም ያሉት አቶ ይበልጣል፣ በዕቅዱ መሰረትም ፕሮጀክቱ እስከ ጥር ወር መገባደጃ ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ወደሥራ ለመግባት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ (The World Heritage Committee) አባል ሆና ተመረጠች።

በአመት አንድ ጊዜ የሚሰበሰበው እና 21 አባላት ያሉት ኮሚቴ የዓለም ቅርስ ስምምነት አተገባበርን የመከታተል እና የዓለም ቅርስ ፈንድ የገንዘብ አጠቃቀም የመወሰን ሥልጣን የተሰጠው ነው። ኢትዮጵያ የኮሚቴው አባል ሆና የተመረጠችው የአባል አገራት ጠቅላላ ጉባኤ በፓሪስ ባደረገው ስብሰባ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት በድረ–ገጹ አስታውቋል። በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አራት አመታት የኮሚቴው አባል ሆና እንደምታገለግል ገልጸው በግል የፌስቡክ ገጻቸው የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።ይኸ ኮሚቴ አባሎቹ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ገንዘብ የመስጠት ኃላፊነት ጭምር አለው።ግብጽ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ኦማን፣ ታይላንድ፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተመረጡ አዲስ የኮሚቴው አባላት ሆነዋል።

Via Sheger Tribune
@YeneTube @FikerAssefa
አክሱም ዩኒቨርስቲ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን አሳውቋል።

ዶ/ር ፀሃዬ አስመላሽ ከ ግንቦት 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2012 ዓ.ም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ይሁን እንጂ በ ህዳር 2012 ዓ.ም ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በግል ጉዳይ ምክንያት የመልቀቅያ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ ቦርዱም የዶ/ር ፀሃዬ የመልቀቅያ አይቶ ከተወያዬ ቦኃላ በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው ሲሆን ቦርዱ በመቀጠልም የውሳኔ ሃሳቡ ወደ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ የሚኒስቴር መስርያቤቱም የቀረበለት የውሳኔ ሃሳብ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህግና ደምብ መሰረት ውሳኔው ተቀብሎታል፡፡በመሆኑም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህግና ደምብ መሰረት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት እስኪሾም ድረስ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን ታውቋል።

ምንጭ: አክሱም ዩኒቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
ከትናንት በስቲያ ሁለት የምዕራብ ሸዋ ባለስልጣናት በጥይት ተመተው ተገደሉ!

በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የጀልዱ ወረዳ አመራር የሆኑ ሁለት የአካባቢው ባለስልጣናት ከትናነት በስቲያ ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ።የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ረጋኔ ከበበ እና የጎጆ ከተማ የፖለቲካ ዘረፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገረመው በጎጆ ከተማ ማክሰኞ ምሽት 12 ሰዓት አካባቢ በጥይት ተመተው መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተናግረዋል።

https://telegra.ph/BBC-11-28
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብልፅግና ፓርቲ ምስረታ ሁሉንም ህጋዊ መሰረት የያዘና ህግን ተከትሎ የተፈፀመ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠ/ሚ ዐቢይ የብልጽግና ፓርቲን አቋምና ምኞት በተመለከተ በፌስቡክ ገፃቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትላንትናው ዕለት በልደታ አካባቢ በሚገኙ ሶስት ትምህርት ቤቶች ላይ ተማሪዎች በምግብ ተመርዘዋል ተብሎ የተሰሩት ዜናዎች ትክክል አይደሉም ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአሐዱ እንደገለፀው በትላንትናው ዕለት በፍሬህይወት አፀደ ህፃናት እና ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ ተማሪዎች መታመማቸውን ገልጿል፡፡የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሶስት ትምህርት ቤት ብለው የዘገቡት ትክክል አይደለም ያለው ከተማ አስተዳደሩ በፍሬህይወት ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች እና መምህራን ላይ የማስመለስ እና የሳል ምክልቶች በመታየቱ ከተማ አስተዳደሩ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም እንዲሄዱ ማድረጉን አስታወቋል፡፡207 የሚደርሱ ተማሪዎች ላይ ህክምናው መደረጉን የገለፀው የከተማ አስተዳደሩ ውጤቱም ተማሪዎች ላይ የተከሰተው የምግብ መመረዝ አለመሆኑ ታውቋል ብሏል፡፡

Via አሐዱ ሬድዮ
@YeneTube @FikerAssefa
በመኪና ምርቷ የምትታወቀው የጀርመን ባደን ውርተምበርግ ግዛት እና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ተገናኝተው መክረዋል!

ምክክራቸው ያተኮረውም የጀርመን መኪና አምራች ድርጅቶች እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ቴክኖሎጂዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ ምርት ለማስጀመር ያሰበ ነበር። ባደን ውርተምበርግ መርሴዲስ፣ ፖርሽ እንዲሁም ኦዲ መኪናዎች የሚመረቱበት ግዛት ነው። ኢትዮጵያ የድሬዳዋ ኢንደስትሪ ፓርክን መኪና ለማምረቻነት እንደመረጠች በስብሰባው ወቅት ተነግሯል።

Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ኦሮሚያ በባለስልጣናት ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ በመንግስት የውስጥ አሻጥር የሚፈጸም ነው ብሎ እንደሚያምን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ገለጸ።

ኦነግ በግድያዎቹ “እጁ እንደሌለበት፤ የሚያዘውም ሰራዊት እንደሌለው” አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ስላሉ ግድያዎች በዶይቼ ቬለ ጥያቄ የቀረበላቸው የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ “በእኛ ግምት እና በአንዳንድ ምልክቶች፤ የውስጥ አሻጥር የሚመስል ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።“ከመንግስት የውስጥ መዋቅር በተለይም ከመከላከያው እና ጸጥታ ክፍሉ ውስጥ ሆን ብለው አሻጥር (ሳቦታጅ) የሚሰሩ ይኖራሉ” ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በአካባቢ ባለስልጣናት እና የስራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች እየተፈጸሙ ይገኛሉ።በክልሉ በምዕራብ ሸዋ ዞን ከትናንት በስቲያ በተፈጸመ ጥቃት የጀልዱ ወረዳ ሁለት ባለስልጣናት በጥይት ተመትተው መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።ይህን የምዕራብ ሸዋን ግድያ ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት በምዕራብ ኦሮሚያ ሶስት ዞኖች ብቻ በትንሹ ስድስት የመንግስት ባለስልጣናት መገደላቸውን ከየአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።ግድያዎቹ “በማን እንደሚፈጸሙ በግልጽ የቀረበ ነገር አላየንም” የሚሉት የኦነግ ቃል አቀባይ “የሚታወቅ ነገር የለም። ሆኖም ሰዎች ከተማ ውስጥ ይገደላሉ። መንገድ ላይ፣ በመኪናም ሲሄዱ ይገደላሉ” ሲሉ የችግሩን መኖር አረጋግጠዋል።

አቶ ቀጄላም ሆኑ ግድያዎቹ የተፈጸመባቸው አካባቢዎች የመንግስት ኃላፊዎች የገዳዩቹ ማንነት በግልጽ እንደማይታወቅ ቢናገሩም የየአካባቢው ነዋሪዎች ግን ሸኔ ተብሎ የሚጠራው ከኦነግ ተገንጥሎ የወጣ ክንፍ ታጣቂዎች ግድያዎቹን እንደሚፈጽሙ ሲናገሩ ይደመጣል።“ህዝቡ የሚደርሱ ጥፋቶችን ከጠቅላላው የኦነግ አባላት ጋር በማያያዝ ባልተገባ መንገድ ሲያነሳ ይታያል” የሚሉት አቶ ቀጄላ ውንጀላውን ውድቅ አድርገዋል።“ሸኔ ማለት በድሮው አጠራር የፖሊት ቢሮ አባል ወይም በአሁኑ የመዋቅር ደረጃ የስራ አስፈጻሚ ማለት ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ “በአሁኑ ወቅት እንዲህ ያለው አደረጃጀት ከድርጅታቸው መዋቅር ውጪ መሆኑን አስረድተዋል። “እኛ የምናዝበት ሰራዊት የለንም።ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ነው የመጣነው። አሁንም ፍላጎታችን ያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) የዓለምአቀፍ የቅርስ ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች።

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው፥ ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት የዓለምአቀፍ የቅርስ ኮሚቴ አባል ሆና ተመርጣለች።
ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ወቅት የዩኔስኮ ስራ አስፈፃሚ ቦርድና የዓለምአቀፍ ቅርስ ኮሚቴ አባል ሆና እንደምታገለግልም ነው ኤምባሲው ያስታወቀው።

ኢትዮጵያ የዩኔስኮ የዓለምአቀፍ የቅርስ ኮሚቴ አባል እንድትሆን ለመረጡ ሀገራትም ምስጋናውን አቅርቧል።

የዩኔስኮ የዓለምአቀፍ የቅርስ ኮሚቴ የ21 ሀገራት ተወካዮችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፥ የኮሚቴው አባል ሀገራትም በዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባዔ የሚመረጡ ናቸው።

ኮሚቴው ዓለም አቀፍ የቅርስ ጥበቃ ስምምነቶች በስራ ላይ እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት ያለው ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የቅርስ ፈንድ አስፈላጊነትን የሚያብራራ እና በሀገራት ጥያቄ ላይ ተመስርቶም የገንዘብ ድጋፍ የሚያመቻች መሆኑንም ከዩኔስኮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ኮሚቴው ቅርሶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) መዝገብ ላይ እንዲሰፍሩ እና ቅርሶቹ አደጋ ላይ ሲወድቁም እንዲሰረዙ የማድረግ ሙሉ ስልዕጣን ያለው ነው።

@Yenetube @fikerassefa
ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 4 ተከሳሾች ላይ ከራዳር ግዢ ጋር በተያያዘ አዲስ ክስ ተመሰረተ!

ተከሳሾች 1ኛ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን 2ኛ ሌ/ኮረኔል ፀጋዬ አንሙት፣ 3ኛ ኮረኔል ሸጋው ሙሉጌታ እና 4ኛ ኮረኔል መሐመድ ብርሐን ሲሆኑ የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመምራት ከግዢ መመሪያ ውጭ ጥራቱን ያልጠበቀ ራዳር ከ214 ሚሊዩን ብር በላይ በመግዛት በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ በከባድ የሙስና ወንጀል በዛሬው እለት አዲስ ክስ ተመሰረቷል፡፡

https://telegra.ph/Kinfe-11-28
መንግሥትን ከ214 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ አሳጥተውታል የተባሉ የቀድሞ የሜቴክ አመራሮች በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተ

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው በቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፣ ሌተናል ኮሎኔል ጸጋዬ አንሙት፣ ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታ እና ኮሎኔል መሐመድ ብርሃን የተሰኙ ግለሰቦች ላይ ነው።

እንደ ዐቃቤ ሕግ ክስ አራቱም ተከሳሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር በኮርፖሬሽኑ የሀይቴክ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ የቦርድ ጽ/ቤት ሓላፊ እና የሥነ ምግባር እና የሕግ ክፍል ሓላፊዎች ናቸው።

ግለሰቦቹን ለክስ ያበቃው ወንጀል ደግሞ በ2004 ዓ.ም ያለ ጨረታ ግዥ ተፈጽሞበታል የተባለው የራዳር ጉዳይ ነው።

ከኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የግዥ ፍላጎት ሳይቀርብ ኤልአይቲ እና ሲኢአይሲ ከተሰኙ የቻይና ኩባንያዎች ተመሳሳይነት ያላቸውን ራዳሮች ያለ ጨረታ ግዥ እንዲፈጸም አስደርገዋል ብሏል-ዐቃቤ ሕግ።

በክስ መዝገቡ ሁለተኛ ተራቁጥር ላይ የተጠቀሱት ሌተናል ኮሎኔል ጸጋዬ አንሙት እና 3ኛው ተከሳሽ ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታ ከኩባንያዎች ጋር ያለ አግባብ ተቋሙን ወክለው ውል በመፈራረማቸው ነው የተከሰሱት።

ጠቅላይ አቃቢ ህግ
@YeneTube @FikerAssefa
ኳታር በሱዳን በኩል ሁለገብ አሻጥር እየፈጸመችብኝ ነው ስትል ኤርትራ ከሳለች፡፡ በአጎራባቼ ፖርት ሱዳን የጎሳ ግጭት ታስነሳለች፤ ኤርትራዊያን ሙስሊሞችን ጨምሮ ተቃዋሚዎችን እንደገና ታደራጃለች፤ በሱዳንም ወታደራዊ ሥልጠና ትሰጣለች- ብሏል መንግሥት በሻባይት ድረ ገጽ ባወጣው መግለጫ፡፡ የባለስልጣናትን ግድያም ታቀነባብራለች፤ በከተሞችም ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ እንዲቀጣጠል ቀን ተሌት ትሰራለች ሲል አክሏል፡፡

ምንጭ: ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ መስተዳደር አዲሱ ደሞዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ዛሬ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ከሐምሌ ጀምሮ ያለው አዲሱ ደሞዝ ጭማሪ ለሴክተር መስርያ ቤቶች ሀላፊዎች ለሰራተኞቻቸው የተከማቸውን ክፍያ ጨምሮ አዲሱን ደሞዝ ተግባራዊ እንዲያርጉ የሚያዝ ደብዳቤ ዛሬ ተበትኗል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa