YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ፌደራል ፖሊስ በሻሸመኔ እና በአዲስ አበባ ከ135 ሔክታር በላይ መሬት ላይ በቅሎ የነበረ የኮኬይን እርሻ ማስወገዱን ተናገረ።

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ለልማት ተብለው በታጠሩ ስፍራዎች ላይ የለሙ አደገኛ እጾችን ማስወገዱንም አስታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በዛሬውቅ እለት በሻሸመኔ አካባቢ ባካሄደዉ ዘመቻ በትራንስፖርት ሊጓጓዝ የተዘጋጀው ከ595 ኩንታል በላይ የሚደርስ ካናቢስ እጽ መያዙን ገልጿል።

በተጨማሪም በ135 ሄክታር መሬት ላይ በቅሎ የነበረዉ ካናቢስ የተሰኘዉን አደገኛ ዕፅ ማስወገዱንም ገልጿል፡፡በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ኦፕሬሽን መክትል ዳይሬክቴር ኮማንደር መንግስትአብ በየነ እንደገለፁት 59 ኪ.ግ ካናቢስ፣ 95 ኪ.ግ እና 168 ጥቅል ኮኬይን እንዲሁም 1 ነጥብ 4 ሚሊ ሊትር ፈሳሽ ኮኬይን በኢትዮጵያ አየር መንድ ወደ ዉጭ ሊወጣ ሲል መያዙን ገልጿል፡፡በህገ ወጥ ተግባሩ የተሳተፉ 24 የሚደርሱ የ 10 ሀገራት ዜግነት ያላቸዉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉንም ኮማንደሩ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባም ለመልሶ ማልማት በሚል ሰበብ ግንባታ ሳይገነባባቸዉ ታጥረዉ በቆዩ ቦታዎች ላይ በቅሎ የተገኘዉ ካናቢስ ካናቢስ የተሰኘዉን አደገኛ ዕፅ ማስወገዱን ኮማንደር መንግስተዓብ ተናግረዋል፡፡በሀገራችን “እህል አምርታቹ ከምትሸጡት የበለጠ ዋጋ ያወጣላቿል” በማለት አርሶአደሮችን የሚያሳስቱ ግለሰቦች በመኖራቸዉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበትም ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት ስራ አስፈጻሚና ማእከላዊ ኮሚቴዎች በውህደቱ ላይ የወሰዱትን አቋም አስመልክቶ አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ ይጠራል-ዶ/ር ደብረጺዮን

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ስራ አስፈጻሚና ማእከላዊ ኮሚቴዎች በቅርቡ ስለ ኢህአዴግ ውህደት የወሰዱትን አቋም አስመልክቶ አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ እንደሚጠራ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ።ዶክተር ደብረጺዮን በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ለሃገር አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሰጥተዋል።ህወሃት በትግራይ ህዝብ መስዋዕትነት የተገነባ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ደብረጺዮን፥ በጉባኤው የህወሓት ስራ አስፈጻሚና ማእከላዊ ኮሚቴዎች ስለ ውህድ ፓርቲ የወሰዱትን አቋም አባላቱና ህዝቡ እንዲመክሩበት ይደረጋል ብለዋል።

“የስራ አስፈጻሚውና ማእከላዊ ኮሚቴው የወሰደው አቋም ትክክል መሆኑና አለመሆኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ተወያይተው ይደግፋሉ አልያም የራሳቸውን አቋም ይዘው ይወጣሉ” ያሉት ሊቀመንበሩ፥ ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ ጉባኤው የደረሰበት አቋም የህወሓት ውሳኔ ሆኖ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና ምክር ቤት ውህድ ፓርቲ ለመመስረት የተከተለው አካሄድ ከድርጅቱ ህገ ደንብና አሰራር የወጣ እና የሃዋሳው ጉባኤ ያስቀመጠው አቅጣጫ የሚጥስ በመሆኑ ህወሓት በልዩነት መውጣቱን አስታውሰዋል።የህወሓት አቋም ስለውህደቱም ሆነ ስለኢህአዴግ እጣ ፈንታ የየድርጅቱ አባላት በጉባኤያቸው ተወያይተው ካፀደቁት በኋላ መሆን እንዳለበት ሀሳብ ቢያቀርብም ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ዶክተር ደብረጺዮን ተናግረዋል።

“የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና ምክር ቤት አባላት የእህት ድርጅቶች አባላት ውክልና በመያዝ የአመራር ሚናውን የሚወጣ እንጂ አንዱን አፍርሶ ሌላ ድርጅት እንዲመሰርት ስልጣንና ሃላፊነት አልተሰጠውም” ብለዋል።
“የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የሚፈጥሩት ጥምረት እንደ ኮንትራት ስምምነት የሚታይ በመሆኑ ስለ ፕሮግራሙና አካሄዱ ሳይወያዩ ውህደት መፈፀም ተገቢ አለመሆኑ የህወሓት አቋም ነው” ብለዋል።“ህወሓት ጉዳዩን ወደ አባላቱና ወደ ህዝቡ ከማውረድ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የጀመራቸውን የለውጥና የልማት ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ነው ያሉት።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የዩኒቨርስቲዎች የዛሬ ማለትም የህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም የከሰዓት ውሎ!

📌 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ካለው ትምህርት ጎን ለጎን ከየመማርያ ክፍሉ ከተወከሉ ተማሪዎች ተወካዮች ጋር በዋናው ግቢ (ስድስት ኪሎ) ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ተማሪዎች ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይም የሳይስንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮችና የዩኒቨርስቲው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያም ተማሪዎቹ ሰላማቸውን በጋራ ጠብቀው ትምህርታቸውን ለመከታተል ቃል ገብተዋል፡፡


📌 ወደሰላም በተመለሱት ዩኒቨርስቲዎች ትምህርቱ ተጠናክሮ መሰጠቱ የቀጠለ ሲሆን ወደትምህርት ገበታቸው የሚመለሱ ተማሪዎችም ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡


📌 በተሳሳተ መረጃ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ዝውውር ታገኛላችሁ ተብለው ዩኒቨርስቲዎቻቸውን ለቅቀው በአንድ አከባቢ ተሰባስበው የነበሩ ተማሪዎች ነገሩ ስህተት መሆኑን በመገንዘብ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲዎች በመመለስ ላይ ይገኛሉ፡፡በዚህ አጋጣሚ ተማሪዎች ከተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ውጪ በማንኛውም ምክንያት ወደ ሌለ ዩኒቨርስቲ የሚደረግ ዝውውር ፈፅሞ አለመኖሩን ተገንዝበው በተመደበቡበት ዩኒቨርስቲ ሆነው ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እናሳስባለን፡፡


የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ከኬንያዋ ላሙ ወደብ የአንደኛው ተርሚናል ባለቤት እንደምትሆን ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ለኢትዮጵያ በተሰጠው መሬት ላይ ለሚሰራው ተርሚናል ባለመብትነቱን ሕጋዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዐለም ሀገራቸው ላሙ ወደብን ትታ ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ ኤርትራዋ አሰብ ወደብ አዙራለች የሚባለውን ዘገባ አስተባብለዋል፡፡ የባለቤትነት መብቷ ከተረጋገጠላት ኢትዮጵያ በላሙ ወደብ የበለጠ መዋለ ንዋይዋን ታፈሳለች፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢሕዴን) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሐሙስ ኀዳር 18/2012 መጥራቱ ታውቋል ።

ምንጭ:Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሔ ለማበጀት የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች ባለፈው ታሪክ፣ በአሁኑ ነባራዊ ሁኔታ እና የአገሪቱ የወደፊት እጣ–ፈንታ ላይ እንዲወያዩ ጥሪ አቀረበ።

ኦነግ ለውይይት ዝግጁ የሆኑ ኃይሎች አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ጽህፈት ቤቱ ብቅ እንዲሉ ጠይቋል።ትናንት ምሽት በማኅበራዊ ድረ–ገጾች ባሰራጨው ጥሪ ኦነግ አሁን በአገሪቱ የሚታየው ቀውስ "ኢትዮጵያ ከተመሠረተችበት የተለያዩ አመለካከቶችን አጣምሮ ማስተናገድ ከማይችል ፀረ-ዴሞክራሲ የፖለቲካ ባህል የሚመነጭ" ነው ብሏል።
ግንባሩ "በሕዝቦች ትግልና መስዋዕትነት የተጀመረዉን የለዉጥ ጅማሮ ደግፎ የለዉጡም አካል ሆኖ ለማስቀጠል ቃል ገብቶ ሥልጣኑን የተረከበዉ የዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር እየታዩ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እያከናወናቸዉ ያለ ሥራዎች እንዳሉ ሆነው፣ የተለያየ አመለካከት ያላቸዉ የፖለቲካ ኃይሎችም በመልካም ግንኙነትና በመደማመጥ ለሀገርና ለሕዝቦች ሰላም ሲባል መወያየትና በሚቻላቸዉ ላይ በመተጋገዝ መንቀሳቀስ ወሳኝ ነዉ" ሲል ጥሪ አቅርቧል።

"የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር በሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኃይሎች ተሳትፎ (All Inclusive) ካልሆነ በስተቀር ዘላቂ መፍትሄ" አያገኝም ያለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር "በተለመደዉ መልኩ አንዱ ወገን ሌላዉን በኃይል ደፍጥጦና አፍኖ እልባት ያገኛል ብሎ ማሰብ ከከንቱ ህልምና ምኞት የሚያልፍ አይመስለንም" ሲል አስጠንቅቋል።ኦነግ እንደሚለው "በቃላት ድለላና የተስፋ ዳቦ ብቻ፣ በይቅርታና በእርቅ ስም፣ አልያም የአብሮነትን ጥቅም መስበክና ማወደስን በመሳሰሉት ብቻ የሚፈለገዉ እርቅ፣ የሕዝቦች ነፃነትና አብሮነት፣ ዴሞክራሲ፣ ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ይመጣል ብሎ መመኘት ከምኞት ያልፋል ብሎ ማመን ይከብዳል።"
"የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በዚህች ሀገር የወደፊቱ የፖለቲካ ሂደት ዉስጥ የሕዝቦች ነፃነት፣ እዉነተኛ ዴሞክራሲ፣ ዘላቂ ሰላም እና ዕድገትን እዉን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶችና ኃይሎች ሁሉ ጋር (የትኛዉንም ባላገለለ መልኩ) በመነጋገርና በመወያየት በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ በመተማመን አብረን እየሰራን ያሉንን ልዩነቶች ከመሠረታቸዉ እያጠበብን በመሄድ ለችግሮቻችን የተሟላ መፍትሄ ለማፈላለግ ዝግጁ መሆኑን" አስታውቋል።

ምንጭ:Sheger Tribune
@YeneTube @FikerAssefa
ቦሌ ሚካኤል አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት አንድ ሰው ተገደለ!

በአዲስ አበባ ከተማ ሰኞ ኅዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ቦሌ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከሌላ ሥፍራ የመጡ ናቸው በተባሉ ወጣቶችና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ ሰው እንደ ሞተ፣ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ተሰማ፡፡በተፈጠረው ግጭት ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ የሩዋንዳ ኤምባሲ የጥበቃ አባል እንደሆነ ታውቋል፡፡በፀና ቆስለዋል የተባሉት ሦስት ሰዎች ለሕክምና ወደ ሆስፒታል መላካቸውን፣ ነገር ግን የትኛው ሆስፒታል እየታከሙ መሆናቸው አለመታወቁን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡የግጭቱ መነሻ ቦሌ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የተሰቀሉ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች ‹‹ይነሱ፣ አይነሱ›› በሚል ጭቅጭቅ ነበር ተብሏል፡፡በአካባቢው የነበሩ የሪፖርተር ምንጮች እንደሚያስረዱት፣ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ቀን 11፡00 ሰዓት ገደማ ነበር፡፡

በመጀመርያ ወደ ቦታው የሄዱ ሦስት ወጣቶች ሰንደቅ ዓላማዎቹ እንዲነሳ ሲያስጠነቅቁ እንደነበር፣ በኃይል ለማውረድ ሲሞክሩ ግን ሁኔታው ወደ ግጭት ማምራቱን፣ ከመካከላቸው አንዱ ከተደበደበ በኋላ ግን ከአካባቢው መሰወራቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ቆይቶ ግን ምሽት 3፡30 ሰዓት አካባቢ (የአካባቢው ነዋሪዎች ከፊሉ 40፣ ከፊሉ ደግሞ 100 ናቸው ይላሉ) በርከት ብለው በመመለስ ጥቃት መሰንዘራቸውን፣ ተሰባስበው የተመለሱት ወጣቶች የታጠቁ እንደነበሩና አካባቢውን ለማረጋጋት የከተማው የፀጥታ ኃይል በሥፍራው ተገኝቶ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡የኤምባሲውን የጥበቃ ሠራተኛ የመታው ጥይት ግን ከየትኛው ወገን የተተኮሰ እንደሆነ አለመታወቁን፣ ነገር ግን ከወጣቶቹም በኩል ግን የሚተኩሱ ነበሩ ተብሏል፡፡ ግጭቱን የቀሰቀሱ ሰዎች እስካሁን አለመያዛቸውን፣ ፖሊስ የማጣራት ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ምንጮች አስረድተዋል፡፡የግርግሩ ዓላማ የሃይማኖት ግጭት በመቀስቀስ ሰላም ማደፍረስ የሚመስልም ምልክት እንደነበረው ምንጮች ተናግረዋል፡፡   

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ስም የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል መኖሩን ደርሰንበታል፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግን ለጊዜው የቴሌግራም ቻናል የለኝም ፣ በዚህ የቴሌግራም ቻናል የሚለቀቁ ማናቸውም መረጃዎች የኔ እንዳልሆኑ እወቁልኝ ብሏል!

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ የሶስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ላይ "በምግብ መመረዝ" ተማሪዎች መጎዳታቸው ተገለጸ!

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ከላይ በተጠቀሱት ሶስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የምግብ መመረዝ እንዳጋጠማቸው ገልጿል። የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ህክምና ተቋም በመወሰድ ላይ መሆናቸውንም ቢሮው አስታውቋል።

መንግስት የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ችግረኛ ተማሪዎችን ቁርስና ምሳ በመመገብ ላይ ሲሆን ዛሬ የተመገቡት ተማሪዎች የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገልጿል።


Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የጌዲዮ ዞን ፌደራል መንግስት በክልልነት እንዲያዋቅረው ጠየቀ!

የጌድዮ ዞን አዋሳኝ የሆነው የሲዳማ ዞን በህዝበ ውሳኔ ወደ ከልልነት ማደጉን ተከትሎ ከደቡብ ክልል ጋር ያለው የየብስ ግንኙነት ይቋረጣል።በጌዲዮ ዞን ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ቦጋለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል እራሱን ችሎ በክልልነት ደረጃ ሲወጣ የጌዲዮ ዞን ከየትኛውም የደቡብ ክልል ዞኖች ጋር በጂኦግራፊ አቀማመጥ የማይገናኝ መሆኑን ተከትሎ የአስተዳደር ሁኔታው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ብለዋል፡፡

ዝርዝር
👇👇👇👇👇

https://telegra.ph/Gedeo-11-27
የኦዲፒ ድርጅታዊ ጉባኤ ፓርቲው የብልጽግና ፓርቲን እንዲዋሃድ ወሰነ!

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የብልጽግና ፓርቲን እንዲዋሃድ የፓርቲው ድርጅታዊ ጉባኤ ወሰነ።የፓርቲው አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ በአዳማ ተካሂዷል።ጉባኤው በኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶች ውህደት ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።በጉባኤው ላይም በብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀትና ህገ ደንብ ዙሪያ በስፋት ተወያይቷል።በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በስፋት ከመከረ በኋላም የብልጽግና ፓርቲን ለመዋሃድ ወስኗል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከማለደው ጀምሮ ተዘግቶ የቆየው የደሴ - ኮምቦልቻ - ሚሌ - ጅቡቲ መንገድ ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል። መንገዱ የተዘጋው ባቲ ከተማ አቅራቢያ አንድ የአፋር ክልል ልዩ ፖሊስ አባል መገደሉን ተከትሎ አለመረጋጋት በመፈጠሩ ነበር።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ጠዋት በተካሄዱት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስቸኳይ ስብሰባዎች ሁለቱም ውህደቱን በሙሉ ድምጽ ማፅደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳውቀዋል::

@YeneTube @FikerAssefa
የሀዘን መግለጫ!

*************

በዩኒቨርሲቲያችን የሜድካል ላቦራቶሪ ትምህርት ክፍል የክሊኒካል ኬሚስትሪ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪያችን የነበረችው ኦብሲ ነጋሳ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየች ዩነቨርሲቲዉ የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለመላ ቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ጅማ ዩነቨርሲቲ!

Ibsa Gaddaa
************

Barattuu Digirii 2ffaa Kilinikaal Keemistirii kan turte Obsii Nagaasaa du'aan addunyaa kana irraa boqochuusheetti Yuunivarsiitiin jimmaa gadda itti dhagahame ibsaa maatiifi firoottan ishee hundaaf jajjabina hawwa.

Via:- Yunivarsitii Jimmaa
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ዛሬ ኅዳር 17/2012 ጠዋት ላይ 25 ተማሪዎች እና 5 አስተማሪዎች ላይ በተፈጠረው የጤና ዕክል ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች የተወሰዱ ተማሪዎች ከሁለት ተማሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ፍርህይወት አዳል ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

የ5እና የ7ኛ ክፍል የሚማሩ በተማሪዎቹ እና በአስተማሪዎቹ ላይ የማሳል፣ ማስመለስ፣ ብርድብርድ የማለት እንዲሁም እራሳቸውን የመሳት ምልክት መታየቱን ገልጸዋል።

በትምህርት ቤቱ በሚሰጠው የምግብ አገልግሎት 700 ተማሪዎች የሚመገቡ ሲሆን ነገር ግን 25 ተማሪዎች ብቻ መታመማቸው ታውቋል።

የጤና ዕክል ካጋጠማቸው አንዱ የሆነው ተማሪ ፉአድ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፀው ጠዋት ለቁርስ የተመገቡት ዳቦ በማር ሲሆን ከተመገቡ በኋላ ሕመም እንደጀመራቸው አስታውቋል በቦታው የተገኙት አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሞያዎች ተማሪዎች ጠዋት የተመገቡት ምግብ ለምርመራ ናሙና መውሰዳቸውን የገለፁ ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በአሁን ሰዓት ከኹለት ተማሪዎች ውጭ ሁሉም ተማሪዎች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ለቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን ፍርህይወት አዳል ገልጸዋል።

Via:- አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መንግሥት እያደገ የመጣውን የምግብ ዘይት ፍላጎት ለማርካት የፓልም ዘይት አስመጪዎችን በእጥፍ ማሳደጉን ፎርቹን ዘግቧል።በዚህም መሠረት እያንዳንዳቸው አስመጪዎች በየወሩ ቢያንስ 2 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ማስመጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) መሪዎች ከሱማሊያዋ ጁባላንድ ራስ ገዝ ባለሥልጣናት ጋር በኬንያ ናይሮቢ መክረዋል፡፡ በውይይቱ አዲሱ የኦብነግ ሊቀመንበር አብድራህማን መሃዲ እና የጁባላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ማዶቤ መገኘታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የውይይቱ አጀንዳ በዝርዝር አልታወቅም፡፡ ማዶቤ የኦጋዴን ጎሳ ተወላጅ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያና ኬንያ ጁባላንድ ራስ ገዝ ላይ የተለያየ አቋም ያራምዳሉ፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታቸውን ምስል ከአንገት በታች በታዋቂው የፊልም ተዋናይ ሲልቬስተር ስታሎን(ራምቦ) ጋር በፎቶሾፕ በማገናኘት በትዊተር ገፃቸው መልቀቃቸው የማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ሆኗል። ስለ ጉዳዩ ፎክስ ኒውስ እንዳለው በዲሞክራቶች ሲቀርባቸው የነበረው ክስ ዛሬ የሚሰማበት ቀን በመሆኑ የፖለቲካው ከባድ ሚዛን ሻምፒዮን መሆኔን እወቁልኝ ለማለት ፈልገው ነው ይህን አስቂኝ ምስል የለቀቁት።😊

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ጋር መከሩ!

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡በኪጋሊ ከተካሄደው የአለም አቀፉ የስርአተ ጾታ ጉባኤ ጎን ለጎን ውይይት ያደረጉት መሪዎቹ ሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰላም ሚንስቴር የፖሊስ ዶክትሪን (ገዥ መመሪያ) አርቅቋል፡፡ ረቂቁ ላይ ሚንስቴሩ ዛሬ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበራት ጋር እንደተወያየበት የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ዶክትሪኑ የተረቀቀው በፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ የፖሊስ ተቋም ለማቋቋም፣ የፌደራል-ክልል እና የፖሊስ-ሲቪል ሕዝብ ግንኙነትን ለማሻሻል ነው ተብሏል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa