YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ሌሊት በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቋን እንዲሁም አራተኛ ብሯን አግኝታለች!

ሌሊት በተካሄደ የወንዶች ማራቶን:

1ኛ 🇪🇹ሌለሣ ዴሲሳ 2:10.40 በሆነ ጊዜ ወርቅ፣🇪🇹

2ኛ 🇪🇹ሞስነት ገረመው 2:10.44 በሆነ ጊዜ ብር፣ አግኝተዋል።🇪🇹

Via EAF
@YeneTube @FikerAssefa
የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ እየተከበረ ነው::

የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በድምቀት በመከበር ላይ ነው።በአሉ በአባገዳዎች ምርቃት ተጀምሯል።በአሉ የኦሮሞ ህዝብ የክረምት ወቅት ማለፉንና የጸደይ ወቅት መምጣቱን አስመልክቶ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው፡፡በትላንትናው እለት ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በአል በአዲስ አበባ በድምቀት መከበሩ ይታወሳል።

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በአጣዬ አካባቢ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ መረጋጋቱ ተመልሷል፤ ከኅብረተሰቡ ጋርም ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ አካባቢ ትናንት የታጠቁ ኃይሎች የፀጥታ ማደፍረስ ሙከራ አድርገው መክሸፉን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ እንደገለጹት ደግሞ ዛሬ ጠዋት አካባቢም የታጠቁ ኃይሎቹ ተኩስ ከፍተው ነበር፤ ነገር ግን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተቀናጀ አግባብ ሁኔታውን ተቆጣጥረውታል፡፡የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ከነዋሪዎች ጋር ስለሆኔታው እየተወያዩ እንደሆነ ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ሳዑዲ ያልተጋቡ ጥንዶች ሆቴል እንዲከራዩ ፈቀደች።

ከዚህ ቀደም ጥንዶች በጋብቻ መተሳሰራቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ካላቀረቡ ሆቴል መከራየት እንደማይችሉ የሚከለክለው ሕግ አሁን ላይ ለውጭ አገር ዜጎች ተፈቅዷል።ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን በቅርቡ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩና ያለምንም ጠባቂ ሴቶች ከአገር ውጭ ጉዞ እንዲያደርጉ የሚያዘውን ሕግ ጨምሮ በጣም የከረሩ ሕጎች ላይ የተወሰነ ማሻሻያ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ምንጭ:BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ጎንደር ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ 53 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ሰላምና ደኅንነት ግንባታ መምሪያ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2012 ዓ.ም የሥራ ዘመን ነገ ይጀምራል!

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ያካሄዳሉ።በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ንግግር የያደርገጋሉ።በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አካላት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላትም በፕሮግራሙ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የጭነት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ በከፊል ተነሳ!

በአዲስ አበባ ከተማ በከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ በከፊል መነሳቱ ተገልጿል።የከተማ አስተዳድሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ከዚህ በኋላ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከስራ ሰዓት መግቢያና መውጪያ ሰዓት ውጪ በሆኑት የትራፊክ መጨናነቅ በማይኖርባቸው ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ በከተማዋ እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዷል።በቀጣይ በመዲናዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦች እየተጠኑ መሆኑን ከከተማ አስተዳድሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የጭነት ተሸካርካሪዎች በመዲናዋ በሚኖራቸው እንቅስቃሴ ላይ ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የጊዜ ገደብ የሚያስቀምጥ መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዘሪቱ ከበደ "የኤልያስ መልካ ስንብት መስከረም 26 ቀን ከቀኑ 5 :30 በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል" ብላለች። ስንብቱ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይደረጋል ተብሎ ነበር። የቀብር ሥነ ስርአቱ ከቀኑ በ9 ሰአት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይከናወናል!

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ሁለት የድርጅት ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ እንደገለጹት የሥራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ረፋድ ነው፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ የአማራ ክልልን ሰላምና ደኅንነት ከማይፈልጉ አካላት ጋር በድብቅ ትሥሥር አላቸው በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፀጥታ አካላት የተገኘው መረጃ ያሳያል ሲል አብመድ ዘግቧል።
@YeneTube @Fikerassefa
ከግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በአል ተመላሾች በአሁኑ ሰአት ሸኖ ላይ ከፊትም ከኃላም መንገድ ተዘግቶባቸው ቆመዋል! ከእሬቻ ክብረ በዐል ሲመለሱ ደብረ ብርሃን የታሰሩ ወጣቶች ካልተፈቱ መንገዱን አንክፍትም ተብለዋል::

Via Atnaf Berhane
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ባለፉት 17 ቀናት ከ71ሚሊየን 393ሺ ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ተያዘ!

በጉምሩክ ኮሚሽን ህገ ወጥ ነጋዴዎችን የመቆጣጠሩ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚሁ መሰረት ባለፉት 17 ቀናት በገቢ ኮንትሮባንድነት 1,293,350 ብር የሚገመት የጦር መሳሪያን ጨምሮ ሌሎች 54,371,441 ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ጨምሮ በድምር 55,664,791 ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ዕቃ ተይዟል፡፡በወጪ ኮንትሮባንድም 7,703,985 ብር የሆነ የዉጪ ምንዛሬ፤2,540,240 ብር የሚያወጣ የቁም እንስሳት፤1,850,000 ብር የሚያወጣ ነዳጅና ሌሎች 3,634,093 ብር የሚያወጡ እቃዎች በድምሩ 15,728,318 ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ከአገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይ በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድም ባለፉት 17 ቀናትj 71,393,109( ሰባ አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ አንድ መቶ ዘጠኝ ብር) የሚያወጣ የኮንትሮባንድ እቃ ተይዟል፡፡ህገ ወጥነት ከህግ በላይ ሊሆንና ከህዝቡም ሊሰወር ስለማይችል ህግን በማክበር እንስራ የገቢዎች ሚኒስቴር መልዕክት ነዉ፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚንስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ፣ ‹‹የደንብ ልብሱን ለምን መቀየር አስፈለገ?›› ለሚለው ጥያቄ፣ ‹‹ነባሩ የፖሊስ የደንብ ልብስ አልተቀየረም፡፡ ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ በተጨማሪነት ሊሰጥ ይችላል፡፡ አዲሱ የደንብ ልብስ የተዘጋጀው በሌሎች ክልሎችም እንዳለው ሁሉ፣ ከመደበኛ ፖሊስ በተለየ በከተማው ውስጥ ሁከት ሲፈጠርና ከመደበኛው ፖሊስ አቅም በላይ ሲሆን፣ ያንን #ለሚቆጣጠር ቋሚና ተወርዋሪ ኃይል የተዘጋጀ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ቋሚና ተወርዋሪ›› ኃይሉ በዋና ዳይሬክተር የሚመራና ሙሉ ትጥቅ ያለው ኃይል ሲሆን፣ ለከተማ አስተዳደሩ ጥበቃ የተዘጋጀ የ‹‹ክብር ዘብ›› መሆኑንም ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/YeneTube-10-06
በ17ኛው የኳታር ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና #ማጠቃለያ ዕለት በተካሄደው #የ10,000 ሜትር ወንዶች ሩጫ፤ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያን አግኝታለች።

ዮሚፍ ቀጀልቻ - 26:49.34 -2ኛ (ብር)

አንዱ አምላክ በልሁ, - 26:56.71 -5ኛ

ሃጎስ ገ/ህይወት - 27:11.37-8ኛ

የዩጋንዳ ተወዳዳሪ ወርቅ አግኝቷል

@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ተዘግቶ የነበረው መንገድ ተከፍቷል!

ሸኖ ላይ ለሰዓታት ተዘግቶ የቆየው መንገድ ትናንት ከምሽቱ 5:00 ሰዓት አካባቢ ተከፍቶ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል።መንገዱ በሁለቱም አቅጣጫ ነው የተከፈተው። ደብረ ብርሃን ላይ ታሰሩ የተባሉት ወጣቶችም መፈታታቸው ሰምተናል።

@YeneTube @FikerAssefa
ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት መርሀ ግብር ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተገነቡ 20/80 የጋራ መኖርያ ቤት ኮንደሚኒየሞች ውስጥ 22915 ቤቶች ነገ በአዲስ አበባ ዳርቻ ለልማት በሚል ተነስተዋል ለተባሉ አርሶ አደር አባወራዎችና 18 አመት ለሞላቸው ልጆቻቸው ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቋል።ዋዜማ ራዲዮ ቤቶቹን ለመረከብ ከጫፍ ደርሰዋል ከተባሉ ግለሰቦች መረጃ ያሳያል ብሎ በሰራው ዘገባ ተነሽ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ነገ ማክሰኞ መስከረም 27 ቀን 2012 አ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የትኛው ሳይት ምን አይነት ቤት እንደደረሳቸው ይገለጽላቸዋል ተብሏል።ቀደም ብሎም የእጣ ቁጥር እንደተሰጣቸውም ታውቋል።

     ነገ ለሚከናወነው ስነስርአትም ሲባል ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተመረጡት የጋራ መኖርያ ቤቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚወስዳቸው ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል። ጉዳዩንም የቤቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ሚስጥር እንዲይዙት የተነገራቸው መሆኑን ፣ መረጃው ከወጣም ለሂደቱ እንቅፋት ይሆናል በሚል ተነግሯቸው እንደነበር ገልጸዋል።ለአባወራ አርሶ አደር ባለ ሶስት መኝታ ቤት ኮንደሚኒየም የሚሰጥ ሲሆን 18 አመት ለሞላቸው ለእያንዳንዱ ልጆቻቸው ደግሞ በእጣ ባለ አንድም ባለ ሁለት ክፍል ኮንደሚኒየም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ቀሪ 106 ቤቶችም ለተጠባባቂ ሰዎች መያዙንም ሰምተናል።ለአርሶአደር የልማት ተነሺዎች ከሚተላለፉት የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥም በካራ ቆሬ በረከት ሳይት ከተገነቡት ውስጥ 3,500 ቤቶች እንዲሁም ኮዬ ፈጬ የተገነቡት ይገኙበታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ልናናግራቸው የሞከርን ሀላፊዎች ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተወሰኑት ደግሞ ጉዳዩን እንደማያውቁትም ነው የገለጹልን።

     የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ባለፈው አመት የካቲት ወር መጨረሻ የ40 /60 እና የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣት ስነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር መንግስት በአዲስ አበባ በልማት ምክንያት ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው የጋራ መኖርያ ቤት እንደሚሰጣቸው መግለጻቸው ይታወሳል።የእጣ እድለኞች የሆኑ ቆጣቢዎች በኦሮሞ መብት ተከራካሪ ግለሰቦች አስተባባሪነት በተነሳ የወሰንና የአርሶ አደሮች የካሳ ያንሳቸዋል አመጽ የቆጠቡበትና እድለኛ የሆኑበት ቤት የወሰን ጥያቄ ኮሚቴ ተቋቁሞ ይታያል በመባሉ እስካሁን አልተላለፈላቸውም። ነገር ግን የልማት ተነሽ የተባሉ አርሶ አደሮችንና ልጆቻቸውን የመመዝገብ ስራ በሰፊው ሲሰራ መቆየቱን ከዚህ ቀደም ዋዜማ ራዲዮ መዘገቧም የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት የቤት ተጠቃሚ የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር 22, 915 መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።እነዚህ የልማት ተነሽ እንደሆኑ የተነገረላቸው የቤት ተረካቢዎች ለሚሰጣቸው የጋራ መኖርያ ቤትም ምንም አይነት ክፍያ አይከፍሉም። ሂደቱም ከፍተኛ የህጋዊነትና የፍትሀዊነት ጥያቄን አስነስቷል።

 በመጀመርያ አሁን የጋራ መኖርያ ቤት እንዲያገኙ የሚደረጉት የልማት ተነሽ የተባሉት አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ቁጥራቸው ተጋኗል የሚል ነው።የልማት ተነሽ ያልነበሩ ግለሰቦችም በሰፊው ገብተውበታል ማንነት ላይ የተመሰረተ ምልመላም ተደርጎበታል የሚል ስሞታ በሰፊው እየቀረበ ነው።አሁን የጋራ መኖርያ ባለቤት ይሆናሉ ከተባሉት ውስጥ የዛሬ አምስት አመት አካባቢ ከካራ ቆሬ ለልማት ተብለው የተነሱት አርሶ አደሮች ይገኙበታል። በወቅቱ ከዚህ ስፍራ የተነሱ አርሶ አደር ያልሆኑ ቤተሰቦችም ነበሩ። ይሁን እንጂ የቱንም ያክል ይዞታ የነበራቸው ቢሆንም የተሰጣቸው ግን 75 ካሬ ሜትር ልዋጭ መሬት ብቻ ነው። ልዋጭ መሬቱም ለአባ ወራ ብቻ እንጂ ልጆችን አላካተተም። ቤት መስሪያ ተብሎ የተሰጣቸው ብርም በዛ ቢባል ስምንት ሺህ ብር ነበር።

    አርሶ አደር ለነበሩት ተነሺዎች ግን እስከ 500 ሺህ ብር በጥሬ ተሰጥቷቸዋል። ምትክ ቦታም ለአባወራ 500 ካሬ ሜትር ለልጆቻቸው ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 250 ካሬ ሜትር ተሰጥቷቸዋል። ከነዚህ ተነሽ አርሷ አደሮች ውስጥ አሁን ላይ በጥሩ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉት አሁንም ያለ ምንም ክፍያ የጋራ መኖርያ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በተመሳሳይ ጊዜ በዚሁ ካራ ቆሬ 73 አርሶ አደር ያልሆኑ አባወራዎች ህገ ወጥ ናችሁ በሚል ያለ ምንም ካሳ ቤታቸው ፈርሶ እስካሁን ችግር ውስጥ ያሉ አሉ። ከዚህ ቀደም ከመሀል አዲስ አበባ ለልማት ተብለው የተነሱ ነዋሪዎች ኮንደሚኒየም ሲሰጣቸው ክፍያ ይጠየቁ እንደነበር ይታወሳል።እንዲሁም መንግስት ከቆጣቢ ዜጎች የሰበሰበውን ገንዘብ ጨምሮ የሰራውን የጋራ መኖርያ ቤት የ20/80 ባለእድለኛ ለሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳይተላለፍ የተደረገውን እገዳ ለማንሳት ጥረት ባልተደረገበት ሁኔታ 23 ሺህ የሚደርሱ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለማስተላለፍ መወሰኑ የፍትሀዊነት ጥያቄን አስነስቷል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneRube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ላይ ድርሻ ሊገዛ ነው!

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ድርሻ ለመግዛት ሃሳብ ማቅረቡ ታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ተወልደ ገብረማሪያም እንዳስታወቁት የደቡብ አፍሪካን አየር መንገድ ለመርዳት እና የደቡብ አፍሪካ መንግሰት ፈቃደኝቱን ካሳየ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካው አቻ አየር መንገዱ ላይ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው መጠቆማቸውን ዲጂታል ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa