YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ወደ ናይጀሪያው ሮቻስ ፋዉንዴሽን ለነጻ የትምህርት እድል የሚልኳቸዉን አምስት ወላጅ አልባ ታዳጊዎችን በቢሮአቸዉ አነጋገሩ፡፡ታዳጊዎቹ ከ4 ህጻናት ማሳደጊያዎች የተመረጡ የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸዉ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ዙሪያ የተቋቋመው የኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ የሦስትዮሽ ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን 5ኛ ስብስባውን በካርቱም ሱዳን ማካሄድ ጀምሯል።

የጥናት ቡድኑ እ.አ.አ ከመስከረም 15-16, 2019 በካይሮ በተደረገው ስብሰባ ወቅት በሦስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት እ.አ.አ ከጥቅምት 4-5 2019 በካርቱም በሚካሄደው የሦስቱ አገራት ውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

Via Ethiopian Embassy in Sudan
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ብራስ አካባቢ ባለው የደመራ የባህል ምግብ ቤት አስተናጋጆች ተጣልተው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

በቦሌ ብራስ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የደመራ የባህል ምግብ ቤት የመስተንግዶ ሰራተኞች መካከል በተፈጠረ የግል ጸብ አንድ ሰው ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአይን እማኞች እንዳረገጋጠው ጸቡ የተፈጠረው በምግብ ቤቱ ሁለት አስተናጋጆች መካከል ነው።አንዱ አስተናጋጅም በደረሰበት የስለት ጥቃት ወደ ብራስ ሆስፒታል ተወስዶ ህይወቱን ለማዳን ርብርብ ቢደረግም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።ድብደባውን የፈጸመው ግለሰብ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም በአካባቢው ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል።

via:- ETHIO FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሞ ሸለቆ ተፋሰስ ላይ በተገነቡ ኹለት የስኳር ፋብሪካዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት ሠራተኞች በሥራ ላይ እያሉ መገደላቸውና ሠራተኞች የጸጥታ ሥጋት ላይ በመወደቃቸው ፋብሪካው ሥራ እንዳቆመ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሠራተኞች ማኅበር አስታወቀ።

በአካባቢው ላይ ያለው የእርስ በእርስ ግጭትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንም የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋሻው አይችሉህም ተናግረዋል።

via:- Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የትራክተርና ሌሎች የግንባታ ዕቃዎችን ግዥ ለማከናወን ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር በፊት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 400 ሚሊዮን ብር ገቢ በማድረግ ለጨረታ አሸናፊዎች የሚከፈል የውጭ ምንዛሬ ቢጠይቅም ማግኘት አለመቻሉን አስታወቀ።

በአማራ ክልል የግንባታ እና ሌሎች መሣሪያዎችን ለመግዛት ከ22 ወራት በላይ የውጭ ምንዛሬ በመጠበቅ ተፈላጊ ማሽነሪዎች ተገዝተው ባለመቅረባቸው በክልሉ ልማት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ሲል የአማራ ክልል የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ገልጾል።
@YeneTube @FikerAssefa
በማዕከላዊ ጎንደር፣ ጭልጋ ወረዳ የቅማንት አርሶ አደሮች ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር ግጭት ውስጥ መሆናቸውን ዋዜማ ዘግቧል፡፡

መስከረም 16 የክልሉ ልዩ ሃይል አይከል ከተማ ሲገባ፣ ታጣቂዎች ተኩስ ስለከፈቱበት ግጭቱ መቀስቀሱን የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ጉላንግ እና ቡሆና በሚባሉ ቦታዎች እስከ ትናንት ተኩስ ተሰምቷል፡፡ የክልሉ መንግሥት በበኩሉ ታጣቂዎቹ ከሌላ ወገን ድጋፍ ያገኛሉ ይላል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኦዳ አዋርድ ለሶስተኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው!

የኦዳ አዋርድ ሽልማት ለ3ኛ ግዜ በመጭው ጥቅምት 7 በሸራተን አዲስ እንደሚካሄድ ተገለፀ። በ15/1/2012 ዓ.ም በኢሊያና ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተገለጸው የሽልማቱ አላማ የኦሮሞን የኪነ ጥበብ ስራዎች በአዎንታዊ መልኩ ማበረታታትና የዘርፉን ባለሙያዎች ይበልጥ ማነቃቃት ነው።በዚህ ረገድ የበሻቱ ቶለማርያም መልቲ ሚዲያ በፋና ወጊነት የሚጠቀስ ሲሆን የሽልማት ስርአቱን በተመለከተ የኦሮምያ ባህልና ቱሪዝም ትብብር እንዳለም ተጠቅሷል።

Via Gulele Post
@YeneTube @FikerAssefa
1702 ኪግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ ካናቢስ ተያዘ!

በቀን 18/01/2012 ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በአፋር ክልል ዞን ሶስት ውስጥ ወረር(ልዩ ቦታ አምባሽ) በሚባል ስፍራ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት የመረጃ ሰራተኞች እና ፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት ከፍተኛ ክትትል በአብዱልከሪም መሀመድ(ተጠርጣሪ ግለሰብ) መጋዘን ውስጥ ተከማችቶ ያለው 1702 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ(kanabis) የሚባል አደገኛ እፅ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

Via የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በካታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በወንዶች 5ሺህ ሜትር በሙክታር እንድሪስ ወርቅ በሰለሞን ባረጋ የብር ሜዳልያ አግኝታለች።

@YeneTube @FikerAssefa
Literal meaning of country's name.

India: Land of the Indus

Iran: Land of Aryans

Japan: Land of rising sun

Egypt: Frontier

Nigeria: Land of the Niger river

Italy: Land of young cattle

France: Land of the Franks

Germany: Fertile land

China: Qin state

Indonesia: Indian islands

#Ethiopia: Land of burnt faces (Greece)

@YeneTube @FikerAssefa
በካታር ዶሃ የአትሌቲክስ ቡድናችንን ለመደገፍ ወደ ስቴድዮም የገቡ ኢትዮጵያውያንን ልዩ ድባብ IAAF በአድናቆት በትዊተር ገፁ አጋርቶታል!

@YeneTube @FikerAssefa
በታደሉ ዩኒፎርሞች ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ግለሰብ እንዲያሳውቅና አፋጣኝ ማስተካከያ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

"ከዩኒፎርም ስርጭት ጋር በተያያዘ መጠነኛ ቅሬታዎች እየቀረቡልን ይገኛሉ።
የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛ አላማው ተማሪዎች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ማድረግና እንዲሁም ወላጆችን ከጭንቀት ለማዳን ነው።የከተማ አስተዳደሩ የየትኛውንም ሀይማኖት አስተምህሮትም ይሁን ስርአት ያከብራል።ለተማሪዎች በነጻ የዩኒፎርም ስናዘጋጅም ይህን ባገናዘበ መልኩ ነው።
ነገር ግን አሁን እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች በስርጭት ወቅት የተፈጠሩ በመሆናቸው መስተካከል ይችላሉ።ከዩኒፎርም አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ያለን በመሆኑ ለተማሪዎች በታደሉ ዩኒፎርሞች ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ግለሰብ እንዲያሳውቅና አፋጣኝ ማስተካከያ የምንወስድ መሆኑን እናስታውቃለን።"
- የከንቲባው ጽ/ቤት

@YeneTube @FikerAssefa
ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድረው የቀንጢቻ ታንታለም ፋብሪካ ላለፉት ኹለት ዓመታት ሥራ በማቆሙ ለሠራተኞቹ ደሞዝ እንዲሁም ለሥራ ማስጀመርያ የሚሆን 132 ሚሊዮን ብር ከገንዘብ ሚኒስቴር እርዳታ ጠየቀ።

በኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ቡልቲ ወዳጆ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ፋብሪካው ከተዘጋ አንስቶ ምንም ዓይነት ገቢ ባለማግኘቱ ላለፉት ስድስት ወራት ከመንግሥት በተገኛ 47 ሚሊዮን ብር የሠራተኞቹን ደሞዝ ሲከፍል የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ለሠራተኞቹ የሚከፍለው ገንዘብ የለውም።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና የኢትዮጵያ የአእምሮ ጤና ምርመር ኢንስቲትዩት ህንፃን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

#DPMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የባህል መድሃኒት ጥናትና ምርምር ፍኖተ- ካርታ ይፋ ሆነ፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የባህል መድሃኒት ጥናትና ምርምር ፍኖተ ካርታ ይፋ አድርገዋል፡፡የፍኖተ-ካርታው ዋና አላማ ሃገር በቀል ዕዉቀትን በመሰነድና በመጠበቅ የተጠናከረ ጥናትና ምርምር ማከናወን፣ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የባህል ህክምና አገልግሎት በአገሪቱ እንዲሰጥ ለማድረግ የተዘጋጀ ተብላል፡፡ዶክተር ኤባ አባተ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እንደገለጹት በአገራችን በአማካይ ወደ 80 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የባህል መድሃኒት ተጠቃሚ ቢሆንም ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ግን እምብዛም ነው ብለዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ 500 በላይ ፈዋሽ እጸዋት ቢኖራትም መጠቀም ግን አልተቻለም ብለዋል፡፡በመሆኑም ፍኖተ ካርታው በባህላዊ መድሃኒቶች ዙሪያ ጥናትና ምርምር እንዲደረግ ለባህላዊ መድሃኒት ቀማሚዎች ድጋፍ ለማድረግና ሌሎች ዘርፉን ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እንዲከናወኑ ያስችላል ተብሏል።በቀጣይ በባህል መድሃኒቶች ላይ የተለያዩ ጥናትና ምርምር በጋራ ለማድረግ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሁሉም የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችና ከምርምር ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ ለማድረግ 90 ሚሊዮን ብር እንደመደበ ነው የተገለጸው፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ለጎንደር ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፦

የ2012 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀናት ለነባር ተማሪዎች መስከረም 22 እና 23/2012ዓም እና ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ተማሪዎች መስከረም 28 እና 29/2012ዓ.ም እንደሆነ ማሳወቃችን ይታወሳል።

ነገር ግን በወቅታዊ ችግሮች ምክንያት የመግቢያ ቀናትን ማራዘም አስፈልጓል። ስለሆነም የነባር ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ወደ መስከረም 29 እና 30/2012ዓ.ም እንዲሁም የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ወደ ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2012ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።

Via:- የጎንደር ዮኒቨርሲቲ

@YeneTube @Fikerassefa
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
ኒውዮርክ ታይምስ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ:

"የኢትዮጵያው ገዢ ፓርቲ የሶሻል ሚድያ ንግግሮች ራሱን እንዲደግፉ ለማድረግ ሰዎችን ቀጥሮ ያሰራል/ያሰራ ነበር።"

Via:- elias meseret
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ።በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሩስያ ልዑክ ጎንደርን እየጎበኘ ነው

የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክስርቲያን የውጪ ጉዳይ ኃላፊዎችና የሩሲያ የሚዲያ አባላትን ያካተተ የአገሪቱ ልዑክ ጎንደርን እና በውስጧ የሚገኙ ቅርሶችን እየጎበኙ ነው።
ዘጠኝ የሚደርሱት የልዑካን ቡድኑ አባላት ዛሬ ረፋድ ላይ ደብረ ብርሃን ሥላሴን እና የዓፄ ፋሲል አብያተ-መንግሥትን ጎብኝተዋል።

ለሁለት ቀናት በጎንደር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን የባታ ደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ ባሕታ ለማሪያም ካቴድራል የአቋቋም ትምህርት ቤትን ይጎበኛሉ፡፡
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የመንበረ መድኃኒዓለም እና የቁስቋም ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያንንም እንደሚጎበኙ ታውቋል።

ምንጭ፡- አብመድ
@YeneTube @Fikerassefa