በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ ተቀሰቀሰ
በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ እየተካሄደ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎም ዋና ከተማዋ ካይሮን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
ከዕለተ አርብ ፀሎት በኋሏ ዋራቅ በሚባል አካባቢ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ መልዕክት እያሳሙ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ተቃዋሚዎቹ በሀገሪቱ ያለው የኑሮ መመሰቃቀል እና የሙስና መስፋፋት እንዲቆም መጠየቃቸው ተሰምቷል። የጁምዓ ተቃውሞ በደቡብ ግብፅ በምትገኘው ሉክሰር እና በቁስ አካባቢዎች መቀስቀሱም ተጠቁሟል፡፡
በዋና ከተማዋ ካይሮ ደግሞ የ2011 የተቃውሞ እምብርት የነበረውን የታሂር አደባባይ መግቢያ የፀጥታ አካላት እንደዘጉት ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ በአስተዳደራቸው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ ለተቃውሞ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን የፀጥታ አካላት በዋና ከተማዋ የፀጥታ ቁጥጥሩን እንዲያጠናከሩ ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡
Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa

በስኬት ተጀምሮ በስኬት የተጠናቀቀ ግሩም በዓል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶኮስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ በመስቀል አደባባይ ሁልጊዜም ለመስቀል በዓል እንደሚያደርጉት ለአይን በሚያስደምም፣ ለጆሮ በሚጥም፣ መንፈስን በሐሴት በሚያመጥቅ መንፈሳዊ ትርዒት ደምቀው አድምቀዉናል። በዓሉ በታላቅ ስኬት እንዲከበር ሌት ከቀን የለፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን።
በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል።
Via:- ኢንጂነር ታከሉ ኡማ
@YeneTube @Fikerassefa
በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል።
Via:- ኢንጂነር ታከሉ ኡማ
@YeneTube @Fikerassefa
"የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
ስለ ጽዮን ዝም አልልም"
እነኚህ የሽሮ ሜዳ ወጣቶች ከላይ የተጠቀሰውን መልዕክት በቲሸርታቸው ላይ አሳትመው ወደ መስቀል አደባባይ ሲጓዙ በቲሸርታቸው ላይ ባሳተሙት #ፅሁፍ ምክንያት ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ተደርገዋል።

በሰላም ተከብሯል!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የደመራ በዓል በሰላም መከበሩን አስታወቀ።
እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የኃይማኖቱ ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ጎብኝዎች የታደሙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በያዝነው ዓመት በርካታ ህዝብ የታደመባቸው ሃይማኖታዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከበራቸውን ያስተወሰው ኮሚሽኑ የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡በነገው ዕለት የሚከበረው የመስቀል በዓልም በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንጭ:ፋና
@YeneTube @FikerAssefa

#ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ደመራ አልተደመረም!!
በቢሾፍቱ (በደብረ ዘይት) ከተማ የተዘጋጀው ደመራ ሳይበራ ፕሮግራሙ ተዘግቷል። መንስዔውም የቅድስት ኪዳነምህረት ካህናት ወደ ዳመራው በተደመረበት አደባባይ ቤ/ክ የምትጠቀመውን ሰንደቅ አላማ ለምን ይዛችሁ መጣቹህ በማለት በተለያዩ አካላት #ከበሩ ሊመለሱ ችለዋል።
በዚህም ምክንያት ካህናቱ በሩ ላይ ብዙ ሰዓት ከቆሙ በዋላ ሊመለሱ ችለዋል። ይህንንም የሰሙ ወጣቱ አባቶች ሣይገኙ ደመራውን አናበራም በማለት ደመራውን ሣያበሩ በጸሎት ፕሮግራሙ ሊዘጋ ችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌደራል ፓሊስ ከሀገሪቱ ባንዲራ ውጪ ይዞ መገኘት እንደማይቻል ትላንት ያስታወቀ ሲሆን ዛሬ መልሶ የቤተክርስቲያን የራሷን አርማ እና ሎጎ መጠቀም እንደምትችል ማስታወቁ ይታወሳል።
Via:- #Mike_YeneTube

በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ።
መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር።ምእመናኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆኑት ቲሸርቶች 'የቤተክርስትያን ጉዳይ ያገባኛል'፣ የቤተክርስትያን መቃጠልና ጥቃት ይቁም' የሚሉ ፅሁፎች ያለባቸው እንደነበሩ አባ ወልደየሱስ አስረድተዋል።
አራቱ ደግሞ የሌላ ሰው ባጅ አድርገው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሲውሉ ቀሪዎቹ 12 የሚሆኑት ደግሞ ስለት ይዘው ተገኝተዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳሉ።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተወሰዱት ካዛንችዝ ከሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበርና በኋላ እሳቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሃላፊዎች ከነጋገሩ በኋላ 37 በዋስ መለቀቃቸውን መላከሕይወት አባ ወልደየሱስ ተናግረዋል።
ምንጭ:- ቢቢሲ አማርኛ

ትናንት በካታር ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለግማሽ ፍፅሜ እና ፍፃሜ አልፈዋል።
በ17ኛው የዓለም ሻምፕዮና ለኢትዮጵያ የመጀመርያ በሆነው የሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ድርቤ ወልተጂ በተወዳደረችበት ምድብ አራት 02፡02.71 ደቂቃ በመግባት አምስተኛ ሆና አጠናቃለች። ሆኖም የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፕዮኗ ከተሸናፊዎች ፈጣን ሰዓት ባስመዘገበ በሚለው ህግ ነገ መስከረም 17/2012 ዓ.ም ለሚካሄደው ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።
በሴቶች 3000ሜ መሰናክል የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ መቅደስ አበበ የግሏን ፈጣን ሰዓት በማስመዝብ ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚደረግው የፍፃሜ ውድድር አልፋለች።በወንዶች 5000ሜ ያለፈው የዓለም ሻምፕዮኑ ሙክታር ኢድሪስ፣ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ጥላሁን ሃይሌ፣ እንዲሁም ሰለሞን ባርጋ ለፍፃሜ ውድድሩ አልፈዋል። አባዲ ሃዲስ አልተሳካለትም።
Via VOA

“መደበኛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ማንኛውም ነገር ሊፈጠር ይችላል።
ከጎረቤቷ ሰባት እጅ የምታንስ አገር የሚኖራት ሁለት ምርጫ ነው። አንድም ማፈግፈግ አሊያም ለነጻነት እስከ ሞት መዋጋት። እንዋጋለን። የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቀ አገር እስከ ፍጻሜው የተዋጋ እንደሆነ ጣጣው ከድንበር ይሻገራል፣ ፍዳው ለዓለም ይተርፋል” የፓኪስታኑ ጠቅላይ ምኒስትር ኢምራን ክኻን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ሕንድን፣ ፕሬዝዳንት ናሬንድራ ሞዲን አጥብቀው በነቀፉበት ዓለምን ካስጠነቀቁበት ንግግራቸው
Via Eshete Bekele

🔥1
በአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው።
የከፋ የደህንነት ስጋት ያለባት ሀገሪቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ሰላማዊነት እንዲያስጠብቁ አሰማርታለች።ሆኖም ድምፅ መስጠት በተጀመረ በአጭር ጊዜያት ውስጥ በካንደሃር በሚገኝ የድምፅ መስጫ ጣቢያ አቅራቢያ ፍንዳታ ተከስቷል።ምርጫው ለሁለት ጊዜ ተራዝሞ ነው ዛሬ እየተካሄደ የሚገኘው። የአሁኑ ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ እና የቀድሞ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላህ አብዱላህ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ናቸው።37 ሚሊየን ዜጎች ያላት አፍጋኒስታን 10 ሚሊዮኑ ድምፅ ለመስጠት ተመዝግበውባታል።ጥቃት ይደርሳል በሚል ስጋት ድምፅ መስጠት ከሚችሉ ዜጎች መካከል በምርጫው የተመዘገቡት ግማሾቹ ብቻ ናቸው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ/Fana

የጤፍ ቢራ በአሜሪካ ተመረተ ሰኞ ገበያ ላይ እንደሚውል ሰምተናል።
በኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለቤትነት በአሜሪካ አገር የተቋቋመው ንጉስ ቢራ ኩባንያ በአሜሪካ ከተመረተ ጤፍ የተዘጋጀ ቢራ ለገበያ አቀረበ። ሰኞ መስከረም 19 ለሚጀምረው ስርጭት 19ሺ 200 ጠርሙስ የጤፍ ቢራ የተዘጋጀ መሆኑ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከቢራ ጠማቂው የኩባንያው ቺፍ ፋይናስ ኦፊሰር መኩሪያ ንጉሴ ሰምታለች።
ኩባንያው ቢራው በሚጠመቅበት ቦታ ለተጠቃሚዎች ምርቱን በትኩሱ ለማቅረብ የሚያስችል በመዝናኛ ማዕከል (brew pub)ና የሙዚቃ ኮንሰርት አደራሽ ከፋብሪካው ጀርባ የመግንባት እቅድ እንዳለሁ ገልፀዋል።
Via:- ከማለዳ ጋዜጣ ላይ በየኔቲዩብ የተፃፈ