YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለው የኪሎ ሜትር ገደብ ለአጭር ጊዜ ብቻ መነሳቱ ተነገረ፡፡

ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሀገር አቋርጠው የሚሄዱ ተማሪዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይገጥማቸው በሚል በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለው የኪሎ ሜትር ገደብ ለአጭር ጊዜ መነሳቱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት የተለያዩ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚደራረቡበት በመሆኑ በትራንስፖርት አቅርቦቱ እጥረት ሲያጋጥም ነበር ተብሏል፡፡

አሁን ላይም የትራንስፖርት አቅርቦቱ እንዲሻሻል የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከመስረከም 10/2012 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30/2012 ድረስ ብቻ በኪሎ ሜትር ሳይገደቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

ተማሪዎች የሚጓዙባቸው የክልልና የከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ተቋማት ባለሙያዎችን በመመደብም ተማሪዎች ባልተቆራረጠ ሁኔታ በቀጥታ ወደ ትምህርት ተቋሞቻቸው እንዲደርሱ ትብብር እንዲያደርጉ ሲልም የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጠይቋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተቀመጠና፣ ከዚህ ቀደም ሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች 150 ኪሎ ሜትር ለመለስተኛ ከ150 እስከ 250 ኪሎ ሜትር እና ለሀገር አቋራጭ ከፍተኛ ተሽከርካሪዎች ከ250 ኪሎ ሜትር በላይ ገደብ ማስቀመጡን እና በስራ ላይ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

በተጨማሪም በመናኸሪያዎች ውስጥ ከሚገኙ ማህበራት ጋር በመተባበር በተለይ ለመስቀል በዓል ወደተለያዩ ክልሎች ለሚጓዙ ዜጎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይኖር ከመደበኛ ስምሪቶች በተጨማሪ ሌሎች ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያደርግ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ሰምተናል፡፡

Via:- Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ከ30 በላይ አሽከርካሪዎችና ሰራተኞች ባደረጉት የስራ ማቆም አድማ ታስረው በዋስ ተለቀዋል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዲያ የዘመን መለወጫ “ያሆዴ መስቀላ” በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በሆሳዕና ከተማ ተከበረ።

በዓሉን ለመታደም ከሀዲያ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ከተለያዩ አጎራች አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎችም ታድመዋል፡፡የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ “የያዴ መስቀላ” በዓል ከጨለማ ዘመን ወደ ብርሃን መሸጋገሪያ ላይ መደረሱን የሚበሰርበት በመሆኑ የሀድያ ህዝቦች 2012ን በአዲስ ተስፋና ብልፅግና ለመቀበል ስንቅ የሚሰንቅበት ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ ⬆️ ሀዋሳ ⬆️

ዩንቨርስቲ ለሚገቡ እና ከዚህ ቀደም ለገቡ ተማሪዎች!!

@YeneTube @Fikerassefa
ሰበር ዜና | የፕሪምየር ሊጉ አዲሱ ፎርማት ውድቅ ሆነ!

ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ከፍሎ እንዲደረግ የወሰነው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።
የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን የዘጠኙ የክልልና የ2ቱ ከተማ መስተዳድር እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ከብዙ ውይይቶች በኋላ ነው ውሳኔው ውድቅ የሆነው።እንደ ምክንያት የቀረበውም ጥናት ያልተጠናበት እና የክለቦችን ይሁንታ ያላገኘ በመሆኑ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚለያይ በመሆኑ እንደሆነ ሰምተናል።በቀጣይ ሊጉ በምን መልኩ ይቀጥላል የሚለው ጉዳይ ክለቦቹ ተመካክረው እንዲወስኑ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

Via Soccer Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው በ2011 በጀት ዓመት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤በ1 ሺህ 393 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ19 ሰዎች ላይም የግድያ ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በተጠቀሰው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ በተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

በነዚሁ ግጭቶች ሳቢያም ከሁለት ቢሊየን በላይ ብር የሚገመት የዜጎች ንብረት የወደመ ሲሆን፤1 ነጥብ 2 ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።በዚህ ግጭት የተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶ ከእነዚህ መካከል 645 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ሲሆን 667 ተጠርጣሪዎች እንዳልተያዙ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳና በመተክል ዞን ፤በጎንደርና አካባቢው በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ፤በሰሜን ሸዋ አስተዳደር እንዲሁም በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ከማሻ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎችና የዚሁ ዞን አጎራባች በሆነው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞን በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ በተፈፀመ ብጥብጥና ሁከት በአሶሳ ዞን አራት ወረዳዎች ውስጥ በኦሮሚያና በበርታ ብሄረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተሳታፊ ከነበሩ 1 ሺህ 647 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 185 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Via Federal Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa
Official!
⬆️⬆️
በዘንድሮው ዓመት አዲስ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡም ሆነ ነባር ተማሪዎች የሚከተለውን ፎርም ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በወረዳቸው በሚገኝ ትምህርት ፅ/ቤት ተሞልቶና ተፈርሞ እንዲሁም ማህተም ተደርገበት በዩኒቨርስቲ የምዝግባ ወቅቶች ይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ይሄንን ካላቀረቡ እንደማይመዘገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536
 
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 68.3 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያለበትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በግድቡ የውሃ አሞላል እና በሚለቀቀው የውሃ መጠን ዙሪያ ግብጽ ያቀረበችው የተለዬ አቋም የግንባታ ሥራውን ወደ ኋላ እንደማያስቀረውም ነው ተናግረዋል።እስካሁን ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ግድቡ በፈረንጆቹ 2024 እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ግንባታዉ በታሰበዉ ጊዜ ለማጠናቀቅ የእስካሁኑን ጨምሮ ከ130 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስወጣ ይጠበቃል።

የሁለቱ ቅድመ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች የብረታ ብረት ገጠማና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራም በግማሽ የተጠናቀቀ ሲሆን ግድቡ ሲጠናቀቅም በዓመት በአማካይ 15 ሺሕ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት ሀይል እንደሚያመነጭ አብርሃም በላይ ተናግረዋል።በተጨማሪ የኮርቻ ግድብ ስራው 96 በመቶ፣ የጎርፍ ማስተንፈሻ ስራው 96 በመቶ፣ የሀይል ማመንጫ ክፍል ስራው 70 በመቶ፣ የዋና ግድብ ስራው 80 በመቶ ተጠናቆ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 68.3 በመቶ መድረሱን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
100 ተጨማሪ አዳዲስ አውቶቢሶች ወደ ስራ ሊገቡ ነው፡፡

አውቶቢሶቹ በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል አስተዋፆኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ አውቶቢሶቹ ከነገ ማለትም መስከረም 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ መግባት ይጀምራሉ፡፡በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የብዙሃን ትራንስፖርት አንበሳ እና ሸገር ባስ አገልግሎትን ለማሻሻል በጥናት ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ከዚህ ተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ አውቶቢሶች ከውጪ ለማስገባት እና የትራንስፖርት ስምሪቱን ዘመናዊ የሚያደርግ አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ ነው፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል መንግስት የመስቀል በአልን አስመልክቶ ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ላሉ አመራሮች የእራት ግብዣ አደረገ።

እንደሚታወቀው የደቡብ ክልል የማዳበሪያ ብድር 4.5 ቢሊየን ብር አለበት።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራት ዛሬ ባወጡት መግለጫ ከመንግሥት አካላት ጋር የተነጋገሩባቸውንና የተስማሙባቸውን ነጥቦች ገልጠዋል፡፡ ሕይወታቸውን ላጡ ካህናት፣ ለተዘረፉና ለተቃጠሉ መንግሥት ካሳ እንዲከፍል የሚለው ነጥብ አንዱ መወያያ እንደነበር ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገጹ አስታውቋል፡፡ መግባባት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ለመፍታትም ጊዜ ገደብ ተቆርጧል፡፡ በክልሎች የጋራ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ እና መደበኛ ነባር ቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እንደሚከተለው አሳውቋል። ⬆️

@YeneTube @Fikerassefa
ትናንትና በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ወረዳ በደረሰው የመኪና አደጋ የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን የአማራ ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊው ብስክሌተኛ ሙሉ ክንፈ በሶስት ዓመት ውል የፈረንሳዩ ብስክሌት ክለብ ዴልኮ ተቀላቀለ፡፡ ከዓዲግራት የተነሳው ብስክሌተኛው ሙሉ በትግራይ ለጉናና ትራንስ ተጫውቷል፡፡

Via ሚልዮን ኃ/ስላሴ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች የማይስ አሸናፊዎች (MICE Champion Award) ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

ኢ/ር ታከለ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ ዲያስፖራ ቱሪዝም ኮንፍረንስ ላይ ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል–ሲሲ ኢትዮጵያ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ለመገንባት ስትነሳ አመርቂ ጥናት አልሰራችም ሲሉ ከሰዋል። በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር ፈቅ ሳይል መቀጠሉ በቀጠናው መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ኢንስቲትዩት ቴክኖሎጂ ፋክልቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች መታወቂያ እድሳት ከዛሬ ማክሰኞ 13/01/2012 እስከ አርብ 16/01/2012 መሆኑን ብቻ በጥብቅ ያሳስባል።

#ሬጅስትራር
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536