YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ይሄ ኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት አርብ ዕለት 9:30 የተነሳ ፎቶ ነው አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ካዛንቺስ ወደ ሚገኘው ኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ጎራ አልኩኝ በር ላይ ስደርስ ተዘግቷል 9:30 ላይ ለምኜ ፍጣን መልክት ነው ወደ ሀዋሳ ብዬ EMS ትኬቱን ቆረጥኩ እንደዛ ተንደርድሬ የሄድኩት መልክት ለነገ እንዲደርስልኝ ነበር ነገርግን 270 ኪሎ ሜትር የምትርቀው ሀዋሳ መልክቱ በ3 ቀን ውስጥ እንደሚደርስ አበሰሩኝ።

ጥፋት አንድ 9:30 በር መዝጋታቸው ሁለት ደግሞ ፈጣን ተብሎ በሶስት ቀን የሚደርስ መልክ ኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ብቻ ነው የሚሰጠው።

ምሳሌ :- DHL ከቻይና በሁለት ቀን ውስጥ ያደርሳል ወደ ኢትዮጵያ
@YeneTube @Fikerassefa
ነገ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሚደርሰውን ቃጠሎ እና በቄሶችና በዲያቆናት ላይ የሚደርሰው ግፍ በመቃወም ባህርዳርን ጨምሮ በተለያዩ የአምሓራ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋሉ።

@YeneTube @Fikerassefa
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ከሥልጣን እንዲለቁ ከተካሔዱ ድንገተኛ የተቃውሞ ሰልፎች በኋላ በትንሹ 74 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

@YeneTube @FikerAssefa
የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅትየነበራቸውየአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸውየአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።አልሸባብ እና አይ ኤስ የሽብር ቡድኖቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመላክ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ እንዲሁም የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

ተጨማሪ👇👇👇👇

https://bit.ly/2kJp4zT

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወሻ የሚዘጉ መንገዶች!

ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶች፡-

📌 ከቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
📌 ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቄራ
📌 ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ቡልጋሪያ ማዞሪያ
📌 ከሳርቤቶች አደባባይ ወደ ቄራ
📌 ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
📌 ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ጎፋ ማዞሪያ
📌 ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር
📌 ከቂርቆስ ወደ ገነት ሆቴል
📌 ከመስቀል ፍላወር ወደ አጎና ሲኒማ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው
📌 ከኡራኤል ወደ ጦርኃይሎች አደባባይ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች

ካዛንቺስ->አራት ኪሎ->ሸራተን አዲስ-> ሃራም ቤሆቴል->ጎማ ቁጠባ
📌 ከፒያሳ ወደ ቦሌ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ሃራምቤ
ሆቴል->ፍልውሃ->ካዛንቺስ->ኡራኤል->አትላ ስሆቴል->ቦሌ
📌 ከሳርቤት ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
መካኒሳ አቦ መታጠፊያ->መድሃኒት ፋብሪካ->ሦስት ቁጥር ማዞሪያ-> ብስራተ- ገብርኤል አቅጣጫ->በካርል አደባባይ->ቴሌ->ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት
📌 ከፒያሳ ሳሪስ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች

ቸርችል ጎዳና->ጥቁር አንበሳ->ኦርማ ጋራዥ->በዘውዲቱ ሆስፒታል-> በፍልውሃ->በኡራኤል
📌 እንዲሁም ከፒያሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር ያለውን መንገድ በአማራጭነት መጠቀም ይቻላል።

አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመሮች 991 ፣6727 ፣816 እና በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ011-1-01-02-97

@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ ከ70 በላይ በሚሆኑ የአለም ሀገራት የደጋፊ ማህበር እያደራጀ ነው!

ኢዜማ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ከ70 በላይ የአለም ሀገራት የአለማቀፍ የድጋፍ ማህበር እያደራጀ መሆኑን ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ከተመሠረተ 5 ወራት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሀገር ውስጥ በ #400 የምርጫ ወረዳዎች አባላትንና ደጋፊዎችን አደራጅቶ ለቀጣዩ ምርጫ ዝግጁ ማድረጉን በዚሁ መግለጫው ያስታወቀ ሲሆን፤ የአለማቀፍ ድጋፍ ማህበሩንም የሚያደራጀው በሀገር ቤት የተጠቀመውን የማደራጃ ስልት ተጠቅሞ መሆኑን አስገንዝቧል:: ኢትዮጵያውያን ይኖሩባቸዋል ተብለው በተለዩ ከ70 በላይ ሀገራት በየከተሞቹ የደጋፊ ማህበር ም/ቤት የሚቋቋም ሲሆን፤ የእነዚያ ም/ቤቶች አባላት የሆኑ ግለሰቦች አመራርነት ተመርጠው የክፍለ አለም ደጋፊ ማስተባበሪያ የሚኖረው አደረጃጀት ነው ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#Onthisday

ታሪክ በዛሬ እለት ቺ-ቺ ኋላ ላይ ጂ-ጂ በመባል የሚታወቀው (ታይዋን) የመሬት መንቀጥቀጥ ልክ ከዛሬ 20 በፊት በ1999 ነበር የተከሰተው 2415 ሰዎች ሲሞቱ ለ11305 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል እንዲሁም ከ300 ቢሊየን ዶላር በላይ አውድሟል በተጨማሪ ከ100 ሺ ሰዎች በላይ አፈናቅሏል።

#Factcheck #ታሪክበዛሬዋእለት
@YeneTube @Fikerassefa
#Onthisday

አርሜንያ ከሶቬት ዩንየን በዛሬው እለት በ 1991 መስከረም 10 ነበር የተለያየችሁ።

#ታሪክበዛሬዋዕለት #Factcheck
@YeneTube @Fikerassefa
ግብጽ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ የሱዳንን ድጋፍ ጠየቀች!

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲና የሱዳኑ ጠ/ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በካይሮ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ መምከራቸውን የዘገበው አሶሼትድ ፕሬስ፤ በህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ላይ ግብጽ የያዘችውን አቋም የሱዳን መንግስት እንዲደግፍ የግብፁ ፕሬዚዳንት ማግባባታቸውን ጠቁሟል፡፡ የሱዳን አዲሱ መንግስት በበኩሉ የተለየ አዲስ አቋም አለመያዙ ታውቋል፡፡ የግብጽ መንግስት ከአዲሱ የሱዳን የሽግግር መንግስት ጋር ጠንካራ ወዳጅነት የመፍጠር ፍላጐት እንዳለው አልሲሲ ማስታወቃቸውና ሀገራቸው የአሜሪካ መንግስት ሱዳንን ለአሸባሪዎች ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ እንድታወጣ መጠየቋን አስረድተዋል ተብሏል፡፡

ባለፈው እሁድና ሰኞ በካይሮ በግድቡ ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ለመደራደር የተገናኙት የግብጽ፣ ሱዳንና የኢትዮጵያ ተወካዮች፣ ግብጽ ባቀረበችው አዲስ የውሣኔ ሃሳብ ምክንያት መሰናከሉ የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያም አዲሱን የግብጽ ሃሳብ ‹‹ሉአላዊነቴን የሚዳፈር ነው›› ስትል ውድቅ አድርጋዋለች፡፡ግብጽ በዋናነት ሶስት ጉዳዮችን ለውይይቱ ያቀረበች ሲሆን፤ የግድቡ የውሃ አሞላል በ7 አመት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ኢትዮጵያ በየአመቱ ከግድቡ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃ እንድትለቅ የሚያስገድድ መሆኑ ታውቋል፡፡

‹‹በየአመቱ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃ ለግብጽ ይለቀቅ የሚለው የሀገርን ሉአላዊነት በእጅጉ የሚዳፈር ነው›› ያሉት የውሃ መስኖ እና ኢነርጀር ሚኒስትሩ ኢ/ር ስለሺ በቀለ፤ ‹‹በግብጽ በኩል የቀረበው ሃሳብ ግድቡ ላይ የኢትዮጵያ ጥቅምና የመወሰን መብቷ በግብጽ ይሁንታ እንዲመሠረት የሚያደርግ አደገኛ የድርድር ሃሳብ ነው›› ብለዋል:: ሃሳቡም መቼውንም ቢሆን በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አይኖረውም” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ አሞላል ሂደት በ3 ዓመት የመጨረስ ሃሳብ እንዳላት የተገለፀ ሲሆን፤ ይህን ሃሳብ በጫና ለማስቀየር ግብጽ አለማቀፍ ማህበረሰብ ጫና እንዲፈጥር የማግባባት ስራ እየሰራች መሆኑን ‹‹ኢጅንት ቱዴይ›› የተሰኘው የድረ ገጽ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በሶስተኛነት ግብጽ ያቀረበችው በግድቡ ግንባታ ላይ ግብፃውያን ባለሙያዎች እንዲሳተፉ የሚጠይቅ ሃሳብ መሆኑም ታውቋል፡፡

ሶስቱ ሀገራትም ያቋረጡትን ድርድር ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚቀጥሉ ታውቋል፡፡ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ አንዳንድ የውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሚያቀርቡት ዘገባ በተዛባ መረጃ የታጀበ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር በቀለ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሚዲያዎቹን በማስተባበር ግድቡን ቦታው ድረስ ተገኝተው እንዲመለከቱ የሚያስችል መርሃ ግብር እያመቻቸ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

Via Addis Admas
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በክረምት እድሳት ሲደረግለት በቆየው የቦሌ ህብረተሰብ ትምህርት ቤት በመገኘት የእድሳቱን መጠናቀቅ በማብሰር ዩኒፎርም እና የተሰበሰቡ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለተማሪዎች አበርክተዋል፡፡

የቦሌ ህብረተሰብ ትምህርት ቤት በ2012 የትምህርት ዘመን ከመዋለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ይሆናል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በተያዘው የትምህርት ዘመን 300ሺ የሚሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በምገባ መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ዘንድሮ ስድስት የስኳር ፕሮጀክቶችን ወደ ግል ያዘዋውራል።

ስኳር ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክት ውስጥ ስድስቱን ወደ ግል ለማዘዋወር የዋጋ ግመታና ተያያዥ ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት በስሩ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ለመሸጥ ያወጣው የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያ እንደሌለ ለማስገንዘብ በላከው መግለጫው፤ በ2012 ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር የታቀዱ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ አለማቀፍ እውቅና ያለው የውጭ አማካሪ ኩባንያ ቀጥሮ እያስጠና መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

ከጥናቱ ጐን ለጐን መንግስት ከባለሀብቶችና ኩባንያዎች ጋር የሚያደርገውን ድርድር እንዳጠናቀቀ ወደ ግል ይዞታ የሚዘዋወሩ ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የትኞቹ እንደሆኑ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ኮርፖሬሽኑ በመግለጫው ስታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የወንጂ ሸዋና የመተሃራ ስኳር ፋብሪካዎችንም ሆነ ሌሎቹን ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ከየትኛውም ባለሀብት፣ ኩባንያ ወይም ማህበር ጋር የተደረገ ይፋዊ ድርድርም ሆነ ስምምነት አለመኖሩንም ኮርፖሬሽኑ አስገንዝቧል፡፡ መንግስት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችንና ፋብሪካዎችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር ያሳለፈውን ውሣኔ ተከትሎ፣ ለባለሃብቶችና ኩባንያዎች በቀረበው የመረጃ ጥያቄ መሠረት፣ በርካቶች በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጐት ማሳየታቸውን የኮርፖሬሽኑ መግለጫ አመልክቷል፡፡

Via Addis Admas
@YeneTube @FikerAssefa
የባህርዳር ወጣቶች ለነገው ሰልፍ ያዘጋጁት መስቀል 15 ሜትር ርዝመት እንዲሁም ጎኑ 5 ሜትር ስፋት ያለሁው ሲሆን ነገ በከተማ ይታያል ተብሎ ይጠበቃል።

@YeneTube @Fikerassefa
ኤርትራ ባለፉት 23 አመታት የዝሆኖቿ ቁጥር ከ15 ወደ 250 ከፍ ማለቱን አስታውቃለች። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር እንደሚለው በላዕላይ ጋሽ 44 ሺህ ሔክታር መሬት ለዝሆኖች ተከልሏል። የውሐ እጥረትን ለመፍታት አነስተኛ ግድቦች ለመገንባት ታቅዷል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
#ኢሬቻ_ለፍቅር #ኢሬቻ_ለሰላም #ኢሬቻ_ለአንድነት

ኢሬቻ የሚከበረው ዋቆ ወይንም ፈጣሪን ማመስገኛ በዓል ሲሆን በኢትዮጵያ በኦሮሞ ማህበረሰብ ይከበራል። የዘንድሮን ኢሬቻ ለየት የሚያደርገው በኢትዮጵያ መዲና በሆነችሁ አዲስ አበባ የሚከበር ይሆናል የሀገር ውስጥ የሚዲያ አውታሮች እንደዘገቡት ኢሬቻ ከ150 አመት ብኃላ ወደ ቀድሞ መከበሪያ ቦታ(አዲስ አበባ) ተመልሷል ብለዋል።

#Irreecha_kan jalala, #irreecha_kan nagaya, #irreecha_kan tokkumma

Ayyaanni Irreecha kan kabajamu Waaqa Uumaa hunda irreeffachu yoo ta'u innis kan kabajamu akka aadaa Oromootini. Irreechi bara kana kan adda isa taasisu akka Ityoophiyaatti magaala guddoo Finfinneetti kabajamu yoo ta'u akka miidiyaan biyyoolessa gabaasetti waggaa 150 booda bakka dura itti kabajamutti deebi'ee akka sagantaan kun raawwatamu Hayyoonni Abbooti Gadaa ibsaniiru.


#ኢሬቻ2012 #FactCheck
@YeneTube @FikerAssefa
You did not choose your:-

1 birthplace
2 skin color
3 birth parents, family
4 birth gender
5 birth language
6 birth name
7 ethnicity
8 born abilities

You can choose to be:-

1 kind
2 generous
3 honest
4 grateful
5 respectful
6 optimistic
7 humble
8 teachable
9 faithful
10 happy

@Yenetube @Fikerassefa
የኢሬቻን በአል ምክንያት በማድረግ የሚካሄደው፤ ኢሬቻ ለሰላም ሩጫ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በአሁን ሰአት እየተጀመረ ይገኛል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በወልድያ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና የሃይማኖት አባቶች ሠላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሠላማዊ ሠልፉ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን በግዛቶቿ ላይ ጥቃት የሚፈፅም ማንኛውንም አገር «የጦር አውድማ» እንደምታደርግ የአገሪቱ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን አስጠነቀቁ።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሑሴን ሳላሚ ማስጠንቀቂያ የተደመጠው በሳዑዲ አረቢያ የድፍድፍ ነዳጅ ማቀነባበሪያዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ አሜሪካ ወደ ቀጠናው ተጨማሪ ወታደሮች ለመላክ መወሰኗን ካሳወቀች በኋላ ነው።አርማኮ የተባለው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኩባንያ በሚያስተዳድራቸው ሁለት የድፍድፍ ነዳጅ ማቀነባበሪያዎች ላይ ለተፈጸሙት ጥቃቶች የየመን ሑቲ አማፅያን ኃላፊነት ቢወስዱም አሜሪካ ግን ኢራንን ተጠያቂ አድርጋለች። የአሜሪካ መከላከያ ምኒስትር ማርክ ኤስፐር ከሳዑዲ አረቢያ በቀረበ ጥያቄ መሠረት አገራቸው ወታደሮች ወደ አካባቢው ለማሰማራት መወሰኗን አስታውቀዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች በባህርዳር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በባህርዳር ሀገረ ስብከት የተጠራው ሰልፍ ዛሬ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡በሰልፉ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች በቤተክርስቲያን፣ በምእመናን እና በአገልጋይ አባቶች ላይ እየደረሰ ያለው በደልና ጥቃት እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በዘር ለመከፋፈል እየተካሄደ ባለው ሙከራ ላይ ቤተክርስቲያኒቱ ቀኖናዊ እርምጃ እንድትወስድ እና መንግስትም በበኩሉ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡ በባህርዳር ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ አብያተክርስቲያናት የተውጣጡ ምእመናን በዝማሬ እና በቤተክርስቲያኑ የተለያዩ ስርአቶች በመስቀል አደባባይ ተሰባስብው ጥያቄዎቻቸውን እያቀረቡ ነው።ሰልፉ በደብረማርቆስ ከተማ እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ምንጭ: ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa