YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዱከም ቀስተ ዳመና ስፖንጅ ፋብሪካ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ እስካሁን #በቁጥጥር ስር #አልዋለም

በፊንፊኔ ዙሪያ ዱከም ከተማ የሚገኘው ቀስተዳመና ስፖንጅ ፋብሪካ ዛሬ ረፋድ ላይ ነበር ምክንያቱ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት እሳት አደጋ የደረሰበት።

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት አደጋውን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ነው።

ለፋብሪካው ቅርበት ያላቸው የአቃቂ ንፋስ ስልክ ቄራ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው አቅንተው አደጋውን ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ናቸው ብለዋል።

Via :- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa