YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከከፋ ህዝብ ተወካዮች ጋር በቦንጋ ከተማ ባደረጉት ውይይት ተወካዮቹ ከክልል አወቃቀር: የመንገድ: ውኅ: ጤናና ቤተ መጽሀፍት የመሳሰሉ የመሰረተ ልማት: የሀብት አጠቃቀም: የሥራ አጥነት: የኢንቨስትመንትና ሌሎችም ጥያቄዎች አንስተዋል::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የተነሱ ጥያቄዎችን በምክክር አቅም በፈቀደ መጠን ለመመለስ ቃል ገብተዋል:: አቅም ያላቸው አልሚ ባለሀብቶች እንዲመጡ መሥራትና በመተባበርና በስልጣኔ የመንቀሳቀስን አስፈላጊነት በማንሳት ተፈጥሮንና ከባቢን ለመንከባከብ ያሳዩትን ቆራጥነት አድንቀዋል::

የክልል አደረጃጀት ለውጥ የሁሉም ጥያቄ መልስ አይሆንም ያሉት ጠ/ሚሩ ተያያዥነት ያላቸው አማራጭ አሰራሮች ማየት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል:: ሲያጠቃልሉም በትብብርና በመደመር በመሥራት ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል::

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ።

ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው።ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል።ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።ይሁንን የፕሬዘዳንቱ ንግግር እየደረሰባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ነው የሚል ትችት እየደረሰባቸው ይገኛል።

ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ ለአገር ውስጥ ፖለቲካ የመጠቀም ፍላጎት ስላላቸው ነውም እየተባሉ ይገኛሉ።ፕሬዘዳንት አልሲሲ ስልጣናቸውን እስከ 2034 ድረስ የሚያራዝምላቸውን ህገ መንግስት በአገሪቱ ፓርላማ ማጸደቃቸውና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ትችቶችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።ግብጽ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ጊዜ ወደ ሰባት ዓመት ከፍ ይበልልኝ፣የግድቡን ሁኔታ የሚከታተል በካይሮ እና በአዲስ አበባ ቢሮ ይከፈትና ሌሎች ጥያቄዎችን ማንሳቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የግብጽን አዲስ አቋም ፈጽሞ እንደማትቀበልና ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የከፋ ጉዳት እንደማያደርስ በተደጋጋሚ አስታውቃለች።የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን ብሔራዊ የቴክኒክ አማካሪ በያዝነው ሳምንት በካይሮ ወይም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በኢትዮጵያና ሱዳን በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል።

ባሳለፍነው ሳምንት የሱዳይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ከአዲሷ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በካርቱም ተወያይተዋል።ከዚህ በፊት ሱዳንና ኢትዮጵያ በህዳሴው ገድብ ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ያልተመቻት ግብጽ ውይይቱን በራሷ ፍላጎት ለማስኬድ የተለያዩ አማራጮችን በመከተል ላይ ትገኛለች።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ባለፈው ሳምንት ከዚህ አለም በሞት በተለዩት በቀድሞው የዝምባቢዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ፡፡

በሀራሬ በሚገኘው ብሄራዊ የስፖርት ስታዲየም በተካሄደው ስነ ስርዐትላይ የሀገራትና የመንግስታ መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝደንቶችና በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሽዎች የሚቆጠሩ የነጻነት ታገዮችን በማሰልጠን ዝምባቢዌ ከቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ የራሷን ሚና መጫወቷ ይታወቃል፡፡ ይህ ሁኔታም በተለይም ሮበርት ሙጋቤ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥብቅ እንዲሆን አድርጓል፡፡

Via President Office
@YeneTube @FikerAssefa
በደለል ምክንያት ተዘግቶ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ተከፈተ።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ሆራ ድልድይ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቁም ድንጋይ አካባቢ ሌሊቱን የዘነበ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ነበር መንገዱ የተዘጋው።መንገዱም እስከ ረፋዱ 4:50 ድረስ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ወይም ከደሴ መስመር ወደ አዲስ አበባ የሚያመጣው ዋናው መንገድ ተዘግቶ ቆይቷል።ይህንን የአካባቢው ነዋሪዎች፣አሽከርካሪዎችና የመንግስት ተቋማት ባደረጉት ርብርብ መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተከፍቷል።

ምንጭ:Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ።

ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው።

ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል።

ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።

ይሁንን የፕሬዘዳንቱ ንግግር እየደረሰባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ነው የሚል ትችት እየደረሰባቸው ይገኛል።

ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ ለአገር ውስጥ ፖለቲካ የመጠቀም ፍላጎት ስላላቸው ነውም እየተባሉ ይገኛሉ።

ፕሬዘዳንት አልሲሲ ስልጣናቸውን እስከ 2034 ድረስ የሚያራዝምላቸውን ህገ መንግስት በአገሪቱ ፓርላማ ማጸደቃቸውና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ትችቶችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።

ግብጽ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ጊዜ ወደ ሰባት ዓመት ከፍ ይበልልኝ፣የግድቡን ሁኔታ የሚከታተል በካይሮ እና በአዲስ አበባ ቢሮ ይከፈትና ሌሎች ጥያቄዎችን ማንሳቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የግብጽን አዲስ አቋም ፈጽሞ እንደማትቀበልና ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የከፋ ጉዳት እንደማያደርስ በተደጋጋሚ አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን ብሔራዊ የቴክኒክ አማካሪ በያዝነው ሳምንት በካይሮ ወይም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በኢትዮጵያና ሱዳን በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል።

ባሳለፍነው ሳምንት የሱዳይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ከአዲሷ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በካርቱም ተወያይተዋል።

ከዚህ በፊት ሱዳንና ኢትዮጵያ በህዳሴው ገድብ ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ያልተመቻት ግብጽ ውይይቱን በራሷ ፍላጎት ለማስኬድ የተለያዩ አማራጮችን በመከተል ላይ ትገኛለች።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በሰኔ 15 ግድያ በሽብር የተጠረጠሩ 21 ግለሰቦች አካልን ነፃ የማውጣት ክስ ለፍርድ ቤት አቀረቡ።

በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከተሞች ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከተፈጸመው ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ፣ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ 21 ግለሰቦች አካልን ነፃ የማውጣት ክስ ለፍርድ ቤት አቀረቡ፡፡ሁሉም ተጠርጣሪዎች ታስረው የሚገኙት በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እስረኛ ማቆያ ጣቢያ ሲሆን፣ የጠረጠራቸው ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ነው፡፡

ተጨማሪ👇👇👇👇

https://bit.ly/2kipay9

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሬቻ!!

ኢ/ር ታከለ ኡማ የፊታችን መስከረም 24 2012 , በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረውን የእሬቻ በአል በተመለከተ ከአባገዳዎች፣ ቄሮዎችና ከፎሌ ከ ተውጣጡ ጋር ውይይት አድርገዋል:: በዓሉ ደማቅ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲኪያሄድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም አባገዳዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል::ለዚህም እየተደረጉ ባሉ ቅድመዝግጅቶች ዙሪያ ተወያይተዋል:: የከተማ አስተደደሩም የእሬቻ በአል ከምንግዜውም በላይ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል::የእሬቻ በአል የፊታችን መስከርም 24 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።

ምንጭ: የከንቲባው ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የእርዳታ ጥሪ!!
⬆️⬆️ከላይ በፎቶው ላይ የምትመለከቷት እህታችን ቤቴልሄም አሽኔ ትባላለች ፡፡

በጅማ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ አመት ተማሪ በነበረችበት ወቅት ባጋጠማት የነርቭ ህመም ግማሽ የሰውነቷን ክፍል ሙሉ በሙሉ ማንቀሳቀስ ተስኗት ( ፓራላይዝድ ሆና ) ትምህርቷንም አቋርጣለች ፡፡

ስለዚህ ቤተሰቦቿ መድሀኒቱንና የህክምናውን ወጪ ለመሸፈን በመቸገራቸው የእኛን እርዳታና ትብብር ይሻሉ።

ስለዚህ እህታችን ቤቲ ሙሉ ጤንነቷ ተመልሶ ወደ ትምህርት ገበታዋ መመለስ እንድትችል ሁላችንም ብዙ ትንሽ ሳንል በቻልነው አቅም እንድንረዳት በፍቅር እንጠይቃለን ፡፡

ቤቲን ለመርዳት ከዚህ በታች ያለውን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይጠቀሙ

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000183177293
ገመቹ ተሾመ

#share #share
ከስምንት ሚሊዮን በላይ የአስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተመድ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊና የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ አስታወቁ፡፡
የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ማርክ ሎውኮክ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ምግብ፣ መጠለያ፣ መድኃኒትና ሌሎች አስቸኳይ ዕርዳታዎች ያስፈልጓቸዋል ብለዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ድርቅን፣ ጎርፍን፣ የወረርሽኝ በሽታዎችንና ሚሊዮኖችን ከቤቶቻቸው ያፈናቀሉ የብሔር ግጭቶችን ጨምሮ ተደጋጋሚና ዘርፈ ብዙ ሰብዓዊ ችግሮችን መቋቋም ይኖርባታል፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡እ.ኤ.አ. በ2019 የኢትዮጵያ በሰብዓዊ ዕርዳታ ጥያቄ ምላሽ ዕቅድ መሠረት፣ ቁጥራቸው ከላይ የተገለጸው የአስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች 1.3 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ማግኘት የተቻለው 51 በመቶ ሲሆን፣ ከፍተኛው የዕርዳታ ድጋፍ የተገኘው ከኢትዮጵያ መንግሥት ነው፡፡ መንግሥት 288 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ ከለጋሾች የበለጠ ለምግብ ዕርዳታ ማቅረቡ ተገልጿል፡፡ተመድ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ከፍተኛ የሆነ ዕርዳታ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፣ አስቸኳይ ምላሽ እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ
@YeneTube @FikerAssefa
ንብረትነቱ የሱዳን ጦር የሆነ አንድ ኩባንያ ከኦማር አል-በሽር በሚሰጠው ገንዘብ ለጎረቤት አገራት ወታደራዊ ቁሳቁስ ያሰራጭ እንደነበር የቀድሞው ፕሬዝዳንት የመከላከያ ምስክር ለሱዳን ፍርድ ቤት ተናገሩ።

የመከላከያ ምስክሩ ይኸን ያሉት ከውጭ አገራት ከፍ ያለ ገንዘብ በሕገ-ወጥ መንገድ ተቀብለው ጥቅም ላይ አውለዋል በሚል የተከሰሱት አል-በሽር በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ነው።

አል-በሽር በጦር ኃይሉ ግፊት ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ የአገሪቱ ባለሥልጣናት በመኖሪያ ቤታቸው ባደረጉት ብርበራ 6.9 ሚሊዮን ዩሮ፤ 352 ሺሕ ገደማ ዶላር እና 5.7 ሚሊዮን የሱዳን ፓውንድ ይዘዋል። የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ክስ የሚመለከቱ ዳኛ ገንዘቡ «በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ እና ጥቅም ላይ የዋለ» ነው ቢሉም አል-በሽር ከሳዑዲ አረቢያው ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ከተሰጣቸው የተረፈ ነው ሲሉ ይከራከራሉ። ፕሬዝዳንቱ ሱዳን ከሳዑዲ አረቢያ ባላት ሥልታዊ ግንኙነት የተገኘ ያሉት ገንዘብ «ለግል ጥቅም አልዋለም» ባይ ናቸው።

ይኸንንው ክርክራቸውን ለማስረዳት በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡ የመከላከያ ምስክር እርሳቸው የሚመሩት እና በሱዳን ጦር ሥር የሚገኝ ኩባንያ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ገንዘብ ይቀበል ነበር ብለዋል።

በሱዳን ጦር የማምረቻው ዘርፍ የወከሉት ሳዲቅ ያኩብ «1.2 ሚሊዮን ዶላር ተቀብለናል። በገንዘቡ የተገዙ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ለጎረቤት አገራት ልከናል» ሲሉ ተናግረዋል።

የመከላከያ ምስክሩ ወታደራዊ ቁሳቁሶቹ ለየትኞቹ አገራት እንደተላኩም ሆነ የጦር መሳሪያዎች ይጨምር እንደሆነ በግልፅ ያሉት ነገር የለም።
በሽር በጎርጎሮሳዊው 1989 ዓ.ም. በተካሔደ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ ሱዳን በኤርትራ፣ በኢትዮጵያ፣ በግብፅ የነበሩ የሽምቅ ተዋጊዎችን ትደግፋለች የሚል ወቀሳ ይሰነዘርባታል። የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በአገራቸው የከፋ የርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሱዳን ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን ትደግፋለች ሲሉ ከሰው ነበር።

ምንጭ:- Eshet Bekele
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሶስትዮሽ የሚኒስትሮች ስብሰባ በካይሮ እየተካሄደ ነው።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የሶስትዮሽ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ነው። ስብሰባው በዋናነት የሶስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓመት መስከረም እና የካቲት 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት እና የግድቡን የውሃ አሞላል እና አለቃቅ በተመለከተ ከተደረገው ውይይት የቀጠለ ነው።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመቐለ ዛሬ ሕዝባዊ ስብሰባ ስያካሂድ ውሏል፡፡

በሕዝባዊ ስብሰባው የኢዜማ ምክትል መሪ አንዷለም አራጌ፣ የሺዋስ አስፋ እንዲሁም ሌሎች የፓርቲው አመራሮች ተገኝተው ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በመድረኩ ፓርቲው ፕሮግራሙን አስተዋውቋል፣ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለቀረቡ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥቷል፡፡

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለማቀፍ የሃይማኖት እና የዕምነት ነጻነት መብት ድንጋጌዎች በመጻረር በተለይም በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ላይ የሚደርሱ ውድመቶችና በካህናትና ምዕመናኑም ላይ የሚፈጸሙ የግድያ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ተጠየቀ::

ዛሬ በፍራንክፈርት ከተማ ጥቃቱን ለማውገዝ የተደራጀው ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ የተካፈሉ የዕምነቱ ተከታዮችና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን መንግሥት የሃይማኖት ግጭትና ጥላቻን በመቀስቀስ አገሪቱን ወደብጥብጥ በሚመሩ የጥፋት ኃይሎች ላይ አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድና የዜጎቹንም የደህንነት ዋስትና ሊያረጋግጥ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት:: በቅርቡ ፍራንክፈርት ውስጥ የተካሄደን ሕዝባዊ ስብሰባ "በዛቻና በማስፈራራት ለማወክ ሞክረዋል ፤ የዝግጅቱን አስተባባሪዎችና የዕለቱንም የክብር እንግዳ ለማሸማቀቅ ተንቀሳቅሰዋል" ያሏቸውን ግለሰቦች ጉዳይ ከጀርመን የሕግ አካላት ጋር በመነጋገር በሽብር ወንጀል በፍርድ ቤት እንዲታይ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ያወሱት የጊዜያዊ ሰልፉ ዋና አስተባባሪ እና በጀርመን የረጅም ጊዜ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ስዩም ሃብተማርያም በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያም እንዲሁ በህዝቦች ላይ የሽብር ጥቃት የሚፈጽሙና የሕዝብ ዕልቂትን የሚያስከትል ሃይማኖት ጠል የፖለቲካ ሴራ የሚያቀናብሩ ግለሰቦች ቡድኖችም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች በዓለማቀፉ ችሎት እንዲጠየቁ እናደርጋለን ብለዋል:: 

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
Monthly salaries, 2019. ($US)

San Francisco: $6526

Zurich: $5996

NY: $4612

Sydney: $3599

London: $2956

Tokyo: $2860

Dubai: $2856

Paris: $2565

Berlin: $2473

Riyadh: $1473

Shanghai: $1184

Moscow: $1031

Mexico City: $635

Delhi: $521

Istanbul: $433

Lagos: $236

(Deutsche Bank)
@YeneTube @Fikerassefa
Here How much a beer will cost you in 10 of the world's most expensive cities

#Ethiopia in Resort And Hotel $1.12

10) Tel Aviv, Israel: $2.94

9) New York, USA: $3.33

8) Copenhagen, Denmark: $2.61

7) Seoul, South Korea: $3.13

6) Osaka, Japan: $2.30

5) Geneva, Switzerland: $1.54

4) Zurich, Switzerland: $3.25

3) Hong Kong: $1.77

2) Paris, France: $2.10

1) Singapore: $2.37

(Business insider)
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ሽልማት አሸነፈ!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት ዘርፍ የአለም ቁንጮ ተብሎ ተመርጧል፡፡ በLets Do This የሚታገዘው እና በእውቁ የሩጫ መጽሔት Runner’s World የሚቀርበው The Challenges Award ባለፉት ሦስት ሳምንታት ገደማ በኦንላይን ሲያካሂደው በቆየው ውድድር አንዱ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተወዳደረበት ዘርፍ እስከ ትናንት ሌሊት ማለትም እሁድ መስከረም 4 ቀን ከተሰጠ አጠቃላይ ድምጽ 56 በመቶውን በማግኘት አሸንፏል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ድምጽ መሠጠት ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ በመሪነት የዘለቀ ቢሆንም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት መጥበብ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያዊው የውድድር አዘጋጅ ተቋም በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናት በርካታ ድምጽ በማግኘቱ ልዩነቱን በማስፋት ሁለተኛ ደረጃን ከያዘው እና 24 በመቶ ድምጽ ከወሰደው San Diego Beach and Bay Half Marathon ርቆ በአስተማማኝ የበላይነት ውድድሩን ጨርሷል፡፡ Bay Bridge Half በ10 በመቶ ድምጽ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ዙሪያ አንጋፋ ከሚባሉትና በርካታ አስርተ አመታት ካስቆጠሩት ታዋቂ የጎዳና ውድድሮች ጋር ተፎካክሮ ያመጣው ውጤት ከለጋ እድሜው ጋር ሲነጻጸር ስኬቱን አስደናቂ ያደርገዋል፡፡ ዘንድሮ 19 አመት የሚሞላው የኢትዮጵያው ውድድር ከአመት አመት እያደገ መጥቶ በመጪው ህዳር 45000 ገደማ ተሳታፊዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ዓለም አቀፋዊ እንግዶችም ይኖሩታል፡፡

የሽልማት ስነ ሥርዓቱ ከአንድ ወር በኋላ ኦክቶበር 18 West Kensington በሚገኘው አስደናቂው Queens Club በደማቅ ዝግጅት የሚከናወን ሲሆን በስፖርቱ አለም ከፍ ያለ ስም ያላቸው እንግሊዛዊያን ዝነኞች በዝግጅቱ ይገኛሉ፡፡ በማራቶን የቀድሞዋ የአለም ሻምፒዮን ፓውላ ራድክሊፍ፤ የፓራ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎቹ ሳራ ስቶሪ እና ታኒ ግሬይ ቶምሰን እንዲሁም የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ሪዮ ፈርዲናንድ ከእንግዶቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለዚህ ስኬት እውን መሆን ድምጽ ለሰጡ፤ በተለያየ መንገድ ሌሎች እንዲሰጡ የጋበዙ፤ ጥሪ ያቀረቡና ያመቻቹትን ሁሉ በእጅጉ ያመሰግናል፡፡

Via Great Ethiopia Run
@YeneTube @Fikerassefa
በዴሞክራቲክ ኮንጎው ጀልባ ሰጥሞ 34 ሰዎች ሞቱ።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ በኮንጎ ወንዝ ላይ መንገደኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ጀልባ ሰጥሞ ቢያንስ 34 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ። ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአደጋው 76 ተሳፋሪዎች በህይወት መትረፍ የቻሉ ሲሆን በወቅቱ ጀልባው ከአቅሙ በላይ በጣም ብዙ ሰው ሳይጭን እንዳልቀረ ተገምቷል።ጀልባው ከሃገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በመነሳት ማይ ንዶምቤ ወደተባለችው ሰሜናዊ ግዛት እየተጓዘ ነበር።የአደጋው መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀ የገለጸው ፖሊስ ተሳፋሪዎቹ የውሃ ላይ መንሳፈፊያ ጃኬቶችን አድርገው ነበር ብሎ ለማሰብ እጅግ አስቸጋሪ ነው ብሏል።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ የውሃ ላይ ጉዞ በጣም የሚዘወተር ሲሆን ጀልባዎች የተለያዩ ጭነቶችና ተሳፋሪዎች ከአቅም በላይ ጨነው ሲጓዙ መመልከት የተለመደ ነው።እስከ 40 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ያላቸውና አንዳንዴም ባለሁለት ክፍል ትልልቅ ጀልባዎች ግልጋሎት ላይ ሲውሉ ይስተዋላል። ሁሉም ተሳፋሪዎች ደግሞ ውሃ ዋና ይችላሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።የዴሞክራቲክ ኮንጎ የአስፋልት መንገዶች በጣም የተበላሹና ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ብዙ የሃገሬው ሰዎች በጀልባ የሚደረጉ ጉዞዎችን ምርጫቸው ያደርጋሉ።

ምንጭ:BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው።

የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ኤልዛቤት ትረስ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።ሚኒስትሯ ከዛሬ ጀምሮ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዛሬ ረፋድ ላይም ሚኒስትሯ ከኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረእግዚአብሄር ጋር የሚወያዩ ይሆናል።በተጨማሪም ከውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር በሚያደርጉት ውይይት በሀይል ልማት ዘርፍ ለብሪታኒያ ኩባንያዎች ባለው እድል ዙሪያ እንደሚነጋገሩ በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ቤንች ዞን!!

ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ዛሬ ወደ ቤንች ዞን ሚዛን አማን እንደሚያቀኑ ሰምተናል። ከዞኑ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዝርዝሩን የምንመለስበት ይሆናል።

(YeneTube)
@YeneTube @FikerAssefa