YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ትናንት ምሽት የአዲስ አመት ዋዜማ በባህር ዳር እንዲህ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

Via Nahi/YeneTube
@YeneTube @FikerAssefa
#ሽኔ_ኦነግ በሶስት ወር ውስጥ መንግስታዊ ስልጣን እይዛለሁ ብሎ ጦርነት አውጆ ሕዝባችን ላይ መንገድ ዘግቶ፤ የሕዝብ ልጆች ትምህርት ቤት እንዳይማሩ አድርጎ ፤ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ቀውስ ፈጥሮ በሚፈነጭበት ወቅት ሠራዊታችን በለመደው የግዳጅ አፈጻጸም ስርአት ግዳጁን ተወጥቶ ምእራብ ቀጠናን ከባኮ እስከ አሶሳ ነጻ አውጥቶታል፡፡ አሁን አለን ለማለት ብቻ የሚወራጩ ጫካ ውስጥ የተደበቁ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ለሕዝብና ለመንግስት ስጋት የሚሆን ኃይል ግን የለም፡፡ ይሄ ሠራዊታችን የሰራው ስራ ነው፡፡

-ጀነራል ብርሀኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ

Via Addis Zemen
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ተመሳስለው የተመረቱ ሸቀጦች ንግድን ለመቆጣጠር በሚል በጁሐንስበርግ አሰሳ ሲያደርግ ተይዘው ወደ ሊንዴላ የዲፖርቴሽን ማዕከል ከተወሰዱ ኢትዮጵያውያን አንዱ ዛሬም አለመፈታቱን ፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የጎንደር ከተማ አስተዳዳር በዓሉን ከህሙማንና ድጋፍ ከሚያሰፈልጋቸው ወገኖች ጋር እያከበረ ነው።

የጎንደር ከተማ አስተዳዳር በየዘመን መለወጫ በዓልን ከህሙማን እና ድጋፍ ከሚያሰፈልጋቸው ወገኖች ጋር እያከበረ ነው።የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ እና የከተማው አመራሮች የጎንደር ዩኒቨርስቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሲሳይ ይፍሩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታልና መና የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን እና የነገ ተስፋ የህፃናት ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በህሙማን የመርጃ ማዕከሉ የምሳ ግብዣ ተደርጓል።የበግና ሌሎች ስጦታም ተበርክቷል።የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ፥ አዲሱ ዓመት ያለንን የምናካፍልበት፣ ለሀገራችን ሰላም እና አንድነትና ብልፅግና የምንሰራበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከ9.1 ቢሊዮን ብር በላይ የአረቦን ገቢ አስመዝግበዋል።

በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት 18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ በ2011 የሒሳብ ዓመት ከ9.1 ቢሊዮን ብር በላይ የአረቦን ገቢ ያስመዘገቡ መሆኑ ተመለከተ፡፡በ2011 የሒሳብ ዓመት የአገሪቱን የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጥቅል ሥራ አፈጻጸም የተመለከቱ መረጃዎች እንዲያመለክቱት፣ 18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሰበሰቡት 9.1 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 8.6 በመቶ ዕድገት የታየበት ነው፡፡ በሒሳብ ዓመቱ 18 ኩባንያዎች ከሰበሰቡት አረቦን ውስጥ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት 3.4 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን አረቦን በማሰባሰብ ቀዳሚ ሲሆን፣ 17 የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ደግሞ በጥቅል የሰበሰቡት የአረቦን ገቢ 5.7 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጁባ ተጉዘው ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ተገናኝተዋል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት መሪዎቹ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማቀላጠፍ ድንበሮቻቸውን ስለመክፈት መነጋገራቸውን አስታውቋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ሄይኒከን በሰሜን ተራሮች የሚገኙ ብርቅዬ እንስሳት በአግባቡ እንዲያዙና እንዲጠበቁ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሆነ ፎርቹን ዘግቧል። ኩባንያው ከሚያመርታቸው የቢራ ብራንዶች አንዱ በስፍራው የሚገኘው ዋልያ(Ibex) እንደሆነ ይታወቃል ።

@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ11 ሚሊየን ብር ንብረት ወደመ።

በጅማ ከተማ ትናንት ማታ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ግምቱ 11 ሚሊየን ብር የሚሆን ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዠ ኮማንደር አብዱራዛቅ ነጋ እንደገለጹት አደጋው በትናንትናው እለት ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የተከሰተው በከተማው “መርካቶ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።በአደጋውም ግምቱ 11ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙን ኮማንደር አብዱራዛቅ ተናግረዋል።

ኮማንደር አብዱራዛቅ እንዳሉት በአደጋው 12 ሼድ ኮንቴነር የንግድ ሱቆች በውስጣቸው ከያዟቸው ንብረቶች ር ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።የጅማ ከተማ እና የአየር መንገድ የድንገተኛና የእሳት መከላከያ ተሽከርካሪዎች ከህብረተሰቡና ከጸጥታ አካላት ጋር ሆነው ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ሳይስፋፋ መቆጣጠር እንደተቻለም አንስተዋል።የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን ኮማንደሩ አክለው ገልጸዋል ።

ምንጭ:ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በየካቲት 12 ሆስፒታል የሚታከሙ ህሙማንን ጎበኙ፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት በየካቲት 12 ሆስፒታል የሚታከሙ ህሙማን ጎብኝተዋል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰና የጤና ጥበቃ ሜዲካል አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ያዕቆብ ሰማ የአዲስ አመት በአልን ምክንያት በማድረግ በየካቲት 12 ሆስፒታል ተኝተው የሚታከሙ ህሙማንን መጠየቃቸውን ኤፍቢሲ ዝግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ምክትል ር/መስተዳድር ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል በዛሬው ዕለት አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደም ለግሰዋል።

Via Hagos G.(PhD)
@YeneTube @FikerAssefa
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ!!

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ የ2012 የትምህርት ዘመን የምዝገባ መርሀ ግብር

1) ለጤና ሳይንስ ነባር የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም 8 እና 9 ቀን 2012
ዓ.ም

2) ለሌሎች ነባር ቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች
መስከረም 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ይገልፃል፡፡

የአንደኛ ዓመት ቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች
የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
የአዲስ ዓመት በዓል ከድንገተኛ አደጋና ወንጀል ድርጊቶች ነጻ በሆነ መልኩ መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል የድንገተኛ አደጋና ከወንጀል ድርጊቶች ነጻ በሆነ መልኩ በሰላማዊ መንገድ መከበሩን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።የኮሚሽኑ የኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታው እንደገለጹት፥ የአዲስ ዓመት በዓል ከዋዜማው ጀምሮ እጅጉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል።

ይህ ዜና እስከተዘገበበት ድረስ “በትራፊክ አደጋ ሰው አልሞተም፤ ከባድ የአካል ጉዳት አልደረሰም፤ ከጸጥታና ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘም ምንም የተከሰሰተ ነገር የለም” ብለዋል።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከህብረተሰቡ ጋር የተቀናጀ ተግባር በማከናወናቸው በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መከበሩን ጠቁመው፥ለዚህም ቀደም ብሎ ከመዲናው ነዋሪ ጋር ተወያይቶ ወደ ስራ በመግባቱ ውጤታማ እንዳደረገ ተናግረዋል።ህብረተሰቡ በዓሉ በሰላም አንዲከበር ከፖሊስ ጎን በመቆም ላደረገው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ ዓመት በዓል ከመድረሱ በፊት ወንጀልን ለመከላከል በተደረገ ዘመቻ ሀሰተኛ የብር ኖቶች፣ የውጭ አገር ገንዘቦች፣ የሀሺሽ እቃዎች፣ ሀሰተኛ ፓስፖርቶች፣ ህገ ወጥ መታወቂያዎች መያዛቸውንም ጠቅሰዋል።በሌላ በኩል በአዲስ ዓመት በዓል ምንም አይነት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አለመከሰቱን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።የኮሚሽኑ የኮምዩኒኬሽ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን ከበዓሉ በፊት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በተለያዩ መንገዶች መልዕክቶችን የማስተላለፍ ስራ መከናወኑን ጠቅሰው ። በዚህም የአዲስ ዓመት በዓል ከአደጋ ነጻ ሆኖ መከበሩን ተናግረዋል።ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላሳየው ትብብርም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ!!

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ የ2012 የትምህርት ዘመን የምዝገባ መርሀ ግብር

1) ለጤና ሳይንስ ነባር የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም 8 እና 9 ቀን 2012
ዓ.ም

2) ለሌሎች ነባር ቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች
መስከረም 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ይገልፃል፡፡

የአንደኛ ዓመት ቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች
የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በያዝነዉ የግሪጎሪያን 2019 ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዉስጥ ብቻ 11 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ ከቤት ንብረቱi መፈናቀሉ ተዘገበ።

IDMC በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ ዓለም አቀፍ የተፈናቃዮች ጉዳይ አጥኚ ድርጅት እንደሚለዉ ከጥር እስከ ሰኔ ማብቂያ በነበረዉ ስድስት ወር በደረሰ የተፈጥሮ አደጋ 7 ሚሊዮን ሰዉ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።በዚሁ ጊዜ በተለያዩ ሐገራት የተደረጉና የሚደረጉ ጦርነትና ግጭቶች ደግሞ ከ3.8 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አፈናቅለዋል።በጥናቱ መሠረት በጦርነትና ግጭት በርካታ ሕዝብ ከተፈናቀለባቸዉ ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሶሪያ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የመንን የሚያብጠዉ ጦርነትና ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አፈናቅሏል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በጠርሙስ በላኩት መልዕክት ሕይወታቸው የተረፈው ቤተሰብ።


አሜሪካ ውስጥ ባላሰቡት ሁኔታ የውሃ ፏፏቴ ውስጥ ገብተው አደጋ ላይ የነበሩ ሦስት የቤተሰብ አባላት ለማንኛውም ብለው የድረሱልን መልዕክታቸውን በጠርሙስ ላይ ጽፈው ወደ ወንዝ ከተው ነበር።በሚያስገርም ሁኔታ በጠርሙሱ ላይ የነበረውን መልዕክት ሰዎች አግኝተው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል።

ከርቲስ ዊትሰን፣ የፍቅር ጓደኛውና የ13 ዓመት ልጃቸው ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ነበር ወደ ማዕከላዊ ካሊፎርኒያ ግዛት በመሄድ የቤተሰብ ጉዟቸውን የጀመሩት። እቅዳቸው ደግሞ አሮዮ ሴኮ የተባለውን ወንዝ በመከተል መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ፏፏቴ መመልከት ነበር።ልክ ፏፏቴው ጋር ሲደርሱም በገመድ ታግዘው በመውረድ እዛው አካባቢ ጊዜያዊ መጠለያቸውን ሠርተው ለመቆት ነበር ያሰቡት።በሦስተኛው ቀን ግን ከትልልቅ ቋጥኞች ሥር መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ እራሳቸውን አግኝተዋል።ቋጥኞቹ በሁለቱም በኩል 15 ሜትር ወደላይ ከፍታ ያላቸው ሲሆን፤ ይዘውት የነበረውም ገመድ ወደታች ለመውረድ እንጂ ወደላይ ለመውጣት የሚያገለግል አልነበረም።በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፤ እነሱ የነበሩበትና በቋጥኞቹ መካከል ያለው ቦታ ከወንዙ በሚመጣ ውሃ መሞላት ጀመረ።''ውሃው ከፍ እያለ ሲመጣና ምን አይነት አደጋ ውስጥ እንደገባን ስረዳ ልቤ ቀጥ ብላ ነበር'' ብሏል ከርቲስ ከሲኤንኤን ጋር ባደረገው ቆይታ።

ምንም አይነት የስልክ ኔትዎርክ በቦታው ስላልነበር የድረሱልን መልዕክት ማስተላለፍ እንኳን አቅቶት የቆየው ቤተሰብ በመጨረሻ ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ወሰነ።በእጃቸው ላይ የነበረውን ጠርሙስ በመፈቅፈቅ ''በፏፏቴው በኩል መውጣት አቅቶን ተይዘናል፤ እባካችሁ ድረሱልን'' የሚል መልእክት ጽፈው ወደ ወንዙ ወረወሩት።ጠርሙሱ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል በወንዙ ላይ እየተንሳፈፈ ከተጓዘ በኋላ በአካባቢው ጉዞ እያደረጉ የነበሩ ሁለት ሰዎች ያገኙታል።ወዲያውም ጉዳዩን ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ያሳውቃሉ።የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም ወዲያው ፍለጋቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሦስቱንም የቤተሰብ አባለት ከባድ የሚባል ጉዳት ሳይደርስባቸው አግኝተዋቸዋል።ከርቲስ ዊትሰን እና ቤተሰቡ "ሕይወታችን በመትረፉ እጅግ ደስተኞች ነን። ሕይወታችንን ያተረፉት እነዛ ሁለት ተጓዦችን አግኝተን ማመስገን እንፈለጋለን" ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa