Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን
የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g

ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከመጪው መስከረም ወር 2012 መጀመሪያ አንስቶ በሶማሊኛ እና በትግሪኛ ቋንቋዎች ኅትመት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀቀ።
ድርጅቱ መረጃዎቹን በተለያዩ ቋንቋዎች ለሕዝብ ለማድረስ ኹለቱን ቋንቋዎች ጨምሮ ጋዜጦችን ለማሳተም የሰው ኀይል እና የፋይናንስ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን የይዘት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሄኖክ ስዩም (ዶ/ር) አስታውቀዋል።እነዚህ አዲስ የሚጨመሩት ጋዜጦች እያንዳንዳቸው ስምንት የገፅ ብዛት ይዘው የሚመሰረቱ ሲሆኑ በሳምንት አንዴ አንባብያን እጅ የሚደርስ ሲሆን በሳምንት ውስጥ መቼ እንደሚወጣ አልተወሰነምም ተብሏል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa

የእብድ ውሻ በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው-፡-ዶ/ር ባዬ አሸናፊ
በኢትዮጵያ በክረምት ወቅት የእብድ ውሻ በሽታ በስፋት እንደሚከሰት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ዶ/ር ባዬ አሸናፊ ተናገሩ፡፡ማህበረሰቡ ስለ እብድ ውሻ ላይ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን ፣የበሽታው ክትባት መድሃኒት እጥረት በመኖሩ በሽታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲስፋፋ ያደርገዋል ብለዋል ተመራማሪው በተለይ ከኢቲቪ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ፡፡ ተመራማሪው፣ በክረምት ወቅት ውሾች ምግብ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ ይመጣሉ፤ በዚህ ምክንያት በከተሞች አከባቢ በተለይም በአዲስ አበበ ከተማ ባለቤት የሌላቸው ውሾች ቁጥራቸው ይጨምራል።
መስከረም አካባቢ የውሾቹ መራቢያ ጊዜያቸው ስለሆነ ውሾቹ በጋራ የመንቀሳቀስ እና የመሄድ ሁኔታ ይታያል ብለዋል። በዚህ ምክንያት በእብድ ውሻ የተለከፈ አንድ ውሻ ካለ ለሌሎቹ ውሾች ለማስተላለፍ እና ከውሻ ወደ ሰው የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።የእብድ ውሻ በሽታን 70 በመቶው ክትባት በመስጠት ከአንዱ እንስሳ ወደ ሌላው እንስሳ የመተላለፍ እድሉን ለመቀነስ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።
Via ETV

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትኬት ጠፍቶ አሁንም ሌሶቶ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሶቶ አቻቸዉ ጋር የመልሱን ጨዋታ ከሁለት ቀናት በፊት ካደረገ በኃላ ቡድኑ አሁንም በሌሶቶ ይገኛል ።ብሔራዊ ቡድኑ ትላንት ሌሶቶን ለቆ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ የነበረበት ቢሆንም ከሌሶቶ ደቡብ አፍሪካ ቴኬት ዘግይተዉ በመቆረጡ እና የትኬት ጉዳይ ቀደም ብሎ ባለመታሰቡ ቡድኑ አሁንም ከሌሴቶ መዉጣት አልቻለም።
እንደ ምንጮቻችን መረጃ በአሁኑ ሰአት በሌሶቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች እና ከአሰልጣኞች ዉጪ የቡድኑን የትኬት እና ተያያዥ የጉዞ ጕዳይ የሚስፈፅም የለም ።ብቻ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምናልባት ዛሬ ምሽቱን ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ከሆነ ከደቡብ አፍሪካ ወደ አዲስ አበባ በረራዎች በቀላሉ ስላለ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡ አለበለዚያ ግን አዲስ አመትን ሌሶቶ ሊያከብሩ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ: Ethio Kickoff

የፍትህ ቀን በዛሬው ዕለት በመላ ሀገሪቱ ይከበራል።
ዕለቱ “ፍትህን ማረጋገጥ ይደር የማንለው ስራችን ነው!” በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው።ቀኑን በሚያስተባብረው የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ “የህግ ተገዢ ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የቆየው የፍትህ ወር ማጠናቀቂያ ዝግጅትም በዛሬው ዕለት ይካሄዳል።በዚህ መሰረትም “የፍትህ ቀንን” ምክንያት በማድረግ ከ15ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ዝግጅት ከቀኑ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከናውን ይሆናል፡፡
Via Fana

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ!!
በመጪው የ2012 ዘመን መለወጫ በዓል የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በሃገር አቀፍ ደረጃ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ሆኖም ከበዓሉ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት ሊያጋጥም ስለሚችል፤ የድንጋይ ወፍጮ፣ የብረታ ብረት፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የሲሚንቶ፣ የፕላስቲክ፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት ፋብሪካዎች ከጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 እስከ መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽቱ 12፡00 ድረስ ከዋናው የኃይል ቋት /ከግሪድ/ የምታገኙትን ኃይል እንድታቋረጡ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
እንዲሁም ኤሌክትሪክ በሚቋረጥበት ጊዜ የጥገና ስራ ለማከናወን የተቋማችንን መታወቂያ ወይም የስራ ትዕዛዝ የያዙ ባለሞያዎቻችን በተለያዩ አካባቢዎች ለስራ ጉዳይ ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ፤ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ እየጠየቅን፤ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ጥቆማ ለመስጠት ወይም መረጃ ለመጠየቅ ወደ 905 ነፃ የጥሪ ማዕከላችን መደወል ወይም ከአቅራቢያ ካለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ማሳወቅ የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
መልካም አዲስ አመት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በኬንያ የአይሲኦሎ ፍርድ ቤት አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ ቅጣት አስተላለፈ።
ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን የምትገኘው የአይሲኦሎ ግዛት ፍርድ ቤት ያለ ፈቃድ በኬንያ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ የእስር ቅጣት አስተላልፏል።
Via Addis maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን የምትገኘው የአይሲኦሎ ግዛት ፍርድ ቤት ያለ ፈቃድ በኬንያ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ የእስር ቅጣት አስተላልፏል።
Via Addis maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ለአባላቶቹ እውቅና ሰጠ፡፡
አየር ሀይሉ በ2011 ዓ.ም የሚያስመሰግን ስራ ላከናወኑ አባላቱ እውቅና ሰጥቷል፡፡በተጨማሪም በችሎታና ብቃት ለውጥ ላመጡ አባላት የደረጃ እድገት የሰጠ ሲሆን ጡረታ የወጡ ሰዎችንም በክብር አሰናብቷል፡፡
ምንጭ:OBN
@YeneTube @FikerAssefa
አየር ሀይሉ በ2011 ዓ.ም የሚያስመሰግን ስራ ላከናወኑ አባላቱ እውቅና ሰጥቷል፡፡በተጨማሪም በችሎታና ብቃት ለውጥ ላመጡ አባላት የደረጃ እድገት የሰጠ ሲሆን ጡረታ የወጡ ሰዎችንም በክብር አሰናብቷል፡፡
ምንጭ:OBN
@YeneTube @FikerAssefa
በሐዋሳ በ56 ሰዎች ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ ምልክት መታየቱ ተነገረ፡፡
በሃዋሳ ከተማ በኮሌራ ወረርሽኝ የተጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር 56 መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ቀድረላ አህመድ ለ ኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡የወረርሽኙ ምልክት በነዚህ ሶስት ቀናቶች 56 በሚሆኑ ሰዎች ላይ መታየቱ እና በ 2 ሰዎች ላይ በሽታው መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ወረርሽኙ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት እና የህብረተሰብን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሆኑ አቶ ቀድረላ ተናግረዋል፡፡በሽታውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ክልሉ ከከተማው ጤና ቢሮ ጋር በመሆን ጊዜያዊ ማቆያዎችን በከተማዋ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ላይ መክፈቱንና በዚህም ስርጭቱን ለመግታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
Via Ethio FM

በጅማ ከተማ ቤተ ክርስትያን ተቃጠለ በሚል በተሰራጨ የሀሰት መረጃ ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር መረጋጋቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ከፍያለው ተፈራ በሰጡት መግለጫ፥ በትናንትናው እለት በጅማ ከተማ የሚገኘው የማርያም ቤተ ክርስትያን እና መስቀል ተቃጥሏል በሚል የቤተ ክርስትያን ደወል በመደወል እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በስልክ መረጃ በመለዋወጥ ግርግር ተፍጥሮ ነበር ብለዋል።
ኮሚሽነር ጄነራል ከፍያለው ተፈራ በጅማ ከተማ የሚገኘው የማርያም ቤተ ክርስቲያን እና መስቀል ተቃጥሏል በሚል የተሰራጨው ሀሰት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፥ በከተማዋ ተፈጥሮ የነበረው ግርግርም መረጋጋቱን አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅትም ጉዳዩ በሽምግልና እየተፈታ መሆኑንም ነው ኮሚሽነር ጄነራል ከፍያለው ተፈራ በመግለጫቸው ያስታወቁት።

ተመድ ከውጭ ሀገር ብድር ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀ።
የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንግዌ እንዳሉት ሀገሪቱ ከውጭ ምትበደረው ገንዘብ አሁን ባለበት አያያዝ ከቀጠለ የዕዳ ቀውስ ውስጥ ልትገባ ትችላለች።ለዚህም ካሁኑ ዕዳዎቿን እያቀለለች መሄድ አለባት ብለዋል። ለዚህም ከዚህ በፊት ቻይና ፣ቬትናምና ላኦስ ካደረጉት ልምድ እንዲወሰድ ጠቁመዋል። በቅርቡ ይፋ ከተደረገው የ52.57 ቢሊዮን ዶላር የሀገሪቱ እዳ ውስጥ 26.93 ቢልዮን ዶላሩ ከውጭ የተበደረችው እንደሆነ ይታወቃል ።
ምንጭ:Addis Standard

በ2011 ዓ.ም የመሰናዶ ት/ታችሁን አጠናቅቃችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ላለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የሚቀበለው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተላከለት ትዕዛዝ መሰረት በት/ት ሚኒስቴር ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎችን ብቻ መሆኑን እና ዩኒቨርሲቲው በራሱ የሚመድበው ተማሪ እንደሌለ አውቃችሁ ራሳችሁን ከተሳሳተ መረጃ እና ከአታላዮች እንድትጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
_________________________
Barattoota Bara 2011 Barnoota Qophaa’iinaa Xumurtanii Qormaata Gara Yuunivarsitii Galchu Dabartan Hundaaf
Yuunivarsitiin Jimmaa Bara 2012 barattoota haaraa barnoota sagantaa idilee kan fudhatu akkaataa qajeelfama Ministeera Saayinsiifi Barnoota Olaanaarraa kennameen; barattoota gara Yuunivarsitii Jimmaa ramadaman qofa waan ta’eef; ramaddii kanaan ala barataan simatamee galmaahu akka hinjirre beektanii; namoota odeeffannoo dogoggora ta’e dabarsaniifi isiin
gowwomsuu danda’anirraa akka ofeegdan cimsinee isiin hubachiisna.
Nagaa Wajjiin
Waajjira Reejist

ናይጄሪያ 600 ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ ልታስወጣ ነው።
ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ያለውን መጤ ጠል ጥቃት ተከትሎ 600 ዜጎቿን ልታስወጣ መሆኗን አስታወቀች። ሁለቱ ሀገራት እየደረሰ ያለውን ጥቃት ተከትሎ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።የተወሰኑ ናይጄሪያውያን ረቡዕ ዕለት በሁለት አውሮፕላን እንደሚወጡ በጆሀንስበርግ የሚገኘው የናይጄሪያ ቆንጽላ ቢሮ ለቢቢሲ አስታውቋል።ባለፈው ሳምንት በከተማዋ የውጪ ሀገራት ዜጎች የንግድ ተቋማት ላይ በደቦ በተፈፀመ ጥቃት አስር ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የውጪ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል።
ምንጭ: ዋልታ

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ በኦሮሚያ እውቅና የሰጠነው የተቃውሞ ሰልፍ የለም ብለዋል። ሰልፉ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት የሚፈልጉ ሃይሎች ያቀናጁት እንደሆነ ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ለሚገኙና የህክምና እርዳታ ማግኘት ለማይችሉ ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ማዕከል መከፈቱ ተነገረ፡፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ በአዲስ አበባ በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ ያሉ ዜጎችን ለመርዳት ተቋቁሟል የተባለው ክሊኒክ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የተቸገሩ በጎዳና ላይ ላሉ ዜጎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ነው ሲሉ የነገሩን የሆስፒታሉ ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር ወንድምአገኝ ገዛኸኝ ናቸው፡፡
ተጨማሪ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ከሆነም ከአዲስ አበባ የጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ሆስፒታሎች ሪፈር እንዲፃፍላቸው በማድረግ አገልግሎቱ እንዲሰጥእና በተጨማሪም በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ዜጎችም በተመሳሳይ አገልግሎቱ እየተሰጠ እንደሆነ ዶ/ር ወንድማገኝ ነግረውናል፡፡የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተጨማሪም በማህበራዊ አገልግሎት የካንሰር ህክምና ለመከታተል ከተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ህሙማን የሚያርፉበት እና የምገባ አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል መክፈቱንም ሰምተናል፡፡
Via Sheger Radio

(ሕወሓት) እና (አዴፓ) ቅራኔን በተመለከተ “በአዲሱ ዓመት ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጠን ተወያይተንና ተግባብተን ለመፍታት ዝግጁ ነን” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስሀን ጥሩነህ ተናገሩ።
አቶ ተመስገን ይህን ያሉት አዲሱን 2012 ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው ብሔር ብሄሰቦችና በተለይም ለአማራ ክልል ህዝብ የመልካም ምኞት መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ። እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ችግሮችንን ለመፍታት ዝግጁ ነን ያሉት አቶ ተመስገን ፤ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከ(ሕወሓት) ወገንም ተመሳሳይ ፍላጎት ይኖራል ብለው እንደሚያምም ገልፀዋል፡፡ በአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር መኖሩን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳደሩ በአዲሱ ዓመት ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ይፋ አድርገዋል። አዲሱ ዓመት ለመላው ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በተለይ ለአማራ ክልል ህዝብ የሰላም፣ የብልፅግናና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡
Via DW

የቻይናው ኩባንያ የቤተ መንግሥቱን የመኪና ማቆሚያ 1.5 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሻሽነት ወደ ሙዝየም በመቀየር ላይ ላለው ብሔራዊ ቤተመንግሥት የመኪና ማቆሚያ ለመገንባት ከተወዳዳሩት ኹለት የቻይና ግንባታ ኩባንያዎች መካከል ቻይና ጂያንግ ሱ ኮንስትራክሽን በ1.5 ቢሊዮን ብር ውል ፈፀመ።የአዲስ ኣበባ ኮንሰትራክሽን ቢሮ በቤተ መንግሥቱ ግቢ ውሰጥ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሙዚየም ለመጎብኘት ለሚመጡ ጎብኚዎች ከቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት የሚገነባው ይህ የመኪና ማቆሚያ ግንባታ ወጪ የሚሸፍን ይሆናል።

መስከረም 4፤2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት መግለጫ ሰጡ፡፡
መግለጫውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በቤተክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የመቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያንቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡ሰልፉን በማስመልከት ዝርዝር መግለጫዎችን በመስከረም 2፤2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ የገለጹት ኮሚቴዎች፣ የነበራቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነና በውይይቱ አጥጋቢ መልስ ካገኙ ሰልፉ ሊቀር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ማህበራቱ የሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም በቀጣይ መስከረም 2 በሚኖረው ድጋሚ መግለጫ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ሰልፉ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጠቆም ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሰልፉን ለማዘጋጀት ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ እንደቆዩም የጠቆሙ ሲሆን፤ የሰልፉ አላማም በሰላማዊ መንገድ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታቀደው ሰልፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሆንና ህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያንቷ ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡
Via Walta

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የአፍሪካ የፖለቲካ አማካሪዎች ማኅበር ሽልማት አበረከተላቸው።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ኬሂንዳ ባሚግቤታን ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ማሻሻያ አድርገዋል።በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችና እስረኞች እንዲፈቱና በውጭ የሚኖሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ አገራቸው በነጻነት እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።ወደ አገራቸው ከመጡ በኋላም ከፖለቲከኞቹ ጋር ተቀራርበው መስራታቸውንና ከምሁራን ጋርም የፖለቲካ ከባቢ መፍጠራቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ለሁለት ናይጄሪያዊ ፖለቲከኞች ተመሳሳይ ሽልማት ሰጥቷል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ይህንን ሽልማት ሲቀበሉም ሦስተኛ ግለሰብ ናቸው ብለዋል።
Via ENA