YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ስፖርት!!

ሌሶቶ ከኢትዮጵያ የመልስ ጨዋታ ዛሬ በ9 ሰዓት ይካሄዳል።


ለ2022 ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ከሌሶቶ ጋር ከቀናቶች በፊት ያለ ጎል በአቻ ውጤት የተለያየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመልሱን ጨዋታ ሌሴቶ ላይ ያደርጋል ። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በሌሶቶ የሰአት አቆጣጠር 9 ሰአት በሴሶቶ ስታዲየም ይደረጋል ።

Via Ethio Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በባሀብቶች ድጋፍ የታደሱ ህንፃዎችን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ጋር በመሆን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በባለሀብቶች ድጋፍ እየተደረገላቸው ህንፃዎች ውስጥ እድሳታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ስምንት ህንጻዎችን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅትም በእድሳቱ የተሳተፉ ባለሀብቶችን እና ተባባሪ አካላትን አመስግነዋል።
@YeneTube @FIkerAssefa
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናትና ወጣቶች የምሳ ግብዣ አደረጉ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናትና ወጣቶች የምሳ ግብዣ አደረጉ። ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ለህፃናትና ወጣቶች የምሳ ግብዣ ያዘጋጁን የ2012 ዓ.ም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ መሆኑን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣው ላይም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለህፃናትና ወጣቶች ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልፅግና እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

ምንጭ: የፕሬዝዳንቷ ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናትና ወጣቶች የምሳ ግብዣ አደረጉ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናትና ወጣቶች የምሳ ግብዣ አደረጉ። ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ለህፃናትና ወጣቶች የምሳ ግብዣ ያዘጋጁን የ2012 ዓ.ም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ መሆኑን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣው ላይም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለህፃናትና ወጣቶች ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልፅግና እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

ምንጭ: የፕሬዝዳንቷ ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
83 ልዩ ጫና ያለባቸውን ሆስፒታሎች ላይ ሪፎርም ለማካሄድ የተዘጋጀው ስብሰባ ተጠናቀቀ ።

በ2012 ዓ.ም ከፍተኛ ጫና ያለባቸው የተመረጡ 83 የመንግስት ሆስፒታሎች ላይ I-CARE/ያገባኛል/ በሚል መሪ ቃል የሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የሆስፒታሎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ የኳሊቲ ዳይሬክተሮች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር የተካሄደው የሶስት ቀን ውይይት እና የማናበብ ስራ በዛሬው እለት ተጠናቋል:: ከተመረጡት 83 ሆስፒታሎች በልዩ ሁኔታ ጫና ያለባቸው 22 ሆስፒታሎች ላይ ለሪፎርም ስራ የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሲኖር ይህም 50% ከጤና ሚኒስቴር፣ 30% እንደየተጠሪነታቸው ከክልል/ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር/ ፣ 20% ከሆስፒታሎች የሚያዝ ይሆናል::ይህ የሪፎርም ስራ በ2012 ዓ. ም በተመረጡት ሆስፒታሎች በመተግበር ልምድ የምንወስድበት እና የቀጣዩን የ5 አመት የጤና ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የሚካተት ይሆናል::

ምንጭ:የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ለ350 አባላቱ የማእረግ እድገት ሰጠ።

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ለ350 የሰራዊቱ አባላት ከረዳት ሳጂን እስከ ኮማንደር ድረስ የማእረግ እድገት መስጠቱን የከተማዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።ኮሚሽኑ የ2011 በጀት አመት የአፈፃፀምና የሪፎርም ሥራ የማጠቃለያ መድረኩን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን፥ በመድረኩ ላይ በጡረታ ለሚሰናበቱ 23 አባላቱ የእውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀትን ጨምሮ ሙሉ ልብስና የአመት በአል ስጦታ አበርክቷል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!!

የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ውጤት:

ሌሶቶ 1 -1 ኢትዮዽያ
ብሄራዊ ቡድናችን ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ ተሻግሯል !

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች፣ ቆንስላዎችና ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር የሥራ ኃላፊዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትና የቤተመንግሥት እድሳትን ጎበኙ።

በዛሬው እለት በተካሄደው ጉብኝት ላይም ከ200 በላይ ከሁሉም ሀገራት የኢትዮጵያ ሚሲዮኖችና ቆንስላዎች እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር የሥራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር ያለ አንድ ማህበር የኢትዮጵያ መንግስት በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ላይ አሳይቶታል ያለውን ዝምታ አወገዘ። ማህበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት የተሰኘው ይሄው ማህበር ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫ መንግስት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ ጠንካራ ህግ ሊያወጣ ይገባል ብሏል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት ሰራተኞቹ በታጣቂዎች የተገደሉበት አክሽን አጌይንስት ኸንገር ከነፍስ አድን ሥራዎች በቀር በጋምቤላ የግብረ ሰናይ ስራዎቹን ማቆሙን አስታውቋል። ድርጅቱ እንደሚለው ላለፉት 35 ገደማ አመታት በኢትዮጵያ ሰርቷል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!!

ታምራት ቶላ በብሪቲንያ የግማሽ ማራቶን ውድድር ሁለተኛ ወጣ።

ዛሬ በብሪታንያ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ብሪታንያዊው ሞ ፋራህን ተከትሎ ሁለተኛ ወጣ። በሴቶች ተመሳሳይ ውድድር ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጊ የምንጊዜም ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች።

@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን የቀይ ባህር ግዛት ያሉ የቢኒ አመር እና ኑቢያ ጎሳዎች ዛሬ የእርቅ ስምምነት ተፈራረሙ። የሁለቱ ጎሳዎች ተወካዮች ከስምምነት ላይ የደረሱት የሀገሪቱ ሉዑላዊ ምክር ቤት አባል ጄነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ባደረጉት ግፊት ነው ተብሏል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ የተጠየቀም ሆነ የተፈቀደ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!!

በኦሮሚያ የተጠየቀም ሆነ የተፈቀደ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአፋን ኦሮሞ ለሚታተመው በሪሳ ጋዜጣ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ የቀረበ የሰልፍ ጥያቄም ሆነ የተፈቀደ ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በማንኛውም ጉዳዮች ዙሪያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካሎች ጋር እየተወያየ መፈትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል እንጂ ሰልፍ የሚያስወጣ ምንም ዓይነት ጉዳይ አይኖርም ብለዋል ኮሚሽነሩ። በመሆኑም ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱ አሉባልታዎችን ተከትሎ እንዳይሳሳት ኮሚሽነሩ አበክረው አሳስበዋል።

ለሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች አቅጣጫ የተሰጠ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ከፖሊስ እውቅና ውጪ የሚካሄድ ሰልፍ ካለ የክልሉ ፖሊስ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

Via:- EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ❗️

የእግር ኳስ ችሎታ አለን የምትሉ ዕድሜያቹ ከ18-20 አመት የሆናችሁ ወጣቶች የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ክለብ ለምልመላ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ቦታ :- ሲቪል ሰርቪስ

ማስታወሻ❗️ አዲስ አበባ #ከመገናኛ ወደ አያት ታክሲ ይዛቹ Civil service ብላችሁ መውረድ ትችላላችሁ።
@YeneTube @FikerAssefa
በስጦታ ለአዲስ አበባዬ ለተሳተፉ አካላት እውቅና ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክረምት በጎ ፍቃድ አካል በሆነው ስጦታ ለአዲስ አበባዬ መርሃ ግበር ለተካፈሉ አካላት እውቅና ሰጠ።

በእውቅና ስነ ስርዓቱ ላይ በዘንድሮው ዓመት የክረምት በጎ ፍቃድ ከ702 ሚሊየን በላይ ደብተር በላይ መሰብሰቡ እና ከ160 በላይ ትምህርት ቤቶች መታደሳቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ከ1 ሺህ በላይ የአዛውነቶች እና የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት መካሄዱም ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በዛሬው እለት በብሄራዊ ኩራት ቀን ማጠቃላያ ላይ በዚህ በጎ ተግባር ለተሳተፉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።

@YeneTube @Fikerassefa
የ10 ክፍል ፈተና ዉጤት በተመለከተ

አቶ አርያ ገ/እግዚአብሔር የ12 ክፍል የወጣ ቀን በማግስቱ በETV ላይ ቀጥታ በስልክ ገብተው ስለ 10 ክፍል ተጠይቀው ነበር እንዲህ ሲሉ ነው የመለሱት

""የ10 ክፍል ፈተና እርማት አልቋል ነገር ግን ወደ internet ማስገባት ነው የሚቀረን እንዲሁም ነሀሴ መጨረሻ ላይ እንደሚወጣ ለETV ተናግረው ነበር""

ነገር ግን ዛሬ ጷግሜ 3 ላይ ነን የፈተናዎች ኤጄንሲ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም።

#እኛም የሚመለከተውን አካል ለማናገር ጥረት እያደረግን እንገኛለን ጥረታችን ከተሳካ የ10 ክፍል ውጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን ይፋ የምናደርግ ይሆናል።
@YeneTube @Fikerassefa
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ሩሲያ ተጓዙ።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ማታ ጳጉሜ 3 ቀን 2011 ዓም ወደ ሩሲያ ተጉዘዋል።ክቡር ሚኒስትሩ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ለቭሮቭ ጋር ምክክር ያደርጋሉ።ጉብኝቱ የሁለቱን አገሮች የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የልማት ትብብር እንደሚያሳድግ ታምኖበታል፡፡የሩሲያው የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ዓመት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

Via የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
አቃቂ ገቢያ በተነሳ እሳት ገቢያዉ በሙሉ እየተቃጠለ ነዉ እሳቱን መቆጣጠር አለመቻሉት እየተጠቆመን ይገኛል የሚመለከተው አካል ተጨማሪ ሀይል እንዲጨምር የአከባቢው ነዋሪዎች አሳስበዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
#Update

አቃቂ ገቢያ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ከ 2:30 በላይ ሆነዉ መንደድ ከጀመረ እስካሁን መጥፋት አልቻለም እንዲሁም ውሃ ለሚረጩ መኪናወቹም ለመግባት አመች አልሆነም እሳቱ እንዲባባስ ምክንያት ሆኖታል።

@YeneTube @Fikerassefa
#Update አቃቂ የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ማለት ባይቻልም እሳቱ ጠፍቷል። 4:20 የጀመረው የእሳት ቃጠሎ አሁን 9:25 አከባቢ ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም አከባቢ ላይ ቡቲኮች ኮስሞቲክስ ቤቶች ስለ ሚበዙ እሳቱን በቶሎ ማጥፋት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

የተጣናከረ ዘገባ ነገ የምንቅርብ ይሆናል!

#Mule #John ከአቃቂ
@Yenetube @Fikerassefa