YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቦትስዋና በገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን አማካኝነት አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ቀጠሮ ያዘች፡፡

ፕሬዝዳንት ሞክዌቲ ማሲሲ ቦትስዋና በመጪው ጥቅምት 23 ቀን 2019 (እ.አ.አ.) በሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን አማካኝነት አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ መግለጫውን የሰጡት የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ከተበተኑ በኋላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በቀጣዩ የጥቅምት ምርጫ መሪ ድርጅቱ የቦትስዋና “ዲሞክራቲክ” ፓርቲን እና ዋና ተቀናቃኙን “አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ” ፓርቲን ጨምሮ ከስድስት የማያንሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከመስከረም 26 ጀምሮም እጩ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ክልሎች መመዝገቢያ ማዕከላት ቀርበው እንደሚመዘገቡ የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኦፊሊ ማሮባ አስታውቀዋል፡፡ የአጠቃላዩ ምርጫ አሸናፊዎች 57 የሀገራዊ እና 490 የአካባቢ መስተዳድር ቦታዎችን እንደሚሸፍኑ ነው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ያስታወቁት፡፡

የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምርጫውን ማሸነፍ ከቻለ ፕሬዝዳንት ሞክዌቲ ማሲሲ ቦትስዋናን በፕሬዝዳንትነት በመምራት እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን
@Yenetube @FikerAssefa
በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል። ጉባኤው በቆይታው የ2011 አም የእቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ ላይ የመከረ ሲሆን፥ በሶስተኛው ቀን ውሎም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ መክሯል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ሁዋዌ በቀጣይ የሚያመርተው ስልክ አቅጣጫ አመላካች (ጉግል ማፕ) እና ዩቲዩብን ጨምሮ ሌሎች የጉግል መተግበሪያዎች ላይኖሩት እንደሚችል ተገልጿል። የጉግል ኩባንያ፤ የአሜሪካ መንግሥት የሁዋዌ ምርቶች በአገሪቷ እንዳይሸጡ በመከልከሉ ምክንያት መተግበሪያዎቹን ለቻይናው ግዙፍ ስልክ አምራች ድርጅት- ሁዋዌ ፈቃድ መስጠት አልችልም ብሏል።

-BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባለዲግሪው መፃህፍት አዟሪ በብልሽት ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ ለስራ እንዲሆነው ከከተማ አስተዳደሩ ተበረከተለት።

ከተመረቀ በኋላ መፃህፍት በማዞር ህይወቱን ሲመራ የነበረው ወጣት አንዷለም ይስሃቅ ከከተማ አስተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ በኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተበረከተለት ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ወጣቱ ደርሶበት በነበረው የአእምሮ ህመም ችግር ሳይበገር እና ስራ ጠባቂ ሳይሆን እራሱን ለመለወጥ ያደረገው ጥረት ለብዙዎች አርአያ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል።

ከዚህ ቀደምም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በፋና ቀለማት ላይ ቀርቦ የህይወት ልምዱን አካፍሎ እንደነበረ ይታወሳል።በጥቂት ጊዚያት ውስጥም በከተማዋ ያለ አገልግሎት የቆሙ ሌሎች 700 የሚሆኑ አንበሳ የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተንቀሳቃሽ ሱቆች በመቀየር በከተማዋ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።ይህ ተግባር በአንድ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ የመፍጠር ግዙፍ እቅድ አካል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በችግሮች ሳይበገሩ ራሳቸውን ለመቀየር እየሞከሩ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት አላማ ያደረገ ተግባር ነው።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የኢዜማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከወጣቶች ጋር ተወያዩ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከወጣቶች ጋር ተወያይተዋል።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከወጣቶች ጋር ተወያይተዋል። በዚህም ውይይት ላይ ወጣቶች ለሀገራቸው ከፍተኛ ሚና ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢዜማ ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ወይዘሪት ፂዎን እንግዳዬ « ሀገራችንን ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማሸጋገር እንችላለን» ብለዋል።

ምንጭ:DW
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አምስት ቀናት ግምታዊ ዋጋቸው 13,369,792 ብር የሆኑ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዟል፡፡

Via ገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ባለዲግሪው መፃህፍት አዟሪ በብልሽት ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ ለስራ እንዲሆነው ከከተማ አስተዳደሩ ተበረከተለት!

ከተመረቀ በኋላ ለአራት አመታት መፃህፍት በማዞር ህይወቱን ሲመራ የነበረው ወጣት አንዷለም ይስሃቅ ከከተማ አስተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ በኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶለታል።

ወጣቱ ደርሶበት በነበረው የአእምሮ ህመም ችግር ሳይበገር እና ስራ ጠባቂ ሳይሆን እራሱን ለመለወጥ ያደረገው ጥረት ለብዙዎች አርአያ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል።

በጥቂት ጊዚያት ውስጥም በከተማዋ ያለ አገልግሎት የቆሙ ሌሎች 700 የሚሆኑ አንበሳ የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተንቀሳቃሽ ሱቆች በመቀየር በከተማዋ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ይህ ተግባር በአንድ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ የመፍጠር ግዙፍ እቅድ አካል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በችግሮች ሳይበገሩ ራሳቸውን ለመቀየር እየሞከሩ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት አላማ ያደረገ ተግባር ነው።

Via :-mayorofficeAA
@YeneTube @FikerAssefa
የ10 ክፍል ውጤት በተመለከተ ⬇️


የ10 ክፍል ተፈትናችሁ ውጤታችሁ እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ የቻናላችን ቤተሰቦች #የተረጋገጠ_መረጃ_ከፈተናዎች_ኤጀንሲ እንዳገኘን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ሆኖም በተለያዩ የቴሌግራም ቻናል እንዲሁም ፌስቡክ ላይ እስካሁን እየተለቀቁ ያሉ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ተገንዝባችሁ ትክክለኛውን መረጃ እስከምናደርሳችሁ ድረስ በትግስት ተጠባበቁ።

@YeneTube @FikerAssefa
በድጋሚ ወገኔን ለማስተማር እሮጣለሁ!!

በከተማችን(ወሊሶ )ቅን ወጣቶች የተቋቋመው የ" we are one " የበጎ አድራጎት ማህበር ባሳለፍነው አመት "ወገኔን ለማስተማር እኔም እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የሩጫ ዉድድር ማሰናዳቱ የሚታወስ ነዉ።በዘንድሮ አመትም በተመሳሳይ መሪ ቃል በአይነቱ ልዩ ሆነ ሩጫ ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን እየጠበቀ ይገኛል ታድያ እርሶም ከሰኞ 12/12/2011 ጀምሮ የሩጫ ቲሸርት በመግዛት ከአላማችን ጎን ይሰለፉ!

የቲሸርቱ ዋጋ 100 ብር

የቲሸርቱ መገኛ ቦታ:
ፖስታ ቤት ፣የኛ ህንፃ ፣ክርኪስ እናም ሁሉም ቦታ አዙረው በመሸጥ ላይ ከሚገኙ አባላቶች

ammas lammii koo barsiisuuf aniis nan fiigaa!

Dargaggotaa garalaafeeyii magaalaa keenyaan Kan dhaabbatee waldaan walgargaarsaa "we are one" akkuma bara darbeetti fiigicha guddaa dhaadanoo "lammi koo barsiisuuf aniis nan fiigaa" jedhun qopheessuun isaa ni yadatamaa.alanas fiigicha Haalan adda ta'e qopheessee isiin eegaa Jira. isiinis tishartii kaayyoo Kanaaf qophaa'e biituun nu ciinaa dhaabadha.
Tessoon kenya naannoo mana postaa, gamoo Kenya, kirkisii fi harka miseensota Kenya irra argachu dandessu.

Gatiin tishartiichas qarshii 100 qofa
የነፃ ህክምና በዱከም!!

ከኮሪያ የመጡ የህክምና ባለሙያዎች ከኮሪያ ሆስፒታል ጋር በመጋራ በመሆን በዱከም ከተማ ነፃ የክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የህክምና ባለሙያዎቹ ከዱከም ከተማ ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር ነው ለሶስት ቀናት የሚቆየውን ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት የጀመሩት።በነፃ የህክምና አገልግሎቱ የሰው ሰራሽ ጥርስ ተከላ፣ የውስጥ ደዌ፣ ፊዚዮቴራ እና የነርቭ ህክምና ነው እየተሰጠ ያለው።የነፃ የህክምና አገልግሎቱን በዱከም ከተማ በኮሪያ ባለሀብቶች የተገነባው ኢኮስ የብረታብረት ፋብሪካ መሆኑም ተገልጿል።የዱከም ጤና ጣቢያ ሃላፊ አቶ ታምራት ማሞ እንደለገጹት፥ በ22 የህክምና ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከ1 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢኮስ ብረታብረት ፋብሪካ የነፃ ህክምና አገልግሎት አስተባባሪ ቦ ውንክ ኪን፥ ፋብሪካው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር አብሮ የመስራት እና የማደግ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ይህንን የማህበረሰብ አገልግሎት ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።አገልግሎቱ በቀጣይም በተለያዩ ጊዜያት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉ ሲሆን፥ ከዱከም ከተማ በተጨማሪም በጅማ፣ በሀረር፣ በዲላ እና በድሬ ደዋ ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ምንጭ:ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
#ጂማ
የጅማ ከተማ ፈረንጃራዳ ሰፈር ወጣቶች "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው" በሚል መርህ ለሁለተኛ ጊዜ ዘንድሮም የአልበሳት፣ጫማ፣ ደብተር እና እስክሪፕቶ የማሰባሰብ ፕሮግራም ጀምረናል የመሰባሰብ ፕሮግራሙ እስከ ጳጉሜ 3 የሚቀጥል ሲሆን፣ከ ጳጉሜ 4-6ደግሞ አልባሳት የማከፋፈል ፕሮግራም የሚከናወንይሆናል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሃያ አንድ ዓመቱ የተቀጨው ሕንፃ!!

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሲገለገልበት የቆየው ለገሃር አካባቢ የሚገኘው ባለ አራትና ሰባት ወለል ሕንፃ፣ እንደ ብዙዎቹ የአዲስ አበባ የዕድሜ እኩዮቹ በአገልግሎት ዘመኑ ልክ ባለበት ቦታ ለመቆየት ያልታደለ ሆኗል፡፡ቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ በሚል መጠሪያ ይታወቅ በነበረው መንግሥታዊ ተቋም ባለቤትነት የተገነባው ይህ ሕንፃ፣ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ይኖረዋል ተብሎ የተገነባ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የታሰበው ረዥሙ ዕድሜው ተገቶ ለሃያ ዓመታት ብቻ ቆይቶ እንዲፈርስ ተፈርዶበታል፡፡

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመዲናዋ ውስጥ ከሚገኙ በትልቅነታቸው ከሚጠቀሱት ሕንፃዎች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ሕንፃ፣ ያለ ዕድሜው ሳይታሰብ እንዲፈርስ የተፈረደበት በለገሃር አካባቢ ይገነባል ተብሎ ከሚጠበቀው ግዙፍ የከተማዋ ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ከሰሞኑ ይህ ሕንፃ ወደሚገኝበት አካባቢ ብቅ ለሚሉ ሰዎች፣ በቫርኔሮ ኩባንያ የተገነቡት ጠንካራ ምሰሶዎችና በዕምነበረድ የተለበጠው የሕንፃው አፅም ብቻ ይታያል፡፡ ውስጣዊ አካሉ ከፈራረሰ በኋላ ሕንፃውን ያቆሙትን ምሰሶዎች ማፍረስ ተጀምሯል፡፡ሕንፃውን ቀድሞ በዋና መሥሪያ ቤትነት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት፣ አሁን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጓዙን ጠቅልሎ በቅርብ ርቀት ወደሚገኘው የራሱ ሕንፃ ተዛውሯል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእስራኤል የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

ዶክተር ዐብይ አሕመድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ እና ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር ይወያያሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) በእስራኤል ያድቫሽም ቤተ ሰማእታት መታሰቢያ ሙዚየም የአበባ ጉንጉን ያስቀምጣሉ።

ሙዚዬሙ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በናዚ ጀርመን ለተጨፈጨፉት 6 ሚሊዮን አይሁዳውያን ማስታወሻ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀውልቱን ጎብኝተው የአበባ ጉንጉን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በእስራኤል የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል እና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በዚህ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ እና ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋርም ይወያያሉ።

ምንጭ:- AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ ከደሴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የሚያደርገው ውይይት ተጀምሯል። «እኛ ከእናንተ ልንሰማ፣ ልንመከር እንጂ ልናስተምር፣ ልንመክር አልመጣንም!» የኢዜማ ምክትል መሪ አንዱዓለም አራጌ የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ነው።
Via:- Nardos
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዋሳ ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሀዋሳ ከተማን ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች በመሆኑ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች መጥተው በከተማዋ ቆይታ እንዲያደርጉ የተለያዩ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ጥሪ አቀረቡ፡፡ከሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ አካላት ከተማዋን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድ ለሁለት ቀን ይፋዊ ለስራ ጉብኝት እስራኤል ገብቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም ፌስቲቫል ዛሬ በጅጅጋ ይጀመራል

ሀገር አቀፍ የሰላም ፌስቲቫል ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው ።

የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እንደገለፀው ፌስቲቫሉ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚዘልቅ ነው ።

የርእሰ መስተዳደሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሡልጣን አብዲ አሊ ሸገሕ እንደገለፁት በከተማው የሚካሔደው የሰላም ፌስቲቫል ሀገራዊ የሰላም እሴቶችን ለማጠናከር የሚረዱ የፓናል ውይይቶች ፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና የሙዚቃ ኮንሰርት ያካተተ ነው ።

በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትርና የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በጋራ ባዘጋጁት በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፉ ከአራት ሺህ በላይ እንግዶችና ታዋቂ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪው ገልፀዋል።

ምንጭ፡-ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa