⬆️⬆️
በባሕር ዳር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ልማት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየተወያዩ ነው።
Via Asemahegn Asres
@YeneTube @FikerAssefa

ፎርብስ አፍሪካ የመስከረም (September) እትሙን "ኢትዮጵያ: የአፍሪካ ኩራት" በሚል ርእስ ይዞ ይወጣል። ከፕሬዝደንት ሳህለወርቅ፣ ጠ/ሚር አብይ፣ ዶ/ር ይናገር እና ወ/ሮ ዳግማዊት ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅን ይዞ ይቀርባል።
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ጤፍን ለማምረት ኬሚካል ማዳበሪያን የሚተካ ደቂቅ አካል ተገኘ፡፡
በኬሚካል ማዳበሪያ ምትክ ደቂቅ አካላትን በመጠቀም ጤፍ ማምረት መቻሉን የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡በኬሚካል ማዳበሪያ ምትክ ደቂቅ አካላትን በመጠቀም ጤፍ ለማምረት የሚያስችል ምርምር ተገኝቷል።ግኝቱም በኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት የደቂቅ አካላት ብዝሃ ሕይወት ዳይሬክተር ተመራማሪ በሆኑት አቶ ዘሪሁን ጸጋዬ አማካኝነት በቤተ ሙከራና በተግባር ተረጋግጧል፡፡እንደ ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ ተመራማሪው ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለዕጽዋት ዕድገት ማፋጠኛ የሚሆኑ ደቂቅ አካላትን ለመለየት 1ሺ375 የጤፍ አፈርና የጤፍ ስር ናሙናዎችን ሰብስበዋል፡፡ ከተሰበሰበው ናሙናም ቤተ ሙከራ ግምገማ 38 የባክቴሪያ እና 17 የፈንገስ በድምሩ 55 ከፍተኛ አቅም ያሳዩ ዝርያዎች ተለይተዋል።
Via SRTA

በሀዋሳ ያለው ኮማንድ ፖስት ቢነሳም ችግር እንደማይገጥም ተገለፀ፡፡
ሀዋሳ ለእንቅስቃሴ የሚያሰጋ ሁኔታ ውስጥ አለመሆኗን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡
ኅብረተሰቡ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን እየያዘ ለህግ አካላት በማጋለጥ በየጊዜው ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅትም ከተማዋ የተረጋጋች በመሆኗ የመዝናኛ ቦታዎች 24፡00 አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
ሠላም እንዳይመጣ ህገ ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ ተገኝተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 68 ሰዎች በኮማንድ ፖስቱ ሥር መያዛቸው፤ ከተያዙት ሰዎች መካከል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንደማይገኙበትም ታውቋል፡፡

ስፖርት!!!
የቀድሞ የፋሲል ከተማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሰበታ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።የሁለት አመት ውልም ፈርሟል።
Via Timotios Baye

በሐምሌ አስራ አንዱ ጥቃት ንብረት ለወደመባቸው ግለሰቦች ካሳ እንደሚሰጥ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ተናገረ፡፡
በወቅቱ በነበረው ችግር በከተማዋ የ3 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሀዋሳ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሀላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃን ገ/መድህን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ሁለት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል፤ በአንድ ህንፃ ላይም ጉዳት ደርሶ ነበር ተብሏል፡፡ንብረት ለወደመባቸው የከተማ አስተዳደሩ ካሳ ይከፍላል የተባለ ሲሆን የጠፉ ንብረቶችንም የማስመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰላም የማረጋገጥ ስራ እየተከወነ መሆኑን የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ገለታ ገረመው የከተማዋ ሰላም ወደነበረበት ተመልሷል ብለዋል፡፡የኮማንድ ፖስቱ ሀላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃንም ይህንኑ ይጋራሉ፡፡የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ከመንቀሳቀስ ውጪ የሚሰራው ስራ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ከክፍለ ከተሞች እስከ ቀበሌ በተዋቀረው ኮማንድ ፖስት አማካኝነትም ስለ ሰላም ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ በራሱ ሰላሙን ማስጠበቅ ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡እስከ አሁን በተሰራው ሰላም የማስከበር ስራ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ተብሏል፡፡ከተማዋ ሰላሟን መልሳ ካገኘች የኮማንድ ፖስቱ መቆየት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄም ለሀላፊው ቀርቦላቸዋል፡፡እሳቸውም የኮማንድ ፖስቱን ቆይታ የሚወስነው የክልሉ መንግስት ነው ብለዋል፡፡
ኮሎኔል ተክለብርሃን ገብረ መድህን በአሁኑ ሰኣት በከተማዋ የሚያሳስብ የሰላም ችግር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡
Via Sheger Radio

የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።
ምክር ቤቱ በቆይታው የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ ባለፈም የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።
በተያያዘ ዜና የምክር ቤቱ አባላት ከመደበኛ ጉባኤው አስቀድመው በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ከተማ መክረዋል።ምክክሩ በሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታና ክልላዊ ጉዳዮች ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚለውንና በክልሉ እየተነሱ ያሉት የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በሚመለከት የተደረገ ነው ተብሏል።
ምንጭ: ፋና

በምስሉ የምትመለከቱት ሰው አቶ ወርቁ አይተነው የሚባል ሲሆን በአማራ ክልል በሚገኙ በሁለት ዞኖች ማለትም በሰሜን ጎንደር ዳባት፣ ጠለምት እና ጃናሞራ ወረዳዎች የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን በራሳቸው ወጪ ሙሉ በሙሉ ለመገንባት ቃል ገብቷል፡፡
ፎቶ፦ሳሌም አብዲ
#ዋልተንጉስ_ዘሸገር/ታዲያስ አዲስ
@YeneTube @FikerAssefa
ፎቶ፦ሳሌም አብዲ
#ዋልተንጉስ_ዘሸገር/ታዲያስ አዲስ
@YeneTube @FikerAssefa
እንደ ዴሎይቴ ዶዝዬር ዘገባ የኬንያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ገንዘብ በጥቁር ገበያ ወደ ኬንያ ያሸሽ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ፡፡
በዛሬው ዕለትም ኢ/ር ታከለ ኡማ እራሳቸው እድሳቱን ያስጀመሩትን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቃኘው ሻለቃ ተብሎ በሚጠራው አደባባይ አከባቢ የሚኖሩ እናት መኖሪያ ቤት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ለባለንብረቷ ቤታቸውን አስረክበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር 1000 ለሚሆኑ አረጋዊያን ቤት ለማደስ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም እስከ አሁን 1,573 ለሚሆኑ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ 1,111 ቤቶች እድሳት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለባለንብረቶቹ ተላልፈዋል፡፡
Via Mayor Office

Breaking News!!!
አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡
የስፖርት ኮማሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ርስቱ ይርዳው በምክር ቤቱ ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡ ምክር ቤቱ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስን ከኃላፊነታቸው በማንሳት ነው ለአቶ ርስቱ ይርዳው በዛሬው ዕለት ሹመቱን የሰጠው፡፡

በአማራ ክልል በ150 ሚሊየን ብር ግንባታው የተከናወነው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖሎጂ ተመረቀ።
በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ የተገነባው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ በ150 ሚሊየን ብር የግንባታና የማሽን ተከላ ስራው ተጠናቆ ተመረቀ። ኩባንያውየአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።
-ፋና

ይህ ማስታወቂያ በአፋር ክልል፣ አሳይታ የስደተኞች ጣብያ ትናንት የተለጠፈ ነው!
በርካታ ኤርትራዊያንን ጨምሮ ሌሎች ስደተኞች የምዝገባ አገልግሎት በመቆሙ እየተቸገሩ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ማብራርያ ከሰጠበት በሁዋላ ላይ እመለስበታለሁ።
Via:- Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
በርካታ ኤርትራዊያንን ጨምሮ ሌሎች ስደተኞች የምዝገባ አገልግሎት በመቆሙ እየተቸገሩ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ማብራርያ ከሰጠበት በሁዋላ ላይ እመለስበታለሁ።
Via:- Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የሚዲያ ነፃነት ሙያተኛው በአግባቡ እየተጠቀመበት አይደለም
ነሀሴ 25/2011 በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን የሚዲያ ነፃነት የዘርፉ ባለሙያዎች በአግባቡ እየተጠቀሙበት አይደለም ሲሉ ምሁራን ገለፁ።
የግል መገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው የፖለቲካ ለውጡን ተከትሎ እየተስፋፋ የነበረው የመረጃ ተደራሽነት ተመልሶ እየጠበበ መምጣቱን ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው ሁለንተናዊ የለውጥ ሂደት ካመጣቸው ትሩፋቶች መካከል የመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚስተዋለው የሥራ ነፃነት አንዱ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።
መንግስት ባልተለመደ ሁኔታ የመገናኛ ብዙሃን በነፃነት የሚንቀሳቀሱበትን አመቺ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር የመረጃ ምንጭ አማራጮችም እንዲሰፉ የበኩሉን ተግባር ማከናወኑንም
እንዲሁ።
ለዚህም ማሳያው መስራት ተስኗቸው ከአገር የወጡ ጋዜጠኞች ወደአገር ቤት ተመልሰዋል፤ በአገር ውስጥም ተዘግተው የነበሩየህትመት ሚዲያዎች ሥራቸውን ጀምረዋል ሲሉም ያመለክታሉ።
ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በፊት ለሚዲያ ተቋማት ዝግ የነበሩ የመንግስትና ሌሎች መረጃዎችም በተሻለ መጠን ለመገናኛ ብዙሃን ክፍት መሆናቸውንም የዘርፉ ባለሙያዎችና ምሁራን
ይገልፃሉ።
ይሁን እንጂ የመገናኛ ብዙሃኑ የተፈጠረላቸውን ይህንን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ እየተጠቀሙበት አይደለም ሲሉ ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ምሁር የሆኑት ዶክተር ንጉሴ ተፈራ ይናገራሉ።
ከለውጡ በፊት ‘አድርጉ አታድርጉ’ የሚለው ልዩነትና ግጭት በመንግስትና በመገናኛ ብዙሃኑ መካከል እንደነበር የሚገልፁት ዶክተር ንጉሴ ነፃነቱ ከመጣ በኋላ ግን ልዩነቱና ግጭቱ በህዝቡና በመገናኛ ብዙሃኑ መካከል እየሆነ ነው ሲሉም አመልክተዋል።
ለዚህም ምክንያቱ አብዛኛው የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኛ ሥራውን እያከናወነ ያለው ከሙያው ስነ ምግባርና መርሆ ባፈነገጠ መንገድ መሆኑ ነው በማለት ተናግረዋል።
via:- ዋልታ

ቦትስዋና በገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን አማካኝነት አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ቀጠሮ ያዘች፡፡
ፕሬዝዳንት ሞክዌቲ ማሲሲ ቦትስዋና በመጪው ጥቅምት 23 ቀን 2019 (እ.አ.አ.) በሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን አማካኝነት አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ መግለጫውን የሰጡት የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ከተበተኑ በኋላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
በቀጣዩ የጥቅምት ምርጫ መሪ ድርጅቱ የቦትስዋና “ዲሞክራቲክ” ፓርቲን እና ዋና ተቀናቃኙን “አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ” ፓርቲን ጨምሮ ከስድስት የማያንሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከመስከረም 26 ጀምሮም እጩ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ክልሎች መመዝገቢያ ማዕከላት ቀርበው እንደሚመዘገቡ የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኦፊሊ ማሮባ አስታውቀዋል፡፡ የአጠቃላዩ ምርጫ አሸናፊዎች 57 የሀገራዊ እና 490 የአካባቢ መስተዳድር ቦታዎችን እንደሚሸፍኑ ነው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ያስታወቁት፡፡
የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምርጫውን ማሸነፍ ከቻለ ፕሬዝዳንት ሞክዌቲ ማሲሲ ቦትስዋናን በፕሬዝዳንትነት በመምራት እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡
ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን
@Yenetube @FikerAssefa

በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል። ጉባኤው በቆይታው የ2011 አም የእቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ ላይ የመከረ ሲሆን፥ በሶስተኛው ቀን ውሎም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ መክሯል።
Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ሁዋዌ በቀጣይ የሚያመርተው ስልክ አቅጣጫ አመላካች (ጉግል ማፕ) እና ዩቲዩብን ጨምሮ ሌሎች የጉግል መተግበሪያዎች ላይኖሩት እንደሚችል ተገልጿል። የጉግል ኩባንያ፤ የአሜሪካ መንግሥት የሁዋዌ ምርቶች በአገሪቷ እንዳይሸጡ በመከልከሉ ምክንያት መተግበሪያዎቹን ለቻይናው ግዙፍ ስልክ አምራች ድርጅት- ሁዋዌ ፈቃድ መስጠት አልችልም ብሏል።
-BBC
@YeneTube @FikerAssefa
-BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባለዲግሪው መፃህፍት አዟሪ በብልሽት ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ ለስራ እንዲሆነው ከከተማ አስተዳደሩ ተበረከተለት።
ከተመረቀ በኋላ መፃህፍት በማዞር ህይወቱን ሲመራ የነበረው ወጣት አንዷለም ይስሃቅ ከከተማ አስተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ በኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተበረከተለት ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ወጣቱ ደርሶበት በነበረው የአእምሮ ህመም ችግር ሳይበገር እና ስራ ጠባቂ ሳይሆን እራሱን ለመለወጥ ያደረገው ጥረት ለብዙዎች አርአያ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል።
ከዚህ ቀደምም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በፋና ቀለማት ላይ ቀርቦ የህይወት ልምዱን አካፍሎ እንደነበረ ይታወሳል።በጥቂት ጊዚያት ውስጥም በከተማዋ ያለ አገልግሎት የቆሙ ሌሎች 700 የሚሆኑ አንበሳ የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተንቀሳቃሽ ሱቆች በመቀየር በከተማዋ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።ይህ ተግባር በአንድ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ የመፍጠር ግዙፍ እቅድ አካል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በችግሮች ሳይበገሩ ራሳቸውን ለመቀየር እየሞከሩ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት አላማ ያደረገ ተግባር ነው።

የኢዜማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከወጣቶች ጋር ተወያዩ።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከወጣቶች ጋር ተወያይተዋል።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከወጣቶች ጋር ተወያይተዋል። በዚህም ውይይት ላይ ወጣቶች ለሀገራቸው ከፍተኛ ሚና ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢዜማ ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ወይዘሪት ፂዎን እንግዳዬ « ሀገራችንን ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማሸጋገር እንችላለን» ብለዋል።
ምንጭ:DW