YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር ዛሬ ነሐሴ 24/2011 ለሰባት ድርጅቶች የማዕድን ምርመራ እና ለሦስት ድርጅቶች ደግሞ የማዕድን ምርት ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል። ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች በደቡብ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ብሔራዊ ክልሎች በማዕድን ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።

-አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጅጅጋ ወደ ሶማልያ በረራ ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ ነው!

የአየር መንገዱ ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ አስራት በጋሻው ማምሻውን እንደነገረኝ በረራው እንዲጀመር ፍላጎቱ ስላለ አየር መንገዱም ዝግጅት ላይ ነው። "በረራው አለም አቀፍ ይዘት ስለሚኖረው የኢሚግሬሽን፣ ጉምሩክ እና ተያያዥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው" ብሎ ገልፁዋል።

እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት አንድ ሰው ከጅጅጋ ወደ ሶማልያ ለመሄድ አዲስ አበባ መጥቶ በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል ማለፍ ይጠበቅበት ነበር።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
Proposed BiT 2012 Calendar only entrance date activities.pdf
429.5 KB
⬆️⬆️
Bahir Dar University 2012 E.C Academic Calender

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የ10 ክፍል ውጤት በተመለከተ ⬇️


የ10 ክፍል ተፈትናችሁ ውጤታችሁ እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ የቻናላችን ቤተሰቦች #የተረጋገጠ_መረጃ_ከፈተናዎች_ኤጀንሲ እንዳገኘን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ሆኖም በተለያዩ የቴሌግራም ቻናል እንዲሁም ፌስቡክ ላይ እስካሁን እየትፕለቀቁ ያሉ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ተግንዝባችሁ እኛ ትክክለኛውን መረጃ እስከምናደርሳችሁ ድረስ በትግስት ተጠባበቁ።
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️

በባሕር ዳር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ልማት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየተወያዩ ነው።

Via Asemahegn Asres
@YeneTube @FikerAssefa
ፎርብስ አፍሪካ የመስከረም (September) እትሙን "ኢትዮጵያ: የአፍሪካ ኩራት" በሚል ርእስ ይዞ ይወጣል። ከፕሬዝደንት ሳህለወርቅ፣ ጠ/ሚር አብይ፣ ዶ/ር ይናገር እና ወ/ሮ ዳግማዊት ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅን ይዞ ይቀርባል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ጤፍን ለማምረት ኬሚካል ማዳበሪያን የሚተካ ደቂቅ አካል ተገኘ፡፡

በኬሚካል ማዳበሪያ ምትክ ደቂቅ አካላትን በመጠቀም ጤፍ ማምረት መቻሉን የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡በኬሚካል ማዳበሪያ ምትክ ደቂቅ አካላትን በመጠቀም ጤፍ ለማምረት የሚያስችል ምርምር ተገኝቷል።ግኝቱም በኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት የደቂቅ አካላት ብዝሃ ሕይወት ዳይሬክተር ተመራማሪ በሆኑት አቶ ዘሪሁን ጸጋዬ አማካኝነት በቤተ ሙከራና በተግባር ተረጋግጧል፡፡እንደ ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ ተመራማሪው ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለዕጽዋት ዕድገት ማፋጠኛ የሚሆኑ ደቂቅ አካላትን ለመለየት 1ሺ375 የጤፍ አፈርና የጤፍ ስር ናሙናዎችን ሰብስበዋል፡፡ ከተሰበሰበው ናሙናም ቤተ ሙከራ ግምገማ 38 የባክቴሪያ እና 17 የፈንገስ በድምሩ 55 ከፍተኛ አቅም ያሳዩ ዝርያዎች ተለይተዋል።

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
በሀዋሳ ያለው ኮማንድ ፖስት ቢነሳም ችግር እንደማይገጥም ተገለፀ፡፡

ሀዋሳ ለእንቅስቃሴ የሚያሰጋ ሁኔታ ውስጥ አለመሆኗን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡

ኅብረተሰቡ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን እየያዘ ለህግ አካላት በማጋለጥ በየጊዜው ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅትም ከተማዋ የተረጋጋች በመሆኗ የመዝናኛ ቦታዎች 24፡00 አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

ሠላም እንዳይመጣ ህገ ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ ተገኝተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 68 ሰዎች በኮማንድ ፖስቱ ሥር መያዛቸው፤ ከተያዙት ሰዎች መካከል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንደማይገኙበትም ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!!!

የቀድሞ የፋሲል ከተማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሰበታ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።የሁለት አመት ውልም ፈርሟል።

Via Timotios Baye
@YeneTube @FikerAssefa
በሐምሌ አስራ አንዱ ጥቃት ንብረት ለወደመባቸው ግለሰቦች ካሳ እንደሚሰጥ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ተናገረ፡፡

በወቅቱ በነበረው ችግር በከተማዋ የ3 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሀዋሳ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሀላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃን ገ/መድህን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ሁለት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል፤ በአንድ ህንፃ ላይም ጉዳት ደርሶ ነበር ተብሏል፡፡ንብረት ለወደመባቸው የከተማ አስተዳደሩ ካሳ ይከፍላል የተባለ ሲሆን የጠፉ ንብረቶችንም የማስመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰላም የማረጋገጥ ስራ እየተከወነ መሆኑን የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ገለታ ገረመው የከተማዋ ሰላም ወደነበረበት ተመልሷል ብለዋል፡፡የኮማንድ ፖስቱ ሀላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃንም ይህንኑ ይጋራሉ፡፡የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ከመንቀሳቀስ ውጪ የሚሰራው ስራ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ከክፍለ ከተሞች እስከ ቀበሌ በተዋቀረው ኮማንድ ፖስት አማካኝነትም ስለ ሰላም ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ በራሱ ሰላሙን ማስጠበቅ ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡እስከ አሁን በተሰራው ሰላም የማስከበር ስራ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ተብሏል፡፡ከተማዋ ሰላሟን መልሳ ካገኘች የኮማንድ ፖስቱ መቆየት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄም ለሀላፊው ቀርቦላቸዋል፡፡እሳቸውም የኮማንድ ፖስቱን ቆይታ የሚወስነው የክልሉ መንግስት ነው ብለዋል፡፡
ኮሎኔል ተክለብርሃን ገብረ መድህን በአሁኑ ሰኣት በከተማዋ የሚያሳስብ የሰላም ችግር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።

ምክር ቤቱ በቆይታው የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ ባለፈም የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና የምክር ቤቱ አባላት ከመደበኛ ጉባኤው አስቀድመው በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ከተማ መክረዋል።ምክክሩ በሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታና ክልላዊ ጉዳዮች ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚለውንና በክልሉ እየተነሱ ያሉት የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በሚመለከት የተደረገ ነው ተብሏል።

 ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
በምስሉ የምትመለከቱት ሰው አቶ ወርቁ አይተነው የሚባል ሲሆን በአማራ ክልል በሚገኙ በሁለት ዞኖች ማለትም በሰሜን ጎንደር ዳባት፣ ጠለምት እና ጃናሞራ ወረዳዎች የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን በራሳቸው ወጪ ሙሉ በሙሉ ለመገንባት ቃል ገብቷል፡፡

ፎቶ፦ሳሌም አብዲ
#ዋልተንጉስ_ዘሸገር/ታዲያስ አዲስ
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለው የውሀ ፓርክ በቢሾፍቱ ዛሬ ተመርቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
እንደ ዴሎይቴ ዶዝዬር ዘገባ የኬንያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ገንዘብ በጥቁር ገበያ ወደ ኬንያ ያሸሽ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለትም ኢ/ር ታከለ ኡማ እራሳቸው እድሳቱን ያስጀመሩትን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቃኘው ሻለቃ ተብሎ በሚጠራው አደባባይ አከባቢ የሚኖሩ እናት መኖሪያ ቤት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ለባለንብረቷ ቤታቸውን አስረክበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር 1000 ለሚሆኑ አረጋዊያን ቤት ለማደስ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም እስከ አሁን 1,573 ለሚሆኑ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ 1,111 ቤቶች እድሳት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለባለንብረቶቹ ተላልፈዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
Breaking News!!!


አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

የስፖርት ኮማሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ርስቱ ይርዳው በምክር ቤቱ ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡ ምክር ቤቱ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስን ከኃላፊነታቸው በማንሳት ነው ለአቶ ርስቱ ይርዳው በዛሬው ዕለት ሹመቱን የሰጠው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በ150 ሚሊየን ብር ግንባታው የተከናወነው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖሎጂ ተመረቀ።

በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ የተገነባው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ በ150 ሚሊየን ብር የግንባታና የማሽን ተከላ ስራው ተጠናቆ ተመረቀ። ኩባንያውየአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።

-ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ይህ ማስታወቂያ በአፋር ክልል፣ አሳይታ የስደተኞች ጣብያ ትናንት የተለጠፈ ነው!

በርካታ ኤርትራዊያንን ጨምሮ ሌሎች ስደተኞች የምዝገባ አገልግሎት በመቆሙ እየተቸገሩ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ማብራርያ ከሰጠበት በሁዋላ ላይ እመለስበታለሁ።

Via:- Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa