YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በትምህርት ጉባኤው የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ ተገኝተዋል።እንዲሁም ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የመጡ የትምህርት አመራሮችና ሙያተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ የትምህርት ጉባኤ "ስር ነቀል የትምህርት ስርዓት ለውጥ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገት!“ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምንጭ:Fana
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Kiru 👔
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
🌻🌻እንኳን ለአዲሱ ዓመት🌻🌻
🌻🌻በሰላም አደረሳችሁ!🌻🌻

TARGET MARKETS® እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ታላቅ ቅናሽ ማድረጋችንን ስንገልፅ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው!
@onlinesaleandbuy
📣ፈጣን ታማኝ እና ተደራሽ online shopping

📌እቤትዎ ቁጭ ብለው ያሻዎትን በማይታመን ዋጋ መሸመት ይፈልጋሉ👇

@kiru04
+251 931607806
➡️የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN 👇 ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ።
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFBAc0Ri5bEWs7J4TQ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

💥እንግዲያውስ የምን እየዞሩ shopping ላይ ጊዜ ማጥፋት የፈለጉትን,ይዘዙ የፈለጉትን የግሎ ያድርጉ!!!!👇👇👇

📞+251 931607806
📩 @kiru04

Join us @onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy
JOIN 👇 ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ።
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFBAc0Ri5bEWs7J4TQ
89 ኢንቨስተሮች ተሰናብተዋል!

በጋምቤላ ክልል በአኝዋ ዞን 201 የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች ወደ ሥራ ሲገቡ፤ 89ኙ በገቡት ቃል መሰረት በጊዜ ወደ ሥራ ባለመግባታቸው እና የመሬት መጠቀሚያ ግብር ባለመክፈላቸው እንዲሁም ከልማት ባንክ የወሰዱትን ብድር ባለመመለሳቸው ማሰናበቱን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡጉላ ኡጁሉ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ 201 የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች በዞኑ መዋዕለ ንዋያቸውን አፍሰው ራሳቸውንና ሀገራቸውን በመጥቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንቨስተሮቹ ወደ ልማት ለመግባት በገቡት ውል መሰረት ሥራውን የጀመሩ ሲሆን የመሬት መጠቀሚያ ግብርም እየከፈሉ ናቸው፡፡ 89 ኢንቨስተሮች በገቡት ቃል መሰረት በጊዜው ወደ ሥራ ያልገቡበትን እና የመሬት መጠቀሚያ ግብር ያልከፈሉበትን ምክንያት እንዲያሳውቁና ወደ ሥራ እንዲገቡ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጻፍላቸውም መጥተው ለማሳወቅ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ አቶ ኡጉላ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቶሺባ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ ጠየቁ።
በጃፓኗ ዮኮሃማ ከተማ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የቲካድ7 ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ሚኒገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዛሬው እለት የቶሺባ ኩባንያን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውን የቶሺባ ኩባንያን የኢነርጂ ዘርፍ የሆነውን (Toshiba energy systems and solutions corporation) ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በተጨማሪም ከቶሺባ ኩባንያ ዋና ሀላፊ ጋርም ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ መጪው ዘመን የአፍሪካ በመሆኑ ቶሺባ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ነዋዩን ቢያፈስ ትርፋማ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በኢነርጂ ዘርፍ ሰፊ ዕድል እንዳለም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የገለጹት።

Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ኦዲፒ በ2012 እቅድ ላይ እየመከሩ ነው።

የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) በ2012 እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።የውይይት መድረኩ በዛሬው እለት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የውይይተ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅትም፥ መድረኩ በምን ጉዳዮች ላይ ሊያተኩር ይገባል የሚለውን ማብራራታቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በኢራን ላይ በፈፀመችው የሳይበር ጥቃት ሀገሪቱ በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት የምትፈፀምበት መሳሪያ ላይ ጉዳት ማድረሷ ተገለፀ፡፡

የኢራን ብሄራዊ ዘብ  አብዮት በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚጠቀምበት መሳሪያ በሰኔ ወር ላይ  በአሜሪካ የሳይበር ጥቃት እንደተፈፀመበት ተጠቁሟ፡፡፡

በዚህም ኢራን  በፔርሺያ ባህረሰላጤ በተለያዩ ሀገራት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የምታሳድረው ተፅዕኖ ለመቀነስ እንደሚያስችል ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡

ኢራን የተፈፀመባትን ጥቃት ተከትሎ የወታደራዊ መገናኛ ኔትወርኩን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ጥረት እያደረገች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በጥቃቱ  የጠፋውን መረጃ መመለሷ ተነግሯል፡፡

ይህ ጥቃት ያልተነገረው የሁለቱ ሀገራት የሳይበር ጦርነት መሆኑን ያሳየው ዘገባው ይህም አሜሪካ በኢራን ለተፈፀመባት ጥቃት የአፀፋ ምላሽ  እየሰጠች መሆኑን የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡ ሲ ኤን ኢ ቲ
@YeneTube @FikerAssefa
በአለም ገና ሰበታ አካባቢ የሚገኘው ኤቨረስት ዩዝ አካዳሚ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ስርዓተ ትምህርት አላከበረም በሚል መዘጋቱ ተገለጸ።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በአፍ መፍቻ ቋንቋ እያስተማረ አይደለም በሚል የዘጋው ት/ቤት ወላጆችን ለእንግልት ዳርጓል።

የት/ቤቱ መምህራንና ወላጆች ደግሞ ሌሎች ብዙ በአማርኛ ቋንቋ የማያስተምሩ ቢኖሩም በአማርኛ ስላላስተማረ ነው ት/ቤታችን እንዲዘጋ የተደረገው እያሉ ነው፡፡

በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ልጆቻቸውን ለመጪው ዘመን ያስመዘገቡ ወላጆች ተንገላታን፣ምን ማድረግ እንዳለብንም ግራ ገባን ሲሉ ቅሬታቸውን ለጣቢያችን አሰምተዋል፡፡

በአለም ገና ሰበታ አካባቢ የሚገኘው ኤቨረስት ዩዝ አካዳሚ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ስርዓተ ትምህርት አላከበረም ተብሎ ተዘግቷል፡፡

ወላጆቹ ሰበታ ትምህርት ቢሮ በመሄድ ፤ ለማስመዝገቢያ ገንዘብ ከፍለናል ፣ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የመጪው ዓመት ትምህርት መጀመሪያ ቀንም እየተቃረበ ነው ፣በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ ሌላ ትምህርት ቤት ለልጆቻችን አናገኝም፤ብናገኝም ለዚህ ትምህርት ቤት ከምንከፍለው ሁለት ሺህ ብር ተጨማሪ ወጪ ይጠይቀናል በማለት በኦሮሞ ባህል መሰረት አባ ገዳን ጭምር ይዘው ቢማፀኑም ከፈለገ ትምህርት ቤቱን ሸጦ ገንዘባችሁን ይክፈላችሁ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ምላሹ ያስከፋቸው ሶስት ሺህ አካባቢ የሚሆኑ ወላጆችም የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ቢሮ ድረስ በመሄድ ቅሬታቸውን አቅርበናል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶም ጊዜው የመደመርና የይቅርታ እንደሆነ ጠቅሰው ትምህርት ቤቱ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮን በፅሁፍ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ገቢውን አሳውቆ ግብር እንዲከፍል፣ በዚህ ድርጊቱ ቀጥሎ ቢገኝ እና ትምህርት ቤቱ ቢዘጋ ወላጆች ሀላፊነቱን ትወስዳላችሁ የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ትምህርት ቤቱ እንዲከፈት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተውልን በር ብለዋል እነዚህ ወላጆች፡፡

ሃላፊው ግን ቃላቸውን ጠብቀው ትምህርት ቤቱን አላስከፈቱልንም የሚሉት እነዚህ ወላጆች በድጋሚ ጥያቄ አቅርበው የራሳችሁ ጉዳይ የፈለችሁበት ቦታ ማስተማር ትችላላችሁ የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ሰምተናል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሀላፊውን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

የክልሉን ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ግርማ ባይሳ ወላጆቹ ላነሱት ጥያቄ ትምህርት ቤቱ ከዚህ ቀደም ተማሪዎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲያስተምር ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው እና ይህንንም ባለማድረጉ እንዲዘጋ መወሰኑን ነግረውናል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ቤቱ ባለቤትና ዳይሬክተር በፖሊስ ተይዘው እንደታሰሩ ወላጆቹ ነግረውናል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @FikerAssefa
ባለፉት 2 ቀናት ብቻ ተሽከርካሪዎችና ከ2. 3 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ።

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሕግን ለማስከበር እየሠሩት ባለው ሥራ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ኬላዎች የተለያዩ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸው ተገልጿል።በዚህም መሠረት ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የሰሌዳ ቁጥሩ ኦሮ 3-66095 የሆነ ሚኒባስ ግምታዊ ዋጋቸው 290 ሺህ ብር የሆኑ የተለያዩ አልባሳት ጭኖ ከአወዳይ ከተማ ወደ ምሥራቅ ሐረርጌ ሲንቀሳቀስ መያዙ ታውቋል።

በተመሳሳይ ቀን የሰሌዳ ቁጥሩ ድሬ 3-04756 የሆነ ሀይሉክስ መኪና ግምታዊ ዋጋቸው 80 ሺህ ብር የሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ጭኖ ሲንቀሳቀስ በክልሉ ፖሊስ ኮንትሮባንድ መከላከል ቡድን ተይዟል።በዚያው ዕለት የሰሌዳ ቁጥር ሱማ 3-00607 የሆነ ተሽከርካሪ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ ሲንቀሳቀስ አውበሬ መቆጣጠርያ ጣቢያ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።ነሐሴ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ ሱማ 3-04446 የሚል ሐሰተኛ ታርጋ የለጠፈ ተሽከርካሪ ጂግጂጋ አካባቢ ሲንቀሳቀስ የኮንትሮባንድ መከላከል ሠራተኞች ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጅማ አባ ጅፋር ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል። የቅጣቱም መንስኤ ለተጫዋቾች በአግባቡ ደሞዝ አለመክፈሉ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦነግ ወታደራዊ ክንፍ ከፖለቲካ አመራሩ ራሱን አግልሎ መንግስትን በሀይል ለመታገል መወሰኑ ተሰምቷል ፤ መንግስት ብርቱ ማስጠንቀቂያ ስጥቷል ተብሏል።ከዚህ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃውን በኢትዮ FM የዋዜማ ራዲዮ ሳምንታዊ ፕሮግራም ዛሬ 12:00 ላይ ይከታተሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
የጉደር ፋጦ ግድብ በ950 ሚሊዮን ብር ሊገነባ ነው።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን 950 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የጉደር ፋጦ ወንዝ ላይ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል። ኮርፖሬሽኑ ከውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመስኖ ልማት ኮሚሽን ጋር ተፈራርሞ ሥራ ሊጀምር መሆኑን ነው የገለጸው።ከአዲስ አበባ በ150 ኪሎ ሜትር ርቆ ኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ልዩ ስሙ መልኬ ዴራ ቀበሌ ውስጥ በፋጦ ወንዝ ላይ የሚገነባው የጉደር ፋጦ ግድብ በሶስት ዓመታት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን፣ በአካባቢው ላለው ማህበረሰብ እንዲሁም፣ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፆ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ለገበያ ማረጋጊያ የተገዛው ስንዴ ጅቡቲ ወደብ ላይ አምስት ወር ተከማችቶ በመቆየቱ ከጥቅም ውጭ እየሆነ ነው ተባለ፡፡ስንዴውን ያመጣው የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በውሉ መሰረት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ወደ ሃገር ሊያጓጉዝ ውል ቢገባም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

ምንጭ: ሸገር ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ለማካሄድ የሚያግዝ 175 ማሽን ተገዝቶ ወደ አማራ ክልል መግባቱን የጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከቅድመ ካንሰር ደረጃ ካለፈ የጨረር ህክምና ነው የሚያስፈልው፡፡ አገልግሎቱ ደግሞ በጥቁር አንበሳ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ ለታካሚዎች አስቸጋሪ እንደሚያደርገው በባሕር ዳር ፈለገ ህይዎት ሪፈራል ሆስፒታል የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ማንደፍሮ ሞላ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ የማህፀን በር ካንሰር ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ በሚባል ተህዋስያን አማካኝነት ነው የሚከሰተው፡፡ ህመሙ በማህጸን አካባቢ ቁስለት በመፍጠር ሴቶችን ለሞት እንደሚዳርጋቸውም ነው ዶክተር ማንደፍሮ የተናገሩት፡፡በመሆኑም በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ሴቶች ከ21 ዓመት ጀምረው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

-አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የመመዝገቢያ መስፈርቶች⬆️⬆️⬆️

@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና!!
አካል ጉዳተኛው አሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አለፈ።

ባሳለፍነዉ ሰኞ ነሐሴ 20/2011 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ ለጉዳይ ባቀኑበት አቃቂ ክፍለ ከተማ ድረስ ኹናቸው የተባሉ ዐይነስውር ግለሰብ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብተው በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወታቸው ማለፉ ታዉቋል።በአደጋው ሕይወታቸው ያለፈው ግለሰብ ጉዳይ ለመጨረስ ባቀኑበት አቃቂ ክፍለ ከተማ 7ኛ ፎቅ ደርሰው ወደ ታች ለመውረድ የአሳንሰሩን ቁልፍ ተጭነው ቢከፈትላቸውም አሳንሰሩ ግን ወለል አልነበረውም፤ 21 ሜትር በሚገመተው የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ተምዘግዝጎ በመዉረድ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።በብሔራዊ ዐይነ ሥውራን ማህበር ሥር በሚተዳደረው የወላይታ ዐይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ትምህርቱን ተከታትለዋል። በዘንድሮ ዓመትም በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ማሰልጠኛ ፕሮግራም በዲፕሎማ ተመርቀዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ደኅንነታቸውና ጥራታቸውን ያልጠበቁ 4,763.62 ቶን የተለያዩ ዓይነት የምግብ ምርቶችን በኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ቁጥጥር ወቅት አግኝቼ አስወግጃለው ብሏል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በከተማይቱ አዉሮፕላን ማረፊያ አጠገብና አካባቢ የተገነቡ «ሕገ-ወጥ» ያላቸዉን ቤቶች ማፍረስ ጀመረ።

ቤቶቹን የሚያፈርሰዉ ግብረ-ኃይል «ሥራ» እንዳይታወክ የከተማዋ አስተዳደር፣ የፌደራል ፖሊስን እና ባካባቢዉ የሠፈረዉ የሐገር መከላከያ ሠራዊት ፀጥታ እያስከበሩ ነዉ።ይሁንና የቤቶቹን መፍረስ የሚቃወሙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ቤቶቹን በሚያፈርሱት ላይ
ድንጋይ በመወርወር እና ጎማ በማቃጠል እርምጃዉን ተቃዉመዉታል።

አንዳንድ ተሽከርካሪዎች በድንጋይ መመታታቸዉን የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ ዘግቧል።የድሬዳዋ መስተዳድር ቤቶቻቸዉ ለሚፈርሱባቸዉ ነዋሪዎች ተለዋጭ ሥፍራም ሆነ ካሳ ሥለመስጠት-አለመስጠቱ ግን የተባለ ነገር የለም።ኢትዮጵያ ዉስጥ የአዲስ አበባን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞች ባለስልጣናት «ሕገ-ወጥ» የሚሏቸዉ ቤቶች ከመገንባታቸዉ በፊትና ሲገነቡ፣ እንዳይገነቡ ከመከላከል ይልቅ ከተገነቡና ሰዎች በየቤቶቹ መኖር ከጀመሩ በኋላ ማፍረስ የተለመደ ነዉ።

እየተገነቡ በኃይል በሚፈርሱ ቤቶች ምክንያት ለሚባክነዉ ሐብት፣በነዋሪዉ ላይ ለሚደርሰዉ መንገላታትና ኪሳራ ብዙ ትኩረት የሚሰጠዉ ወገን ያለ አይመስልም።

የድሬዳዋ መስተዳድር በከተማይቱ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የተሰሩትን «ሕገ-ወጥ» ቤቶች ማፍረስ የጀመረዉ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ቤቶቹ ካልፈረሱ በረራ እንደሚያቋርጥ ካስጠነቀቀ በኋላ ነዉ።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
#ሰበር_ዜና

ምርጫ ቦርድ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውስኔ መስጫ ቀንን ይፋ አደረገ።

ቦርዱ ዛሬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውስኔ መስጫ ቀን ህዳር 3 ቀን 2012 ዓም እንዲሆን ተወስኗል።

ቦርዱ ለዚህ ስራም ከነሀሴ 30 ቀን 2011 ዓም አንስቶ 8ሺህ 460 ምርጫ አስፈጻሚዎችን እንዲሁም 1 ሺህ 692 የህዝበ ውሳኔ ደምጽ መስጫ ጣቢያዎችን አደራጃለሁ ብሏል።

ለህዝበ ውሳኔው ስራ ማስኬጃ 75 ሚሊዮን 615 ሺህ ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ወጪውን የደቡብ ክልል ምክር ቤት ይሸፍናል ተብሏል።

Via:- EthioFM
@YeneTube @FikerAssefa
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ያለበትን ሂደት አስልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያስፈጽምለት መጠየቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቦርዱ አመራሮች ከተሟሉለት በኋላ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን በሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ቦርዱን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ማድረግ የሚገባቸውን ዝግጅቶች በዝርዝር አሳውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ቦርዱ ለምክር ቤቱ በላከው ደብዳቤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ

1. በአሁኑ ወቅት የክልሉም የዞኑም አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሃዋሳ ከተማን አስመልክቶ የህዝበ ውሳኔው ውጤት የሲዳማን ክልላዊ መንግስት መቋቋም የሚያረጋግጥ ቢሆን ከተማዋን አስመልክቶ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብቶችና ግንኙነቶች ከዚህም ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎችን የሚያስተናግዱበትን አሰራር ዘርግቶ ለቦርዱ በጽሁፍ እንዲያሳውቅ

2. የህዝበ ውሳኔው ጸጥታና ደህንነት ማስጠበቅን አስመልክቶ የፌደራል የክልል እና የዞኑ ፓሊስ በትብብር የሚሰሩበትን ሁኔታ የሚያመቻች የስራ እቅድ አዘጋጅቶ ለቦርዱ እንዲያሳውቅ

3. የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ የሌሎች ብሄር ብሔረሰብ አባላት ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚኖራቸውን ህጋዊ የመብቶች ጥበቃን በተመለከተ ግልጽ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፍ እንዲያዘጋጅና እንዲያሳቅ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የክልል ምክር ቤት በበኩሉ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ምላሹን ለቦርዱ አቅርቧል፡፡ በምላሹም ክልሉ ካለበት ሁኔታና የስራ ጫና አንጻር የሲዳማ ዞን ክልላዊ መንግስት ሆኖ ቢቋቋም ከሃዋሳ ከተማ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ህጋዊ ማእቀፍና እና በዞኑ የሚኖሩ ሌሎች የብሔር ብሔረሰብ አባላት ስለሚኖራቸው የመብት ጥበቃ ጊዜ ወስዶ መወያየት እንደሚገባው፣ ህግ ማውጣት ድረስ የሚደርስ ስራ መሆኑን ህግ ማውጣት ደግሞ፣ ማርቀቅ፣ ህዝብ አስተያየት መሰብሰብ እንዲሁም ማጽደቅን የሚጨምር ስራ በመሆኑ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ክልሉ በኮማንድ ፓስት ስር የሚተዳደር በመሆኑ የተጠቀሱት የአሰራርና የህግ ማእቀፎችን የሚፈልጉ ጉዳዮችን ለማቅረብ ተለዋጭ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል፡፡

በዚህም መሰረት ቦርዱ የተለያዩ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ ምክር ቤቱ ምላሹን እስከ ነሃሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቅ በሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ጠይቋል፡፡

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በነሃሴ 16 ቀን 2011 አ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ህዝበ ውሳኔው የሲዳማን ክልል መሆን ቢያረጋግጥ የሃዋሳ ከተማን አስመልክቶ ሁለቱ አካላት ስለሚኖራቸው ግንኙነትና የሃብት ክፍፍል ህግ ለማውጣትና ህጋዊ ማእቀፍ ለማዘጋጀት እንዲሁም በዞኑ የሚኖሩ ሌሎች ብሔረሰብ አባላትን ስለሚኖራቸው መብትና ጥበቃ ከህገ መንግስቱ በተጨማሪ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፎችን ለማዘጋጀት ጊዜ ስለሚያስፈልግ አሁን ማቅረብ እንደማይችል ገልጾ ነገር ግን ከህዝበውሳኔው አስቀድሞ የህግ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎቹን በማጽደቅ እንደሚያቀርብ አረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን ዋና ዋና ውሳኔዎች አስተላልፎ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡

1. ቦርዱ ከነሃሴ 20 ቀን 2011 አ.ም እስከ ህዳር 10 ቀን 2012 ድረስ የሚቆይ የህዝበ ውሳኔውን የድርጊት መርሃ ግብር እና በጀት አዘጋጅቶ ለደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት እና ለሚመለከታቸው አካላት የላከ ሲሆን በእቅዱ መሰረት የህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫ ቀን ህዳር 03/2012 አ.ም ይሆናል፡፡

2. ቦርዱም በድርጊት መርሃ ግብሩ መሰረት፣ የባለድርሻ አካላትን ማስተባበር እና የአፈጻጸም ውይይት የማድረግ ስራውን ከነሃሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ሳምንታት የሚያከናውን ሲሆን ከዚህም ተጨማሪ የ 8,460 (ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ) ምርጫ አስፈጻሚዎችን መመልመል 1,692 ( አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት) የድምጽ መስጫ ጣቢያዎችን ማደራጀት፣ የህዝበ ውሳኔ መመሪያዎች የማውጣትና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመት የመሳሰሉትን ስራዎች ያከናውናል፡፡

3. ቦርዱ በተጨማሪም ከመስከረም 07 ቀን 2012 አ.ም ጀምሮ የህዝበ ውሳኔውን ጸጥታና ደህንነት ጥበቃ የእቅድ ዝግጅት ለማከናወን ከፌደራል፣ ከክልል እና ከዞን የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ እቅድ የማውጣት ውይይቶችን ያደርጋል፡፡

4. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የሀዋሳን ከተማ የወደፊት ሁኔታ፤ የሀብት ክፍፍል እና የሌሎች ብሄረሰብ አባላትን የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎችን ማውጣት ስራ እስከ መስከረም 22 ድረስ ያጠናቀቃል፡፡

5. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ቦርዱ ባቀረበው ዝርዝር የበጀት እቅድ መሰረት ህዝበ ውሳኔን ለማፈጸም የሚያስፈልገውን 75,615,015.00 (ሰባ አምስት ሚልዮን ስድስት መቶ አስራ አምስት ሺህ አስራ አምስት) ብር በጀት እስከ መስከረም 12 ቀን 2012 አ.ም ድረስ ወደ ቦርዱ የባንክ አካውንት ያስተላልፋል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ የቴክኒክ ጉዳዮች በቀሪው ጊዜ ሲያጠናቅቅ ባለድርሻ አካላትም በተሰናዳው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በመወጣት ሕዝበ ውሳኔው በታቀደለት ጊዜ መሰረት እንዲከናወን የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ያስታውቃል፡፡

ነሃሴ 23 ቀን 2011 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
#FraudAlert Ethio Telecom ከአጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ ሲል ከላይ የምታዩትን መልዕክት አስተላልፏል ።

#Share
@YeneTube @FikerAssefa