YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሃገራችንን ሁኔታ ለመፍትሄ የቸገረና ውስብስብ እያደረጉ ካሉት ነገሮች ዋነኛው የሚዲያዎች ኃላፊነት እያጡ መምጣት ነው አለ ኢዜማ

ሚዲያዎቻችን የፖለቲካው ምህዳር ነፀብራቅ ሆነዋል ያለው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ሚዲያዎች የሉም በሚባል ደረጃ ጥቂት ሆነዋል ብሏል፡፡

የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ሚዲያዎች የፖለቲካ ምህዳሩን ልዩነቶች የራሳቸው በማድረግ አልያም ልዩነቱን በፈጠሩ አካላቶች ስር ሆነው ፤እንዲሁም ውስብስብ የሆነውን የሃገራችንን ሁኔታ ይበልጥ ውስብስብና ለመፍትሄ አስቸጋሪ እያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

ሚዲያዎቹ የራሳቸውን አቋም ይዘው፣መሄድ የምንፈልገው ወዲህ ነው ብለው፤ለራሳቸው አላማ መስጠት የተሳናቸው ይመስለኛል ብለዋል አቶ ናትናኤል፡፡

የተነሱለትንና ከሚዲያ የሚጠበቀውን አላማ ማገልገላቸውን ወደ ጎን በማለት የፖለቲካ አመለካከቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች አገልጋይ ከመሆናቸውም በላይ እነዛ አመለካከቶች ተቀባይ እንዲሆኑ እየሰሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይሄ አያዋጣም ያሉት አቶ ናትናኤል ማንኛውም ሚዲያ ሆነ ጋዜጠኛ የማወጣው መረጃና እንደ ሃገርና ህዝብ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል በማለት ማሰብና ሃላፊነት መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ናትናኤል ገለጻ የተከሰተ ነገር ሁሉ እውነት ስለሆነ መዘገብ መነገር የለበትም፡፡ ይልቁንም የሚያስከትለው ጥፋት ካለ መገምገም ይኖርበታል፡፡

የሚዲያ ባለቤቶችና ተዋንያንን ጨምሮ ሃገር ሲፈርስ ሁሉም ነው የሚፈርስበት፤ ያሉ ሲሆን በተለይ ሚዲያ ካለው ሀይል አንፃር ጉዳት እንዲያደርሱ ሰዎችን ሊያነሳሳ ይችላልና እዚህ ላይ ጥንቃቄ መውሰድ ተገቢ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Via:- Ethio Fm
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ፣ የመድሃኒት ዕጥረት ተባብሷል- ብሏል የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር፡፡ በተለይ የአስም፣ ስኳር እና ደም ብዛት መድሃኒቶች ዕጥረት አሳሳቢ መሆኑን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ለሸገር ተናግረዋል፡፡ መድሃኒቶቹ ባንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልቃሉ፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው መድሃኒት መጠንም በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ሐኪሞች የሚያዟቸው መድሃኒቶች በሕጋዊ መንገድ የገቡ ወይም ትክክለኛ መድሃኒት መሆን ይሁኑ አይሁኑም በቂ ማረጋገጫ የለም፡፡ መንግሥት ለመድሃኒት ግዥ በቂ የውጭ ምንዛሬ እንዲመድብም ማኅበሩ ጠይቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት የኒውክሊየር ሃይል ቴክኖሎጅ የመሸጥ ሃሳብ እንዳላት ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ የሩሲያ ኒውክሊየር ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ናይጀሪያ እና ግብጽ ጋር ውሎችን ፈጽመዋል፡፡ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የተገቡት ውሎች ግን መለስተኛ የሚባሉ ናቸው፡፡ ውል የሚገቡ ሀገሮች ከሩሲያ የረጅም ጊዜ ብድር ያገኛሉ፡፡ እስካሁን ግን ሩሲያ ለናይጀሪያና ግብጽ ከጀመረቻቸው በስተቀር፣ በአፍሪካ ያጠናቀቀችው የኒውክሊየር ግንባታ የለም፡፡

-Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
@kiru04
+251 931607806
➡️የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN 👇 ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ። 👇

@onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFBAc0Ri5bEWs7J4TQ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አማራ መስተዳድር ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ከሁለት ወር በፊት በተፈፀመዉ ግድያ የተጠረጠሩ የቀድሞ ባለስልጣናትን ጉዳይ የሚመለከተዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበዉን ይግባኝ ዉድቅ አደረገ።የተጠርጣሪዎቹን ጉዳይ ይመለከት የነበረዉ የባሕርዳር ወረዳ ፍርድ ቤት፣ መርማሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጣቸዉ አቅርበዉት የነበረዉን ጥያቄ ከዚሕ ቀደም ዉድቅ አድርጎት ነበር።ከሁለት ሳምንት በፊት እዚያዉ ባሕርዳር ያስቻለዉ የወረዳዉ ፍርድ ቤት መርማሪዎች በ15 ቀናት ዉስጥ ክስ እንዲመሰርቱ አዝዞም ነበር።መርማሪዎች የወረዳዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመቃወም ያቀረቡትን ይግባኝ ሲመረምር የሰነበተዉ የባሕርዳርና አካባቢዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ዛሬ ይግባኙን ዉድቅ አድርጎ የወረዳዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ አፅድቆታል።ባለፈዉ ሰኔ 15 የአማራ መስተዳድር ከፍተኛ ባለስልጣናትን ገድለዋል፣ አስገድለዋል ወይም ከገዳዮች ጋር ተባብራዋል በሚል ጥርጣሬ ከታሰሩት መካከል የቀድሞዉ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጌድየር ጄኔራል ተፈራ ማሞና የክልሉ የሠላምና ግንባታ የሕዝብ ደሕንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ ይገኙበታል።ከሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት ጋር ሌሎች 46 ተጠርጣሪዎች ከሰኔ 16 2011 ጀምሮ እንደታሰሩ ነዉ::
via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመሠርቱት ካቢኔ ከፖለቲከኞች ይልቅ ባለሙያዎችን ያካተተ እንደሚሆን አስታወቁ።አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር እንደሚሉት የሚሾሙት ሚንስትሮች ሐገሪቱ ያለባትን ሁለንታናዊ ችግሮች የማቃለል ሙያዊ ብቃት ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ የአዲሱን ካቢኔ አባላት ዛሬ ማምሻ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ።የሱዳን የጦር ጄኔራሎችና የጄኔራሎቹን አገዛዝ ሲቃወም የነበረዉን ሕዝብ ሲያስተባብሩ የነበሩ የነፃነትና የለዉጥ ኃይላት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ከመከላከያና ከሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትሮች በስተቀር የተቀሩትን የሚመርጡት ጠቅላይ ሚንስትሩ ናቸዉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሚንስርነት የሚመርጡት ደግሞ የነፃነት እና የለዉጥ ኃይላት ከሚያቀርቡላቸዉ እጩዎች መካከል ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትር ሐምዶክ ትናንት የ49 እጩዎች ዝርዝር እንደደረሳቸዉ አስታዉቀዋል።ከ49ኙ መሐል 14ቱን በሚንስትርነት ይሾማሉ።የሴቶች መብት አቀንቃኞች ባዲሱ ካቢኔ የሴቶች ተሳትፎ ከፍ እንዲል ግፊት እያደረጉ ነዉ።
@YeneTube @FikerAssefa
3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ የቅድመ ሰው የራስ ቅሪት አካል በአፋር ክልል ተገኘ።

በአፋር ክልል አዲስ የተገኘው ቅሪተ አካል “አውስትራሎፒቲከስ አናመንሲስ” በሚባል የቀድሞ ሰው ዝርያ ውስጥ የሚመደብ ሲሆን እስከ ዛሬ ስለ ዝርያው ያልታወቀውን የፊት እና የጭንቅላት ቅርፅ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳያል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጣቸው።

ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሀገር ላይ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት ከሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ግንኙነት መሰረት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡እንደ ዶክተር ኤርጎጌ ገለፃ ከዚህ በፊት በሀገወጥ መንገድ ለሄዱት ዜጎች የተሰጠው ህጋዊ ፈቃድ ቢያስደስታቸውም ከዚህ በኋላ በሀገ ወጥ መንገድ ለሚሄዱ ዜጎች ምንም አይነት ምህረት እንደማይደረግና ሲያዙም ቀጥታ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ ያመለክታል፡፡

ምንጭ:EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የብሪታኒያ ፓርላማ ሊዘጋ ነው።

ባለፈዉ ሐምሌ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስልጣን የያዙት ቅኝ አክራሪዉ ፖለቲከኛ ቦሪስ ጆንሰን የሐገሪቱ ንግሥት ፓርላማዉን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያግዱ ጠይቀዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማዉ እንዲዘጋ የፈለጉት መንግስታቸዉ ከአዉሮጳ ሕብረት ጋር ሳይስማማ ሐገሩን ከሕብረቱ ቢያስወጣ ከማርላማዉ ሊገጥመዉ የሚችለዉን ተቃዉሞ ለማገድ ነዉ።ጆንሰን በመጪዉ ጥቅምት ብሪታንያን ከሕብረቱ አባልነት ለማስወጣት ዐቅደዋል።

ምንጭ:DW
@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በጤናው ሴክተር ለ3ኛ ጊዜ ተከበረ።

ይህ በዓል በሀገር ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ ‘’የትምህርት ጥራን ለማሻሻል ምክንያታዊ ወጣት እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በጤናው ሴክተር ለ3ኛ ጊዜ “የጤናን ግብ ለማሳካት ምክንያታዊ ወጣት እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል ዛሬ በፓናል ውይይት እና የደም ልገሳ ፕሮግራም ተከብሯል፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከነገ ጀምሮ ማየት ውጤታቹን ማየት ትችላላችሁ ተብላቿል!! ፣የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና የወሰዳችህ በሙሉ

የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና የተሰጠን ሲሆን ወጤቱንም ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም ለጤና ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው ተቋማት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ተማሪዎች ውጤታቸውን በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ይችላሉ፡፡

ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ወርቅ እና ነሀስ👏👏👏
በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች

3 ሺ መሰናክል

1ኛ መቅደስ አበበ
3ኛ ወይንሸት አንሳ
ማለዳ በተከናወነው የ20 ኪ,ሜ የእርምጃ ውድድር

በወንዶች ዮሐንስ አልጋው - ብር
ዮሐልዬ በለጠው - ነሀስ

Via Ariyat Raya
@YeneTube @FikerAssefa
የካናዳው አውሮፕላን አምራች ደ ሐቪላንድ ኩባንያ 25ኛውን ዳሽ 8-400 አውሮፕላን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስረከቡን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ባለፈው ነሐሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. መረከቡን ኩባንያው ገልጿል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካናዳዋ ኦንታሪዮ ከተማ የሚመረቱትን ዳሽ 8-400 አውሮፕላኖች በአብዛኛው ለአገር ውስጥ በረራ ይጠቀምባቸዋል። አውሮፕላኑን ለመረከብ ወደ ካናዳ ያቀኑት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም ዳሽ 8-400 በአቅሙ እና ለደንበኞቹ ምቹ በመሆኑ በአፍሪካ ከሚገኙ አየር መንገዶች ለተጀመረው ሽርክና እና በገበያው ለተወጠነው ዕድገት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። የካናዳው ኩባንያ 600ኛ ስሪቱ የሆነውን አውሮፕላን ሲሸኝ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነሲሴ ጫሊ ተገኝተዋል።

Via Sheger Tribune
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from HEY Online Market
Iphone_7_( 32 GB)
#BigDiscount
Color : Rose gold
and Matte black
Storage: 32 GB
Price : # 9,999 birr

Contact us
0953964175
0925927457
0956111111
ከቲካድ የመሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ጸጥታ ላይ የሚመክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው ::

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከጃፓን አቻቸው ሽንዞ አቤ ጋር ተወያዩ።

በጃፓን ዮኮሀማ እየተካሄደ ባለው የቲካድ 7 የመሪዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ በሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት ዙርያ ነው ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ ጋር የመከሩት።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ለልማት ተሰጥተው ለአመታት ታጥረው የተቀመጡ 262 ቦታዎች እስከ መጪው መስከረም ወር የማይለሙ ከሆነ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በ2012 የራዲዮ ግንኙነት መሳሪያዎችን በሙሉ አቅም ልታመርት ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በተያዘው በጀት ዓመት የራዲዮ ግንኙነት መሳሪያዎችን በሙሉ አቅም ለማምረት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው መሳሪያዎቹ ከዚህ ቀደም ከውጪ ወደ አገር ውስጥ ይገቡ እንደነበር ገልፆ፥ ይህም ለአገር ደኅንነት ከፍተኛ ስጋት እንደነበሩ ገልጿል።
ምርቶቹንም በአገር ውስጥ ለማምረት በተደረገው ቅድመ ዝግጅት ለባለሙያዎች በውጭ አገርና በአገር ውስጥ ስልጠና እንደተሰጠም ታውቋል።

ምንጭ:Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ለምህንድስና ተማሪዎችና በልምድ ለሚሠሩ ባለሙያዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው።

ስልጠናው ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ ይካሄዳል ከዩኒቨርስቲ ለሚመረቁ የምህንድስና ተማሪዎችና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ዉስጥ በልምድ እየሠሩ ላሉ ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙያዊ ብቃት እንዲኖራቸዉ የሚያስችል ፕሮጀክት በጀርመን የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማህበር መተግበር ጀመረ።ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ጋር በትብብር ዳብሮ አሁን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመግባት ላይ መሆኑን የጀርመን የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ሔንዝ ሪትማን ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa