YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባንኩ ደንበኞች ያስተላለፈው መልክት⬆️

"ነሃሴ 18 ዕለት በመላሁ ሀገሪቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት እንደማይሰጥ ገልፀዋል"።

@YeneTube @FikerAssefa
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ መግለጫ

በህገ ወጥ የመማር ማስተመር ስራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ባልተፈቀደላቸው የትምህርት መስክ ላይ ተሰማርተው ተገኘተው እገዳ የተጣለባቸው 18 የግል ካምፓሶች የሃገሪቱ የትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደራቸውን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ገለጸ።

ኤጀንሲው በዚህ ህገ ወጥና የማይጠበቅ ስራ ተሰማሩ ያላቸው ባህርዳር ፣ ጅማ ፣ ሀረማያ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች የተቋማቱን ሃብትና መምህራን በመጠቀም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን ተገቢነት የጎደለው ስራ ላይ ተሰማርተው መቆየታቸውን፣ አሁን ግን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ክልከላ ተከትሎ 3ቱ ከድርጊታቸው የተቆጠቡ ሲሆን ጅማ ዩኑቨርሲቲ ግን የሚኒስቴሩን አቅጣጫ ወደጎን በማለት አሁንም አስተምራለሁ እያለ ተማሪዎችንም እየመዘገበ እንደሚገኝ ኤጀንሲው ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ መንግስት የማያውቃቸውን ተማሪዎች እያስተማሩ ከፍተኛ ገንዘብ እየሰበሰቡ ነው የሚለው ኤጀንሲው በተለይ ጅማ ዩኑቨርሲቲ የሚያስከፍለው ገንዘብ የተጋነነና አዲስ አበባ ላይ አብሮት እየሰራ ያለውንም ተቋም እውቅና የሰጠሁት ባለመሆኑ ተገቢው እርምጃ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንዲወሰድበት ተይቋል።

በእነዚህ ተቋማት የተመረቁም ይሁን እየተማሩ ያሉት ተማሪዎች እጣን በተመለከተ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ወደፊት እርምጃ እንደሚወሰድና ግልጽም እንደሚደረግ ተገልጿል።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
እንዳያመልጦ❗️

ዛሬ አርብ ነሐሴ 17 ቀን ምሽት በ3:00 ሰዓት በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በውስጥ ጽዳት ምንነት አስፈላጊነትና አተገባበር ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት ይከታተሉ::

@YeneTube @FikerAssefa
ኃይሌ ቃሉን ተገበረ❗️

አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ትምህርት ቤቱን ሊያስመርቅ ዋግ ኽምራ ገብቷል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም ነበር በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ የሚገኘውን የገልኩ የዳስ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ደረጃውን የጠበቀ አድርጎ ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠው፡፡

በወቅቱ “ትምህርት ቤቱን ለ2012 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ ከዳስ ለማላቀቅ ጥረት አደርጋለሁ” ብሎ ነበር፡፡ ግንባታው አራት ወራት ባልሞላ ጊዜ ተጠናቅቆ ለምረቃም ለማስተማርም ተዘጋጅቷል። ኃይሌ ቃሉን እውን አድርጓል፡፡

አትሌቱ በድጋሜ ወደ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተመልሷል፡፡ ትናንት ማታ በሰቆጣ፣ ዛሬ ደግሞ ፃግብጂ ወረዳ ገልኩ ትምህርት ቤት ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ጠብቆታል፡፡ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሦስት ወራት ውስጥ በሁለት ሕንፃዎች የተከፈሉ ስምንት ክፍሎችን ነው ያስገነባው ተብሏል፡፡

ኃይሌ ትምህርት ቤቱን ሊያስመርቅና ለትውልድ ቀረፃ አደራውን ሊያስተላልፍ ወደ ዋግ የመጣው ከባለቤቱ ጋር ነው፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በትምህርት ቤቱ ምረቃ ተገኝተዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
33 የምግብ አምራችና አስመጭዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

በ33 የምግብ አምራችና አስመጪ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የተቋሙን የ2011 እቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ አስመልክቶ ትናንት መግለጫ ሰጥቷል። የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሳምሶን አብርሃም እንደተናገሩት ህገ ወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ በተገኙ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

“ህገወጥ ተግባራትን በፈፀሙ አካላት ላይ ምርቶችን ከማስወገድ አንስቶ ተቋማቱን እስከ ማስዘጋት ደርሰናል” ያሉት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ከዘርፉ የማስወጣት እና በህግ የመጠየቅ ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ ጥቆማዎችን መሠረት በማድረግ መድሃኒት እና ምግብ አስመጪዎች ላይ ፍተሻዎችን በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ነው ያስታወቁት፡፡

የታሸጉ ምግቦች በብዛት በበረሃማ አካባቢዎች ስለሚገቡ ወደ አደገኛ ኬሚካልነት እንደሚቀየሩና በኅብረተሰቡ ላይም ከፍተኛ የጤና ጉዳት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ ተመላክቷል። እንደ አዲስ ዘመን ዘገባ በበጀት ዓመቱ በኅብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሁም ድንገት በተደረገ ፍተሻ ከ4 ሺህ 763 ቶን በላይ ምግብ መያዙን አቶ ሳምሶን አስታውቀዋል።

በ33 የምግብ አምራችና አስመጪ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

Via:- AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኤርትራ ከ4000 በላይ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ሳዋ ማሰልጠኛ ላከች፡፡ እንደ ዶቸ ቬሌ ዘገባ እነዚህ ተማሪዎች ከሰባት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ ናቸው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
"ባለፈው በጀት ዓመት 791 የሚደርሱ የበይነ መረብ ጥቃቶችን መከላከል ተችሏል።" ኢንሳ

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 17/2011 ዓ.ም (አብመድ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ሊያደርሱ የነበሩ 791 የሚደርሱ የበይነ መረብ ጥቃቶችን መከላከሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለጸ ።

በኤጀንሲው የኢትዮጵያ ሳይበር የድንገተኛ ዝግጁነት እና ምላሽ ሰጭ ዲቪዥን ኃላፊ አቶ አብርሃም ገብረጻዲቅ በሀገሪቱ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የበይነ መረብ ጥቃቶችን አስቀድሞ በመከላከል እና ከተከሰቱ በኋላ የከፋ ጉዳት እንዳያደርሱ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በ2011 በጀት ዓመት በሀገሪቱ ላይ የተቃጡ የበይነ መረብ ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከል በመቻሉ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ማዳን መቻሉንም ነው የገለፁት።

በገንዘብ ሊተመን የማይችል ሰላም እና ፍትህን ማስጠበቅ መቻሉንም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በያዝነው በጀት ዓመት ሀገራዊ የበይነ መረብ ጥቃት የመከላከል ሽፋንን በማሳደግ እና ዓለም አቀፍ ትስስርንና ቅንጅትን በማጠናከር የሀገሪቱን ቁልፍ የበይነ መረብ መሠረት ልማቶች ደኅንነት የማስጠበቅ ሥራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

Via:- AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአስቸኳይ እረፍታቸውን አቋርጠው እንዲመጡ ተጠሩ።

የምክር ቤቱ አባላት ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ስራቸውን አጠናቀው ለእረፍት የተበኑት።

ይሁንና የምክር ቤቱ አባላት ነገ ለአስቸኳይ ስብሰባ እረፍታቸውን አቋርጠው እንደተጠሩ የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ስራ ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ነገ ሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ተጠርተዋል።

ምክር ቤቱ በነገው ውሎውም የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በዚህ አዋጆች ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁን እንደማይቀበሉት ማሳወቃቸው ይታወሳል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአገሪቱ ከሚያስገነባቸው 6 እስር ቤቶች መካከል ይኸ በድሬዳዋ የሚገኝ ነው። እስከ 6 ሺሕ ታራሚዎች ይይዛል የተባለው እስር ቤት በሚቀጥለው አመት ሥራ ይጀምራል ተብሏል። ያዩት እንደሚሉት VIP ክፍሎች ጭምር አለው።

Via:- Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘመናዊ የሲስተም ማሻሻያ ለማድረግ ቅዳሜ ነሃሴ 18 ቀን 2011 አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቀ፡፡

ባንኩ ዘመናዊ የዲጅታል ባንክ አገልግሎቶቹን ለማስፋት፣ ለደንበኞች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የቴክኖሎጂ አቅሙን ለማሳደግ እየንቀሳቀሰ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
በዚህ መሰረት ነሃሴ 18 ቀን 2011 የሲስተም ማሻሻያ የሚያደርግ በመሆኑ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች አገልግሎት እንደማይሰጡ ተጠቁሟል፡፡

የኤቲ ኤም ማሽኖች እና የሲ.ቢ .ኢ ብር ግን የተለመደውን አገልግሎት እንደሚሰጡ ባንኩ አስታውቋል፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንኮክ እና ሀኖይ ከተሞች አዲስ የጭነት በረራ ጀመረ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ቦርድ በቂ ጥናት ሳይደረግባቸው ግንባታቸው በተጀመሩ 12 ማምረቻ ፋብሪካዎች ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

ኮርፖሬሽኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች ቢሊየን ብሮችን በመመደብ የ12 ፋብሪካዎች ግንባታ ጀምሮ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚንስትር አሎክ ሻርማና ልዑካቸውን ዛሬ ጠዋት ተቀብለው አነጋገሩ::
ሁለቱ ወገኖች እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ተወያይተዋል::
ሀገርበቀል የለውጥ ማሻሻያዎችን ያደነቁት ሚንስትር ሻርማ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ያላቋረጠ ጥረት አመስግነዋል::

#PMOEthiopia
@YeneTube @Fikerassefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአስቸኳይ እረፍታቸውን አቋርጠው እንዲመጡ ተጠሩ።

የምክር ቤቱ አባላት ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ስራቸውን አጠናቀው ለእረፍት የተበኑት።
ይሁንና የምክር ቤቱ አባላት ነገ ለአስቸኳይ ስብሰባ እረፍታቸውን አቋርጠው እንደተጠሩ የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ስራ ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ነገ ሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ተጠርተዋል።
ምክር ቤቱ በነገው ውሎውም የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በዚህ አዋጆች ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁን እንደማይቀበሉት ማሳወቃቸው ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በወርልድ ቴኳንዶ የወንዶች ውድድር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

በውድድሩ በ63 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ታሪኩ ግርማ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

እንዲሁም በ54 ኪሎ ግራም በሰለሞን ቱፋ የነሀስ ሜዳሊያ አስመዝግባለች፡፡

ታሪኩ የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ውድድሩን ከጊኒው ሶሞሀ ሳሊያ ጋር ተጫውቶ 25 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ተከታዩ ዙር አልፏል።

በመቀጠልም በሩብ ፍፃሜውና በግማሽ ፍፃሜው ተጋጣሚዎቹን በማሸነፍ ለፍጻሜ ውድድር በቅቷል።

በትናንቱ የፍጻሜ ጨዋታም የቱኒዚያውን ከዛሚ ያሲንን ስምንት ለስድስት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሌላም በኩል በቦክስ ውድድር በ63 ኪሎ ግራም አትሌት ሳሙኤል ሙሉጌታ እንዲሁም በ69 ኪሎ ግራም አትሌት መስፍን ብሩ የኬፕ ቨርዴ እና የናሚቢያ አቻዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል።
Via:- Fana
@YeneTube @FikeeAssefa
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግስት ግቢ ውስጥ ችግኝ ተከሉ፡፡
አርቲስቶቹ በመላው የሀገሪቱ ክልሎች ተንቀሳቅሰው ህዝቡን በማነሳሳት ችግኝ ተከላው ከታቀደው በላይ እንዲከናወን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ፕሬዚዳንቷ አመስግነዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ 4.23 ቢሊዮን ብር (120 ሚሊዮን ፓውንድ) እርዳታ መስጠቷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የእርዳታ ስምምነቱን የገንዘብ ምኒስትር ድኤታው አድማሱ ነበበና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ልማት ምኒስትር አሎክ ሻርማ ፈርመውታል።
@YeneTube @FikerAssefa
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተሰጠን ቀጠሮ ብንገኝም ህክምና ግን እያገኘን አይደለም ሲሉ የካንሰር ህሙማን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅሬታ አቀረቡ፡:

ታካሚዎቹ ምንም እንኳን በቀጠሮ ተደውሎ በሆስፒታሉ ብንገኝም የካንሰር መድሃኒት ስላለቀ ሆስፒታሉን ልቀቁ ተብለናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በከፍተኛ ፍለጋ ከውጭ ሃገር መድሃኒት ቢገኝም የ60 ብር ዋጋ ያለው መድሃኒትን በ6 ሺህ ብር እንዲገዙ መጠየቃቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

ታካሚዎች ይህንን ለማድረግ ደግሞ የአቅም ችግር አለብን ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶክተር ይርጉ ገብረህይወት ሆስፒታሉ ያልከፈለው 151 ሚሊየን ብር ማለትም የ5 አመታት እዳ ስላለበት የመድሃኒት አቅርቦት ችግር አጋጥሞታል ነው ያሉት፡፡

ሆስፒታሉ በአንድ አመት ብቻ ግማሽ ሚሊየን ታካሚዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ከዚህም 80 በመቶ የሚሆኑት በነጻ ታካሚ በመሆናቸው በየጊዜው የበጀት ችግር እንደሚያጋጥመው ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ 70 የካንሰር መድሃኒት ዓይነቶችን ሆስፒታሉ የሚፈልግ ቢሆንም ለታካሚዎች እያቀረበ የሚገኘው ግን 30 ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፤ ከእርዳታ ሰጭዎች በነጻ የሚሰጥ መድሃኒት መኖሩን በመጥቀስ።

እንደ እርሳቸው ገለጻ ሆስፒታሉ ያጋጠመው የመድሃኒት እጥረት የካንሰር መድሃኒት ብቻ አይደለም።

የሆስፒታሉ እዳ እንዲከፈል ከጤና ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከሌሎችም ጋር እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ለካንሰር ህክምና አገልግሎት መስተጓጎል ጊዜያዊ መፍትሄ እየተፈለገ ነው ብለዋል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ሩሲያ በአርክቲክ ላይ ተንሳፋፊ የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ይፋ አደረገች፡፡

ተንሳፋፊው የሃይል ማመጫዋ ከአርክቲክ ሙርማንስክ ፖርት ወደ የሩቅ ምስራቅ ቹኮታ አካባቢ 500 ኪሎ ሜትር መቀሳቀስ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

በዚህም ከአንድ ቦት ወደ ሌሎች ርቀት ቦታዎች በመንቀሳቀስ ሃይል ለማቅረብ ታስችላለች ነው የተባለው፡፡

በተለይም ታዋቂ በሆነው ቻውን ቢልቢን የተባለው ቹኮታካ ውስጥ ወርቅን ጨምሮ ሌሎች ማዕደናት ማውጫ ቦታ ሀይል ለማቅረብ እንደምታስችልም ነው የተነገረው፡፡

ይሁን እንጅ በዓለም አቀፍ የውሃ አላት ደህንነት ላይ የሚሰራው “ግሪን ፒስ” የተባለው ድርጅት ፕሮጀክቱ ለውሃ አካለት አደገኛ መሆኑን ትችት እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ሩሲያ ፕሮጀክቱን ይፋ የደረገችው በአርክቲክ የኒውክሌር ሃይል ሞተር ፈንድቶ 5 የኒውክሌር እንጅነሮች ከሞቱ ከ2 ሳምታት በኋላ መሆኑን ዘገባው አስታወሷል፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ላይ ለተነሳው ሰደድ እሳት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ገለጹ።
መሪዎቹ በአማዞን ደን ለተነሳው እሳት አስቸኳይ መፍትሄ መስጠትና ጉዳዩ በቡድን ሰባት ሃገራት ስብስባ ላይ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ማክሮን ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው፥ በትዊተር ገጻቸው ላይ “ቤታችን እየነደደ” ነው ሲሉ አስፍረዋል።
የአማዞን ህልውና የዓለማችን አንገብጋቢው ጉዳይ ነው ሲሉም የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጸውታል።

ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ይሻል የሚሉት ማክሮን ሃገራቸው በምታስተናግደው የቡድን ሰባት አባል ሃገራት ስብሰባ ላይም አጀንዳ ሊሆን እና አስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባም ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብራዚል በተለይም በአማዞን ክልል የሚነሳው የእሳት አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በደኑ ከቀናት በፊት የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም አድማሱን እያሰፋ ከፍ ያለ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

የአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪዎች ደግሞ ለተነሳው እሳት የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮን ይወቅሳሉ።

ፕሬዚዳንቱ ገበሬዎችና ከደን ውጤቶች የጣውላ ምርት አምራቾች ደኑን እንዲጨፈጭፉ ፈቅደውላቸዋል በሚል ትችቱ በርትቶባቸዋል።

እርሳቸው ግን ውንጀላውን ያስተባብላሉ፤ የማክሮንን አካሄድም “በብራዚል ጉዳይ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የታለመ” በሚል አጣጥለውታል።
የምድራችን ሳንባ በመባል የሚታወቀውና የዓለማችን ትልቁ ደን አማዞን የአየር ንብረት ሚዛንን ለመጠበቅ ይረዳል።

ከዚህ ባለፈም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆነውን ኦክስጅን በብዛት አምቆም ይገኛል፤ የ3 ሚሊየን የዱር እንስሳት እና እፅዋት መገኛ መሆኑም ይነገራል።

Via:- fbc
@Yenetube @Fikerassefa