YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#FakeNewsAlert

"የ55ቱ ብሔር ብሔረሰብ መቀመጫ ከተማ አርባ ምንጭ እንዲሆን መደረጉን የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ ገለፁ" ተብሎ በጋሞ ሚዲያ ኔት ወርክ የተገለፀው ስህተት መሆኑን የሲዳማ ዞን የሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ባለፈው የዴኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን ተከትሎ በተላለፉት ውሳኔዎች መነሻ የተዛቡና በትክክል ከምንጩ ያልሆኑ አሉባልታዎች በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ሲተላለፉ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም በተሳሳተ ሁኔታ የዴኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉትን በሙሉ በአርባ ምንጭ ከተማ ማዕከል አድርገው እንዲቀጥሉ ተወስኗል በማለት የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል ተብሎ በመለቀቁ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሼር እና ላይክ በማድረግ ኮሜንቶች በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ የሲዳማ ዞን የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ደርሶበታል፡፡

ይህ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ከሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ያልወጣ መረጃ መሆኑንና ምንም ዓይነት ገለፃ ያልሰጡበት ጉዳይ በመሆኑ መቆም አለበት፡፡

በተጨማሪም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ በጋሞ ሚዲያ ኔት ወርክ በኩል የተሳሳተ መረጃ በሶሻል ሚዲያ ላይ የተለቀቀው ስህተት በመሆኑ ለሁሉም ሶሻል ሚዲያ ተከታዮች የማስተካከያ መልዕክት ያስተላልፉ ዘንድ በመጠየቅ ለወደፊቱም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሳያጣሩ ሼር እና ላይክ እንዳያደርጉ ለሁሉም ሚዲያ ተከታዮች መልእክት ማስተላለፋቸውን የሲዳማ ዞን ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ያሳስባል፡፡

ምንጭ: Sidama Zone Administration PR Office
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ዶ/ር ደብረፂዮን ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናገሩ ተብሎ የተለቀቀዉ መረጃ ፈጠራ/ሀሰት ነዉ ። ከላይ ያለዉ ምስል ከሳምንት በፊት ከታተመዉ ጋዜጣ የተወሰደ ነዉ፣ የወጣዉን ዕትም እና ተመሳሳይ የቅፅ ቁጥር በመጠቀም የተቀናበረ (photoshop) ነዉ።

ሪፖርተር ጋዜጣ የተመሠረተበት ዓመት ጳጉሜ 6 ቀን 1987 ዓ.ም ሲሆን በግራ በኩል በምታዩት የሀሰት ምስል 21987 ተመሰረተ ተብሎ ተለጥፎል።

Via Dawit Endeshaw
@YeneTube @FikerAssefa