ህወሓት 44ኛ ምስረተ በዓል ‼️
የህወሓት 44ኛ የምስረታ በዓል የትግልና ድል ጉዞ የምንዘክርበት ብቻ ሳይሆን ለነገ #ትምህርት #የምንወስድበትም ነው- የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ
የህወሓትን 44ኛ የምስረታ በዓል የካቲት 11 ምክንያት በማድረግ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ፥ በዓሉ የትግልና ድል ጉዞ #የምንዘክርበት ብቻ ሳይሆን ለነገ ትምህርት የምንወስድበት ቀን ነው ብሏል።
ህወሓት ከ44 ዓመት በፊት ትግል ሲጀምር በሀገሪቱ የነበረው ፍፁም ፀረ #ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በመገርሰስ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት የሚኖርባት ዴሞክራሲያዊት #ኢትዮጵያን ለመፍጠር አላማ ያነገበ እንደነበርም መግለጫው አስታውቋል።
በ17 #የትጥቅ ትግል አመታት ለመገመት የሚያስቸግር የህይወት፣ አካልና ንብረት መስዋእት መከፈሉን ያስታወሰው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ፥ በዚህም ኢትዮጵያን ከመበታተን በማዳን ባለፉት 27 ዓመታት ወደ አዲስ የልማትና #የዴሞክራሲ ምዕራፍ መሸጋገር መቻሉን ገልጿል።
ከብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ በመሆን በተደረገው ትግል የኢትዮጵያ ህዝቦች በሀገራዊ ጉዳዮች በእኩልነት የሚወስኑበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ መፈጠሩም አንስቷል።
በዚህም መሰረት “የህወሓት 44ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ስናከብር ባለፉት አመታት የተመዘገቡትን ድሎች በመያዝ ሀገራችን ባለፉት 27 አመታት የጀመረችው የለውጥ፣ ሰላምና ብልፅግና ጉዞ ወደኋላ እንዳይመለስ አጠናክረን ለመስራት ቃል በመግባት ነው” ብሏል።
የትናንት ወጣቶች ለህዝቦች ነጻነት፣ ሰላም መረጋገጥና እኩልነት ሲሉ ለፈጸሙት ጀግንነትና ለከፈሉት መስዋእትነት ዘላአለማዊ ክብር ይገባቸዋል ያለው ኮሚቴው፥ ለህዝቦች ነጻነት፣ እኩልነትና ሰላም መረጋገጥ ሲሉ በጀግንነት ያለፉት ታጋዮችን ከድህነት የማውጣት አላማን ከግብ ለማድረስ ዛሬም እንደ ትናንቱ በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የሰላም እጦቶችን በመቅረፍ፥ የህዝብ በተለይም የወጣቱን መሰረታዊ የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በመመለስ የተጀመረውን የተሃድሶ ጉዞ ማሰቀጠል እንደሚገባም ገልጿል።
የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዋስትና የሆነው የኢፌዴሪ ህገ መንግስትና ፌዴራላዊ ስርዓት በመጠበቅ የህግ የበላይነት እንዲከበር ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግም መግለጫው አሳስቧል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ለወንድም ኤርትራ ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት፥ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ በትጥቅ ትግሉ ሁለቱም ህዝቦች አብረው መታገላቸውና መስዋእት መክፈላቸውን አንስቷል።
የደርግ ስርአት ከወደቀ በኋላም ህወሓት የኤርትራን ህዝብ ውሳኔን በመደገፍ ከህዝቡ ጎን መሰለፉን በመግለፅ፥ በአሁኑ ወቅት ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ትግልም ከኤርትራ ህዝብ ጎን እንደሚሰለፍ አረጋግጧል።
ባለፉት 20 አመታት በማያስፈልግ ጦርነት ቆይተናል ያለው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ፥ የነበረው ሁኔታም በሁለቱም ወንድም ህዝቦች ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ገልጿል።
ይሁን እንጂ አሁን በተከፈተው አዲስ የሰላምና የወንድማማችነት ምዕራፍ በመጠቀም ተደጋግፈን ወደ ብልፅግና ልንጓዝ ይገባል ብሏል።
በዚህ ጉዞ ሁለቱም ህዝቦች ተጠቃሚ ማድረግ ስለሚቻል፥ ይህን እውን ለማድረግም የትግራይ ህዝብና መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ በማለትም አረጋግጧል።
የህወሓት 44ኛ የምስረታ በዓል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
@YeneTube @FikerAssefa
⬇️ኮሜንት መስጠት ከፈለጉ ⬇️