YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ ግዛት በውጭ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ጥቃት የአንድ ኢትዮያጵያዊ ህይወት ሲያልፍ አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በመሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቆም እየሰራ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ኢትዮጰያውያን ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያሳሰበ ሲሆን፥ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲም በሀገሪቱ ሀውቴን ግዛት ሶዌቶና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በትናትናው ዕለት ማሳሰቢያ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።

ባወጣው ማሳሰቢያ፥ ከነሃሴ 23 2010 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ ጀምሮ በሀውቴን ግዛት ሶዌቶና አካባቢው በኢትዮጵያውያን ዜጎች ንብረትና ሀብት ላይ ጥቃት መድረሱን አስታውቋል።

በአካባቢው ከሚገኙ የማህበረሰብ አደረጃጀቶችና ዜጎች ላይ በገኘው መረጃም ጥቃቱ መፈፀሙን መረዳት እንደቻለም ኤምባሲው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሪቶሪያ ኤምባሲ ጉዳዩን ለመንግስት አካላት ከማቅረቡ በተጨማሪ ዲፕሎማቶቹን በማሰማራት ከዳያስፖራ ፎረም ጋር በትብብር ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ስለሆነም በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው ኤምባሲው ያሳሰበው።
ተጨማሪ መረጃ ዜጎችም ዜጎች በ0123462110 እና በ0123462947 የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚችሉም ገልጿል።
©fbc
@yenetube @mycase27
#በኢትዮጵያ ያለው የመሰረተ ልማት ግንባታ ባለሀብቶችን ለመሳብ እንደሚያስችል ፕሬዚዳንት #ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለፁ።

ፕሬዚዳንቷ #በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው የኢንቨስትመንት #ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር በባቡርና በአየር ትራንስፖርት ኢትዮጵያ ያላት አቅም ባለሀብቶችን #ለመሳብ ያስችላል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ በሀገሪቱ ልማት ላይ ሚና እንዳለው ታምናለች ብለዋል ፕሬዚዳንቷ ባደረጉት ንግግር።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27