YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ እና አካባቢው #ውጥረቱ አይሏል፡፡

DW ሬዲዮ እንደዘገበው በቤንሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ከቤንሻንጉል የመጡ ታጣቂዎች ዕሁድ ዕለት #በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል ትናንት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተው #ሁለት ሰዎች ሞተዋል፡፡

ቁጥራቻው ለጊዜው #ያልታወቀ ሰዎችም ተጎድተዋል፡፡ ዛሬ ከቀትር በፊት እስካለው ጊዜ በከተማዋ ውጥረት እንደነበር እና አብዛኛው እንቅስቃሴም ተስተጓጉሎ ውሏል፡፡
ምንጭ ፦ DW
@yenetube @mycase27