YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ #የመጀመርያ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ ለመጀመር ወደ ፓሪስ አቀኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንሳይ ቆይታቸው ከፕሬዘዳንት #ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይመክራሉ።

የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ እንዲሁም በፈረንሳይ ያለውን ቅርስን የመጠበቅና የመንከባከብ ክህሎት የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለመታደግ መዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ይወያያሉ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት ኢማኑኤል ማክሮን ከወራት #በፊት ያቀረቡላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነው።
©ebc
@yenetube @mycase27