YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና #በጫካ ውስጥ ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው #ተገለፀ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ግለሰቦችን በመመልመል በጫካ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች መያዛቸውን ፖሊስ ገለጸ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ እንደገለፁት፥ በሕገ ወጥ መንገድ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት አሠልጣኞች ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር የዋሉትም ከኅብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሆኑ ነው የተገለፀው ፡፡

ግለሰቦቹ የሚያሰለጥኗቸውን አካላት ከአሶሳ ዞን መንጌ፣ አሶሳና ኦዳቢልድግሉ ወረዳዎች በመመልመል ሲያሰለጥኑ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ የተጀመረው የምርመራው ውጤት በፍጥነት አጠናቆ ለህግ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፁት ኮማንደሩ የምርመራ ውጤቱንም በየጊዜው ለሕዝቡ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡

ኅብረተሰቡ በሕገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማሩትን ግለሰቦች ጉዳይ በማሳወቅ ትብብሩን #እንዲቀጥል ምክትል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

በክልሉ ህዝብ ላይ ጥፋት ለመፈጸም በአሶሳ ወረዳ ገንገን ቀበሌ በጫካ ውስጥ ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 51 ተጠርጣሪዎች በቅርቡ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው #ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ኢዜአ
@yenetube @mycase27