YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
2😁2
በዎላይታ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በትናንትናው ዕለት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎች የሴሬ ፍንጫዋ ቀበሌ ነዋሪና የአንድ ቤተሰብ አባልት ሲሆኑ፤ በቦርኮሼ ቀበሌ እና በሰሬ ፍንጫዋ ቀበሌ መካከል ባለዉ በፍንጫዋ አዋሳኝ ፏፏቴ አጠገብ ለሣር አጨዳ በሄዱበት በተከሰተው በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

ከአደጋው ሕይወታቸው ካለፉት ሰዎች ውስይ የአንዲት ሴት ልጅ አስክሬን መገኘቱ የተገለጸም ሲሆን፤ የእናቷ እና የወንድ ልጅ አስክሬን ባለመገኘቱ የአከባቢው ማህበረሰብና የፀጥታ አካላት በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የአየር መዛባትን ተከትሎ የሚመጣው የክረምት ወቅት ዝናብ እንደዚህ ዓይነትና ሌሎች አደጋዎች እንዳይከሰት በሁሉም አከባቢ ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የወረዳው ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳስቧል።በአደጋው ቀጠና ያሉ ሰዎችን እንደዚህ ዓይነትና ሌሎች አደጋዎች እንዳይርስባቸው ወደ ሌላ ቦታ የማሸጋገር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
8😭5
2
YeneTube
Photo
የአለም ባንክ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ የመደገፍ ፍላጎት አለኝ ማለቱ ተሠማ።

በሌላ በኩል በሪል ስቴት አልሚዎች እና በቤት ገዥዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በድርድር መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰራ የግልግል ዳኝነት ቡድን እየተቋቋመ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ልማት ከተጀመረ 30 ዓመት ሆኖታል።

በእነዚህ ጊዜያት በርካታ ዜጎች የቤት ባለቤት መሆናቸው፤ የብዙዎች የአኗኗር ዘይቤም መቀየሩ ይጠቀሳል።የዚያኑ ያህል ዘርፉ ላይ የሚነሱ ችግሮችም አሉ።

አንዱ በሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰሩ ቤቶች አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ታሳቢ ያደረጉ አይደሉም፤ ውድ ናቸው የሚል ነው።የቤቶቹ ዋጋ እነዚህኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥያቄ ሲቀርብ ይሰማል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር የተመሰረተው የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ግን የቤቶቹ ዋጋ ውድ ነው በሚለው ሃሳብ አይስማማም።አቶ ከድር ሰይድ የማህበሩ ዋና ፀሃፊ ሲሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሪል ስቴት ቤቶች ባለቤት እንዲሆኑ መፍትሄው በአነስተኛ ወለድ ፤ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ የሚቀርበው ሌላው ቅሬታ ባሉት ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ቤቶችን ሰርተው አያስረክቡም የሚል ነው።በዚሁ ምክንያት በአልሚውና እና በደንበኛው መካከል አለመግባባቶች ሲፈጠሩ አንዳንዴም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሲያመራ ይታያል።

የተባሉት ችግሮች እንደሚገጥሙ የሚናገሩት ዋና ፀሃፊው አቶ ከድር - የግልግል ዳኝነት አይነት ስራ የሚሰራ ቡድን ማህበሩ እያቋቋመ እንደሚገኝ ነግረውናል።ማህበሩ በቅርቡ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር መወያየቱን የነገሩን አቶ ከድር በውይይቱ ባንኩ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ መደገፍ እንደሚፈልግ ተረድተናል ብለዋል።የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አሁን ላይ 57 አባላት እንዳሉት ሠምተናል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
26🔥6
አየር መንገዱ ባለው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሀገር ውስጥ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ!

‎የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሀገር ውስጥ በረራዎቹ ከትናንት ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም መስተጓጎል እንደገጠማቸው አስታውቋል።

በዛሬው ዕለትም ተመሳሳይ የአየር ፀባይ በተወሰኑ ጣቢያዎች ላይ ሰለተስተዋለ ወደ እነዚህ ጣቢያዎች የሚደረጉ በረራዎች ማድረግ አለመቻሉን አየር መንገዱ ለአሐዱ በላከው መግለጫ አመላክቷል።

የአየሩ ሁኔታ ሲሻሻል መደበኛ በረራዎች ወዲያውኑ የሚቀጥሉ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ በዚህ ምክንያት ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
15👎3
ብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ አለምአቀፍ ገበያዎች እንዲያስፋፋ ማሳሰቢያ ተሰጠ!

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች በማስፋፋት ሽያጩን እንዲያሳድግ መክሯል።

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እንዳስታወቀው፣ ፋብሪካው ዕድገቱን ማስቀጠል እንዲችል የግብይት ሥራዎችን ማጠናከር፣ ወደ ውጭ ገበያ መግባትና የሀገር ውስጥ የስርጭት መረቡን ማሻሻል ይኖርበታል ብሏል።

በተጨማሪም፣ የፋብሪካውን ምርታማነትና የማምረት አቅም በማሳደግ እንዲሁም ገቢ የሚያስገኙ ንብረቶችን በአግባቡ በመጠቀም ትልቅ ዋጋ መፍጠር እንደሚችል አስረድቷል።

ይህ የተባለው የፋብሪካው 2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት ነዉ። መንግስታዊዉ ኩባንያው በዓመቱ ከታክስ በፊት 340 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ሲደርስ፣ አጠቃላይ ገቢው ደግሞ 2.6 ቢሊዮን ብር መሆኑም ተመላክቷል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
11😁6👎2👍1🔥1