YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአፍሪካ ትልቁ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የገንዘብ አስተባባሪነትን በይፋ ተረከበ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና፣ የ7.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበትን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ በዋናነት እንዲያስተባብር የሚያስችለውን ስምምነት ሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአቡሴራ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ በየዓመቱ 60 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።ይህ አቅም ሙሉ በሙሉ ሲጠቀም እስከ 110 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን ማስተናገድ ይችላል። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ እ.ኤ.አ. በ2025 መጨረሻ ላይ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
19👎13😭2🔥1
የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 914 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መስጠቱን ዳሸን ባንክ አስታወቀ!

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ ደንበኞቹ 914 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 257 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ለነዳጅ ግዥ የቀረበ መሆኑን ገልጿል፡፡

ባንኩ እ.ኤ.አ በሃምሌ ወር 2025 ብቻ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞች 112 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማቅረቡን ጠቁሞ ከዚህም ውስጥ 33 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ለነዳጅ ግዥ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ዳሸን ባንክ በዚሁ ወር 73 ነጥብ1 ሚሊየን ዶላር የተለያዩ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እንዲውል ማቅረቡን ገልጾ ከዚህም በተጨማሪ ወደተለያዩ የውጭ አገራት ለሚጓዙ ደንበኞቹ 5 ነጥን 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መስጠት ችሏል፡፡

ባንኩ በያዝነው ወር የመጀመሪያ ስድስት ቀናት እንዲሁ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞች 11 ሚሊየን ዶላር ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡ባንኩ ደንበኞቹ የሚያቀርቧቸውን የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎች ለማሟላት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

[KGEthiopia]
@YeneTube @FikerAssefa
29👍1
የኢትዮጵያ የኢነተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 55 ሚሊየን ደርሷል ተባለ!

ቁጥሩ የኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ ከመጀመሩ በፊት 17 ሚሊየን እንደነበር የኢኖቬሽና እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ አቢዮት ባዩ ገልፀዋል፡፡

25 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ለፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ እንደተመዘገቡም አክለዋል፡፡ በ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ 1.8 ሚሊየን ዜጎች እየተሳተፉ እንደሆነ እና 1 ሚሊየን የሚሆኑት የእውቅና ሠርትፍኬት እንደተሠጣቸውም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በ2018 ዓ.ም ህዳር ወር ፊውቸር ቴክ ኤክስፖ 2025ን ታስተናግዳለች፡፡ ዝግጅቱ ስታርታፕችን ከኢንቨስተሮች ለማገናኘት እና የንግድ አጋርነቶችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
11😁3🔥1
በትግራይ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ 22 ሰዎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ!

በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ያቄር ቀበሌ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ከግንቦት ወር በኋላ 22 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።

በቀጣይ ሳምንታት እርዳታ የማይደርስ ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊያልቁ እንደሚችሉ የቆላ ተምቤን ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎይቶም ገብረ ሐዋርያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከሰዎች በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸውን ላላፊው ጨምረው አስታውቀዋል።

108 ሺህ አካባቢ ነዋሪዎች ካሏት የቆላ ተምቤን ወረዳ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ በከፋ ሁኔታ የተጠቃችው 4112 ነዋሪዎች ያሏት ያቄር የተሰኘችው ቀበሌ ናት።

ወረዳው በፊትም ቢሆን ድርቅ የሚያጠቃው አካባቢ ቢሆን በዘንድሮው ክረምት በተለየ መልኩ ዝናብ ባለመዝነቡ የተዘሩ ሰብሎች ለመብቀል ባለመቻላቸው የድርቁ መንስዔ እንደሆነ አቶ ጎይቶም ያስረዳሉ።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c62w8y75v67o

@YeneTube @FikerAssefa
😭3719
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትግራይ ክልል 60 ሺህ ወጣቶች መሰደዳቸው ተሰማ!

የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ በተፈጠረው የከፋ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ በርካታ የትግራይ ወጣቶች ወደ ስደት እያመሩ መሆኑ ይገለፃል።ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከትግራይ የተለያዩ አካባቢ ወደ አረብ ሃገራት እንዲሁም በሊብያ በኩል ወደሚደረግ ስደት የሚያመሩ ወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የሚገልፀው የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በዚሁ ሂደት በሚፈጠሩ አደጋዎችም በሺህዎች የሚቆጠሩ መነሻቸውን ትግራይ ያደረጉ ወጣቶች ለሞት እየተጋለጡ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል።

ከቢሮው የተገኘ መረጃ ባለፈው ዓመት እና በያዝነው 2017 ዓ.ም. ቢያንስ 60 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ከክልሉ ተነስተው ወደ ዓረብ ሃገራት እንዲሁም ወደ ሊብያ ማምራታቸው ያመለክታል። ከእነዚህ መካከል ሁለት ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች በስደት በሚያጋጥሙ መጥፎ ሁኔታዎች መሞታቸው መረጋገጡን የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ለዶቼቬለ እንዳሉት፥ በተደረገው ጥናት መሠረት 32 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ባለፈው ዓመት፣ በያዝነው ዓመት ደግሞ 28 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች መደበኛ እና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከትግራይ በመነሳት ተሰደዋል።

ሓላፊው «ይህ ቁጥር በጥናት የተረጋገጠ እንጂ፥ መረጃቸው ያልተገኘ በርካታ ወጣቶች መሰደዳቸውን መገንዘብ ይቻላል» ብለዋል።አቶ ሓይሽ ስባጋድስ «በስደት በተደጋጋሚ በሚከሰቱ አደጋዎች ምክንያት ሁለት ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አረጋግጠናል» ሲሉ አክለው ገልፀዋል።ቢሮው ያደረገው ጥናት ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች ያላካተተ እንዲሁም የመረጃዎች እጥረት ያሉበት በመሆኑ የሕገወጥ ስደቱ እና ሞት መጠኑ ከተጠቀሰው ሊበልጥ ይችላል ተብሏል።

የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ለወጣቶች ስደት ሥራ አጥነት የመጀመርያው ምክንያት ነው፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ደግሞ በሁለተኛነት እንደሚጠቀስ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የደላሎች ማታለያዎች እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶችም ወጣቶችን ለስደት እየገፉ እንዳሉ ተመልክቷል።ከጦርነቱ በኋላ የተለየ ትኩረት በመስጠት በወጣቶች ሥራ ፈጠራ እንዲሁም ሌሎች ተስፋ በሚሰጡ ሁኔታዎች ላይ መሥራት አለመቻሉ ፍልሰቱ እንዲባባስ እንዳደረገውም ተገልጿል። የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ችግሩን ለመፍታት ከፌደራል መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ እንደሚጠበቅ ያነሳሉ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
24😭9👍3
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
4
Forwarded from YeneTube
በ 25% ዲስካውንት ለገበያ አቅርበናል!

📌 ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት        

👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል  
መገልገያዎች    
👉 ሦስት ሊፍት   
👉 ባለ 3 ፎቅ የመኪና ማቆሚያ ቦታ    
👉 ቴራስ    
👉  ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት    
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር

📌 የካሬ አማራጮች
👉ባለ 1መኝታ - 63 ካሬ
👉ባለ 2 መኝታ - 86  እስከ 103 ካሬ
👉ባለ 3 መኝታ - 132  እስከ 146 ካሬ        

👉1 መኝታ 63ካሬ=      
        10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር       
                   ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር 
👉2መኝታ 86 ካሬ       
          10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር       
                  ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር       
👉3መኝታ 114 ካሬ     
           10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር     
                   ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር  

ለበለጠ መረጃ 
☎️ +251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

What's app
https://wa.me/251976195835

TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate
4😭1
Forwarded from ALX Ethiopia
🚀 Want to become a Virtual Assistant? Join our live Telegram session to learn about the programme, how to apply, and get your questions answered!

Don’t miss it - happening this Saturday, 3 ነሐሴ 2017 (August 9, 2025) starting at 11፡00 (5:00 PM) in our Telegram group
👉🏾 t.me/virtualassistantapplicationguide

#ALXEthiopia #ALXAfrica #ALXTribe #AIwithALX #VirtualAssistant
1
"በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል" ተግባር የተሰማሩ 138 ተጠሪጣሪዎች ባንክ ሒሳብ ታገደ!

"ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች" የባንክ ሒሳብ መታገዱን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ገለፀ፡፡

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑ በህገ ወጥ መጠቀም የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት እንደሚያሰቀጣ አሳስቧል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀልን እንደ መደበኛ የንግድ ስራ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በመሆናቸው ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱን አገልግሎቱ ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በዚህ መሠረትም ክትትል ተደርጎ የተደረሰባቸው እና በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ተደርጓል ነው ያለው፡፡

ይህ የተገለፀው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸውን ተከትሎ ነው።

አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ተማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል።

በተለይ በቅርብ ቀናት በዱባይ ከገበያ ሁኔታ ያፈነገጠ የትይዩ ገበያውን የሚያስፋፉ ህገወጥ ድርጊቶች እንዳሉ መረዳቱን ገልጾ የገለጸው ባንኩ፤ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
31😁7😭3
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሶማሊላንድን የእውቅና ጥያቄ እንደሚያውቁና ውይይት መኖሩንም ገለጹ!

ከአዘርባጃን እና ከአርሜኒያ መሪዎች ጋር ትላንት ምሽት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊላንድን ዓለም አቀፍ ዕውቅና የማግኘት የረጅም ጊዜ ጥያቄን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ስለ ሶማሊላንድ ጥያቄ ተጠይቀው ሲመልሱ፣ ትራምፕ "ጥሩ ጥያቄ ነው፣ አሁን እየተመለከትነው ነው" ብለዋል፣ ይህም ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳዩን በንቃት እያጤነችው መሆኑን ያመለክታል ሲል ሆርን ትሪቢውን ዘግቧል።

ሶማሊላንድ እ.አ.አ ከ1991 ጀምሮ ከሶማሊያ ነፃነቷን መልሳ ካወጀችበት ጊዜ አንስቶ፣ ከሶማሊያ ጋር ሲነፃፀር በተሻለ መረጋጋት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ቢኖራትም፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መደበኛ ዕውቅና ለማግኘት ጥረት እያደረገች ነው።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ እ.አ.አ በ2025 የዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፣ እውቅና ማግኘታቸው "ቅርብ ነው" ብለው ተስፋቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስም ቀዳሚ ልትሆን እንደምትችል ገልጸው ነበር።

እ.አ.አ በ2025 ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የአሜሪካ ጉብኝታቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለስልጣናት እና የከፍተኛ የአፍሪካ ቀንድ ወታደራዊ መኮንንኖች ጋር ውይይቶች እንደሚያደጉ ይጠበቃል።

የሶማሊላንድ ስትራቴጂካዊ የቀይ ባህር አቅራቢያ የሚገኝ ቦታዋ፣ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ያቀረበችው ጥያቄ እና ለአስፈላጊ ማዕድናት የሚሰጠው የፍቃድ እድል፣ በተለይም በትራምፕ አስተዳደር ላይ የሚያደርጉትን የሎቢ ጥረቶች አጠናክሮታል ተብሎ ይገመታል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
25🔥4👍3
የዩክሬይን ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ ፕረዚደንት ትራምፕ በመጨው አርብ ከሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ሊያካሄዱት ያቀዱት ንግግር «የዩክሬንን ሉአላዊ ግዛት የሚቆርስ ነው» ሲሉ ተቃዎሞአቸውን አሰሙ።

ሁለቱም ፕረዚደንቶች የዩክሬይንን ግዛት በሩስያ ሥር እንዲቆይ የሚል ስምምነት ካደረጉ «ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነውም ብለዋል።

ፕረዚደንቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ተቀርጾ ባሰራጩት መልዕክታቸው «ዩክሬይን መሬቷን ለወራሪዎች አሳልፋ አትሰጥም» ሲሉ ተደምጠዋል። «ለግዛታዊ አንድነታችን የሚሆን ምላሽ በሕገ-መንግስታችን አለ» ያሉት ዘለንስኪ ከዚህ የሚያፈነግጥ የለም ሲሉ አክለዋል። በዩክሬይን ሰላምን ለማምጣት በሚደረጉ ውይይቶች ለመካፈል ዝግጁ ነን ያሉት ፕረዚደንት ዘለንስኪ ዩክሬይን ያገለለ ንግግር «ጸረ ሰላም ነው» ሲሉ ተቃውመዋል።

የፑቲንና የትራምፕ ንግግር በሩስያ የተያዙ የዩክሬይን ግዛቶችን በሩስያ ሥር እንዲቆዩ የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ዘለንስኪ ይህ ደግሞ «ተግባራዊ ሊሆን የማችል » ብለውታል።

የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲንና የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን አርብ በአላስካ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
18😁3
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንግድ ባንክን አዲስ ሎጎ አገዱ!

የንግድ ምልክቱን ለመቀየር 600 ሚሊየን ብር መድቦ ሲሰራ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጨረሻው ሰአት አዲሱን ሎጎ ይፋ የማድረግ እቅዱን ሰርዟል።በምክንያት የተጠቀሰው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ስለ አዲሱ ሎጎ መተዋወቅ መረጃውን ከቀናት በፊት ከሰሙ በሀኋላ በሰጡት ትእዛዝ ነው።

አዲሱ ሎጎ ፈጠራ የጎደለው ነው የሚሉት ተቺዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩም ላሳለፉት ውሰኔ ይሄንኑ በምክንያት ጠቅሰው፤ ምልክቱ የኢትዮጵያን ፊደል አለማካተቱ በተጨማሪ ምክንያት ጠቅሰዋል ሲል ሪፖርተር ነው የዘገበው።

ከቅረብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ሃብት እየመደቡ የፋይናንስ ተቋማት የንግድ ምልክቶቻቸውን እየቀየሩ እና እያሻሻሉ ተስተውለዋል።ሆኖም የሚያስተዋውቋቸው ምልክቶች ከፍተኛ ትችትን ከማስተናገድ አልዘለሉም።

ግዙፍ መንግስታዊ የፋይናንስ ተቋም የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ስር ነቀል ለውጥ እያደረገ መሆኑ ይታወሳል።አሁን ያለው የንግድ ምልክቱ ለበርካታ አስርት አመታት ሲጠቀምበት የኖረ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
83😁31👍10👎5🔥2
የትግራይ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ አፈንጋጭ ታጣቂ ቡድን ዛሬ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል በማለት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ቢሮው፣ ታጣቂ ቡድኑ "ጠብጣብ" በተባለ ቦታ ላይ አደረሰው ባለው ጥቃት የአንድ የክልሉ ጸጥታ ኃይል አባል ሕይወት መጥፋቱን ገልጧል። ይህ አጥፊ ተግባር ከቀጠለ ቡድኑን በሚመሩና በሚያስተባብሩ አካላት ላይ ርምጃ እወስዳለሁ በማለት ያስጠነቀቀው ቢሮው፣ ደም መፋሰሱ ባስቸኳይ ይቁም በማለት ጥሪ አድርጓል።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa
29😁9
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም ከ71 በመቶ በላይ ደረሰ!

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግንባታ አፈጻጸም 71 ነጥብ 47 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት፤ ኮይሻ ከዓባይ ግድብ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛው ግዙፍ የውኃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው።

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፤ የግንባታው አፈጻጸም 71 ነጥብ 47 በመቶ ደርሷል ብለዋል።ግንባታው በ2021 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ አመላክተው፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት 6 ሺህ 460 ጊጋ ዋት ስዓት ኃይል ያማመንጨት አቅም እንደሚኖረው አስታውቀዋል።የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 201 ሜትር ቁመትና 1 ሺህ 12 ሜትር ርዝመት እንደሚኖረው መገለጹ የሚታወስ ነው።

Via Gazette Plus
@YeneTube @FikerAssefa
23🔥6👍5👎1
የሀበሻ ቢራ ዋና ባለድርሻ ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ድርሻቸውን በ5,900 ብር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ!

የሀበሻ ቢራ ዋና ባለድርሻ የሆነው ባቫሪያ ኦቨርሲዝ ቢሩስ ቢ.ቪ. (BOB) የተባለ የውጭ ኩባንያ፣ ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን በአንድ (1 ሺህ ብር) አክሲዮን 5,900 ብር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ።ይህ ጥያቄ በኩባንያው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ምዝገባ ዙሪያ ውዝግብ በነበረበት ወቅት ይፋ መሆኑን ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

አብዛኛውን ድርሻ የያዘው ባቫሪያ ኦቨርሲስ ቢራ ፋብሪካ (BOB) ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ለመግዛት ያቀረበው ይህ ዋጋ፣ ቀደም ሲል በዴሎይት ከተገመተው ዋጋ በ 34% ብልጫ አለው። የኩባንያው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የሽያጩ ጊዜ እስከ ነሐሴ 31 ቀን 2025 ድረስ የተራዘመ ነው።

የኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች ግን ቅሬታቸውን በማንሳት፣ አነስተኛ ድርሻ ያላቸው ባለሀብቶች ትርፋቸውን ወደ ካፒታል እንዳይቀይሩ ወይም አክሲዮናቸውን በገበያ ላይ እንዳይሸጡ ሲከለከሉ፣ አብዛኛውን ድርሻ የያዘው ባቫሪያ ግን ድርሻውን እንዲያሳድግ ልዩ ዕድል ተሰጥቶታል የሚል ክስ አቅርበዋል።

ባለአክሲዮኖች ይህ እርምጃ ሕጋዊ መሠረት የለውም እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ይጎዳል በማለት እየተከራከሩ ነው።የሀበሻ ቢራ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር መስፍን አቢ ቀደም ሲል በሰጡት ምላሽ፣ ባለአክሲዮኖች የ ESX ምዝገባ እስከሚጠናቀቅበት ህዳር 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠብቁ ወይም በጠቅላላ ጉባዔ የጸደቀውን የገንዘብ ትርፍ እንዲቀበሉ ሁለት አማራጮች እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
20👀1