#Update
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር ዋለ!
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተችሏል።አደጋው ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤው እየተጣራ ይገኛል።
እሳቱን ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ እና የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ብርቱ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀድሞ ስሙ ኦቶና ሆስፒታል አንጋፋ እና ከወላይታ ዞን ውጪ በአጎራባች ዞኖች ላሉ ነዋሪዎች ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ነው።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

❤25😭3