YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የማይክሮሶፍት ሰርቨሮች በቻይና የበይነ መረብ ጠላፊዎች ተጠልፏል ሲል ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አስታወቀ

የቻይና  የበይነ መረብ ጠላፊዎች የማይክሮሶፍት ሼር ፖይንት ሰነድ ሶፍትዌር ሰርቨሮችን ሰብረው የንግዶቹን መረጃ በመጠቀም ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን ኩባንያው ገልጿል።በቻይና በመንግስት የሚደገፈው የሊነን ቲፎን እና ቫዮሌት ቲፎን እንዲሁም በቻይና ላይ የተመሰረተው ስትሮም 2603 በድርጅቶች ጥቅም ላይ የሚዉሉ ነገር ግን ክላዉድን መሰረት ባደረገ አገልግሎት ውስጥ ያለዉን ተጋላጭነቶችን ተጠቅመዋል ተብሏል ።

የዩናይትድ ስቴትስ የቴክኖሎጂ ግዙፍ ድርጅት በምላሹ የደህንነት መስፈርትን ሰዎች እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡ማይክሮሶፍት በሰጠው መግለጫ በሌሎች ግብረ አበሮች ላይ የሚደረገው ምርመራ አሁንም እንደቀጠለ ነው ብሏል።ኩባንያው እንዳስታወቀዉ የበይነ መረብ ጠላፊዎቹ የደህንነት ማሻሻያ ባላደረጉ ስርዓቶች ኢላማ ማድረግ እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቋል፡፡

ምርመራውን በተመለከተ የድረ-ገፁን ብሎግ ከተጨማሪ መረጃ ጋር ማሻሻያ እንደሚያደርግ አክሏል።በብሉምበርግ ኒውስ የተገመገመው የሳይበር ደህንነት ድርጅት ዘገባ እንደገለጸው ጠላፊዎቹ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገውን የጤና እንክብካቤ አቅራቢውን ስርዓት በመጣስ በደቡብ ምስራቅ እስያ የሚገኘውን የህዝብ ዩኒቨርሲቲን ኢላማ አድርገዋል። ሪፖርቱ የትኛውንም አካል በስም አይለይም፣ ነገር ግን ጠላፊዎቹ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ስፔን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስዊዘርላንድ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካን ጨምሮ የሼርፖይንት ግልጋሎትን ለመጣስ ሞክረዋል ብሏል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
14👍1😭1