YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ፋኖ ኃይሎች በ #ኦሮሚያ ክልል ተደራጅተው እንደሚንቀሳቀሱ ገለፁ፤

ይሁን እንጂ በክልሉ በቅርቡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ግድያ ላይ "እጃችን የለበትም" ሲሉ አስተባብለዋል


የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ  ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የስድስት ወር ሕፃን ጨምሮ ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ በተባለው ጥቃት ላይ "እጄ የለበትም" ሲል አስተባበለ።

በክልሉ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ  ሐምሌ 4 ቀን ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች “በፋኖ ታጣቂዎች” መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎችና የኖኖ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በወቅቱ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ ለአዲስ ስታንዳርድ ማብራሪሪያ የሰጡት አንድ የፋኖ አመራር፣  “በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል”  የፋኖ አደረጃጀት በክልሉ ታህሳስ 7 ቀን በይፋ ተመስርቶ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8628
16😁1