YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ውጤት ነገ ይለቀቃል

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።


የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል። በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።

ተማሪዎችም ትክክለኛውን መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ገፆች ላይ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

Via:- ትምህርት ሚንስተር
@Yenetube @Fikerassefa
👍337👎3
313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ

እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው አጸፋዊ የአየር ጥቃቶች 313 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል ሲል ቢቢሲ አስነብበዋል።

ሚኒስቴሩ 2 ሺህ ሰው መቁሰላቸውንም አክሎ ገልጿል። ከእስራኤል በኩል ደግሞ ቢያንስ 300 እስራኤል መገደላቸውን በቱርክ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል።

ኤምባሲው የእስራኤልን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ በርካቶች ታግተዋል ብሏል።

በተጨማሪም ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቆስለው በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ ከእነዚህም ውስጥ 19ቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብሏል። አኃዙን በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት በይፋ አላረጋገጠም።

@Yenetube @Fikerassefa
👍40😭308
ሰበር ዜና

የማራቶን የዓለም ክብረወሰን ተሰበረ

ኬኒያዊው የ23 አመት አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም የማራቶንን የአለም ክብረወሰን ሰበረ በአሜሪካ ባንክ ቺካጎ ማራቶን በ2፡00፡35 በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍648🔥4
መርጌታ ላቀው የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን  0915968136
                

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለሁሉ ሠናይ
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለመክስት
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ

ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ


ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
0915968136
 
👍71
⚡️በግሎብዶክ የወደፊት ሕይወትዎን ለመቅረጽ ዝግጁ ነዎት?

ገደብ የለሽ እድሎችን ለመጠቀም፣
ወደ ብሩህ ጊዜ መንገዱን ለመክፈት እኛን ያግኙን።

Join us here:
🔻Telegram: t.me/GlobeDockConsultancy
🔻TikTok: https://www.tiktok.com/@globedockedu

📞 +251969959595 or +251942202070
👍42
በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል- ተመድ

በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ መፈናቀላቸውን እና ከነዚህም ውስጥ 74 ሺዎቹ በትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶች እየፈጸመች ትገኛለች።

እስራኤል በፈጸመችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች ከ400 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ2 ሺህ በላይ መቁሰላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።

እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባህር እገዳ የጣለች ሲሆን በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።

በተመሳሳይ ግብጽ በራሷ ወሰን በጋዛ ድንበር በኩል የሚገቡ እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።

@YeneTube @FikerAssefa
👍25😭224👎3🔥1
የ2015 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!

የ2015 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 3.2 በመቶ ብቻ ከ50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ አሁንም በከተማ እና ገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ ሆኖ መታየቱን አመልክተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
👍21👎51
የ2015 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ያመጡት 3 በመቶዎቹ ብቻ ናቸዉ ተባለ!

የ2015 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡በዚህም በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 3.2 በመቶ ብቻ ከ50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ አሁንም በከተማ እና ገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ ሆኖ መታየቱን አመልክተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍12😭12🔥76
በጋዛ ላይ ‘ሙሉ ከበባ’ ታዘዘ!

ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ ታዘዘ።በጋዛ 'ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ትዕዛዝ ሰጥተዋል።የጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።

እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባህር እገዳ የጣለች ሲሆን በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።በተመሳሳይ ግብጽ በራሷ ወሰን በጋዛ ድንበር በኩል የሚገቡ እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።

በተያያዘ ዜና የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ ያሉ ማህበረሰቦችን ሙሉ በቁጥጥሩ ስር ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።ሆኖም በአካባቢው የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ጋር ያለው ውጊያ መቀጠሉም ተነግሯል። እስራኤል በግዛቶቿ ውስጥ ባሉ ሰባት እና ስምንት ቦታዎች ውጊያዎች እየተካሄደ መሆኑንም አስታውቃለች።

ከጋዛ የሚወነጨፉ ሮኬቶች አሁንም እየተተኮሱ ሲሆን በእየሩሳሌም ቢያንስ ሶስት ፍንዳዎት ተሰምተዋል ተብሏል።እነዚህ ሮኬቶች ኢላማዎችን ይምቱ ወይም በእስራኤል መቃወሚያ እየከሸፉ ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍48👎17😭83
‹‹ በእርስ በእርስ ጦርነት እና ዕልቂት የማይተካ ዋጋ ከፍለናል፤ እየከፈልንም ነው ›› - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በእርስ በእርስ ጦርነትና ዕልቂት የማይተካ ዋገ ከፍለናል እየከፈለን ነው ›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ፕሬዝዳንቷ ይህን የተናገሩት የ6ኛው የሁለቱ እንደራሴዎች ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በተካሄደበት ወቀት ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

‹‹ ኢትዮጵያ በታሪኳ ቅኝ ሊገዟት የዘመቱባትን ሁሉ በአንድነት በመቆም አልገዛም ያለችና ህዝቦቿም ከጫፍ እስከ ጫፍ ዘምተው አንድነቱን ጠብቀው አቆይተውልናል ›› ያሉት ፕሬዝዳንቷ ‹‹ አሁን ላይ ግን ሁላችንንም ሊያግባባ የሚችል ሀገራዊ ሀሳብ መፍጠር ተስኖናል ›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

‹‹ ሁላችንንም ሊያሰባስብ የሚችል ትርክት መገንባት ተስኖናል ›› ሲሉ የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ ‹‹ በአብዛኞቻችን ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሀገረመንግስት ማፅናት አቅቶናል ›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡የፕሬዝዳንቷ የመክፈቻ ንግግር ሲቀጥል ‹‹ እርስ በእርስ ልዩነቶቻችንን ማቻቻል አቅቶን ወደ እርስ በእርስ እልቂትና ጦርነት ዉስጥ በመግባት እንደ ሀገር የማይተካ ዋጋ ከፍለናል፤ እየከፈልንም እንገኛለን ›› ሲሉ ቁጭት ያዘለ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍78👎2619😭2
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ነገ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት ይችላሉ፡፡

የ2015 ዓም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፦

በዌብሳይት - https://eaes.edu.et/
በአጭር መልዕክት - 6284
በቴሌግራም - https://tttttt.me/eaesbot

@YeneTube @FikerAssefa
👍2810👎1🔥1
በባጃጅና ሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ነገ እንደሚነሳ ተገለፀ!

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በሞተር፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከነገ ጀምሮ ያነሳ መሆኑን አስታውቋል።ሆኖም ፍቃዱ የሚመለከታቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጿል።

የሞተር ሳይክሎችም በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ህጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ መሆኑን ማሳወቁን ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ነገር ግን ከዚህ ህጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍30
🔑Our commitment to excellence goes beyond the norm.

We don't just match students with universities; we nurture dreams and provide comprehensive career counseling throughout their educational journey.

At GlobeDock, we believe in turning aspirations into reality.


Join us here:
🔻Telegram: t.me/GlobeDockConsultancy
🔻TikTok: https://www.tiktok.com/@globedockedu
🔻Visit our Office: Dembel to Meskel Flower Road, Jema'a building 6th floor.(You can use Google map)

📞 +251969959595 or +251942202070
👍52
የዓለም የምግብ ድርጅት በኢትዮጵያ ለፍልሰተኞች የሚያደርገውን ርዳታ ቀጠለ!

የርዳታ ምግብ ላልታሰበለት ዓላማ እየዋለ እና ተሰርቆ ለገበያ እየቀረበ ነው በሚል ባለፈው ሰኔ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የምግብ ስርጭት አቋርጦ የነበረው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ 900 ሺሕ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች ምግብ በማደል ፕሮግራሙን መልሶ ጀምሯል።

ዕደላውን መልሶ የጀመረው፣ የቁጥጥር ሥርዐቱን በማሻሻል እንደሆነም ታውቋል። በፍልሰተኞች መጠለያ የሚገኙት 24 ማከማቻዎች አሁን ድርጅቱ እንደሚቆጣጠራቸውና፣ የተረጂዎች ምዝገባም በዘመናዊ መንገድ እንደሚደረግ ድርጅቱ ገልጿል።

በአምስት ክልሎች ባሉ የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ሰዎች እንዲሁም አዲስ ከሱዳን የገቡ ፍልሰተኞች የምግብ ዕደላ እየተደረገላቸው እንደሆነ ድርጅቱ ሮም ከሚገኘው ጽ/ቤቱ ዛሬ አስታውቋል። ባለፉት ስድስት ወራቶች ውስጥ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ 35ሺሕ የሚሆኑ ፍልሰተኞች በአስቸኳይ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ፤ ከሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ የመጡ 850 ሺሕ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን በማስተናገድ ላይ መሆኗል ድርጅቱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ ለሚያሻቸው ዕደላው እንዲቀጥልም፣ የቁጥጥር ሥርዐቱን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ሙከራ መልካም ውጤት እያሳየ እንደሆነ የምግብ ድርጅቱ ጨምሮ ገልጿል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍11👎2
የሰሜን ሸዋ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ “ከሰሞኑ ያወጣሁትን ዘገባ ከበላይ አካል በደረሰብኝ ጫና አንስቻለሁ” አለ!

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ “ከወሎ እና ከሰሜን ሸዋ ዞን ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ድብደባ እና ዝርፊያ ተፈጽሞባቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል” በሚል ያወጣነውን ዘገባ፤ ከበላይ አካል በደረሰብን ጫና እንድናነሳ ተገደናል ሲል ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባለሙያ፤ “ሰሞኑን ከአማራ ክልል ደሴና አካባቢው እንዲሁም ከደብረ ብርሃን መናኸሪያ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተጓዦች፤ ከኦሮሚያ ክልል እስከ አዲስ አበባ ባሉት አገር አቋራጭ መንገዶች ዘረፋና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡

በተጓዦች ላይ የደረሰውን ዘረፋና ድብደባ በተመለከተ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን መንገደኞች በደብረብርሃን መናኸሪያ እና አካባቢው ተዘዋውረን አነጋግረን ዘገባ ሰርተን ነበር ሲል መምሪያው አሳውቋል፡፡

“ዘገባውን በዞኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የለጠፍን ቢሆንም፤ የዞን እና የክልሉ የበላይ ኃላፊዎች ባደረሱብን ጫና ዘገባውን እንድናነሳ አስገድዶናል፡፡” ብለዋል፡፡

በማሕበራዊ ትስስር ገጾቻቸው አጋርተውት የነበረው ዘገባ ምንም አይነት ስህተት የሌለበት እንደነበርም የጠቆሙ ሲሆን፤ ድብደባና ዘረፋ የተፈጸመባቸው ተጓዦች የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡

ድርጊቱ የተፈመው ከደብረብርሃን ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ በምትገኝ ሸኖ ከተማ ላይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

“ከድብደባው የተረፉት ተጓዞች ለምግብና መጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ፤ በደብረብርሃን መናኸሪያ ውስጥ ሌሎች ተጓዞችን ርዳታ ሲጠይቁም አስተውለናል፡፡” ብለዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የደብረ ብርሃን መናኸሪያ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ቡድን መሪ ስዩም ተፈራ በበኩላቸው፤ “ሰሞኑን ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተጓዦች ድብደባ እና ዝርፊያ፣ ደርሶባቸዋል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ከ3 ሺሕ በላይ ተጓዦች መመለሳቸውን እና ከእነዚህም ውስጥ አስራ አንድ ተሳፋሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ከተከለከሉት ሰዎች መካከል የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በብዛት እንደሚገኙበት ገልጸው፤ ድርጊቱ ትናንት ሰኞ መስከረም 29/2016 ቀጥሎ መዋሉንም ጠቁመዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍40😭43👎2🔥1
የአፍሪካ አገራት በእስራኤል እና ሐማስ ግጭት የተለያየ አቋም ይዘዋል!

የአፍሪካ መሪዎች የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲያቆሙ ሁሉንም ተፋላሚ ወገኖች ጠይቀዋል።የአገራቱ አቋም ግን ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ አልነበረም።

ዛምቢያ፣ ኬንያ እና ጋና ሐማስን በግልጽ አውግዘዋል።እስራኤልን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ደቡብ አፍሪካ ለፍልስጥኤማውያን ያላቸውን ድጋፍ በይፋ ገልጸዋል።እስራኤል ባለፉት አስር ዓመታት በአህጉሪቱ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ አሳድጋለች።በርካታ የአፍሪካ አገራትም ኤምባሲዎቻቸውን ከቴል አቪቭ ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር አቅደዋል። ይህ ግን እስራኤል በዚህ ግጭት ከአፍሪካ የምትጠብቀውን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አላስገኘላትም።

የአፍሪካ ህብረት በፈረንሳይኛ እና በእንግሊዘኛ መግለጫ አውጥቷል። የግጭቶቹ መነሻ "የፍልስጥኤም ህዝብ በተለይም ነፃ እና ሉዓላዊ መንግስት የመመስረት መሠረታዊ መብቶች መነፈግ" መሆኑን ገልጿል።

“ሊቀመንበሩ ሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ ግጭቶችን እንዲያቆሙ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ጠረጴዛው እንዲመለሱ ጠይቀዋል። የፍልስጥኤምን ህዝብ እና የእስራኤላውያንን ጥቅም ለማስጠበቅ የሁለት መንግስታትን መርህ ተግባራዊ እንዲደረግም በአስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል” ሲሉ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ አክለዋል።

እስራኤል ቀደም ሲል በአፍሪካ ህብረት ስብሰባዎች ላይ በታዛቢነት ለመሳተፍ የነበራት ፍላጎት በአንዳንድ አገራት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ተፋላሚ ወገኖች ወደ "ሁለት አገራት መፍትሔ" እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። በተከሰተው ግጭት ማዘናቸውን በመግለጫቸውም አስታውቀዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረትም ሙሴቬኒ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአውሮፓውያኑ 2016 እና 2020 አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት እአአ በ2020 በእስራኤል እና በሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ሠርተዋል።

ድጋሚ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ግን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፍልስጥኤማውያን ድጋፍ ሰጥተዋል።

"በአሁኑ ጊዜ በፍልስጥኤም እየተከሰተ ያለውን አደገኛ እና አሳሳቢ ሁኔታ ሱዳን በቅርበት እየተከታተለችው ነው። የፍልስጥኤም ህዝቦች ነፃ አገር እና ህጋዊ መብት እንዲኖራቸው ሱዳን ድጋፏን በድጋሚ ትገልጻለች።ዓለም አቀፍ የግጭት አፈታቶች እንዲተገበሩ እና ንፁሃን ዜጎችን ከጥቃት እንዲጠብቁ ትጠይቃለች" ሲል በመንግስታዊው የዜና ወኪል ሱና በፌስቡክ ገጹ መግለጫውን አስነብቧል።

ደቡብ አፍሪካ "አፋጣኝ የተኩስ አቁም" እንዲደረስ ጥሪ አቅርባለች።የአገሪቱ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ቢሮ "ቀጠናው በተባበሩት መንግስታት የሁለት መንግሥታት መፍትሔ እና በእስራኤል እና በፍልስጥኤም መካከል ፍትሐዊ እና ሁሉን አቀፍ ሠላም እንዲሰፍን ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች የሚተገብር የሠላም ሂደት ይፈልጋል" ሲል አስታውቋል።

ናይጄሪያ በበኩሏ “አሁን ያለው የተባባሰው የብጥብጥ እና የበቀል አዙሪት በህዝብ ላይ የማያቋርጥ የስቃይ አዙሪት እንዲኖር ያደርጋል” በማለት አስጠንቅቃለች።የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ “የጉዳቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ተፋላሚዎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

"ኬንያ ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት ለሆነ ሽብርተኝነት ምንም አይነት ምክንያት ሊኖር እንደማይገባ አጥብቃ ታምናለች። ወንጀለኛው ማንም ይሁን ማን፤ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሁሉም የሽብርተኝነት፣ የአመጽና የጽንፈኝነት ድርጊቶች አስጸያፊ፣ ህገወጥ እና ኢፍትሐዊ ነው" ሲሉ ኤክስ ላይ ጽፈዋል።የዛምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስታንሊ ካኩቦ የሐማስን ጥቃት በማውገዝ እስራኤልን ደግፈዋል።

"በሚያሳዝን ሁኔታ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት በሆነው እና በእስራኤል ላይ በቅርቡ የተፈጸመውን ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን። ሁሉንም ጥቃት እና የጥቃት ድርጊቶች በማያሻማ ሁኔታ እናወግዛለን። ዓለም አቀፍ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን መከተል አስፈላጊ መሆኑንም አበክረን እናሳውቃለን" ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍585
ኢሰመኮ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው እንደሚታሰሩ ገለጸ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሚታሰሩ መሆናቸውን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገልጿል።

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2014 እስከ ሰኔ ወር 2015 ድረስ ያለውን የሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ኹኔታን ያካተተ ዓመታዊ ባለ 46 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም አደረኩት ባለው ክትትል በሶማሌ ክልል ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ ያሉ ታራሚ ሕፃናት ለአካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንደሚያዙ፤ እንዲሁም በሚቆዩባቸው ጊዜያት የሕፃናቱን ዕድሜ ያላገናዘበ የኃይል እና የእርምት እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው አመላክቷል።

በተመሳሳይም በጉለሌ ክፍለ ከተማ በየካቲት ወር 2015 በእንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት የክፍለ ከተማው ፖሊስ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ተማሪዎችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ ግንቦት 4/2015 ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ጉብኝት በወቅቱ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ 64 ሕፃናት ታስረው መገኘታቸውንና ሕፃናቱ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በእስር እንዲቆዩ መደረጉ አሳሳቢ ሆኖ መገኘቱን አውስቷል፡፡

በወላጅ ወይም አሳዳጊ ጥበቃ ሥር የመቆየት እንዲሁም በዋስ የመለቀቅ መብቶቻቸውም በአብዛኛው የማይከበርላቸው መሆኑ፣ በሚቀርብባቸዉ ክስ ላይ መልስ ለመስጠት ዕድል የማያገኙና በተጨማሪም በቂ የሕግ ባለሙያ ድጋፍ ማግኘት እንደማይችሉም ተገልጿል።

እንዲሁም በወንጀል ተግባር ላይ ለተገኙ ሕፃናት በአገሪቱ ሕግ የተቀመጠው ጥበቃ በአብዛኛው የማይፈጸም መሆኑ ጠቁሟል።

ይህም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ ሕፃናት ላይ የወንጀል ምርመራ መደረጉ፣ ተጠርጣሪ ሕፃናት ወዲያውኑ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ የማይደረግ ከመሆኑም ባሻገር ቃል የሚሰጡት ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሌሉበት መሆኑን  ገልጿል።

በመጨረሻም በሚሻሻለው የወንጀል ሥነ ስርዓት እና የማስረጃ ሕግ ለሕፃናት ልዩ ጥቅም ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያስገድድ መርሕ እንዲካተትና በወንጀል ለተጠረጠሩ ሕፃናት ከመደበኛ የፍትሕ ሂደት ውጪ ተፈፃሚ የሚሆኑ የሥነ ሥርዓት እርምጃዎችን እንዲካተቱ ኢሰመኮ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍284👎3
በሶማሌ ክልል ንብረታቸው ለወደመባቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እየተካሄደ ነው!

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የገበያ ማዕከል በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በዝግጅቱ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ተወላጆች፣ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚህም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጅግጅጋ ከተማ ገቢ የማሰባሰብ ስራ መከናወኑንና የዛሬው ቴሌቶንም የዚሁ ዕቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቀጣይም ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ገቢ የማሰባሰብ ተግባር ይካሄዳል ተብሏል፡፡ሰኔ 2015 ዓ.ም በሱማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በገበያ ማዕከል በደረሰ የእሳት አደጋ ከ900 በላይ ሱቆችና ግምታቸው ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሆነ ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
👍34👎31
🔑Our commitment to excellence goes beyond the norm.

We don't just match students with universities; we nurture dreams and provide comprehensive career counseling throughout their educational journey.

At GlobeDock, we believe in turning aspirations into reality.


Join us here:
🔻Telegram: t.me/GlobeDockConsultancy
🔻TikTok: https://www.tiktok.com/@globedockedu
🔻Visit our Office: Dembel to Meskel Flower Road, Jema'a building 6th floor.(You can use Google map)

📞 +251969959595 or +251942202070
👍3