YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ የሚደረጉ የአምስቱ ታላላቅ ሊጎች የተመረጡ ጨዋታዎች የቤቲንግ ግምትና መረጃዎች

ሆፈንሃይም፣ ዶርትመንድ፣ ፉልሃም ፣ አስቶንቪላ እና ኒውካስትልን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት

ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇

http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የአምስቱ-ታላላቅ-ሊጎች-የተ/

ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett
👍12🔥2
ፀሐይ ባንክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ!

መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ስምምነት ያደረጉት ፀሐይ ባንክ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይ ባንኩ ለካፒታል አስታዉቋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር የተደረገው ስምምነት በባንኩ በኩል "የክለብ ደጋፊዎች የአባልነት ክፍያቸውን እንዲከፍሉ ፣ ለተጨዋችም እንዲሁም ለሰራተኞቹ የደመወዝ ሂሳብ በባንኩ በኩል ተፈፃሚ እንደሚሆን ፣ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች እና የክለቡ ቲሸርቶች በተቋሙ እንደሚሸጥ ገልጿል።

ፀሐይ ባንክ ለክለቡ በስፖንሰርሺፕ መልኩ በየዓመቱ 10 በመቶ የሚያድግ የ5 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያደርግ ሲሆን እስከ 40 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የረጅም ጊዜ ብድር እንደሚያመቻች ስምምነቱን ባደረገበት ወቅት አስታውቋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍38👎64
የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ!

ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት የ2016 ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደርን ይፋ አድርጎል።

መስከረም 14 2016 ዓ.ም የአንደኛው ወሰነ ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት ይጀምራል፡፡

ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ ይችላሉም ብሏል።

ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለመምህራንና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትውውቅይ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ባወጣው ካላንደር ተመላክቷል።

ከመስከረም 7 እስከ 11/ 2016ዓ፣ም የትምህርት ሳምንት ሆኖ እንደሚከበርም ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍35👎114
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል አምጡ” በሚል ግድያዎች መፈጸማቸው ተገለጸ!

በመንግሥት የጸጥታ አካላት የታሰሩ ሰዎች “ለታጣቂ ቡድኑ ድጋፍ ታደርጋላችሁ” እንዲሁም “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል” በሚል ምክንያት እንደሆነም ኢሰመኮ ገልጿል። በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ውሏቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ነዋሪዎች ተይዘው የሚቆዩበት ጊዜያዊ ማዕከል እንዳለም ተመልክቷል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው፤ ሙሉውን ለማንበብ:

https://bbc.in/3PJten6
👍387👎6
የ2016 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27 ይከበራል!

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 27 በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👎89👍218
በሰሜን ሸዋ ሙሉ ወረዳ ከኹለት ዓመት በላይ በዘለቀው የታጣቂዎች እገታ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ገለጹ!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሙሉ ወረዳ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ በመባል በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን፤ ከኹለት ዓመት በላይ እያደረሰ ባለው ተደጋጋሚ ጥቃት የተማረሩ ነዋሪዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ለቀው እስከመውጣት መድረሳቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው ማህብረሰብ ላይ እገታና ጥቃት ማድረስ ከጀመረ ከኹለት ዓመት በላይ እንደሆነው የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርገው የአፈና እና ዝርፊያ ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ዱበር፣ ጫንጮ፣ ሱሉልታ እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ተፈናቅለው እየሄዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ ለአብነትም ባለፈው ቅዳሜ ጳጉሜ 04/2015 በወረዳው ውስጥ ድሬ ከተባለ አካባቢ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን ነው የገለጹት።

ቡድኑ በተለይም ከኹለት ወራት ወዲህ በነዋሪው ላይ የሚፈፅመውን ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉን በመጥቀስም፤ "ይህ ኹሉ ሲፈጸም የሚያስቆም የመንግሥት አካል የለም።" ሲሉ አክለዋል።

ነዋሪዎች ከዚህ ባለፈው በእጅ ስልካቸው እየተደወለ “ይህን ያህል ብር ካላመጣችሁ እንገላችኀለን፣ ቤታችሁንም እናቃጥላለን” በሚል ዛቻና ማስፈራሪያ መማረራቸውን ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ በሚያደርገው እንቅስቃሴ በተለይም በወረዳው ዋና ከተማ ዕሮብ ገበያ እና በተወሰኑ የገጠር ቀበሌዎች የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አገለግሎት መስጠት እንዳልቻሉ ተመላክቷል።

በተመሳሳይ በዞኑ ወረጃርሶ ወረዳ ጎሃፅዮን ከተማ እና በተለያዩ የወረዳው የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ነዋሪዎችን አፍነው እንደሚወስዱ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚጠይቁ መረዳት ተችሏል።አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ የሙሎ ወረዳ ሠላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት የጠየቀች ሲሆን፤ "በአካል መጥታችሁ ጠይቁን" በማለታቸው ምላሹን ማካተት አልቻለችም።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍315
የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባሄና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ!

20ኛዉ የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች እና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን ጉባሄና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ

ባለስልጣኑ ይህን አስመልክቶ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በመጪዉ ጥር ወር ላይ የሚካሄደው ጉባሄ የኢትዮጵያ ቡና በአፍሪካ እና በዓለም ገበያ ይበልጥ ለማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጥር ገልጿል።

"Speciality Coffee at Origin" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ጉባሄዉ ላይ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የዓለም አቀፍና የቀጠናዊ የቡና ቆይዎች ነጋዴዎች አምራች ገዥዎች እና የዘርፉ ባለሞያዎች በአንድ ጣሪያ ስር ለማሰባሰብ ታቅዷል።

የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባሄና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን "IACO" ከጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በዚሁ ጊዜ የመጀመሪያዉ የአፍሪካ ቡና ሳምንት የሚካሄድ መሆኑ ካፒታል ሰምቷል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍178👎2🔥1
የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር  በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ!

በሪያድ በመካሄድ ላይ ባለው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ቅርሶች በተጨማሪ ይሄንኛው አስረኛ ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍357
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች!

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ በኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን የተያዘውን ክብረ ወሰን በመስበር የዲያመንድ ሊግ አሸናፊ ሆነች።

አትሌቷ ክብረ ወሰኑን የሰበረችው 14:00.21 በሆነ ሰዓት በመግባት መሆኑን ዎርልድ አትሌቲክስ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
98👍44🔥4
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
2👍1
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
👍87
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍42
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
4👍3
በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት አለፈ!

መስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም እለተ ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከጉንዶ መስቀል ከተማ ወደ ኩቲ 53 በሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 ( 75263 ኦሮ ) የሆነ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላሻ ተሽከርካሪ ፤ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ 30 ባጋጠመዉ የመገልበጥ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በአደጋዉ ህይወታቸዉን ያጡት  8 ወንዶች እና 7 ሴቶች ናቸዉ።

ሌሎች 4 ሰዎች በእጅግ ከባድ የተባለ ጉዳት ደርሶባቸው በጳዉሎስ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኢንስፔክተር ባዩሳ ደበላ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ለአደጋዉ መንስኤ የተሽከርካሪዉ የቴክኒክ ብቃት ማነስ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም በ 30 ሰዎች ላይ 18 ሴት እና 12 ወንዶች ከባድ የተባለ ጉዳት እንዲሁም በ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል ነዉ የተባለዉ።

ተሽከርካሪዉ ዳገት በመዉጣት በነበረበት ወቅት ወደ ኋላ በመመለሱ አደጋዉ ማጋጠሙን የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል። በአደጋዉ አሽከርካሪዉ እና ረዳቱ ወዲያዉኑ ህይወታቸዉ ማለፉንም አክለዋል።በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሌሎች 30 ሰዎች በፍቼ እና ጉንዶመስቀል ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ባዩሳ ደበላ ጨምረዉ ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
👍285🔥1
በምዕራብ ጎጃም በምትገኘው የደንበጫ ከተማ ትላንት በተካሄደ የድሮን ጥቃት 16 ወጣቶች ተገድለው 3 መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

የቆሰሉ ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።በደንበጫ ከተማ ከቅዳሜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውግያው እንደቀጠለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ገልጸዋል። ውግያው ቅዳሜ በርትቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን አልፎ አልፎ ከሚሰማ የተኩስ ድምጽ በስተቀር ረገብ ማለቱን ነው እኒህ የአይን እማኝ የተናገሩት።

ትናንት እሁድ በከተማዋ በተካሄደ የድሮን ድብደባ ስለሞቱት ወጣቶች ማንነት የተጠየቁት እኚህ የዓይን እማኝ «የፋኖን ኃይል ለመርዳት የተዘጋጁ መሣሪያ ያልታጠቁ ወጣቶች ናቸው» ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪ በገጠራማ አካባቢዎች የሄሊኮፕተሮች ድብደባ የነበረ ቢሆንም በቤቶች ላይ ከደረሰ ውሱን ጉዳት በስተቀር በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተናግሯል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍233
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ!

የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ አሳልፏል።

የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርስነት የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።

45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሁለት ታላለቅ የቱሪስት መዳረሻዎችን በአለም ቅርስነት ማስመዝገቧን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍287👎2
የፌደራሉ ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእንባ ጠባቂ ተቋምን ምክረ ሃሳቦች ለመቀበል እምቢተኝነት ያሳያሉ ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ በሰጡት ቃል ከሰዋል።

እንዳለ፣ ኹለቱ የፖሊስ ኮሚሽኖች ተባባሪ ባለመኾናቸው ተቋሙ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመምራት ተገዷል ብለዋል። የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽንም፣ ተመሳሳይ ችግር እንደሚታይበት ዋና እንባ ጠባቂው ጠቅሰዋል።

አንዳንድ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ እንደ ባሕርዳር፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ የመሳሰሉ የክልል ከተማ አስተዳደሮችና የክልል ቢሮዎች፣ የሕዝቡን የአስተዳደር በደሎች ለመስማትና የተቋሙን የመፍትሄ ሃሳቦች ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የማይኾኑት፣ "ማን ይነካናል?" በሚል አስተሳሰብ እንደኾነም እንዳለ ለጣቢያው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍434
ኢራን ከዩናትድ ስቴትስ ጋራ የእስረኞች ልውውጥ እንደምታደርግ አስታወቀች!

ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ፣ ዛሬ ሰኞ፣ የእስረኞች ልውውጥ እንደምታደርግ አስታውቃለች። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ተጥሎበት የነበረው ስድስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር፣ ደቡብ ኮርያ ከሚገኝ የባንክ ሒሳቧ ወደ ኳታር ባንክ እንዲዘዋወር ስትጠብቅ እንደቆየች ገልጸዋል፡፡

የገንዘብ ዝውውር ስምምነቱ፣ በኢራን ታስረው ለሚገኙ አምስት አሜሪካውያንና በዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ አምስት ኢራናውያን የእስረኞች ልውውጥ መንገድ እንደከፈተ ተናግረዋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ግለሰቦችን ጠቅሰው የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት፣ ኳታር፣ ገንዘቡ ዛሬ ሰኞ እንደተላለፈ ለኢራንና ለአሜሪካ አሳውቃለች።

በጉዳዩ ላይ፣ እስከ አሁን ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የተገኘ ማረጋገጫ የለም፡፡ የዋይት ሐውስ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ፣ ባለፈው ሳምንት ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ የባይደን አስተዳደር፣ የእስረኛ ልውውጡ በቅርብ ጊዜ እንደሚከናወን ያለውን ተስፋ አመልክተው ነበር።

በእስረኛ ልውውጡ የሚለቀቁት ሦስቱ አሜሪካውያን፥ ሲያማክ ናማዚ፣ ኢማድ ሻርጊ እና ሞራድ ታህባዝ ናቸው፡፡ እኒኽ ሦስቱ፣ ከሌላ ስማቸው ካልተገለጹ ሁለት አሜሪካውያን ጋራ፣ ከነበሩበት በታህራን ከሚገኝ እስር ቤት ወጥተው በመኖሪያ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ ተገልጿል።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ አምስቱም አሜሪካውያን ያለአግባብ መታሰራቸውን ትከራከራለች። ኢራን በበኩሏ፣ በስምምነቱ መሠረት እንዲፈቱ የምትፈልጋቸውን አምስት ኢራናውያንን ለይታ አሳውቃለች።

ወደ ኳታር የተላለፈው የኢራን ገንዘብ፣ ለሰብአዊ ጉዳዮች ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ነው የተወሰነው፡፡ ኢራን፣ ገንዘቡን ለሌላ ተግባር ልትጠቀምበት ትችላለች፤ የሚለውን ጥርጣሬ፣ የባይደን አስተዳደር፣ ገንዘቡ ለተፈቀደለት ጉዳይ ብቻ ስለመውጣቱ ክትትል ይደረጋል፤ ሲል ውድቅ አድርጓል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍244
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
👍3