YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
👍4
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍51👎1
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍4👎1
ከየመን ወደ አገራቸው ለመመለስ መንገድ ያጡ ኢትዮጵያውያን አጣብቂኝ ገብተዋል!

በጦርነት በተበታተነችው በየመን ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች፣ ገቢ ለማስገኘት የሚያስችል ሥራም ኾነ ወደ አገራቸው መመለሻ መንገድ ማጣታቸውና በአጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት፣ በክልሎቹ ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ፣ ከዐማራ ወይም ከትግራይ ክልል ወደ የመን የመጡ ፍልሰተኞችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመኾኑ፣ ውሳኔውን የተቃወሙ ስደተኞች ወደ አደባባይ እንዲወጡ ምክንያት ኾኗል።

በፈቃደኝነት ከየመን ወደ አገራቸው ለሚመለሱ ስደተኞች የሚቀርበውን ሰብአዊ ርዳታ የሚቆጣጠረው ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ በቅርቡ፣ በክልሎቹ ባለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ፣ ወደ ትግራይ እና ዐማራ ክልሎች የሚመለሱትን ስደተኞች ማጓጓዝ እንዳቋረጠ ታውቋል። ድርጅቱ፣ ከስደት ተመላሾቹ ወደ አገራቸው የመመለስ ጉዞን ማስቆም ባይችልም፣ ሊመለሱ የሚችሉበትን ኹኔታም ግን እያመቻቸ እንዳልሆነ ተገልጿል።

በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፣ በየዓመቱ የተሻለ የሥራ ዕድል ፍለጋ፣ ለሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ሰለባ በሚኾኑበት አደጋ ባልተለየው ጉዞ ወደ አረብ አገሮች ያቀናሉ። ውሳኔውን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ ባለፈው ሳምንት፣ ከየመኗ ዋና ከተማ ዔደን ከሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ደጃፍ ትዕይንተ ሕዝብ ማካሔዳቸውን ተከትሎ፣ ግጭት እንደተፈጠረና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም እንደተገደሉ ተዘግቧል።

አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው፣ የዐማራ ተወላጆች መብቶች ተሟጋቹ “የዐማራ ማኅበር በአሜሪካ” የተባለው ድርጅት ሊቀ መንበር ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ፣ ውሳኔው፥ የዐማራ እና የትግራይ ተወላጆች የኾኑ ስደተኞችን ለይቶ የተፈጸመ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በተናጠል ያደረገው አግላይ ፖሊሲ ውጤት ነው፤ ይላሉ።

“እነኚኽ ኢትዮጵያውያን፣ ወደ አገራቸው ተመልሰው የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች የሚያስፈልጓቸው አገልግሎቶች ተሰጥተዋቸው፣ በዐዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች እንዲኖሩ ሊደረጉ ይችላሉ። የዐማራ ተወላጆች በመኾናቸው ብቻ፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ ሊያቅታቸው አልያም የግድ ወደ ዐማራ ክልል መሔድ የለባቸውም። የዐማራ ተወላጆች፣ በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ይኖራሉ፤” ብለዋል።

በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በፕሪቶርያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ በትግራይ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነት ባለፈው ጥቅምት ተቋጭቷል፡፡ በአንጻሩ በሕዝብ ብዛቱ በአገሪቱ ሁለተኛ በኾነውና የፋኖ ታጣቂ በሚገኝበት የዐማራ ክልል፣ ሌላ ዐዲስ ግጭት መቀስቀሱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሐምሌ ወር መገባደጃ፣ በዐማራ ክልል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት፣ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁ የሚታወስ ነው።

በ18 ዓመቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተጓዘችው ሮማን፣ ምንም እንኳን የሥራ ዕድል ማግኘቱ ቢሳካላትም፣ ሥራ ለመሥራት የሚቻልበት ኹኔታ ግን እጅግ አዳጋች እንደ ነበር አስረድታለች። ዶር. መሳይ ሙሉጌታ፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር ናቸው። ዜጎች፣ አደገኛውን የስደት ጉዞ እንዳያደርጉ የማቀብ መፍትሔው፣ ኢኮኖሚያዊ ነው፤ ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ሂዩማን ራይትስዎች በቅርቡ ያወጣው አንድ ዘገባ፣ የሳዑዲ አረቢያ ድንበር ጠባቂዎች፣ እ.አ.አ. ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የየመንና የሳዑዲን ድንበር ለማቋረጥ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንደገደሉ አመልክቷል።

የመብቶች ተሟጋቹ ቡድን አክሎም፣ ግድያዎች፣ በሰብአዊነት ላይ ከተፈጸሙ ወንጀሎች እንደሚቆጠሩ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፣ የተባሉትን ግድያዎች ለማጣራት ምርመራ እንደሚያካሒድ ሲያስታውቅ፣ የሳዑዲ መንግሥት በአንጻሩ፣ ክሡን አስተባብሏል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍231
የምርት ሙከራ የተከናወነባቸዉ ስድስት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ጉድጓዶች ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምርት ሙከራ ከተከናወነባቸዉ ስድስት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ጉድጓዶች 25 ሜጋ ዋት ኃይል መገኘቱን አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል የጂኦተርማል ሴክተር ልማት በአሉቶ ላንጋኖ የከርሰምድር ፕሮጀክት ከተቆፈሩት 10 የኃይል ማመንጫ ጉድጓዶች የስድስቱ ቁፋሮ ተጠናቆ ምርት መስጠት ጀምሯል ብሏል።

"ቀሪ የአራት ጉድጓዶች ሙከራ ስራ እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ሊጠናቀቅ እንደሚችል" ተጠቁሟል።

ካፒታል ከተቋሙ ባገኘዉ መረጃ "ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ 70 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ታልሟል በመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሜጋ ዋት ከተከናወነ በኃላ ሁለተኛው ይቀጥላል"።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍19🔥21
በትግራይ ክልል ነገ መደበኛ ትምህርት ይጀመራል!

የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት ነገ እንደሚጀመር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የ2016 የትምህርት ዘመንን ነገ ለማስጀመር ለትምህርት ማሕበረሰቡ ሥልጠና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

በዚህም ባለፉት 5 ቀናት ለመምህራን እና ለትምህርት ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን ነው የገለጸው፡፡

ስልጠናው እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ቢሮው ምስጋና አቅርቧል፡፡በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ በየአካባቢው የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ቢሮው ጥሪ አቀርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍357
ሰሞኑን በሱማሌ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ግጭት እንደተከሰተ ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮቿ ተረድታለች።

ግጭቱ የተካሄደው፣ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ወደ ሱማሌ ክልል ፋፈን ዞን ጅግጅጋ ከተማ በሚወስደው መስመር በባቢሌ ከተማ አቅራቢያ እንደነበር ታውቋል። ግጭቱ በትክክል በየትኞቹ አካላት መካከል እንደተካሄደ ግን ለጊዜው ማረጋገጥ አልተቻለም። በአካባቢው በሚገኙ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ላይ ኹለቱ ክልሎች ቀደም በይገባኛል ጥያቄ ሲወዛገቡ የነበረ ሲኾን፣ ከጥቂት ዓመታት በፊትም ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የኾነ ግጭት ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። የሰሞኑን ግጭትና ውጥረት ተከትሎ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት በአካባቢው እንደተሠማራ ተሰምቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍12🔥1
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ባለፈዉ ዕሁድ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰዉ ተገደለ፤ ቆሰለ፤ በሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ።

ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያና ወደ ጅቡቲ በሚወስደዉ አዉራ መንገድ ዳር በምትገኘዉ «አዉራ ጎዳና» ወይም «ቆርኬ» ተብላ በምትጠራዉ ከተማና አካባቢዋ በሐብትና በቦታ ይገባኛል ሰበብ የጊዜዉ ግጭት ይነሳል።ባለፈዉ ዕሁድ የተቀሰቀሰዉ ግን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከሚነሳዉ ግጭት የከፋና በከባድ መሳሪያ የታገዘ ዉጊያ እንደነበር የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታዉቀዋል።ለጠቡ መነሻ ነዋሪዎቹ የሚሰጡት አስተያየት እንዳሉበት አካባቢና እንደየጎሳቸዉ የሚቃረን ነዉ።አንዳዶቹ ነዋሪዎች ግጭቱ የተነሳዉ የፋኖ ታጣቂዎች «በአካባቢዉ የሠፈረዉን የኦሮሚያ ፖሊስ በማጥቃታቸዉ ነዉ» ይላሉ።ሌሎች ግን ባካባቢዉ የፋኖ ታጣቂ አለመኖሩን አስታዉቀዋል።

ቀደም ሲል አካባቢዉን የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከአካባቢዉ ሲለቅ ሠራዊቱን ተክቶ አካባቢዉን የሚቆጣጠረዉ የኦሮሚያ ፖሊስ ነዉ።ግጭቱ የተደረገዉም «ባካባቢዉ አርሶ አደርና በኦሮሚያ ፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ነዉ» ባዮች ናቸዉ።

አስተያየት ሰጪዎቹ በግጭቱ መነሻና በተዋጊዎቹ ማንነት ላይ ልዩነት ቢኖራቸዉም በግጭቱ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ወደ መተሐራና ወለንጪቱ ከተማ መወሰዳቸዉን አስታዉቀዋል።በግጭቱ ከ2 ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ መፈናቀሉ፣ ግምቱ በዉል ያልታወቀ ሐብትና ንብረት መዉደሙንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዳግም ባካባቢዉ በመስፈሩ ግጭቱ መብረዱንም ነዋሪዎቹ አስታዉቀዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍316
በጦርነቱ ወቅት የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ኃይል ለቤተሰቦቻቸው መርዶ የመንገር ስርዓት በቅርቡ በይፋ እንደሚካሄድ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

በጦርነቱ ወቅት የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ኃይል ለቤተሰቦቻቸው መርዶ የመንገር ስርዓት በቅርቡ በይፋ እንደሚካሄድ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩ በትክክል ባያስቀምጡትም "በሺዎች የሚቆጠሩ" ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸው ተናግረዋል። የሟች ቤተሰቦች ከማርዳት በተጨማሪ፣ የመደገፍ ስራም እንደሚከወን ጠቁመዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍273
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
👍7
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
2👍1
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍1
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍3
የአገው ለፍትሕ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሁለት አመራሮቹ በመተከል እንደታሰሩ ገለጸ!

የአገው ለፍትሕ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ ሁለት ከፍተኛ የአመራር አባላቱ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ታስረው እንደሚገኙ አስታወቀ፡፡

ባጠቃላይ ታስረው የነበሩት አምስት አመራሮች መሆናቸውን የገለጹት የፓርቲው ሰብሳቢ ዶር. ዐዲሱ መኰንን፣ ከአምስቱ አመራሮች ሁለቱ፣ ካለፈው ዓመት ጳጉሜን 4 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ገልጸዋል፡፡ ሌሎቹ ሦስት አመራሮች ደግሞ፣ ሁለቱን ለመጠየቅ በሔዱበት ከመስከረም 2 ቀን ጀምሮ ታስረው፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ስለመለቀቃቸው ተናግረዋል።

የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋቅወያ በበኩላቸው፣ “ግለሰቦቹ የታሰሩት፣ ከአገው እና ከጉምዝ ሰዎችን መልምለው በጫካ ሲያሠለጥኑ ተገኝተው ነው፤” ብለዋል። የፓርቲ ሊቀ መንበር፣ ውንጀላው ሐሰት ነው፤ ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍101
በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ የተሟላ መሠረተ ልማት የሌለው እና ከፍተኛ የንጽሕና ጉድለት ያለበት መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ሥራ ክፍል የሪጅን ዳይሬክተር ሰላማዊት ግርማይ እንደገለጹት በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ማእከል ከተማ መስተዳደሩ ውሎ እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ አረጋውያን፣ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን የሚያቆይበት ነው፡፡

ሆኖም ማቆያ ማእከሉ ለሰዎች ማቆያ ተብሎ የተዘጋጀ ሳይሆን፤ ለኢንዱስትሪ ዕቃዎች ማከማቻ የተዘጋጀ በመሆኑ የተሟላ መሠረተ ልማት የሌለው እና ከፍተኛ የንጽሕና ጉድለት ያለበት ነው ብለዋል፡፡በቅርቡም በማእከሉ በተባይ የሚመጣ በሽታ ተከስቶ ነበር ያሉ ሲሆን በመጠለያ ጣቢያው ከነበሩ ሰዎች መካከል 1 መቶ 90 የሚሆኑ ሰዎች በሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ሲያገኙ የ3 ሰዎች ሕይወት ድግሞ አልፏል ብለዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👍16👎1
በሰሜን ጎንደር ዞን ከ200 ሺህ በላይ ወገኖች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ!

በሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ፡፡የሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ ይርዳው ሲሳይ እንደገለጹት÷ በዞኑ በድርቅ ምክንያት 452 ሺህ 851 ሰዎች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ከዚህ ውስጥ 202 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።በድርቁ ምክንያት 19 ሺህ 174 ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ማሳ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡በእንስሳት ላይም ተመሳሳይ ጉዳት እየደረሰ ሲሆን÷ ወደ ሌሎች አካባቢዎች የማዘዋወር ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በበየዳ፣ ጠለምትና ጃናሞራ 4 ሺህ 88 ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው መሄዳቸውንም ነው ሀላፊው የተናገሩት።በችግሩ ምክንያት የተላላፊ በሽታዎች ወረርሽኝ መከሰቱን ጠቅሰው÷ ሁሉም አካል የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ ሊረባረብ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍253
ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የተመረጡ ጨዋታዎች የቤቲንግ ግምትና መረጃዎች

አርሰናል፣ ማን ዩናይትድ፣ ጋላታሳራይ፣ ናፖሊንና ሪያል ማድሪድን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት

ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇

http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የአውሮፓ-ቻምፒዮንስ-ሊግ-የ/

ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett
👍82
በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገቡ!

በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ከ11 ሺህ 581 በላይ ተማሪዎችን በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገለጸ፡፡የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ዳንኤል ውበት 3 ሺህ 134 ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ ተማሪዎች ዝግጅት እንዲያደርጉ ቀደም ብሎ መሠራቱን ገልጸዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚጓዙበት ወቅት የመጓጓዣ ኹኔታ ምቹ እንዲኾን መሠራቱንም አመላክተዋል። በዞኑ 6 ሺህ 119 ተፈታኝ ተማሪዎች መኖራቸውን ኀላፊው አንስተዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአሥተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ልጅዓለም ጋሻው በሶስት ዞኖችና በጎንደር ከተማ የሚገኙ ከ11 ሺህ 581 በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንዲያጠናቅቁ ዩኒቨርሲቲው በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸል ሲል አሚኮ ዘግቧል።ተፈታኝ ተማሪዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተናቸውን ማጠናቀቅ አለመቻላቸውን በማስታወስ በአሁኑ ወቅት ፈተናውን ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍209
የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ቁልፍ ሰብረው በገቡ ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ መወሰድ መጀመሩ ተገለጸ!

በሸገር ከተማ የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ቁልፍ ሰብረው በገቡ ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ለባለዕድለኞች የተላለፉ ቤቶችን ሰብረው የገቡ ግለሰቦችን ማስለቀቅ መጀመሩን፣ በሸገር ከተማ የቤቶች ልማት ማስተዳደርና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሠረት አበበ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ከቤቶቹ ሕጋዊ ባለቤቶች በተገኙ ጥቆማዎች መሠረት ጽሕፈት ቤቱ ከሕግ አስከባሪዎች ጋር በመሆን የባለዕድለኞቹን ሕጋዊ ሰነዶች በማረጋገጥ፣ በሕገወጥ መንገድ የተያዙት ቤቶች እየተለቀቁ መሆናቸውን ወ/ሮ መሠረት ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት በኮዬ ፈጬ ከሚገኙ 10/90 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 2,236 ቤቶች ሕጋዊ ባልሆኑ ግለሰቦች መያዛቸውን፣ 1,232 ሕገወጥ ግለሰቦችን በማስለቀቅ ቤቶቹ ለባለቤቶቹ እንዲተላለፉ መደረጋቸውን ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

በሕገወጥ መንገድ ወደ ኮንዶሚኒየሞቹ የሚገቡና የሚወጡ ግለሰቦች ሕጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው፣ እንዲሁም የግለሰቦቹን ማንነት ማወቅ ባለመቻሉ ነዋሪዎች ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውም ተነግሯል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
👍54👎98🔥1
ለሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተፃፈ አጭር መልእክት:

ሀገራችን ካፈራቻቸው የመጠቀ የስነ-ፅሁፍ እና የሀይማኖታዊ አስተህምሮቶች እውቅት ባለቤት የሆኑት እርስዎን በርካቶች እንደ ታላቅ የቀለም ቀንዲል፣ ወንድም፣ መካሪ እና አስተማሪ ይመለከትዎታል።

በቅርብ አመታትም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ስለሚገኙ ያለብዎትን ድርብ ሀላፊነት ማየት ይቻላል።

ይሁንና ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች እና ጦርነቶች ዙርያ ያስተላለፏቸው እና እያስተላለፏቸው የሚገኙ አንዳንድ መልዕክቶችን የተመለከቱ አንዳንድ ዜጎች "ዲያቆን ዳንኤልን ምን ነካብን" ሲሉ ይደመጣል፣ እውነት ለመናገር ይህ ከእርስዎ የቅርብ ወዳጆች ዙርያ ጭምር ይሰማል።

ይህን አጭር መልዕክት ልፅፍልዎት የወደድኩት በዚህኛው ወይም በዛኛው ንግግርዎት ዙርያ ሳይሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ባሉ የግጭት ተሳታፊዎች መካከል እርቅ እንዲወርድ እና ሰላም እንዲሰፍን በተለያዩ አካላት አንዳንድ ስራዎች እየተሞከሩ ባለበት በዚህ ወቅት እርስዎም ይህን ሊደግፍ የሚችል መልዕክት በማስተላለፍ ድርሻዎን እንዲወጡ በትህትና ለመጠየቅ ነው።

እርስዎም እንደሚረዱት ማንም ሰው ማንንም ካለ ፍላጎት ማህበራዊ ሚድያ ላይ ይህን ፃፍ ወይም አድርግ ሊል አይችልም፣ ነገር ግን እንደ አንድ ታናሽ ወንድም ጉዳዩን ብዙ ግዜ ሳስበው የነበረ በመሆኑ እንዲሁም የብዙ ሰው ጥያቄ እና ሀሳብ ነው ብዬ ስላሙንኩ አሁን ላቀርብልዎት ወሰንኩ።

ከሰላምታ ጋር።

ተፃፈ በኤልያስ መሰረት
👍164👎5110