YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ታሪካዊው የአክሱም ሐውልት በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግር ምክንያት ወደ አንድ አቅጣጫ አዝምሟል ተባለ!

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ‹‹ በአክሱም በተካሄደው ጥናት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት በአካባቢው ያለው ታሪካዊው ሃውልት ወደ አንድ አቅጣጫ የመዝመም ሁኔታ እንደተስተዋለበት መመልከቱን ›› ይፋ አድርጓል።ባለስልጣኑ ሃውልቱ ወደአንድ አቅጣጫ ለማዝመሙ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግር መንስዔ መሆናቸውን ይግለጥ እንጂ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ የተባሉት ችግሮች ምን እንደሆኑ በውል ስለመናገሩ በኢዜአ ዘገባ አልተካተተም፡፡

በባለስልጣኑ የቅርሶች ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክተር ሃብታሙ አብረሃ ‹‹ 31 ሜትር ቁመት ያለውና ወደ ሰሜን አቅጣጫ የዘመመው የአክሱም ሃወልት ከአራት ዓመታት በፊት በ115 ሚሊዮን ብር በጀት ለመጠገን የፌዴራል መንግስት ከአንድ የጣሊያን ተቋራጭ ጋር ውል መግባቱን ›› አስታውሰዋል።

‹‹ በውሉ መሰረት ተቋራጩ ለጥገና የሚያስፈልጉ ዕቃዎች መጓጓዝ በጀመረበት ወቅት በኮሮናና በጦርነት ምክንያት እንደተቋረጠ ›› ያስታወሱት ሃብታሙ ‹‹ አሁን በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውሉን በማደስ የጥገና ስራ በተያዘው በጀት ዓመት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ›› ተናግረዋል።ባለሰልጣኑ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፈጥሯል ያለውን ‹‹ ሰላም በመጠቀም ቅርሶች ያሉበትን ደረጃ ለመለየት አስቸኳይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን ›› ገልጿል።

ከእነዚህ ታሪካዊ ስፍራዎችና ቅርሶች መካከል የአክሱም ሃውልትና የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት እንደሚገኙበት ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡በሌላ በኩል ከአለት ተፈልፍሎ የተሰራው ታሪካዊው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ማደስ የሚያስችል ከቀድሞ በተጨማሪ የባለሙያዎች ጥናት መካሄዱን ገልጸዋል።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ተጀመረ፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና  ኮሌጅ የኩላሊት እጥበት መስጫ ማዕከል( Dialysis center ) የእጥበት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ መሳሪያዎች ረዘም ላለ ጊዜ በማገልገላቸው እድሳት ስለሚያስፈልጋቸው ለተወሰነ ጊዜያት ማእከሉ አገልግሎቱን አቋርጦ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የማዕከሉ የእጥበት መሳሪያዎች እድሳት በመጠናቀቁና አስፈላጊ ግብኣት በመሟላቱ  አገልግሉቱን በያዝነው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ መጀመሩ ሆስፒታሉ አሳዉቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሀዋሳ ከተማ ያሉ የንግድ ተቋማት በአንድ ወር ውስጥ የደህንት ካሜራ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ መመሪያ ወጣ!

የሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የንግድ ተቋማት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የደህንት ካሜራ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣ። መመሪያውን ተግባራዊ የማያደርጉ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ላይ የእስር አሊያም የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ቢሮው መመሪያውን ይፋ ያደረገው፤ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 17፤ 2015 በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው። የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ሀዋሳ የሚገኙ የንግድ ተቋማት፤ የደህንነት ካሜራ እንዲገጥሙ የሚስገድደው መመሪያ የወጣው በሁለት ምክንያቶች ነው ተብሏል።

በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ድርጅቶች ፊት ለፊት “የሞተር ሳይክል ስርቆቶች” በተደጋጋሚ እንደሚፈጸሙ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተናገሩት የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፤ ይህንን ድርጊት እና በድርጅቶቹ ውስጥ በሀሰተኛ የገንዘብ ኖት የሚደረጉ ግብይቶችን “ለመቆጣጠር” መመሪያው መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በአዲሱ መመሪያ መሰረት በከተማይቱ የሚገኙ የንግድ ተቋማት በድርጅታቸው ውስጥ እና ወደ ውጭ የሚመለከቱ የደህንነት ካሜራዎችን መግጠም ይኖርባቸዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
👇👇👇

https://www.betsket.com/ጋላታሳራይ፤-ኢንተር-ማያሚን፤-ቦካ-ጁኒዮ/
1👍1
የ11 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ መንግሥት የፖለቲካ አለመረጋጋቶችንና ግጭቶችን "በኃይል ለመፍታት" የሚያደርገው ጥረት እንዳሳሰበው ዛሬ አስታውቋል።

ስብስቡ፣ መንግሥት በትግራይ፣ በኦሮሚያና በቅርቡ በአማራ ክልል ግጭቶችን በኃይል ርምጃ ለመፍታት ያደረገው ሙከራ ለፖለቲካዊ አለመረጋጋቱና ውጥረቱ "ዘላቂ መፍትሄ አላመጣም" ብሏል።

"አስቸኳይ" እና የ"አፋጣኝ ዘላቂ የመፍትሄ ርምጃ" አስፈላጊነት የማይቀለበስ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው ስብስቡ፣ "አካታችና ኹሉን ዓቀፍ" የፖለቲካ ኃይሎች ውይይት እንዲደረግ፣ በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የተቋረጠው ድርድር እንዲቀጥል፣ በመንግሥትና በአማራ ፋኖ ታጣቂዎች መካከል "ግጭት እንዲቆም" እና "ውይይት ወይም ድርድር እንዲጀመር" ጠይቋል። መግለጫውን ካወጡት የስብስቡ አባላት መካከል፣ ኦፌኮ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ አረና ትግራይና የአፋር ነጻነት ፓርቲ ይገኙበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመጪዎቹ ሶስት ዓመታት “በአማካይ 8.3 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል”- ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በአማካይ 8.3 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ ዓመት በ9.2 በመቶ ያድጋል በሚል እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፤ ከሶስት ዓመት በኋላም በዚህ የእድገት መጠን ደረጃ ላይ እንደማይደርስ የፌደራል መንግስት ይፋ ያደረገው ሰነድ አመልክቷል።

የፌደራል መንግስት የልማት እቅድ ሲያዘጋጅ የረጅም ጊዜውን በአስር ዓመት እና የመካከለኛ ጊዜውን ደግሞ በሶስት ዓመት ይከፋፈላል። በዚህ አሰራር መሰረት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት፤ ከ2013 ዓ.ም እስከ 2015 ድረስ የቆየ የመጀመሪያውን የመካከለኛ ጊዜ እቅድ አዘጋጅቶ እስከተጠናቀቀው በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ሲተገብር ቆይቷል።

በዚህ እቅድ የመጀመሪያ ዓመት፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ 8.5 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እቅድ ተይዞ ነበር። በ2014 ዓ.ም ወደ 8.7 በመቶ ከፍ እንደሚል የተገመተው የእድገት ምጣኔ፤ በዘንድሮው ዓመት ወደ 9.2 በመቶ እንደሚመነደግ በፌደራል መንግስት የእቅድ ሰነድ ላይ ሰፍሯል። ሆኖም ይህ እቅድ በተከታታይ ሶስት ዓመታት አለመሳካቱ ባለፉት ቀናት በተደረገ “የመካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም” ግምገማ ላይ ይፋ ተደርጓል።


Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን በአውሮፕላን አደጋ ሞተ!

የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን (ቫግነር) መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ሩሲያ ውስጥ ባጋጠመ የአውሮፕላን አደጋ ሕይወቱ አለፈ።ከፕሪጎዢን በተጨማሪም በአውሮፕላኑ ውስጥ አብረውት የነበሩት ዘጠኝ ሰዎችም ሞተዋል።

ቀደም ሲል ከቅጥረኛ ቡድኑ ቫግነር ጋር ግንኙነት ያለውና ግሬይ ዞን የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል እንደዘገበው ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት የነበረው ጄት በአየር መከላከያ መመታቱን ነው።እንደ ዘገባው ከሆነ ጄቱ የተመታው በሰሜናዊ ሞስኮ ቴቨር ክልል ውስጥ ነው።

ፕሪጎዢን ከጥቂት ወራት በፊት በሩሲያ ጦር ላይ ያልተሳካ አመጽ መምራቱ ይታወሳል።ዮቭጌኒ ፕሪጎዢን በአገሩ ላይ ያስነሳው ነውጥ ከከሸፈ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መልዕክቱን በቪዲዮ ከሰሞኑ አስተላልፎ ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Forwarded from YeneTube
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
👍2
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ተቀላቅላለች።

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ፥ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት ተቀብሏል።

“ብሪክስ” በፈረንጆቹ ሠኔ 16 ቀን 2009 የተመሠረተ ሲሆን “ብሪክ” በሚል ምኅፃረ-ቃል ይጠራ ነበር፡፡

የተመሠረተውም ÷ በብራዚል ፣ ሩሲያ ፣ ሕንድ እና ቻይና የጋራ አነሳሽነት ነው፡፡

“ብሪክ” ኋላ ላይ “ብሪክስ” የሚለውን ሥያሜ ያገኘው በፈረንጆቹ 2010 ላይ የደቡብ አፍሪካን የአባልነት ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ቡድኑ ከቀላቀላት በኋላ ነው፡፡

“ብሪክስ” አባል-ሀገራቱ በምጣኔ-ሐብት ለመዋኀድ ዓላማ ሰንቀው ያቋቋሙት ቡድን ነው፡፡

ቡድኑ ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ እስከ ፈረንጆቹ 2050 የዓለምን ምጣኔ-ሐብት ለመቆጣጠር ግብ አስቀምጧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
ቻይና ÷ኢትዮጵያ ብሪክስን በመቀላቀሏ የደስታ መልዕክት አስተላለፈች

ቻይና ÷ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን በመቀላቀሏ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡

የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ጉዳዩን አስመልክቶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ÷ ቻይና ለብሪክስ መስፋፋት በተለይም የኢትዮጵያን በአባልነት መቀላቀል እንደምትደግፍ አስታውቋል፡፡

ቻይና ሁሉን አካታች እና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓት ለመፍጠር የብሪክስ አባል ሀገራትን መስፋፋት እንደምትደግፍ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ በጉባዔው ብሪክስን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሀገራት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውም ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢያን÷ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን በመቀላቀሏ ለኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቻይና በብሪክስ ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትብብር ለማጠናቀር ቁርጠኛ መሆኗንም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia #BRIKS

@Yenetube @Fikerassefa
1👍1
የስልጤ ዞን የኩተሬ ከተማ ነዋሪዎች በወረዳ እንደራጅ የሚል ጥያቄን አንግበው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

መንግስት በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በክላስተር አደረጃጀት ካዋቀራቸው አራት ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስር የተካተተው ስልጤ ዞን ውስጥ የምትገኘው የኩተሬ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በወረዳ እንደራጅ ጥያቄያቸውን ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ለአሻም እንደነገሯት ‹‹ የወረዳነት የጥያቄያቸው መነሻ የእድገት፣ የመልካም አስተዳደርና የመሰረተ ልማት መስፋፈት ፍላጎቶች እንዲሟሉላቸው ታስቦ መሆኑን ›› አስረድተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ‹‹ ከአምስት አመታት በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸውን ሲያነሱ የፌደራል፣ የክልሉና የዞን አመራሮች በተገኙበት ብልፅግና ፓርቲ ምርጫን ካሸነፈ የመጀመሪያ የሚመለሰው ጥያቄ የኩተሬ የወረዳነት ጥያቄ መሆኑን ቃል መግባቱን ›› አስታውሰው ‹‹ ይህ ግን ተፈፃሚ አለመሆኑን ›› በመጥቀስ ይወቅሳሉ፡፡

አሻም የሰልፈኞችን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አማን ከድርን እንዲሁም የስልጤ ዞን አስተዳዳሪ አሊ ከድር ምላሽ በዘገባው ለማካተት ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡የሥራ ሃላፊዎች ምላሽ በሰጡበት አፍታ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
👍21
Forwarded from YeneTube
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
👍1