YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጉባኤ በዛሬ ውሎው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እና አፈ ጉባኤ ሹመትን አጽድቋል፡፡በዚህ መሰረትም አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።

አቶ እንዳሻው ከቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ጋር የሕገ-መንግስት ርክክብ ማድረጋቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ፋጤ ስርሞሎን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ እና መነቴ ሙንዲኖን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አቶ ጥላሁን ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።ከዚህ ቀደም በነበራቸው የስራ ኃላፊነት የህዝብ አገልጋይ ሆነው የሰሩ ብቃት ያለው አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ መሆናቸውም በምክር ቤቱ ተብራርቷል።

በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ሳይበገሩ ኃላፊነታቸውን በብቃት ስለመወጣታቸውም ተጠቁሟል።አቶ ጥላሁን ከበደ የህዝብን ድምጽ የሚያከብሩ፣በብዝሀነት የሚያምኑ ሁሉንም ህዝብ ያለ አድሎ ያገለገሉ እንደነበርም በምክር ቤቱ አባላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።ምክር ቤቱ የርዕሰ መስተዳድሩን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
👇👇👇

https://www.betsket.com/ማንችስተር-ሲቲ፤-ሆፈንሃይም፤-ሞልድንና/
👍1
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን ጸደቀ!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሦስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ያጸደቀው።

በዚህም መሠረት:-

-የም ዞን

-ምስራቅ ጉራጌ ዞን

-ጠምባሮ ልዩ ወረዳ

-ቀቤና ልዩ ወረዳ

-ማረቆ ልዩ ወረዳ

ሆነው የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል በሞሽኑ ቀርቦ መጽደቁን ደሬቴድ ዘግቧል።ከትናንት ጀምሮ ለኹለት ቀናት ሲከናወን የቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በቡዳፔስት የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 10ሺህ ሜትር ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኙ!

በቡዳፔስት የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኙ።

በሀንጋሪ እየተካሄደ ባለው  የ19ኛው የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጀመሪያው ቀን የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩም ጉዳፍ ፀጋይ 1ኛ፣ ለተሰንበት ግደይ 2ኛ እና እጅጋየሁ ታዬ 3ኛ በመውጣት ለሀገራቸው የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ለሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስአበባ ፤ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ቢነሳም አሁንም አሽከርካሪዎች ሌለ ሰዉ መጫን አይችሉም ተብሏል!

በአዲስአበባ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ከነገ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ መነሳቱን የአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳዉቋል።

ቢሮዉ አሽከርካሪዎች ሌላ ተጨማሪ ተሳፋሪ ሳይጨምሩ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይችሉም አሳዉቋል። ለዚህኛዉ ክልከላዉም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከዚህ ቀደም የማሽከርከር እግዳዉ ሲጥል ምክኒያት እንዳልሰጠዉ ሁሉ በዚህም ያስቀመጠዉ መንስዔ የለም።

በተጨማሪም ከተፈቀደው የሰው መጫን አቅም በላይ በሚጭኑ ማህበራትና አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ያገነኘው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ የመረጥንላችሁ ጨዋታ:
👇👇👇

https://www.betsket.com/ሳልዝበርግን-እና-ላዚዮን-የተመለከቱ-የጨ/
የስፔን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ!

በአውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ጣምራ አስተናጋጅነት እየተደረገ የነበረው የሴቶች ዓለም ዋንጫ በስፔን ብሔራዊ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ስፔን እንግሊዝን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን መሆን ሲችሉ የማሸነፊያውን ብቸኛ ግብ ኦልጋ አስቆጥራለች።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
💥💥ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሆነው በቀላሉ ከቤት ሆነው የሚሰሩበትን የሶሻል ሚድያ ማስታወቂና አሰራር ስልጠና እንዲሁም መሰረታዊ የኮምፒውተር ኘሮግራሚንግ በቤቶ ሆነው በ 2 ወር ብቻ የተፈላጊ ሙያ ባለቤት ይሁኑ!

- ስልጠናው ቨርቹዋል ስለሆነ በየትኛውም ቦታ ሆነው መማር ይችላሉ!

- ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ የስራ እድል እናመቻቻለን!

- ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፊኬት ያገኛሉ!

- ከተለያዩ ውጭ ሀገር መግዛት የሚችሉበት እንዲሁም የሶሻል ሚድያ ማስታወቂያ መስራት የሚችሉበት የራሳቹን የቨርቹዋል ማስተር ካርድ ያገኛሉ!

- የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ!

- የተለያዩ ኦላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

🎓 ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል!

ለተጨማሪ መረጃ 0954742475 ይደውሉ
ወይንም በቴሌግራም @Bekalu_gebremariam ያዋሩን
Forwarded from Setu
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
Forwarded from YeneTube
🌼 🎁የአዲስ አመት ገጸበረከት ከ ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር የ15% ቅናሽ  ጋር እና ከልዩ ልዩ ስጦታዎች ጋር ይዞላችሁ ከተፍ ብሏል 🌼🎁🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


  🌼🎁ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር ሀዋሳ 🌼🎁እጅግ ውብና ማራኪ የ2016  የፋሽን ጥግ  የሆኑ  የፈርኒቸር ውጤቶች አቅርበንሎታል 🤗
ስለሆነም ከወዲሁ ለበአሉ ከመቼውም ጊዜ  በላቀ ልዩ ዝግጅት አድርገን ለውድ ደንበኞቻችን እነሆ ብለናል  🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
 
   ከ ምናቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ፡-
🌼የሌዘር እና የጨርቅ ሶፋዎች

🌼 የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

 🌼 ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

🌼 የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

🌼የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

 🌼 ዘመናዊ ኪችኖች

🌼  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን፡፡
       
                ልዩነታችን
ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን ማደሳችን፣

ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኀላ  ከአነስተኛ የገንዘብ ጭማሪ ጋር በአዲስ እቃ መለወጣችን ከሌሎች ልዩ ያደርገናል

መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በማንኛውም በዓላት ወቅት 15% የዋጋ ቅናሽ የምናደርግ መሆናችን፣
አድራሻችን፡-ሀዋሳ ከአረብ ሰፈር ወደ እርሻ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከራስ ጤና ሆቴል ፊትለፊት ከንግድ ባንክ አንደኛ ህንጳ ለይ እንገኛለን

በስልክ ቁጥሮቻችን ፡
0924711168 /0912340763 ሀሎ ይበሉን

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገጳችንን ይጎብኙ    
: 👇👇👇👇
https://tttttt.me/tedyaberalanganofurniturehawassa
"በየመን ድንበር በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ዓረቢያ ጦር ተገድለዋል" - ሂዩውማን ራይትስ ዎች

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩውማን ራይትስ ዎች << በየመን ድንበር በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ዓረቢያ ጦር መገደላቸውን >> አጋልጧል።

መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ ኒውዮርክ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች ተከራከሪው ድርጅት ሂዩውማን ራይት ዎች ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የምርመራ ሪፖርት <<  የሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ሃይሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከየመን ለመሻገር ሲሞክሩ መገደላቸውን >> አስታውቋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ከምስክሮች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፣ በሳተላይት ምስልና በቪዲዮ የታገዘው ሪፖርት ይፋ ባደረገበት ወቅትም <<  ግድያው ሰፊና ስልታዊ መሆኑን >> አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ << የሳዑዲ ጦር፤ ድንበር ጠባቂዎችንና ምን አልባትም ሌሎች ልዩ ክፍሎችን ጨምሮ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመቶዎች ወይንም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውንና በህይወት የተረፉትንም ለእስር፣ ለእንግልት፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ኢ ሰብዓዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል >> ሲል ወንጅሏል።

ጉዳዩን አስመልክቶም የሳውዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የሳዑዲ የተለያዩ ተቋማት፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርና የሰብአዊ መብት ኮሚሽንን አስተያየት እንዲሰጡ ቢጠይቅም ምላሽ አለማግኘቱን ሂውማን ራይት ዎች ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
1👍1