YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ወደ አውሮፓ ማቅናታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ!

የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ከነሐሴ 13 ጀምሮ እስከ 19/2015 ድረስ ወደ አውሮፓ በማቅናት፤ ከኅብረቱ አገራት ጋር በኢትዮጵያ ወቅትዊ ጉዳዮችና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እንደሚመክሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በድረገጹ ባሰፈረው መረጃ፤ ማይክ ሀመር በስዊድን ስቶኮልም እና በቤልጂየም ብራስልስ በሚኖራቸው ቆይታ፤ በአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ተዎካዮች ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ አስታውቋል፡፡

በዚህም በቅድሚያ በስቶኮም ዓለም አቀፍ የውሃ ተቋም በተዘጋጀው የዓለም የውሃ ሳምንት መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን፤ በመድረኩ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እንደሚመክሩ ተመላክቷል።

እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛው በቤልጂየም ብራስልስ በሚኖራቸዉ ቆይታ፤ ከአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ተዎካዮች ጋር ተገናኝተው ኅብረቱ እና አሜሪካ በኢትዮጵያ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ሰላማዊ ሰዎችን በመጠበቅ ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አምባሳደሩ ከአዉሮፓ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር በጋራ በፕሪቶሪያ የተፈረመዉ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚደረግበት ሁኔታ፣ ፍትሕ እና ተጠያቂነትን በማስፈን ዙሪያም ከኢትዮጵያ አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ግማሽ ያህሉ መሬት በተፈጥሯዊና በሰው ሰራሽ ምክንያቶች የተጎዳ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ማለትም 54 ሚሊየን ሄክታር የሚሆነው መሬት ለምነቱ የተጎዳ እንደሆነ ጥናቶች አመላክተዋል ሲሉ የተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ ዶክተር አደፍርስ ወርቁ ናቸው፡፡

ለግጦሽ እና ለእርሻ የሚያገለግለው ይህ አፈር በበርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለምነቱን እንደሚያጣም ጠቁመዋል፡፡አስተባባሪው ይህን የተናገሩት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተዘጋጀው አዲስ ወግ የውይይት መድረክ ላይ ነው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በየዓመቱ 92 ሺ ሄክታር ደን እንደሚጨፈጨፍ ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ በአፈር መከላትና በአፈር መታጠብ በአንድ ዓመት ብቻ 4.3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደምታጣም ነው የተናገሩት፡፡ዘላቂ የመከላከል ስራዎች ካልተሰሩ በ20 ዓመት ውስጥ ይህ አሃዝ ወደ 228 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሊያድግ እንደሚችል በጥናቶች ተገምቷል ብለዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
በሲዳማ በሙስና ተሳትፈዋል የተባሉ 25 አመራሮችና ባለሞያዎች ታሠሩ!

የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት በሙስናና ብልሹ አሠራር ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን 25 አመራርና ባለሞያዎችን ይዞ አሠረ ፤ ክልሉ 10 ከፍተኛ አመራሮችንም ከኃላፊነት አነሳ፡፡የክልሉ መንግሥት ይህን ያስታወቀው ላለፉት ዐሥር ቀናት በሀዋሳ ከተማ ሲያከሄድ የቆየውን የ2015 ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ዛሬ ባጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡

በግምገማ መድረኩ ማብቂያ ላይ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ “መድረኩ በሲዳማ ክልል የልማት ሥራዎችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ አደናቃፊ ሁኔታዎችን በመታገል ህዝብን የሚጎዱ ተግባራትን አንጥሮ ለማውጣት ትግል የተካሄደበት ነው“ ብለዋል።

በግምገማው በሙስናና በብልሹ አሠራር ላይ ተሳትፈው የተገኙ 25 አመራሮችና ባለሙያዎች በህግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ሌሎች 10 ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ ከኃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ዝርፊያ ፈጽመዋል በተባሉ 97 ሰዎች ላይ ታሳታፊዎችን የመለየትና ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል፡፡

ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ሌብነትና ብልሹ አሠራር መታየቱንና ግምገማው እየተካሄደ ባለበት ወቅት ከተጠያቂነት ለማምለጥ መድረኩን አቋርጠው በመውጣት የሸሹ ሥለመኖራቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ መናገራቸውን የክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል ሥለተባሉት ዐሥሩ ከፍተኛ አመራር ማንነትም ሆነ የግምገማ መድረኩን አቋርጠው ሸሽተዋል ያሏቸው አመራር በሥም አልጠቀሱም፡፡ያም ሆኖ የሲዳማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ባለፈው ዓርብ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ከንቲባ ፀጋዬ በመድረኩ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን በመግለጫቸው የጠቀሱት አቶ አብረሃም ከንቲባው ባሳዩት የሥራ ድክመት ከኃላፊነታቸው እና ከፓርቲ አባልነት እንዲነሱና በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑን ተናግረው ነበር፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
👇👇👇

https://www.betsket.com/አርሴናል፣-ቶሪኖንና-ሁራካንን-የተመለከ/
👍1
ሶማሊያ ቲክቶክ እና ቴሌግራምን አገደች!

ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሶማሊያ ቲክቶክ እና ቴሌግራም የተባሉትን ማኅበራዊ ሚዲያዎችን እንዲሁም 1ኤክስቤት (1XBet) የተባለውን የስፖርት ውርርድ ገጽን እንዲዘጉ አዘዘች።በወጣቶች ዘንድ ሰፊ ተጠቃሚ የላቸው ቲክቶክ እና ቴሌግራም የአሸባሪዎች መረጃ ማስተላለፊያ ሆነዋል ብሏል የሶማሊያ መንግሥት።

መተግበሪያዎቹ “አሸባሪ ድርጅቶች እና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውለዋል” ብሏል የአገሪቱ መንግሥት ባወጣው መግለጫ።የሶማሊያ የኮሚዩኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ ያሉ የኢንተርኔት አግልግሎት አቅራቢዎች እስከ ሐሙስ ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም. ድረስ ትዕዛዙን ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ቲክቶክ እና ቴሌግራምን እንዲሁም የስፖርት ውርርድ ገጹን የመዝጋት ውሳኔ የተሰማው የሶማሊያ መንግሥት አልሸባብን ለማጥፋት ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ነው።የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በርካታ የሶማሊያ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኘውን ጸንፈኛውን እስላማዊ ቡድን አል-ሸባብን በአምስት ወራት ውስጥ አጠፋለሁ ብለው ነበር።

በቅርቡ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሹ ኢንተርኔት እና ማኅበራዊ ሚዲያን በተመለከተ በተካሄደ ኮንፈረንስ ላይ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እና ኢንተርኔት በአጠቃላይ በተለይ በወጣቱ ላይ “ሕይወት እስከ ማሳጣት” የሚደርስ ጉዳት እያደረሰ ነው የሚል ሃሳብ በስፋት ተንጸባርቆ ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል መንግስት በአስር ዞኖች እና አንድ የከተማ አስተዳደር ስር ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ አገደ!

የክልሉ መንግስት ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፈው፤ በአስሩ ዞኖች እና በደብረ ታቦር ከተማ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸው “ደረሰኞች እና ቼኮች በመዘረፋቸው” መሆኑን ገልጿል።የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ እገዳው ተግባራዊ እንዲደረግ፤ የክልሉ “የመንግስት ሀብት ለሚንቀሳቀስባቸው” ባንኮች ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ነሐሴ 9፤ 2015 በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁን የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አለምነህ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

እግዱ ከተጣለባቸው አስር ዞኖች መካከል፤ በስራቸው ያሉ ሁሉም መዋቅሮች ላይ  እርምጃው ተግባራዊ የሚደረግባቸው አራቱ ናቸው።የገንዘብ እንቅስቃሴ እገዳው ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚደረገው በምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንደሆነ በአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አደራጀው ካሴ ተጽፎ ለባንኮች የተሰራጨው ደብዳቤ ያመለክታል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በተመለከተችው በዚሁ የደብዳቤ ክፍል ላይ እገዳው ተግባራዊ የሚደረግበት ብቸኛ የከተማ አስተዳደር ደብረታቦር ነው። 

የክልሉ መንግስት እገዳ “በተመረጡ አካባቢዎቻቸው” ብቻ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው፤ የማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ ዞኖች እንዲሁም የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መሆናቸው በደብዳቤው ላይ ሰፍሯል። የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ይህንን ትዕዛዝ በዞኖች ላይ ከማስተላለፉ አራት ቀናት አስቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የሀገሪቱ ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ፤ የክልሉ መንግስት በሚያስተዳድራቸው የባንክ ሂሳቦች ስር ያለ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት መንገድ ላይ ገደብ ጥሎ ነበር።

በዚህ ገደብ መሰረት፤ የአማራ ክልል የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ እና የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሐሪ “በጋራ ፈርመው ትዕዛዝ ካልሰጡ በስተቀር” የክልሉን መስሪያ ቤቶች ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደማይቻል የብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። የብሔራዊ ባንክ ይህንን ገደብ ያስቀመጠው፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያስፈጽም የተቋቋመው ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ነው። 

ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ለብሔራዊ ባንክ ያቀረበው ጥያቄ፤ የአማራ ክልል መንግስት የባንክ ሂሳቦች “ላልተፈለገ ዓላማ ማስፈጸሚያ እንዳይውሉ እና እንዳይመዘበሩ የጥንቃቄ እርምጃ” እንዲወሰድ የሚያሳስብ ነበር። በዚህ ጥያቄ መሰረት ነሐሴ 5፤ 2015 የተላለፈው የብሔራዊ ባንክ ገደብ ተግባራዊ ሆኖ የቆየው ለአራት ቀናት ብቻ ነው። የብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በጻፈው ሌላ ደብዳቤ፤ ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ በቀረበ ጥያቄ ትዕዛዙ መሻሩን አስታውቋል። 

የገደቡ መነሳት የአማራ ክልል መንግስት የባንክ ሂሳቦች፤ በመደበኛው የአስተዳደር ስርዓት እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ በአማራ ክልል ያለው የገንዘብ ዝውውር ወደ መደበኛ ስርዓቱ እንዲመለስ የተደረገው፤ “የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ተረጋግቶ እየተመለሰ ስለሚገኝ” እንደሆነ በባለፈው ሳምንቱ ደብዳቤው ላይ ጠቅሷል። ሆኖም ይህ ገደብ በተነሳበት ዕለት፤ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለባንኮች ሌላ የእግድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በደብዳቤዉ የተላለፈው ይህ እግድ በአስር ዞኖች እና አንድ የከተማ አስተዳደር ስር ያሉ አካባቢዎችን የሚመለከት እንደሆነ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ በደብዳቤው ላይ ዘርዝሯል። “ወረዳዎች ላይ፣ ዞኖች ላይ፣ አሁን በክልሉ በተፈጠረው ጸጥታ ምክንያት አንዳንድ ችግሮች ስላሉ፣ ቼኮች ደረሰኞች የጠፉበት ሁኔታ ስላለ፤ እነሱ እስከሚጣሩ ድረስ ዞኖች የሰጡንን መረጃ መሰረት በማድረግ የባንክ አካውንቶቹ እንዲታገዱ [ተደርጓል]” ሲሉ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ቢሮው ይህንን እርምጃ የወሰደው “የመንግስት ሀብት ለብልሽት እንዳይዳረግ፣ እንዳይባክን በማሰብ” መሆኑን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ፤ ይህ እግድ የሚቆየው “ዝርፊያ ተፈጸመ” በተባለባቸው አካባቢዎች የሚደረገው ማጣራት እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንደሆነ አክለዋል። የማጣራት ስራው ተጠናቅቆ በአካባቢዎቹ የባንክ ሂሳቦች ውስጥ ያለው ገንዘብ እስከሚለቀቅ ድረስ ግን “የስራ ማንቀሳቀሻ እንቅስቃሴዎች የሚቆሙበት ሁኔታ ይፈጠራል” ሲሉ እግዱ ለጊዜው የሚያስከትለው ችግር እንደሚኖር ኃላፊው አምነዋል። 

እገዳው በመንግስት ስራ ላይ መስተጓጎል ሊፈጥር ቢችልም ፤ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ክፍያ ግን “እንደማይቋረጥ” አቶ ደሳለኝ ለዜና ወኪሉ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ተመልክቷል። በዚህ ረገድ ችግር የማይፈጠረው ፤ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ “በአካውንታቸው [በቀጥታ] የሚገባ” በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል። 

የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ የገንዘብ እንቅስቃሴ እግድ መጣሉን ቢያረጋገጥም ትዕዛዙ ከተላለፈባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የምስራቅ ጎጃም ዞን፤ ይህ አይነቱ ክልከላ እስካሁን በይፋ እንዳልደረሰው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቋል። የገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ ስለተጣለ እግድ “መረጃ” እንዳልደረሳቸው እና እስካሁንም ስለጉዳዩ “አለመስማታቸውን” የሚናገሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው፤ “አሁን ስራ ስለጀመርን፤ የዞን አስተዳደር [ገንዘብ] እናንቀሳቅሳለን” ብለዋል። 

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
💥💥ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሆነው በቀላሉ ከቤት ሆነው የሚሰሩበትን የሶሻል ሚድያ ማስታወቂና አሰራር ስልጠና እንዲሁም መሰረታዊ የኮምፒውተር ኘሮግራሚንግ በቤቶ ሆነው በ 2 ወር ብቻ የተፈላጊ ሙያ ባለቤት ይሁኑ!

- ስልጠናው ቨርቹዋል ስለሆነ በየትኛውም ቦታ ሆነው መማር ይችላሉ!

- ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ የስራ እድል እናመቻቻለን!

- ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፊኬት ያገኛሉ!

- ከተለያዩ ውጭ ሀገር መግዛት የሚችሉበት እንዲሁም የሶሻል ሚድያ ማስታወቂያ መስራት የሚችሉበት የራሳቹን የቨርቹዋል ማስተር ካርድ ያገኛሉ!

- የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ!

- የተለያዩ ኦላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

🎓 ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል!

ለተጨማሪ መረጃ 0954742475 ይደውሉ
ወይንም በቴሌግራም @Bekalu_gebremariam ያዋሩን
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
የአማራ ክልል ምክር ቤት ለመጪው አርብ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!

የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት አዳራሽ በመጪው አርብ ነሐሴ 19/2015 የሚካሄድ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ለክልሉ ምክር ቤት አባላት ጥሪ የተላለፈው ትላንት ሰኞ ረፋድ መሆኑን ኹለት የምክር ቤቱ አባላት ነግረውኛል ሲል “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘግቧል።

የክልሉ ምክር ቤት አባላት ስብሰባው ከሚካሄድበት ዕለት አንድ ቀን በፊት በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ቢነገራቸውም፤ የስብሰባው አጀንዳ እንዳልተገለጸላቸው አመልክተዋል።

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ምክር ቤት አባል፤ “አስቸኳይ ስብሰባ ስለሆነ አጀንዳውን መናገር አልፈለጉም” ያሉ ሲሆን፤ ሆኖም “ወቅታዊ የክልሉ ጉዳዮች” የስብሰባው አጀንዳ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

በአርቡ የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ “በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ” ይደረጋል ተብሎ ከሚጠበቀው ውይይት በተጨማሪ፤ “ሹመት ሊኖር ይችላል” ሲሉ አንድ የምክር ቤት አባል የተናገሩ ሲሆን፤ ሌላ የክልሉ የምክር ቤት አባልም “በአንዳንድ አመራሮች ላይ ሹም ሽር የመደረግ ዕድል አለ” ሲሉ ግምታቸውን ማስቀመጣቸውንም ዘገባው አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጉምቱው ጋዜጠኛ ያዕቆብ ወልደማርያም በ94 ዓመታቸው አረፉ!

አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም የኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና አዘጋጅና በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ለ56 ዓመታት ያለማቋረጥ በመሥራት የሚታወቁት ጉምቱ ጋዜጠኛ ሲሆኑ፣ በ94 ዓመታቸው ትናንት ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓም ከዘህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ያዕቆብ ከሄራልድ ከለቀቁ በኋላ በመነን መጽሔት፤ በቮይስ ኦፍ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ ሪፖርተር በኤዲተርነት የሠሩ ሲሆን በሚሠሩትም ሥራ ደስተኛ ነበሩ፡፡ በንጉሡ ዘመን ለ15 ዓመታት፤ በደርግ ዘመን ለ17 ዓመታት፤ ከዚያ በኋላ ላለፉት 24 ዓመታት በጠቅላላ ለ56 ዓመታት በሙያቸው አገልግለዋል፡፡ አቶ ያዕቆብ ከ1983ዓም በኋላ ዘሰን፤ ዘሪፖርተር፤ ፎከስ በተሰኙ የኅትመት ውጤቶች ላይ ሠርተዋል፡፡

አቶ ያዕቆብ የራሳቸውን ግለ ታሪክ በ1995 ዓም አሳትመዋል። አቶ ያዕቆብ ባለትዳርና የ ልጆች አባት ናቸው፡፡ ቀብራቸው ገገ ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አቀኑ ዘጠኝ ሰዓት እንደሚፈጸም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት ተሳትፎ አገደ!

የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሐምሌ 26 ቀን 2023 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ኒጀርን ከሁሉም እንቅስቃሴዎቹ እንዳትሳተፍ ማገዱን አስታወቀ፡፡ህብረቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች በምርጫ ስልጣን የያዙትን ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙምን ከእስር እንዲፈቱ እና ወደ ቤታቸው እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል።

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት÷ የምዕራብ አፍሪካ ህብረት (ኢኮዋስ) ለወታደራዊ ጣልቃገብነት ተጠባባቂ ሃይል ለማንቀሳቀስ ያሳለፈውን ውሳኔ መመልከቱንም ሬውተርስ ዘግቧል፡፡የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እንደዚህ አይነት ሃይል ማሰማራት ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና የደህንነት አንድምታ እንዲገመግም ጠይቋል።የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ዲሞክራሲን ወደነበረበት ለመመለስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ካልተሳካ ወታደሮቹን ወደ ኒጀር ለመላክ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የአፍሪካ ህብረት ሁሉም አባል ሀገራቱ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኒጀርን ወታደራዊ ኃይል ህጋዊ ሊያደርግ ከሚችል ማንኛውም እርምጃ እንዲቆጠቡ ጠይቋል፡፡ከአፍሪካ ውጭ የትኛውም ተዋናይም ሆነ ሀገር የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበለውም በአጽንኦት አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በሳዑዲ በድንበር ጠባቂዎች ተፈጽሟል ስለተባለው የኢትዮጵያዊያን ግድያ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገለጸ!

የኢትዮጵያ መንግሥት በሳዑዲ አረቢያና የመን ድንበር ላይ “በድንበር ጠባቂዎች ተፈጽሟል” የተባለውን የኢትዮጵያዊያን ግድያ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር ሲሞክሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ- የመን ድንበር ላይ “በጅምላ ተገድለዋል” በሚል ሂውማን ራይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት ላይ የተላለፈውን መረጃ በትኩረት እየተከታተልኩኝ ነው ብሏል፡፡

መንግሥት ከሳዑዲ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ጉዳዩን በአስቸኳይ በማጣራት እንደሚያሳውቅ የገለጸ ሲሆን፤ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስም አላስፈላጊ የሆኑ ግምቶችን ከማድረግ መቆጠብ እንደሚገባም አሳስቧል።ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረብያ መሰል አሰቃቂ ድርጊቶችን እንደሚያወግዙ የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ኹለቱ አገራትም የረዥም ጊዜ ጠንካራና ጥሩ የኹለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩውማን ራይትስ ዎች እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ወር ድረስ፤ የየመን ድንበርን ለመሻገር የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን ትናንት ነሐሴ 15/2015 ባወጣው የምርመራ ሪፖርት ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ድርጅቱ እማኞች “የሳዑዲ ወታደሮች ከባድ መሳሪያዎች በመጠቀም ድንበሩ ለማቋረጥ በሚሞክሩ ሰዎች ላይ ኹሉ ተኩስ እንደሚከፍቱና ጉዳት ደርሶባቸዉ ሕይወታቸዉ ያላለፈ ሰዎችንም እየፈለጉ ወደ ማጎሪያ ካምፕ እንደሚያስገቡ ነግረውኛል” ሲል ባወጣው ሪፖርት ላይ ገልጿል።ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቱ፤ ለእነዚህ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሕጻናት እና ሴቶች ሞት፣ የአካል ጉዳት እና ስቃይም የሳዑዲ ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርጓል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጸሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 16፤ 2015 በዋናው ቅጥር ግቢ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር ስር ያሉ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ የተዘጋጀው አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር።የዚህን አዋጅ መውጣት ተከትሎም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ያስቻለው ደንብ፤ ከሶስት ሳምንት በፊት ሐምሌ 28፤ 2015 በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል።የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በዛሬው መግለጫቸው፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታውቀዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሚኒስትሩ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ምዕራብ ትግራይ ወደነበረበት ይመለሳል አሉ!

መከላከያ ሚንስትር አብርሃም በላይ የምዕራብና ደቡባዊ ትግራይ አካባቢዎች በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት መሠረት "ወደነበሩበት ይመለሳሉ" በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የአሸንዳ በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው መሆኑ ታውቋል።

ዶ/ር አብርሃም በመልዕክታቸው ፣ ከግዛቶቹ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎች "በሕገ መንግሥታዊ አግባብ" ይስተናገዳሉ ብለዋል።

መንግሥት የምዕራብ እና ደቡባዊ ትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው ለመመለስ እንቅስቃሴዎች እያደረገ መኾኑን የጠቀሱት ሚንስትሩ ፣ በግዛቶቹ በጦርነቱ ወቅት በተቋቋሙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች ሕዝብ በሚመርጠው መዋቅሮች እንደሚተኩም አብርሃም ጠቁመዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa