YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከተለያዩ የመንግስት የስራ ኃፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፤ ከዚህ ቀደም የቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩትበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ነበር።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት መተኮስ ክልክል ነው - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየአካባቢው በሚከናወነው የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት ወቅት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይህንኑ የፀጥታ ስራ በአግባቡ ለመምራት እና ለመቆጣጠር ሲባል እንዲሁም አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በቡሄ በዓል የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት ወቅት ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ሕገ-መንግሥት በአብላጫ ድምጽ ጸደቀ!

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሔደ በሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግሥት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባኤ፤ የቀረበው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ሕገ-መንግስት ይዘት ለጉባኤው አባላት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ የጉባኤው አባላትም በቀረበው ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ ገንቢ አስተያየት በመስጠት እንዲጸድቅ ይሁንታን አግኝቷል።

በዚህም መሰረት የቀረበው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት በ 10 ተቃውሞ በ2 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል። በተጨማሪም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ለጉባኤ አባላቱ ቀርቦ ተዋውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ ምሽት የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
👇👇👇

https://www.betsket.com/ቫሌንሲያ፣-ኖቲንግሃም-ፎረስት፣-ቦካ-ጁኒ/
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩ የምክር ቤት አባላትን እንዳያገኙ መከልከላቸውን ጠበቆች ተናገሩ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ተከትሎ የታሰሩትን የፌደራል እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት እንዳያገኙ መከልከላቸውን ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ ተናገሩ።ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ እንዳሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገርን በፖሊስ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ፈቃድ አላገኙም።

ፖሊስ ያለ መከሰስ መብት ያላቸው ደንበኞቻቸውን በሕገ ወጥ መንገድ እንዳሰራቸው በመጥቀስም ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ነሐሴ 02/ 2015 ዓ.ም. ጠበቆቻቸው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አካልን ነጻ የማውጣት ክስ መስርተው ጉዳዩን እየተከታተሉ ይገኛሉ።ከፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሙሊሳ አብዲሳ ጋር መወያያታቸውን እና አቶ ክርስቲያንን ማግኘት እንዲችሉ መጠየቃቸውን የሚናገሩት ጠበቃ ሰለሞን፣ “በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሰሩ ስለሆነ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጠበቃም እንዳያገኙ የሚከለክል ስለሆነ ማግኘት አትችሉም፤ ነገር ግን ደኅንነቱን በተመለከተ አረጋግጥላችኋለሁ” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

“ቤተሰቦቹን ስንጠይቅም ‘በሩቁ እናየዋለን። ምን እንደሆነ አላወቅንም’ ነው የሚሉን፤ እንደ ጠበቃ ግን ሁለቱም የምክር ቤት አባላት በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አናውቅም። አላየናቸውም፤ አላገኘናቸውም” ብለዋል።ጠበቃ ሰለሞን ጨምረውም ደንበኞቻቸው እስካሁን ቃል ስለመስጠት አለመስጠታቸውም ሆነ በምን ተጠርጠረው እንደተያዙ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአቶ ክርስቲያን ታደለ ቤተሰብ ወ/ሮ በዛብሽወርቅ ካሳ፣ አቶ ክርስቲያንን በቀን አንድ ጊዜ እንዲያዩት እንደተፈቀደላቸው እና ምግብ አቀብለው እንደሚመለሱ ገልጸው፣ ነገር ግን ቀርበን መነጋገር ስላልተፈቀደልን ስለሚገኝበት የጤና ሁኔታ ማወቅ አልቻልንም” ብለዋል።“በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተደበደበ፣ ታመመ የሚሉ ብዙ መረጃዎችን የሚሰሙ ሰዎች ይደውሉልናል። እኛም አይተነው ከመጣን በኋላ መልሰን እስከምናገኘው ድረስ ‘ምን ሆኖ ይሆን?’ እያልን ጊዜውን በጭንቀት ነው የምናሳልፈው። የደረሰበት የጤና እክል ካለም ቀርበን ለመጠየቅ አልቻልንም። አልተፈቀደልንም” ሲሉም ቤተሰቡ ስጋት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ አርብ፣ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው መግለጻቸው ይታወሳል።በወቅቱ “ሕጋዊ ሰው ነኝ፣ ለምንድን ነው የምትፈልጉኝ?” ብሎ ሲጠይቁ ከፖሊሶቹ መካከል አንደኛው “በቦክስ ደበደበው” ብለዋል በወቅቱ እዚያው የነበሩት የምክር ቤት አባሉ የቤተሰብ አባል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
መርማሪዎችና ጋዜጠኞች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ ተጠየቀ!

አማራ ክልል ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተጣለ ወዲህ ተፈፅመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን መርመር እንዲቻል ባለሥልጣናቱ ለገለልተኛ መርማሪዎችና ለመገናኛ ብዙኃን ያልተገደበ ፍቃድ በአፋጣኝ እንዲሰጡ ዓለምአቀፉ የመብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ክልሉ ውስጥ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ኃይልና በታጠቁ የፋኖ ሚሊሽያ መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ መሃል “ብርቱ” ያላቸው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየደረሱት መሆኑን ቡድኑ ዛሬ፤ ዓርብ ባወጣውና ዌብሳይቱ ላይ ባሠፈረው ፅሁፍ አስታውቋል።

በክልሉ ውስጥ በዚህ ሣምንት የአየር ድብደባ መፈፀሙንና ብዙ ሲቪሎች መገደላቸውን፤ ፍኖተ ሰላም፣ ባህር ዳርና ሸዋ ሮቢት ውስጥ መደዳ ግድያ መፈጸሙንና የሰፋ ጉዳት መድረሱን መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ያመለከተው አምነስቲ ኢንተርናሽናል “ሁኔታው ምርመራ ሊደረግበት የሚገባ ነው” ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስተያየት የሰጡት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ታይገሪ ቻጉታ "አማራ ክልል ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን የሚናገሩ አቤቱታዎችን ተከትሎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ባለሙያዎች ኮሚሽንና ሌሎችም ገለልተኛ መርማሪዎች፣ እንዲሁም ነፃ መገናኛ ብዙኃን በጥልቀት መመርመር እንዲችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተገደበ ፍቃድ መስጠት አለበት" ማለታቸውን የቡድኑ ፅሁፍ ጠቁሟል።ዳይሬክተሩ አክለውም "መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎቹ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር እና መጠበቅ አለባቸው" ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስተያየት የሰጡት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ታይገሪ ቻጉታ "አማራ ክልል ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን የሚናገሩ አቤቱታዎችን ተከትሎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ባለሙያዎች ኮሚሽንና ሌሎችም ገለልተኛ መርማሪዎች፣ እንዲሁም ነፃ መገናኛ ብዙኃን በጥልቀት መመርመር እንዲችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተገደበ ፍቃድ መስጠት አለበት" ማለታቸውን የቡድኑ ፅሁፍ ጠቁሟል።

ዳይሬክተሩ አክለውም "መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎቹ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር እና መጠበቅ አለባቸው" ብለዋል።ባለፈው ሃምሌ 28/2015 ዓ.ም. የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመንግሥቱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ አቅም የሚሰጠው እንደሆነ የጠቆሙት ቻጉታ "አሁን ጊዜው ዓለምአቀፍና አህጉራዊ አካላት በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ክትትል የሚያላሉበት አይደለም” ማለታቸውን የአምነስቲ ፅሁፍ አመልክቷል።

ባለፈው ሣምንት ማክሰኞ፤ ነሃሴ 2 በፓርላማው የፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግሥት ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመያዝ፣ የሰዓት እላፊ ገደብ የመጣል፣ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብትንና የመሰብሰብ ነፃነትን የመገደብ ሰፊ ሥልጣን የሚሰጥ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተጨማሪም ክልሉን በሃገሪቱ የደኅንነት ጉዳዮች ኃላፊ በሚመራው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጥታ ተጠሪ በሚያደርገው የአስቸኳይ ጊዜው ማዘዣ ማዕከል ሥር እንዲውል የሚያደርግ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውሷል።

ለዚህ የዛሬ የአምነስቲ መልዕክት የኢትዮጵያን መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደርነው ተደጋጋሚ ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። ይሁን እንጂ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ባለፈው ሣምንት ዐርብ በሰጡት መግለጫ “መንግሥት ማንኛውንም ጥቃት መከላከል የሚያስችል ኃይል አስታውቀው “የአማራ ክልል ግጭት በሰላም እንዲፈታ ከተፈለገ ግን ‘ፅንፈኛና ዘራፊ’ -- ያሉት አካል -- “ትጥቅ ፈትቶ ወደተዘጋጁለት ካምፖች መግባት ይኖርበታል” ማለታቸው ተዘግቧል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
💥💥ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሆነው በቀላሉ ከቤት ሆነው የሚሰሩበትን የሶሻል ሚድያ ማስታወቂና አሰራር ስልጠና እንዲሁም መሰረታዊ የኮምፒውተር ኘሮግራሚንግ በቤቶ ሆነው በ 2 ወር ብቻ የተፈላጊ ሙያ ባለቤት ይሁኑ!

- ስልጠናው ቨርቹዋል ስለሆነ በየትኛውም ቦታ ሆነው መማር ይችላሉ!

- ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ የስራ እድል እናመቻቻለን!

- ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፊኬት ያገኛሉ!

- ከተለያዩ ውጭ ሀገር መግዛት የሚችሉበት እንዲሁም የሶሻል ሚድያ ማስታወቂያ መስራት የሚችሉበት የራሳቹን የቨርቹዋል ማስተር ካርድ ያገኛሉ!

- የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ!

- የተለያዩ ኦላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

🎓 ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል!

ለተጨማሪ መረጃ 0954742475 ይደውሉ
ወይንም በቴሌግራም @Bekalu_gebremariam ያዋሩን
Forwarded from Setu
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
Forwarded from YeneTube
🌼 🎁የአዲስ አመት ገጸበረከት ከ ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር የ15% ቅናሽ  ጋር እና ከልዩ ልዩ ስጦታዎች ጋር ይዞላችሁ ከተፍ ብሏል 🌼🎁🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


  🌼🎁ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር ሀዋሳ 🌼🎁እጅግ ውብና ማራኪ የ2016  የፋሽን ጥግ  የሆኑ  የፈርኒቸር ውጤቶች አቅርበንሎታል 🤗
ስለሆነም ከወዲሁ ለበአሉ ከመቼውም ጊዜ  በላቀ ልዩ ዝግጅት አድርገን ለውድ ደንበኞቻችን እነሆ ብለናል  🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
 
   ከ ምናቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ፡-
🌼የሌዘር እና የጨርቅ ሶፋዎች

🌼 የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

 🌼 ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

🌼 የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

🌼የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

 🌼 ዘመናዊ ኪችኖች

🌼  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን፡፡
       
                ልዩነታችን
ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን ማደሳችን፣

ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኀላ  ከአነስተኛ የገንዘብ ጭማሪ ጋር በአዲስ እቃ መለወጣችን ከሌሎች ልዩ ያደርገናል

መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በማንኛውም በዓላት ወቅት 15% የዋጋ ቅናሽ የምናደርግ መሆናችን፣
አድራሻችን፡-ሀዋሳ ከአረብ ሰፈር ወደ እርሻ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከራስ ጤና ሆቴል ፊትለፊት ከንግድ ባንክ አንደኛ ህንጳ ለይ እንገኛለን

በስልክ ቁጥሮቻችን ፡
0924711168 /0912340763 ሀሎ ይበሉን

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገጳችንን ይጎብኙ    
: 👇👇👇👇
https://tttttt.me/tedyaberalanganofurniturehawassa
👍2
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በኒጀር ላይ ጣልቃ ሊገቡ የሚችሉበትን "ቀነ ገደብ" አስቀመጡ!

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዋና ጥምረት የሆነው ኢኮዋስ ዲሞክራሲያዊ ስርአትን ለመመለስ በኒጀር ላይ ወታደራዊ ጣልቃገብነት ሊያካሂዱ የሚችሉበትን ሚስጥራዊ "ቀነገደብ" ማስቀመጣቸውን ተናገሩ።

ኢኮዋስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ውጤት አልባ የሚሆኑ ከሆነ ስልጣን ከተቆጣጠረው ጁንታ ጋር ማለቂያ የሌለው ንግግር አያደርግም ብሏል።

ይህ አቋም ይፋ የሆነው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ ኃላፊዎች በጋና የሁለት ቀን ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ነው።

ቀደም ሲል ኢኮዋስ የኒጀር ዱንታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ፕሬዝደንት ባዙምን ወደ ቦታቸው እንዲመልስ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
ሩሲያ ኒዩክሌር መታጠቋ ከደህንነት ስጋት ጠብቋታል - ላቭሮቭ

ሩሲያ የኒዩክሌር የጦር መሳሪያ መታጠቋ ከየትኛው የውጭ ሃይል የደህንነት ስጋት እየጠበቃት ነው አሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ።ሚኒስትሩ “ኢንተርናሽናል አፌርስ” ከተሰኘው የሀገሪቱ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ሞስኮ ለምዕራባውያን የኒዩክሌር ጦርነት አደጋን ማስታወሷን ቀጥላለች ብለዋል።

“በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ለተደቀነባት የውጭ ሃይሎች የደህንነት ስጋት ምላሽ መስጠት የምንችለው በኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

የሩሲያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭም ባለፈው ወር ዩክሬን የጀመረችው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ስኬታማ የሚሆን ከሆነ ሩሲያ የኒዩክሌር መሳሪያዎቿን ልትጠቀም ትችላለች ማለታቸው ይታወሳል።

የኬቭ መልሶ ማጥቃት በተፈለገው ፍጥነት መሄድ ባይችልም ምዕራባውያን የሚያደርጉት የመሳሪያ ድጋፍ ግን ቀጥሏል።ይህ የመሳሪያ ድጋፍ መቀጠል አሜሪካ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በመጨረሻም ኒዩክሌር ከታጠቀችው ሩሲያ ጋር በቀጥታ ፍልሚያ ውስጥ እንደሚከታቸው ነው ላቭሮቭ የተናገሩት።

ይህን የኒዩክሌር ጦርነት ለማስቀረትም ሊደርስ የሚችለውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ ለምዕራባውያኑ ደጋግመን እየነገርናቸው ነው ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ታክቲካል የኒዩክሌር መሳሪያ እጠቀማለሁ በሚለው ዛቻዋ “የእውነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

@Yenetube @Fikerassefa