YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
1
በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ጊዜያዊ አስተዳደሩ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ!

በትግራይ ክልል የተከሠተው የአንበጣ መንጋ፣ በ17 ወረዳዎች እንደተዛመተ፣ የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ገልጿል። እስከ አሁን መንጋው፣ በአምስት ወረዳዎች ውስጥ ጉዳት እንዳደረሰም፣ ቢሮው አስታውቋል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ ዘንድሮ፣ በክልሉ የተዛመተው የአንበጣ መንጋ፣ በቅርብ ጊዜያት ከታዩ ወረራዎች፣ የከፋ እንደኾነ፣ ሰሞኑን ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ (OCHA)፣ በክልሉ የተዛመተው የአንበጣ መንጋ፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ የክልሉ አርሶ አደሮችን ሕይወት አደጋ ላይ እንደጣለ አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በታንዛንያ የታሰሩ አምስት ሺሕ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ!

በታንዛኒያ እስር ቤቶች የሚገኙትን አምስት ሺሕ ዜጎችን በተመለከተ በኹለቱ አገራት መካከል ሲካሄድ የቆየው ውይይት በመጠናቀቁ እስረኞቹን ወደ አገራቸው ለማጓጓዝ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በታንዛኒያ ከሕገ ወጥ ፍልሰት ምክንያት እስከ ሦስት ዓመት የተፈረደባቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው የተጠቀሰ ሲሆን፤ የጦርነት ቀጠና በሆነችው የመን ውስጥም በአስከፊ ሁኔታ እና ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ተጠቁሟል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሳውዲና አረብ አገራትም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ በርከት ያሉ ዜጎች መኖራቸውን በማንሳት፤ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ በኬንያ፣ ዚምባቡዊ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክ ተይዘው እስር ቤት የገቡ መኖራቸውን ገልጿል።

በየዓመቱ ከ150 ሺሕ እስከ 200 ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን፣ ወደተለያዩ አገራት በሕገ ወጥ መንገድ እንደሚሰደዱ የጠቀሰው ተቋሙ፤ በጉዟቸውም እስር እና የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው አመላክቷል።ከደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ ከጉራጌ፣ ወላይታ፣ ስልጤ፣ ከንባታ እና ሀድያ ዞኖች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለስደት እንደሚዳረጉ ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት ከሳውዲ አረቢያ 133 ሺሕ ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጊያለሁ ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፤ ከታንዛኒያ በተጨማሪ በሌሎች አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉትንም ለማስመለስ ተመሳሳይ ጥረት እየተደረገ ነው ማለቱን የአሜሪካ ድምጽ ዘግባል።በርካታ ኢትዮጵያውያኑ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሌሎች አገራት ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት በአውሬ፣ በድንበር ጠባቂዎችና በወንበዴዎች ጥቃት እንዲሁም በረሃብና በውሃ ጥም ለሞትና ለአካል ጉዳት እንደሚዳረጉም ነው የተገለጸው።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
እስራኤል በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣዉን የዉስጥ ግጭት በመንተራስ ቤተእስራኤላውያን የምታሶጣበትን የኢምግሬሽን ፖሊሲዋን ልትገመግም ነዉ ተባለ!

እስራኤል በኢትዮጵያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያንን የምታጓጉዝበትን ፖሊሲ ልትገመግም እንደሆነ ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል። ሀገሪቱ ለዚህ እንደምክንያት ያስቀመጠችዉ ደግሞ በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣዉን የዉስጥ ግጭት መበራከት ነዉ።

ባሳለፍነዉ ሳምንት በእስራኤል የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በእየሩሳሌም ከተማ በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በአፋጣኝ ከግጭት ቀጠናዎች እንዲወጡ እና ወደ ሀገሪቱ እንዲጓጓዙ በመጠየቅ ሰልፍ ማድረጋቸዉን ብስራት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል። ሰልፈኞቹን እንዲበተኑ በተደረገ ጥረትም ከሀገሪቱ ፖሊሶች ግጭት ዉስጥ መግባታቸዉ አይዘነጋም።

ከዚህ ሰልፍ በኋላም የኢሚግሬሽን እና ስደተኛ ተቀባይ ሚኒስትሩ ኦፊር ሶፈር ፤ በሀገሪቱ የስደተኞች ፖሊሲ ላይ የግምገማ ሂደቱን የሚከታተሉ ባለሙያ መመደባቸዉ ተሰምቷል። እስራኤል በቅርቡ 204 ቤተ እስራኤላውያን እና ዜጎቿን ከጎንደር እና ግጭት ከነበረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ማስወጣቷ ይታወሳል።

ሚኒስትሩ ለዚህ ዉሳኔ የበቁት ፤ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡትን የቤተእስራኤላውያን ቁጥር ለመጨመር ከሚሰሩ ማህበረሰብ እንቂዎች ጋር ከተቃዉሞ ሰልፉ በኋላ ካደረጉት ንግግር በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።

✍️ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ ምሽት የመረጥንላችሁ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች:

👇👇👇

https://www.betsket.com/የአውሮፓ-ኮንፈረንስ-ሊግ-ቅድመ-ማጣሪያ-ጨ/
የጎንደር ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል!

በጎንደር ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ዙሪያ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊና የጎንደር ቀጣና ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጋራ ውይይቱ ዓላማ በጋራ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለመሻት መሆኑን ገልጸዋል።

(ኢ.ፕ.ድ)
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ተነስተው “በህግ እንዲጠየቁ” በሲዳማ ክልል ውሳኔ ተላለፈ!

ላለፉት ሶስት ዓመታት ገደማ የሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጸጋዩ ቱኬ፤ በ“ብልሹ አሰራር” እና “አፈጻጸም ድክመት” ተገምግመው ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የሲዳማ ክልል ምንጮች ገለጹ። አቶ ጸጋዬ ከኃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ትላንት ረቡዕ ነሐሴ 10፤ 2015 ከተደረገ ግምገማ በኋላ መሆኑን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

በሲዳማ ክልል ደረጃ ያሉ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም እየተገመገሙበት ያለው መድረክ መካሄድ የጀመረው ካለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ነሐሴ 7፤ 2015 ነው። በዚህ መድረክ ላይ የተሳተፉ አንድ ምንጭ፤ ከሀዋሳው ከንቲባ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉ አመራሮች ላይ ግምገማ መደረጉን አመልክተዋል። ከእሁድ ጀምሮ የነበሩትን ግምገማዎች በአካል ተገኝተው የተሳተፉት አቶ ጸጋዬ፤ እርሳቸውን በሚመልከተው የትላንት ከሰዓቱ ግምገማ ግን አለመገኘታቸውን እኚሁ ምንጭ አክለዋል።

በትላንቱ ግምገማ ላይ አቶ ጸጋዬ “ከፍተኛ ሙስና ውስጥ መግባታቸውን” የሚያመለክቱ፣ “በሰነዶች የተረጋገጡ” መረጃዎችን መቅረባቸውን በመድረኩ የተሳተፉ ሁለት የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ተናግረዋል። በዚሁ ግምገማ “ከፍተኛ ተመራጭ የነበረችው የሀዋሳ ከተማ ወደ ኋላ መሄዷ” መነሳቱን የጠቆሙት ምንጮች፤ የከተማዋ ከንቲባ “የአቅም ውስንነት ጭምር አለባቸው” መባሉን ጠቅሰዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ዳሸን ባንክ ከማስተርካድ ጋር በመተባበር ከተለመደው በስም ከሚታተም የፕላስቲክ ካርድ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነ አለም አቀፍ ቅድመ ክፍያ ካርድ፣ ቨርቹዋል ካርድን ወደ ስራ አስገባ፡፡

ካርዱ ደንበኞች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ገንዘባቸውን ያለምንም ስጋት መጠቀም የሚችሉበት አማራጭ መሆኑን የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ አመልክተዋል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ከንቲባው ከስራቸው ተሰናብቷል የተባለው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲሉ ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ!

ሀዋሳ ከተማን ላለፉት ሶስት ዓመታት በከንቲባነት ያገለገሉት አቶ ፀጋዬ ቱኬ በብልሹ አሰራር ምክንያት ከስራቸው ተሰናብተዋል መባሉ ሀሰት ነው ሲል የከተማ አስታዳደሩ ፕሬስ ሴክረተሪ ገልጿል።

ሙሉ መግለጫ "ብልሹ አሰራር በመቃወማቸውና በአፈፃፀም በመብለጥ በተደናገጡ አመራሮች ሴራ በሌሉበት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በሚል መረጃው በአስቸኳይ ይስተካከል! ከእናንተ ሚዲያ አይጠበቅም።

ላለፉት ሦስት 3  ዓመታት ገደማ የሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት ረ/ፕሮ ጸጋዬ ቱኬ፤ የበላይ አመራሩን የሌብነት ቅሌት እና ጥልቅ መረጃ በመያዛቸው እና ሌብነትን እፀየፋለሁ፣ ለህልውናዬ እገዛለሁ በማለታቸው፣

እንዲሁም ከክልሉ አመራር በስራ በትጋትና በውጤት በመብለጣቸው በተቀነባበረ ሴራ፣ በህገ-ወጥ አሰራር የግምገማ መስመርን በጣሰ መልኩ፣ አመራሩን በእጅ አንሱልን ልምምጥና ቅንብር   የመንግስት አካሄድ ባዋረደ መልኩ፣ ለወሬ አመሻሽ ሚዲያን በመጋበዝ በተደረገው የማንጫጫት ግምገማና  የውሸት ጩሄት ተነሱ ተባለ፣ እንጅ ረዳት ፕሮ ፀጋዬ ቱኬ ሚዲያችሁ ሳያጣራ እንደገለፀው የተነሱ አይደለም።

በአፈፃፀም በመብለጥና ብልሹ አሰራርን አልመግብም በማለታቸው ብቻ ሲመቱ የከረሙና በሌሉበት የተወሰነባቸው ምሁር መሪ ናቸው። ይስተካከል። እንደተለመደው ከብዙ ጎኖች መረጃ ውሰዱ። ከግለሰቦች ተከፋይ እየወሰዳችሁ። የከተማም ሆነ የአመራር ገፅታ እንደ ግምገማ እንዲበላሽ አታድርጉ።"

@YeneTube @FikerAssefa
👍21
🌼 🎁የአዲስ አመት ገጸበረከት ከ ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር የ15% ቅናሽ  ጋር እና ከልዩ ልዩ ስጦታዎች ጋር ይዞላችሁ ከተፍ ብሏል 🌼🎁🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


  🌼🎁ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር ሀዋሳ 🌼🎁እጅግ ውብና ማራኪ የ2016  የፋሽን ጥግ  የሆኑ  የፈርኒቸር ውጤቶች አቅርበንሎታል 🤗
ስለሆነም ከወዲሁ ለበአሉ ከመቼውም ጊዜ  በላቀ ልዩ ዝግጅት አድርገን ለውድ ደንበኞቻችን እነሆ ብለናል  🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
 
   ከ ምናቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ፡-
🌼የሌዘር እና የጨርቅ ሶፋዎች

🌼 የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

 🌼 ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

🌼 የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

🌼የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

 🌼 ዘመናዊ ኪችኖች

🌼  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን፡፡
       
                ልዩነታችን
ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን ማደሳችን፣

ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኀላ  ከአነስተኛ የገንዘብ ጭማሪ ጋር በአዲስ እቃ መለወጣችን ከሌሎች ልዩ ያደርገናል

መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በማንኛውም በዓላት ወቅት 15% የዋጋ ቅናሽ የምናደርግ መሆናችን፣
አድራሻችን፡-ሀዋሳ ከአረብ ሰፈር ወደ እርሻ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከራስ ጤና ሆቴል ፊትለፊት ከንግድ ባንክ አንደኛ ህንጳ ለይ እንገኛለን

በስልክ ቁጥሮቻችን ፡
0924711168 /0912340763 ሀሎ ይበሉን

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገጳችንን ይጎብኙ    
: 👇👇👇👇
https://tttttt.me/tedyaberalanganofurniturehawassa
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው!

ነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልልን በአዲስ ለማደራጀት የተጠራ 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ መርኃ ግብር በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው ለቀጣይ ሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ እና የህገ መንግስት ማሻሻያ ረቂቅ ሰነዶች ቀርበው በምክር ቤት አባላት ውይይት ተደርጎባቸው የሚፀድቁ ይሆናሉ ተብሏል።

አዲሱን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን በመመስረት የተለያዩ ሹመቶች እንደሚከናወኑ ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምሥረታ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ተሰማምተው በአንድ ክልል እንዲደራጅ በማለት ድምጻቸውን በሰጡት መሠረት ነው የክልሉ ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ያለው።

በጉባኤው ላይም የዞኖቹና የልዩ ወረዳዎች አመራሮች ተገኝተዋል።በጉባኤው ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ መንግስት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ አዘጋጅቶ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በመሸጥ በከፍተኛ የማጭበረበር ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ!

ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ አዘጋጅቶ ለተለያዩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች  ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በመሸጥ በከፍተኛ የማጭበረበር ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው   አድራሻው የማይታወቅ ሰለሞን ሙሉ ከውን  በተባለ ግለሰብ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት በዚሁ መታወቂያ የተዘጋጀ የንግድ ፍቃድ  በማውጣት የማሽነሪዎች እና የመሣሪያዎች ኪራይና ሽያጭ የንግድ ዘርፍ ላይ ተመዝግቦ ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ ሳያደርግ የሸጠው እቃ ሳይኖር  ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ ለተለያዩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በ30 ቢሊዮን 152 ሚሊዮን 434 ሺህ 002 ብር ከ03 ሣንቲም በመሸጥ መሆኑ ታውቋል።

ግለሰቡ የማጭበርበር ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ለበርካታ ጊዜያት ተደብቆ እንደነበር ቢሆንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ  ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ኅብረተሰቡም ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ በአካል ቀርቦ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫና አማኑኤል ከተሞችና በየአካባቢያቸዉ ትናንት ዉጊያ ሲደረግ መዋሉን ነዋሪዎች አስታወቁ።

የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ባካባቢዉ የሸመቀዉ የፋኖ ታጣቂ ቡድን የገጠሙት ዉጊያ እየበረታና እየቀዘቀዘ ለረጅም ሠዓታት ሲደረግ ነበር።በዉጊያ በሰዉና በንብረት ላይ ሥለደረሰዉ ጉዳት ግን በዝርዝር የተነገረ ነገር የለም።እስካለፈዉ ስምንት ማብቂያ ድረስ ግጭት ሲደረግባቸዉ የነበሩት የአማራ ክልል ትላልቅ ከተሞች ሰሞኑን አንፃራዊ ሰላም ሠፍኖባቸዋል።

ከባሕር ዳር የደረሰ መረጃ እንዳመለከተዉ ባሕርዳር፣ ጎንደርና ደብረ ብርሐንን የመሰሉት ትላልቅ ከተሞች በመግስት የፀጥታ ኃይላት ቁጥጥር ስር ዉለዋል።የየከተማዉ ሕዝብ እንቅስቃሴም ወደ ወትሮዉ እየተመለሰ ነዉ።መደብሮች፣ የአገልግሎች መስጪያ ተቋማት፣ የትራንስፖርት አገልግሎትም ወደነበረበት እየተመለሰ ነዉ።ይሁንና ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በግጭቱ ምክንያት የትራንስፖርት የሰዎችና የሸቀጦች ዝዉዉርና አቅርቦት ተቋርጦ ሥለነበር በአብዛኛዉ አካባቢ በተለይ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ሲበዛ ጨምሯል።

የየከተሞቹ ነዋሪዎችም ከሥጋትና ዉጥረት አልተላቀቁም።በአማራ ክልል ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈዉ ሐምሌ ማብቂያ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ከየአካባቢዉ መረጃ ማግኘትና የተገኘዉን መረጃ ማረጋገጥ በጣም እየከበደ ነዉ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa