YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በትግራይ ክልል 16 ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መታየቱ እና በአዝርእትና የተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

የትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው መነሻው የአፋር ክልል በረሃዎች ያደረገ የበርሃ አንበጣ መንጋ በትግራይ ሶስት ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች መንሰራፋት የጀመረው ካለፈው ሐምሌ 20 ጀምሮ ሲሆን እስካሁን ባለው በ79 የክልሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚገኝ 35 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈኑ ተነግሯል።

የትግራይ ምስራቃዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች የበርሃ አምበጣ መንጋ እየታየባቸው መሆኑ የገለፁት በትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የአዝርእት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት አቶ ገብረህይወት ሃይለስላሴ ከሐምሌ መጨረሻ ወዲህ ባለው ግዜ የበርሃ አንበጣ መንጋው ሽፋን እየሰፋ እና አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ገልጸዋል።

የክልሉ ባለስልጣናት የበርሃ አንበጣ መንጋው ለመከላከል ህዝብ እያደረገው ካለ እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ የፌደራል መንግስቱም በኬሚካል አቅርቦት እና ሌሎች መንገዶች እየደገፈ መሆኑ የገለጹ ሲሆን፥ በቀጣይነት ግን የበርሃ አንበጣ መንጋው ከምንጩ የማድረቅ ስራ በሚፈለፈልበት አፋር ክልል ሊከናወን እንደሚገባ፣ ይህም ለፌደራሉ መንግስት እና ለFAO ማሳወቃቸውን በትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የአዝርእት ጥበቃ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ሲል ዶይቸ ቨለ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
🌼 🎁የአዲስ አመት ገጸበረከት ከ ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር የ15% ቅናሽ  ጋር እና ከልዩ ልዩ ስጦታዎች ጋር ይዞላችሁ ከተፍ ብሏል 🌼🎁🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


  🌼🎁ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር ሀዋሳ 🌼🎁እጅግ ውብና ማራኪ የ2016  የፋሽን ጥግ  የሆኑ  የፈርኒቸር ውጤቶች አቅርበንሎታል 🤗
ስለሆነም ከወዲሁ ለበአሉ ከመቼውም ጊዜ  በላቀ ልዩ ዝግጅት አድርገን ለውድ ደንበኞቻችን እነሆ ብለናል  🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
 
   ከ ምናቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ፡-
🌼የሌዘር እና የጨርቅ ሶፋዎች

🌼 የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

 🌼 ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

🌼 የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

🌼የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

 🌼 ዘመናዊ ኪችኖች

🌼  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን፡፡
       
                ልዩነታችን
ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን ማደሳችን፣

ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኀላ  ከአነስተኛ የገንዘብ ጭማሪ ጋር በአዲስ እቃ መለወጣችን ከሌሎች ልዩ ያደርገናል

መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በማንኛውም በዓላት ወቅት 15% የዋጋ ቅናሽ የምናደርግ መሆናችን፣
አድራሻችን፡-ሀዋሳ ከአረብ ሰፈር ወደ እርሻ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከራስ ጤና ሆቴል ፊትለፊት ከንግድ ባንክ አንደኛ ህንጳ ለይ እንገኛለን

በስልክ ቁጥሮቻችን ፡
0924711168 /0912340763 ሀሎ ይበሉን

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገጳችንን ይጎብኙ    
: 👇👇👇👇
https://tttttt.me/tedyaberalanganofurniturehawassa
የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከ3 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ የአዋሽ ወንዝ ከልክ በላይ መሙላቱን ተከትሎ፤ 657 አባወራዎች ወይም 3 ሺሕ 156 ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የምዕራብ ሸዋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ መምሪያ አደጋው የደረሰው ነሐሴ 05/2015 ሌሊት ላይ መሆኑን ገልጾ፤ ነዋሪው ከቤቱ ወጥቶ በመሸሹ በሰው ሕይወት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳላደረሰ አስታውቋል፡፡

ነዋሪው ነፍሱን ለማዳን ባደረገው ሽሽት ከቤት ባዶ እጁን በመውጣቱና፤ መኖሪያ ቤቱ በወንዙ መሙላት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ አሁን ላይ ከፍተኛ ለሆነ የምግብ እና መጠለያ ችግር መዳረጉ ተጠቅሷል፡፡የወረዳው አስተዳደር እና የምዕራብ ሸዋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ መምሪያ፤ ተጎጂዎቹን ለመርዳት ጥረት ቢያደርጉም ከችግሩ ስፋት አንጻር በበቂ አለመሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጎርፉ በ500 ሄክታር መሬት ላይ የለማን ሰብል ሙሉ ለሙሉ ያወደመ ሲሆን፤ በአርሶ አደሮች የወደፊት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀና እና መሬቱን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ እንደሆነም ተነግሯል፡፡አደጋው ከተከሰተ አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ አስቸኳይ ድጋፍ ለተፈናቃዮቹ ለማድረግ ቸልተኝነት ታይቷልም ነው የተባለው።

በተጨማሪም ሰዎች ከአደጋው ሸሽተው በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያሉ በመሆኑ፤ ለተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩም ተጠቁሟል።ለተጎጂዎቹ ምግብ፣ ልብስ፣ ጊዜያዊ መጠለያ፣ የንጽሕንና መጠበቂያ እና ሉሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶች የሚያስፈልግ በመሆኑም ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
‹‹በፍኖተ ሰላም ከተማ በንጹሐን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት አወግዛለሁ›› -እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነሐሴ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ ‹‹በፍኖተ ሰላም በንፁሃን ዜጎች ላይ ተፈፅሟል›› ያለውን ‹‹የድሮን (የሰው አልባ አውሮፕላን) ጥቃት እንደሚያወግዝ›› ተናግሯል፡፡

ፓርቲው ‹‹ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በእጅጉ እየተባበሰ መጥቷል›› ያለው ችግር ‹‹ በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት አስቸኳይ የአገር አድን ጥሪ አድርጎ ሁሉም ስለ ኢትዮጵያ ይመለከተኛል የሚል አካል ያለውን ጥያቄ ይዞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲነጋገር ጥሪ ማድረጉን ›› አስታውሷል፡፡

‹‹ በተለይም መንግሥት በአማራ ክልል እያደረገ የሚገኘው ዘመቻ አጥፊ፣ የግጭት አዙሪቱን የሚያባብስ እና ከቀደመው ስህተት ትምህርት ያልተወሰደበት ታሪካዊ ስህተት ›› ነው ሲል የወቀሰው ፓርቲው ‹‹ በአስቸኳይ ሁሉን አቀፍ ውይይት ተጀምሮ ከጦርነቱ በመለስ መፍትሄ እንዲበጅም ማሳሰቡንም ›› አክሏል፡፡

ይሁንና ‹‹ መንግሥት ለአገራችን ችግሮች በመፍትሔነት ያስቀመጥነውን ምክረ ሃሳብ በቀናነት ተቀብሎ ተግባራዊ በማድረግ አገርን ከከፋው ጥፋት ለመታደግ ከመሥራት ይልቅ ጆሮ ዳባ ልበስ ጉዞውንና የኃይል አማራጩን ተያይዞታል ›› ሲል ከስሷል፡፡

‹‹ እየተወሰደ ባለው የኃይል እርምጃ ንጹሃን ዜጎች ዕለት በዕለት እየረገፉ ነው ›› የሚለው ፓርቲው እሑድ ነሐሴ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በፍኖተ ሰላም ከተማ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል ›› ሲል ወንጅሏል፡፡ በዚህም ‹‹ ከ40 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ከመረጃ ምንጮች አረጋግጬያለሁ ›› ብሏል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው ባስቀመጠው ምክረ ሀሳብ ‹‹መንግስት በአማራ ክልል እያከናወነ የሚገኘውን ጦርነት በአስቸኳይ አቁሞ፤ ችግሮች በውይይት ማዕቀፍ ብቻ እንዲፈቱ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡ አክሎም ‹‹ ለውይይቱም አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲያመቻች በድጋሚ አጥብቄ እጠይቃለሁ›› ሲል መግለጫውን ቋጭቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኤምፔሳ (M-PESA) አገልግሎት ጀመረ!

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ከዛሬ ነሐሴ 10/2015 ጀምሮ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

ባለፉት ሦስት ወራት አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ከባንኮች ጋር የሚያስፈልጉትን የአጋርነት ስምምነቶች በመፈራረም እንዲሁም ወኪሎችንም በመመልመል እና በማሰልጠን ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ኹሉም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች የኤምፔሳ አገልግሎትን ለማግኘት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የአንድሮይድ (Android) እና የአይኦኤስ (IOS) ስልክ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም መስመራቸው *733# ላይ በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል።

የኤምፔሳ መተግበሪያ በ5 ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከፕሌይስቶር በማውረድ መጠቀም የሚችሉት ሲሆን፤ የአይኦኤስ (IOS) ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በቀጣዩ ሳምንታት በአፕስቶር እንደሚያገኙም ተገልጿል።

የሳፋሪኮም ደንበኞች ኤምፔሳን በመጠቀም በአገር ውስጥ ገንዘብ መላክ፣ ከአገር ውስጥና ውጪ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያዎችን መክፈል፣ የአየር ሰዓት መግዛት፣ ወደ ባንክ ሒሳቦቻቸው ገንዘብ ማስገባት ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ ወደ ኤምፔሳ መላክ መላክ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
የአዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ በዓል በመጪው ቅዳሜ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊካሄድ ነው!

-የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም ለሳምንቱ መጨረሻ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቷል

በህዝበ ውሳኔ የተመሰረተው 12ኛው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ይፋዊ የምስረታ በዓሉን በሳምንቱ መጨረሻ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊያደርግ ነው። የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም በተመሳሳይ ቀናት አስቸኳይ ጉባኤ መጥራቱን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በአርባ ምንጭ ከተማ የሚካሄደው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ምስረታ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኤደን ንጉሴ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከነገ በስቲያ አርብ ነሐሴ 12፤ 2015 በሚኖረው መርሃ ግብር፤ የአዲሱ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤውን እንደሚያደርግ ኃላፊዋ አስረድተዋል።

በዚሁ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የአዲሱን ክልል ህገ መንግስቱን ተወያይተው ያጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል። በማግስቱ ቅዳሜ ደግሞ 12ኛው የፌደሬሽኑ ክልል በይፋ የምስረታ ፕሮግራሙን እንደሚያካሄድ ኤደን ጠቁመዋል። የአዲሱ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የካቤኔ አባላትም በዚሁ ቀን ይሾማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልጸዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን አራት ወረዳዎችና ሦስት የከተማ አስተዳደር ነዋሪ ተወካዮች “ምሥራቅ ጉራጌ ዞን “ የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀርላቸው በሠላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡

አባላቱ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮችን ያካተተ የዞን መስተዳድር እንዲደራጅ ጠይቀዋል፡፡ ሠልፈኞቹ የያዟቸው መፈክሮችም እስካሁን ባለዉ ጉራጌ ዞን ሥር ከሚገኙ የአስተዳደር መዋቅሮች መካከል አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮች “ ምሥራቅ ጉራጌ ዞን “ የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀር የሚጠይቁ ናቸው፡፡

“የምሥራቅ ጉራጌ ዞን “ በሚል በአዲስ ዞን እንዲዋቀሩ ሠልፈኞቹ ጥያቄ ያቀረቡባቸው የመስቃን ፣ የምሥራቅ መስቃን ፣ የሶዶ ፣ የቡኢ ወረዳዎችና እንዲሁም የቡታጅራ ፣ የሶዶ እና የኢኒሴኖ ከተማ አስተዳደሮች ናቸው፡፡ ዶይቸ ቨለ እንደዘገበዉ ሠልፈኞቹ ከአራቱ ወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች የተወከሉ የማህበረሰብ ክፍሎች መሆናቸውን የሠልፈኖቹ ተወካዮች ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
1👍1
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

የዛሬ ምልከታችን:

👇👇

https://www.betsket.com/የቤትስኬት-ምልከታ/
ቴሌ ብርን በመምሰል በቴሌግራም አማካኝነት እየተፈፀመ የሚገኝ የማጭበርበር ድርጊት

(Via Ethiopia Check)

ከሰሞኑ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት የሆነውን ቴሌ ብርን መስሎ በመቅረብ እና የተለያዩ ሰዎችን በማናገር እየተፈፀመ የሚገኝ የማጭበርበር ድርጊት እንዳለ ኢትዮጵያ ቼክ መመልከት ችሏል።

ይህ የቴሌግራም ቻናል ቦት "Telebirr Online customer servive" የሚል ስም ያለው ሲሆን የቴሌ ብር አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ደረጃ ለማሳደግ (upgrade ለማድረግ) በሚል የስልክ እና የሚስጥር ቁጥር በመጠየቅ የሚሰራ የማጭበርበር ድርጊት እንደሆነ ማየት ችለናል።

"የቴሌ ብር ደንበኝነት ደረጃን (customer level) በኦንላይን ለማሳደግ በመጀመርያ ትክክለኛ የእርስዎ አካውንት እና ስልክ ቁጥር መሆኑን ማረጋገጥ ስላለብን ሙሉ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና የቴሌ ብር ይለፍ ቃል (PIN CODE) ይላኩልን። በመቀጠል ከጥሪ ማዕከላችን የምንልክሎትን ስድስት ዲጂት የማረጋገጫ ኮድ (verification code) ይልኩልናል፣ ይህን አገልግሎት ለማግኘት ቢያንስ 1 ሺህ ብር አካውንትዎ ላይ ሊኖር ይገባል" በማለት የማጭበርበር ድርጊት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ አንዳንድ ግለሰቦች ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ መገንዘብ እንደቻለው አንድ ሰው ስልክ ቁጥሩን እና የይለፍ ቃሉን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ከሰጠ የማረጋገጫ ቁጥሩ (verification code) እንዲመጣ ማድረግ ይቻላል። ይህን ከኢትዮ ቴሌኮም የሚመጣ የማረጋገጫ ቁጥር አሳልፎ መስጠት ደግሞ ለዘረፋ ያጋልጣል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ኢትዮ ቴሌኮምን ያነጋገረ ሲሆን የድርጅቱ ዋና የኮሚዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ይህ የቴሌግራም ቦት ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጠው "እኛ ብቸኛ የምንጠቀምበት ቦት "አርዲ/Ardi" የሚባል ሲሆን ይህም በተረጋገጠው የቴሌብር አካውንቶች ላይ ይገኛል" ብለዋል።

የማረጋገጫ ቁጥርን አሳልፎ መስጠት ለመጭበርበር ስለሚያጋልጥ ጥንቃቄ እናድርግ።

@YeneTube @FikerAssefa
ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት "በሰላማዊ መንገድ በንግግር" ለመፍታት ጥረት እያደረገ መኾኑን ተናግረዋል።

ደመቀ ይህን የተናገሩት፣ ትናንት ከፍትህ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ጋር በመኾን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ውስጥ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የውጭ አገራት ዲፕሎማቶች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። መንግሥት ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት የጀመረው ጥረት በተጨባጭ ምን እንደኾነ ግን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አልገለጠም። ፍትህ ሚንስትር ጌዲዮንም፣ መንግሥት በክልሉ ሕግና ሥርዓት ለማስከበርና ሰላማዊ ሰዎችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎችና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማወጅ ያስፈለገበትን ምክንያት ለዲፕሎማቶቹ አብራርተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
🌼 🎁የአዲስ አመት ገጸበረከት ከ ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር የ15% ቅናሽ  ጋር እና ከልዩ ልዩ ስጦታዎች ጋር ይዞላችሁ ከተፍ ብሏል 🌼🎁🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


  🌼🎁ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር ሀዋሳ 🌼🎁እጅግ ውብና ማራኪ የ2016  የፋሽን ጥግ  የሆኑ  የፈርኒቸር ውጤቶች አቅርበንሎታል 🤗
ስለሆነም ከወዲሁ ለበአሉ ከመቼውም ጊዜ  በላቀ ልዩ ዝግጅት አድርገን ለውድ ደንበኞቻችን እነሆ ብለናል  🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
 
   ከ ምናቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ፡-
🌼የሌዘር እና የጨርቅ ሶፋዎች

🌼 የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

 🌼 ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

🌼 የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

🌼የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

 🌼 ዘመናዊ ኪችኖች

🌼  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን፡፡
       
                ልዩነታችን
ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን ማደሳችን፣

ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኀላ  ከአነስተኛ የገንዘብ ጭማሪ ጋር በአዲስ እቃ መለወጣችን ከሌሎች ልዩ ያደርገናል

መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በማንኛውም በዓላት ወቅት 15% የዋጋ ቅናሽ የምናደርግ መሆናችን፣
አድራሻችን፡-ሀዋሳ ከአረብ ሰፈር ወደ እርሻ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከራስ ጤና ሆቴል ፊትለፊት ከንግድ ባንክ አንደኛ ህንጳ ለይ እንገኛለን

በስልክ ቁጥሮቻችን ፡
0924711168 /0912340763 ሀሎ ይበሉን

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገጳችንን ይጎብኙ    
: 👇👇👇👇
https://tttttt.me/tedyaberalanganofurniturehawassa
👍1