YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
🔥1
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
ያለርዳታ 10 ወራትን ያስቆጠሩ በትግራይ መጠለያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች በእጅጉ እንደተቸገሩ ገለጹ!

ላለፉት ዐሥር ወራት የርዳታ እህል እንዳልተሰጣቸው የገለጹ፣ በትግራይ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ በእጅጉ መቸገራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

ለደኅንነታቸው በመስጋት ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጭዎች፣ ከሥፍራው በስልክ እንደገለጹልን፣ በማይ ዓይኒ እና በዓዲ ሓሩሽ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ፣ 1ሺሕ700 ስደተኞች ይኖራሉ፡፡ ኾኖም፣ በመጠለያ ጣቢያዎቹ፣ መሠረታዊ አገልግሎት ባለመኖሩ፣ ለከባድ ችግር እንደተጋለጡ አስታውቀዋል፡፡ በሕክምና ዕጦት ምክንያት፣ በቅርቡ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም ገልጸዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ፣ ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር/UNHCR/ በበኩሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ፣ “ስደተኞቹ፣ በዚያ አካባቢ ኾነው አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁንም ወደ ቦታው መግባት አንችልም፤” በማለት ገልጿል፡፡

Via VoA
Photo: File
@YeneTube @FikerAssefa
የ1 ዓመት ህጻን ልጅ ሰርቃ በገንዘብ ለመደራደር የሞከረችው የቤት ሰራተኛ በእስራት ተቀጣች!

በሸገር ከተማ አስተዳደር  መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ህጻን በማገት ከፍተኛ ብር ሲጠይቁ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ  ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርምራ ክፍል ዋና ኃላፊ ኢንስፔክተር ብርሃኔ ወየሳ ተናግረዋል።

አንደኛ ተከሳሽ ኡርጌ በቀለ የተባለችው ግለሰብ በአንድ መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ስትሰራ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር እድሜ ያላትን ልጅ ለመጠበቅ ከተቀጠረችበት ቤት ልጅ ሰርቃ በገንዘብ ለመደራደር መሞከሯ ተገልጿል።ግለሰቧ በተቀጠረች በሁለተኛው እለት ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ አቡሽ ከተባለ ግብረአበሯ ጋር በመሆን ልጅ ሰርቃ በመውሰድ ለተባባሪዋ አስረክባዋለች።

ልጅቷን መታገቷን እና ገንዘብ ከፍለው ልጃቸውን መውሰድ እንደሚችሉ በማለት የህጻኗን ቤተሰቦች ያስፈራራሉ።ወላጆች  ጉዳዩን ወዲያውኑ  ወደ መልካ ኖኖ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ያመለክታሉ፡፡ ፖሊስም ባደረገው ክትትል ተከሳሽ ኡርጌ በቀለ  በቁጥጥር  ስር ማዋል ተችሏል።

ግለሰቧ በቁጥጥር  ስር ከዋለች በኀላ ህጻኗን ያገቱበትን ቦታ  ለፖሊስ በመጠቆሟ ህጻኗን ማግኘት ተችሏል።በተጨማሪ ተከሳሿ ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት የተለያዩ ጌጣጌጥ ፣ አልባሳት እና የሞባይል ስልክ ግምቱ ከ36 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት መስረቋ ተረጋግጧል።

ፖሊስ በተከሳሾች ላይ ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለሸገር ከተማ ዓቃቢህግ ጽ/ቤት በመላክ ክስ እንዲመሰረት አድርጎል።ክሱ የቀረበለት የሸገር ከተማ ከፍተኛ  ፍርድ ቤት ሁለቱን ተከሳሾች ጥፋተኛ በማለት በ12 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ኢንስፔክተር ብርሃኑ ወይሳ ጨምረው ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat]
@YeneTube @FikerAssefa
1
‹‹ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ሰብዓዊ ረድዔት ማቅረቤን በጊዜያዊነት ለማቆም ተገድጄያለሁ ›› - ሴቭ ዘ ቺልድርን

የሕፃናት አድን ድርጅት(ሴቭ ዘ ቺልድርን) የሚዲያ ኮሚኒኬሽንና አድቮኬሲ ክፍል ሃላፊ ሕይወት እምሻው በክልሉ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ‹‹ ተባብሶ በቀጠለው ግጭት ›› ምክንያት ‹‹ የሰብዓዊ ረድዔት አቅርቦቱን በጊዜያዊነት ለማቋም መገደዱን ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡

ድርጅቱ ‹‹ በክልሉ ለሚገኙ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ህፃናትና ሌሎች ዜጎች እርዳታ ለማድረስ ምቹ ሁኔታዎች እንዲኖር ›› በሚል ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ያወጣውን ጋዜጣዊ መግለጫ አስመልክቶ ከአሻም ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ሃላፊዋ ‹‹ በክልሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ከ580 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚገኙ ›› አመልክተዋል፡፡

‹‹ ለተፈናቃዮቹ የተለያዩ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ሲያቀርብ መቆየቱን ›› ገለፁት ሕይወት ‹‹ አሁን ላይ ግን በክልሉ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ በመተማ፣ በሰሜን ወሎ ባሉ ፕግራሞች እንዲሁም ከሰቆጣ ቢሮው ተነስቶ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሲቀርቡ የነበሩ የእርዳታ አይነቶች ለጊዜው ለማቆም መገደዱን ›› ነግረውናል፡፡

‹‹ ይህም በተለይ ከባለፈው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የተፈናቃይ ቁጥር ላለበትና የእለት ደራሽ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከባድ መሆኑን ›› ጠቁመዋል፡፡

ሀላፊዋ አክለውም ‹‹ በሁሉም ወገን ያሉ የግጭቱ ተሳታፊ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ በምንም ዓይነት መንገድ መቋረጥ ስለሌለበት ለዚህ መተባበር እንዲኖርባቸው ›› አመልክተው ‹‹ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ሰራተኞችንም ከአደጋ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው ›› ጠይቀዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ተቋርጦ የነበረው ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) መደበኛ በረራ ነገ እንደሚጀመር ተገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5/2015 እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

በዚህም መንገደኞች በአየር መንገዱ ድረ-ገጽ (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያዎቹ (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟቸው የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአማራ ክልል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ፤ ማክሰኞ ነሐሴ 2/2015 ባወጣው መግለጫ፤ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች፤ ለሦስት ተከተታይ ቀናት መሰረዛቸውን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ይህንንም ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ፤ ዛሬ ነሐሴ 4/2015 እንደሚጀምር በትናንትናው ዕለት አስታውቆ ነበር፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር በከተማዋ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እርምጃውን እየወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር በቅንጅት በመሰራትም ላይ ይገኛል።

ቢሮው እንደ ገለፀው፣ ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት አስተማሪ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጸው።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥቲ አስተዳደር ቢሮ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ መሆኑን ገልፆ ይህንን አስጸያፊ በሰውም በአምላክም ዘንድ የተጠላ ደርጊት በሚፈጽሙና በሚያስፈጽሙ የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቆማት ላይ ካለ አንዳች ርህራሄ ከህብረተሰቡ በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ ጋር በመተባበር እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በዚሁ መሰረት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ "አበባ ገስት ሐውስ" በሚባል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ከህብረተሰቡ ለሰላምና ፀጥታ ቢሮ በደረሰ ጥቆማ መሰረት  እርምጃ የወሰደ ሲሆን የተቋሙን ኃላፊ በከተማው ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል።

ከግብረሰዶም ፀያፍ ተግባር ጋር የተገናኘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ከዚህ በፊትም የተገለፀ ሲሆን አሁንም ህብረተሰቡ ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

በሚደርሰው ጥቆማ መሰረትም ቢሮው የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቁን ከከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍2
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
የተመድ የባለሙያዎች ቡድን መንግሥት በአማራ ክልል የሚወስደው እርምጃ ተመጣጣኝ እንዲሆን አሳሰበ!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ቡድን ዓለም አቀፍ ኮሚሽን በአማራ ክልል ከተጣለው አስቸኳይ ጊዜ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወስደው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተመጣጣኝ እንዲሆን አሳሰበ።

ኮሚሽኑ በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ በተለይ ደግሞ በአማራ ክልል እየተባባሰ ነው ያለው የፀጥታ መደፍረስ አሳስቦኛል ያለ ሲሆን፣ የመንግሥት ሕግ የማስከበር እርምጃ ተመጣጣኝ እንዲሆን ጠይቋል።

ኮሚሽኑ በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውሶ፣ ከዚህ ቀደም ተፈጻሚ ሆነው በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸሙ ነበር ብሏል።

በመሆኑ የባለሙያዎች ቡድኑ በሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀጽ 4 መሠረት መንግሥት ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያስፈጽም የሚወሰዱ አርምጃዎች የአስፈላጊነትን፣ የተመጣጣኝነትን እና አንድ ወገንን ለይቶ ያለማጥቃት መርሆን መከተል አለበት ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ቡድን በዚህ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ የሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እና ግጭት አቁመው ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሰሩ ጠይቋል።

ይህ የባለሙያዎች ቡድን የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ በአገሪቱ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በገለልተኛነት እንዲመረምር በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ኃላፊነት እንደተሰጠው ይታወሳል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa