የውጭ ምንዛሬ ክፍፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የብሄራዊ ባንክ ቦርድ ወሰነ።
በዚህም የውጭ ምንዛሬ ክፍፍሉ ቀደም ሲል ከነበረው 70/30 ወደ 50/50 እንዲስተካከል አድርጓል። በውሳኔው መሰረት ባንኮችለ ከውጭ ምንዛሬ ግኝታቸው 50 በመቶ ለብሄራዊ ባንክ 40 በመቶውን የውጭ ምነዛሬውን ላመነጨው አካል እንዲሁም ቀሪውን 10 በመቶ ለባንኮች እንዲከፋፈል ተወስኗል።ቦርዱ የዋጋ ግሽበትን ለመግታት በርካታ የገንዘብ እና የፊሲካል ውሰኔዎችን ማሳለፉን ነው የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የገለፁት።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

👍1
ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤታቸው እንደታሰሩ ገለጹ!
የዐማራ ክልል ልዩ ኀይል አደረጃጀት በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት፣ በዋና አዛዥነት ያገለገሉት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ባለቤታቸው ወሮ. መነን ኀይለ፣ ትላንት ምሽት፣ ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ ኀይሎች ተወስደው እንደታሰሩ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
በበነጋው ዛሬ፣ ወሮ. መነን ይገኙበታል ወደተባለው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ቢሔዱም ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ፣ ብርጋዴር ጀነራሉ ተናግረዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ፣ ትላንት በወቅታዊ ኹኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ በዐዲስ አበባ ከተማ፣ ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ጋራ በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች እንዳሉ አመልክቷል።

✅✅✅ "Do or Die..!" ✅✅✅
የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!
ቤት ...❓
መሬት...❓
መካዝን...❓
ኢንዳስትሪ...❓
ኢንቨስትመንት...❓
ሪል ስቴት ..❓
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..❓❓❓
አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው
..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..
መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!
+251937736408
https://tttttt.me/shger21
Inbox @FikreabAmanu
ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0

"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665

Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።
ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን። ለአሁን ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን የሴቶች እለም ዋንጫ ትንተና ይዘን አንድ ብለን ጀምረናል፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።
ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!
https://www.betsket.com/australia-w-vs-france-w-tips/

👍1🔥1
የዐማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ በአፋጣኝ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የትብብር ጥሪ አቀረበ!
በዐማራ ክልል ሰሞኑን በተስፋፋው ግጭት ሳቢያ፣ የ130ሺሕ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ሥርጭት መስተጓጎሉን የገለጸው የክልሉ ግብርና ቢሮ፣ በአፋጣኝ ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ ይቻል ዘንድ የትብብር ጥሪ አቀረበ፡፡
የግብርና ቢሮው ምክትል ሓላፊ አቶ አበጀ ስንሻው፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በመጪው 10 ቀናት ውስጥ፣ ወደ ክልሉ የገባው 130ሺሕ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ ወደ የአርሶ አደሩ ቀዬ ተጓጉዞ ካልደረሰ፣ በቀጣዩ ዓመት ረኀብ ሊከሠት ይችላል፡፡ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው፣ አቅርቦቱ እጅግ ዘግይቷል፤ ብለዋል።

የብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል የመሠረታዊ ኮማንዶ አባላት በማሥመረቅ ላይ ነው!
የብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል፤ የ41ኛ ዙር ዞብል ኮርስ የመሠረታዊ ኮማንዶ አባላትን በዛሬው ዕለት በማሥመረቅ ላይ ይገኛል፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተውበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል የተገነባውን ከአስር ሺሕ በላይ ሰው መያዝ የሚችል አንፊ ቲያትር መርቀው የከፈቱ ሲሆን፤ በማሠልጠኛ ማዕከሉ ችግኝ በመትከልም የአረንጓዴ መርሃ ግብር አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በመርሃ -ግብሩ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የ41ኛ ዙር ዞብል ኮርስ ተመራቂ መሠረታዊ ኮማንዶዎች ቀይ ቦኔት እንዲለብሱ ፈቅደዋል።
የ41ኛ ዙር መሠረታዊ ኮማንዶዎች በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን፤ በማሥከተል ተማራቂ መሠረታዊ ኮማንዶዎች በሠልፍ በክብር እንግዶች ፊት አልፈዋል። በተጨማሪም ሰልጣኞቹ ያገኙትን ክህሎት በትርኢት ለታዳሚያን አሳይተዋል።
ተመራቂ የኮማንዶ አባላቱ ለኮማንዶ ብቁ የሚያደርጋቸውን መሥፈርት አሟልተው ከመሠረታዊ ወታደር ማሠልጠኛ ማዕከላት የተመለመሉ ሲሆን፤ ለስድስት ወራት ፈታኝ የሆነውን የኮማንዶ ሥልጠና ተከታትለው በመመረቅ ላይ እንደሚገኙ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በቀጣዩ ሣምንት የአውሮፕላን ርጭት ይጀመራል!
የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በቀጣዩ ሣምንት በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት እንደሚጀመር ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡እስካሁን አንበጣው እንደሀገር ከፍተኛ ጉዳት አለማድረሱን የገለፀው ሚኒስቴሩ፥ በቀጣይም ጉዳት እንዳይደርስ እየተሠራ ነው ብሏል።በሚኒስቴሩ የእጽዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በላይነህ ንጉሴ የአንበጣ መንጋው ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ አለመግባቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ግብርና ሚኒስቴር ከክልሎቹ ጋር በመቀናጀት የአንበጣ መንጋ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ጉዳት እንዳያደርስ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።ሚኒስቴሩ ለክልሎች የአንበጣ መንጋ መከላከያ ኬሚካል፣ የኬሚካል መርጫ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የባለሙያዎች ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት።
ወቅቱ ለአንበጣ መራባት ምቹ መሆኑን እና ለሰውም ሆነ ለተሽከርካሪ በማይመች ተራራማ ቦታ ላይ እያረፈ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በቀጣይ ሣምንት የአውሮፕላን ርጭት ይጀመራል ነው ያሉት፡፡በ62 ሺህ 107 ሔክታር ላይ የበረሃ አንበጣ አሰሳ ተካሂዶ፥ በማደግ ላይ ያለ የበረሃ አንበጣ በትግራይ፣ አፋርና አማራ ክልሎች 12 ሺህ 653 ሔክታር መውረሩን አብራርተዋል።
ከዚህ ውስጥ 470 ሔክታር በባሕላዊ መንገድ መከላከል መቻሉን ነው ያስረዱት።ዘንድሮ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ካለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ የከፋ እንዳልሆነ የጠቀሱት አቶ በላይ÷ ባለፈው ዓመት በስድስት ክልሎችና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተከስቶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት በአማራ ክልል ብቻ እንዲገደብ፤ ጊዜውም ወደ አንድ ወር እንዲያጥር ኢሰመኮ ምክረ ሃሳብ አቀረበ!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተፈጻሚነት ጊዜ “ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት ላልበለጠ ጊዜ ብቻ” እንዲሆን እንዲያደርግ እና የተፈጻሚነት ወሰኑንም በአማራ ክልል ብቻ እንዲገድብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ። በአዋጁ ለአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ “የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖችን እና መዋቅሮችን መልሶ ለማቋቋም” የተሰጠውን ስልጣን ፓርላማው እንዲሰርዝም ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እነዚህን ጥያቄዎች ያቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ባለ 22 ገጽ የምክረ ሃሳብ ሰነድ ላይ ነው።ኢሰመኮ ይህንን ምክረ ሃሳብ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 6፤ 2015 ይፋ ያደረገው፤ የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ከነገ በስቲያ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሄድ መገለጹን ተከትሎ ነው።
ብሔራዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም፤ የሰብአዊ መብቶች ስጋቶች እና የማሻሻያ ምክረ ሃሳቦች ባካተተበት ሰነድ ላይ በቅድሚያ ያነሳው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተወካዮች ምክር ቤት ያለመቅረቡን ጉዳይ ነው። አዋጁ በፓርላማ ሳይጸድቅ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ተፈጻሚ መሆኑ፤ “የመንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ለበርካታ ቀናት ያለ ምክር ቤቱ እይታ እና ቁጥጥር” እንዲቆይ ምክንያት እንደሆነ ኢሰመኮ አመልክቷል።ፓርላማው በሰኞ ስብሰባው አዋጁን የሚያጸድቀው ከሆነ፤ ድንጋጌው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን አፈጻጸም የተመለከተ ሪፖርት መንግስት እንዲያቀርብ እንዲደረግ ኮሚሽኑ ጠይቋል።
[Ethiopia Insider]

ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር መጠን በ25 በመቶ እንዲገደብ ወሰነ!
የፋይናንስ ዘርፉን ለማረጋጋት የሚረዱ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ይፋ እንደሚያደርግ ሲያስታውቅ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በተያዘው የበጀት ዓመት ለመንግሥት የሚሰጠውን የቀጥታ ብድር መጠን በ25 በመቶ እንዲገደብ ወሰነ፡፡
የብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ወዲያውኑ ሥራ ላይ እንዲውሉ ካሳለፋቸው በርካታ የፖሊሲ ዕርምጃዎች መካከል፣ በተያዘው የበጀት ዓመት ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር መጠን በእጅጉ ለመቀነስ የተወሰነው ይገኝበታል፡፡ የቦርዱ ውሳኔ ይፋ የተደረገው ዓርብ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ነው፡፡
ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት የሚሰጠውን የቀጥታ ብድር መጠን በእጅጉ በመቀነስ ከዓምናው ከሲሶ ወይም ከ1/3ኛ አንዳይበልጥ የወሰነ ሲሆን፣ በሌላ አነጋገር ይህ የብድር መጠን በ25 በመቶ ይገደባል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ቀጥታ ብድርን እንደ የመጨረሻ አማራጭ የሚጠቀመው የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ፣ በበቂ መጠን ለገበያ መቅረብ ሳይችል ሲቀር ብቻ እንደሚሆን መግባባት ላይ መደረሱን ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
Via Reporter

በሃዋሳ ሀይቅ ዳርቻ በታቦር ተራራ ስር የሚገኙት ጨረቃ ቤቶችን ለማንሳት ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ!
ቤቶቹ የያዙት ቦታ ለቱሪስት አገልግሎት መስጫ መሆን እንደሚገባ ለፊደል ፖስት የሀዋሳ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ የገለፁ ሲሆን ጥናቱ በአንድ አመት ውስጥ ተጠናቆ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ከ 2,100 በላይ የጨረቃ ቤቶች በሀይቁ ዳርቻ የተገነቡ ሲሆን ቤቶቹን የያዙት ስፍራ ለሪዞርት ፣ ሆቴል እና ለመሳሰሉት አገልግሎት ይውላል ተብሏል።
ቤቶቹ በሚነሱበት አግባብ ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ከንቲባው ገልፀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍2❤1
በትራፊክ አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በአፋር ክልል ሚሌ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡አደጋው ከሚሌ ከተማ 14 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ሰመራ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከከባድ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በአደጋው የአንድ ቤተሰሰብ አባል የሆኑ አባት፣ እናትና የ4 ዓመት ህጻን ልጅን ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ÷ 7 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል፡፡በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አቅራቢያ በሚገኙ የጤና ተቋማት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የአውሲ-ረሱ ዞን ትራፊክ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የከባድ መኪና አሸከርካሪው በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡የመለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ክትትል እየተደረገ መሆኑን የአፋር ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
Via FBC

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መርምሮ ውሳኔ ያሳልፋል!
የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አርብ ሐምሌ 28/2015 ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ "በአማራ ክልል ለስድስት ወራት እንዲሁም "እንዳስፈላጊነቱ" በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ይተገበራል" ሲል ባስተላለፈው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015" ላይ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ፤ ችግሩ ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ በቀረበው ጥያቄ መሠረት፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ መወሰኑ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አጀንዳ በተመለከተ የጉዳዩን አሳሳቢነት አይቶና ተወያይቶ፤ በዛሬው ዕለት የምክር ቤቱ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲጠራ የወሰነ ሲሆን፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም በአጀንዳነት እንዲቀርብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በዚህም መሰረት ከእረፍት የተጠራው ምክር ቤት በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው፤ በግጭት ውስጥ በሰነበተው የአማራ ክልል ለስድስት ወራት በታወጀውና "እንዳስፈላጊነቱ" በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ይተገበራል በተባለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ፤ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
እንዲሁም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በምክር ቤት አባልነታቸው በቁጥጥር ሥር ያለመዋል ሕጋዊ መብታቸው ሳይነሳ፤ በቁጥጥር ሥር በሚገኙት የምክር ቤቱ አባል ያለመከሰስ መብት ጉዳይ ላይ የውይይት ሀሳብ ቀርቦ ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክር ቤቱ በአስቸኳይ አዋጁ ላይ ለመምከር እና ለመወሰን የጠራውን አስቸኳይ ስብሰባ አስመልክቶ ቅዳሜ ነሐሴ 6/2015 ባወጣው መግለጫ፤ የአዋጁ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ሕጋዊነት እንዲሁም አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆንበት አካባቢ እና የጊዜ ወሰን እንዲመረመር ለምክር ቤቱ ሃሳብ ማቅረቡን አስታውቋል።በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝ እና ያለመከሰስ ልዩ መብት እና ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃም በምክር ቤቱ እንዲመረመር ጠይቋል።
እንዲሁም፤ "በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ውስጥ ተከስቶ የነበረው ችግር ተወግዶ መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ቀድሞ ኹኔታቸው መመለስ መጀመራቸው" በመንግሥት በመገለጹን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያጸድቀው ከሆነ ተፈጻሚነቱ ከአንድ ወር ወይም ከተወሰኑ ሳምንታት እንዳይበልጥ እንዲሁም ከአማራ ክልል ውጭ አዋጁ ተግባራዊ እንዳይሆን መጠየቁን ገልጿል።በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሰሞኑ የተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ የሰብዓዊ፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችን ማስከተሉ ይታወቃል።
[Addis Maleda]

‹‹ በአማራ ክልል በጎንደርና ሸዋ ሮቢት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሐይሎች ሰለመገደላቸው ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ›› - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ‹‹ በአማራ ክልል፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት በርካታ አካባቢዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዘው ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የሚያመላክቱ ተዓማሚነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ›› ብሏል፡፡ኮሚሽኑ ይህን ያለው ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በላከው ባለአራት ገፅ መግለጫ ላይ ነው፡፡
ኢሰመኮ ተፋላሚ ሀይላት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ስፍራ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡በአማራ ክልል ያለው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ እየተከታተለ መሆኑን የገለፀው ኮሚሽኑ ‹‹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመደንገጉ በፊትና በኋላ ከአዲስ አበባና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መረጃዎች እየተቀበልሁ ነው ›› ብሏል፡፡
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ‹‹ ከባድ የመድፍ ተኩስ ጭምር ጥቅም ላይ የዋለባቸው ከፍተኛ ውግያዎች እየተካሄደ መሆናቸውን አረጋግጬያለሁ ›› ያለው ኮሚሽኑ በዚህም ሞት ሰላማዊ ሰዎች እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በመግለጫው አመልክቷል፡፡
መግለጫው ሲቀጥል ‹‹ መንገድ ለመዝጋት የሞከሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጭምር መገደላቸውን ›› ይፋ አድርጓል፡፡ ‹‹እስር ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ተሰብረዋል፤ የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች ተዘርፈዋል፤ ቅድመ ፍርድ ያሉ እና ታራሚዎች አመልጠዋል ›› ሲል አመልክቷል፡፡የአማራ ክልል መንግስት አመራሮች የጥቃት ዒላማ መሆናቸውንም በዚሁ መግለጫው ጠቁሟል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች እንደ ኤሌክትሪክ ሐይል፣ ውሃ፣ ባንክ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሰልክ፣ ኢነንተርኔት ያሉ መሠረታዊ አገልገሎቶች መሰተጓገላቸውንም አክሏል፡፡‹‹በደብረ ብርሃን ከተማ ለሁለት ቀናት፣ በአራት ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በተካሄደ ከፍተኛ ውግያ በሆስፒታል፣ ቤተ ከርስቲያን፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በስራ ቦታዎች ያሉ ሰለማዊ ሰዎች በመድፍና ተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ›› ባይ ነው፡፡
ኢሰመኮ ‹‹ እንደ ደብረብርሃን፣ ፍኖተ ሰላምና ቡሬ ባሉ ከተሞች ‹ የአየር ድበደባዎች › በመፈፀሙ ሰላማዊ ሰዎች፣ በመኖሪያ ቤቶችና ሕዝብ በሚበዛበቸው ስፍራዎች ጉዳት መድረሱን ›› አመልክቷል፡፡ይህ የኮሚሽኑ መግለጫ ሲቀጥል ‹‹ በባህርዳር ከተማ በርካታ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰዎች በየጎዳናውና ከቤታቸው ውጪ ተግደለዋል፤ አንዳንድ ወጣቶችን ደግሞ ለመደብደብና ለመግደል ፍለጋ ሲደረግ እንደነበረ የሚያመላክቱ ተዓማኒ መረጃዎች ደርሰውኛል ›› ሲል ይፋ አድርጓል፡፡
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቱ በአማራ ክልል ብቻ የተገደበ አለመሆኑን የሚጠቅሰው ኮሚሽኑ ‹‹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአማራ ተወላጆችን እያሰረ መሆኑን ›› ገልፆል፡፡በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ያተተው የኮሚሽኑ መግለጫ አምስት ያህል ምክረ ሀሳቦችን ቢደረጉ ሲል በመግለጫው አስቀምጧል፡፡
ከእነዚህም መካከል ‹‹ የፌደራሉ መንግስት የጅምላ እስሩን እንዲያቆም፣ ክህግ አግባብ ውጪ የታሰሩት ሁሉም እንዲፈቱ፣ ኮሚሽኑን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት በየእስር ቤቶቹ ጉብኝት ለማድረግ ያልተገደበ መንገድ እንዲመቻችላቸው ›› የጠየቀበት ይገኝበታል፡፡የመንግስት ባለስጣናትን ጨምሮ ተሰመኒነት ያላቸው ግለሰቦች ሰላማዊ መንገዶችን ከመጠቆም ይልቅ ግጭቱን ከሚያጋግሙ መግለጫዎች እንዲቀቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ያሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባባሩት መንግስታትና ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ግጭቶቹ እንዲቆሙ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ የመነጋገሪያ ስፋራዎችን እንዲያመቻቹ ጠይቋል፡፡
[Asham]

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ እየገቡ መሆናቸውን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የቡድኑ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ሰምተናል።የወረዳው ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ታጣቂዎቹ ከሰሞኑ በስፋት መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ወረዳው የገጠር ቀበሌዎች እየገቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በወረዳው በተደጋጋሚ ባደረሱት ጥቃት በርካታ ዜጎች መገደላቸውንም ነዋሪዎቹ አስታውሰዋል።በተጨማሪም በወረዳው የገጠር ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ታጣቂዎችን ሸሽት ወደ ወረዳዋ ከተማ ጉንዶ መስቀልና ወደሌሎች አካባቢዎች መሰደዳቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ ታጣቂውች በወረዳው የገጠር ቀበሌ በሆኑ ባቡ ድሬ፣ ራቾና ድሬ መንቃታ አካባቢዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ነው የተነገረው።ኦነግ ሸኔ ከ ሁለት አመት በፊት ጀምሮ ወደ ወረዳው በመግባት ዜጎችን በማገት ገንዘብ መቀበል እንዲሁም ግድያና ማፈናቀል እያደረሰ ነው ተብሏል።
በተለይም የደራ ወረዳን ከሰላሌ ጋር የሚያገናኘውን የጀማን ድልድይ በመቆጣጠሩ የወረዳዋ ነዋሪዎች በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ በኩል ወደ አዲስ አበባ እንዲሚመጡ ተገደዋል።የደራ ወረዳ ከአዲስ አበባ 2 መቶ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ወረዳ መሆኑ ይታወቃል።እኛም ወቅታዊውን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማናገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካም።
Via Ethio FM

👍1😁1
በጅማ ዞን በሞቱ ሰዎች ስም የአፈር ማዳበሪያ እንደሚሸጥ ተነገረ!
በጅማ ዞን ቀርሳ እና አሰንዳቦ ወረዳዎች በተደረገ ቁጥጥር በህገወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ዉስጥ ተከማችቶ በዉድ ዋጋ ሊሸጥ የተዘጋጀ 1 ሺህ 47 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ መያዙ ተነግሯል።የአፈር ማዳበሪያዉ ግምታዊ ዋጋዉ 5 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር የሚገመት መሆኑን የጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና የኮሚኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ወንድሙ ሞቲ ተናግረዋል።የቀርሳ ወረዳ የህብረት ስራ ማህበር ማስፋፊያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነዚብ አባተማም ፤ በዞኑ ህገወጥ የፈር ማዳበሪያ ዝዉዉር እና ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዉ ፤ በመዋቅር የተደራጀ ሌብነት ፈተና መሆኑን አክለዋል።
በዚህም አመራሮችን አሳታፊ ባደረገዉ ህገወጥ ድርጊት ፤ በህይወት በሌሉ ሰዎች ስም ጭምር ማዳበሪያ እንደሚወጣ እና እንደሚሸጥ ገልጸዋል። በቀርሳ ወረዳ 314 ኩንታል ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉንም አክለዋል። በወረዳዉ በህገወጥ መንገድ የሚሸጥ አንድ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከ 10 ሺህ ብር በላይ እንደሚጠይቅ ሀላፊዉ ጠቁመዋል።በጅማ ዞን በርበሬ የሚዘሩ አርሶ አደሮች ወቅቱ እንዳያልፍባቸዉ በሚልም በህገወጥ የማዳበሪያ ግዢ ላይ ተሳታፊ ለመሆን እንደተገገዱም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ሰንዳቦ እና ጊቤ ኬላ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 428 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ተጭኖ ሲጓጓዝ መያዙን ኮማንደር ወንድሙ ሞቲ ተናግረዋል። በተጨማሪም ከቦነያ የህብረት ስራ ማህበር በ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ 95 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መያዙንም አክለዋል።
በተመሳሳይ በኦሞ ናዳ ወረዳ ዋቅቶላ ቀበሌ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ዉስጥ 210 ኩንታል ማዳበሪያ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል። የአፈር ማዳበሪያዉ ሲያጓጉዙ የነበሩ እና አራት የህብረት ስራ ማህበራት ሰራተኞችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና የኮሚኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ወንድሙ ሞቲ ጨምረዉ ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]

🔥1