ቦርዱ በዎላይታ ዞን የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ምርጫ አጠቃላይ ውጤት ሰኔ 19 ላይ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ኢትዮጵያን ክልል ለመመስረት በዎላይታ ዞን የተካሄደውን ኹለተኛ ዙር የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ድምጽ አጠቃላይ ውጤት ሰኔ 19/2015 ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ትናንት ሰኔ 12/2015 በዎላይታ ዞን የተካሄደውን ኹለተኛ ዙር የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ መጠናቀቅ አስመልክቶ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፤ በወላይታ ዞን በተካሄደው ድጋሚ የህዝበ ውሳኔ ምርጫ የመራጮች ተሳትፎ የተረጋገጠበት መሆኑን ገልጸዋል።በዞኑ የሚገኙ ኹሉም የምርጫ ጣቢያዎች ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ የምርጫ ሂደቱን ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ሰብሳቢዋ፤ የመምረጥ ዕድል ላላገኙ መራጮች 12 ሰዓት ላይ መጠናቀቅ የነበረበትን የምርጫ ሂደት ወደ አንድ ሰዓት ቦርዱ ማራዘሙን ተናግረዋል።
በመሆኑም እስከ አንድ ሰዓት ከ20 ድረስ በምርጫ ጣቢያዎች መገኘት የቻሉ ኹሉም መራጮች ድምፅ ሳይሰጡ አለመመለሳቸውን ገልጸዋል።ጣቢያዎቹ ወደ ድምፅ ቆጠራ ሂደት የገቡ ሲሆን፤ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ ቆጠራው የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
ቦርዱ በ12 ማዕከላት እና በ1 ሺሕ 812 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ 9 ሺሕ 60 የምርጫ አስፈፃሚዎችን መድቦ መንቀሳቀሱን ያስታወቁት ሰብሳቢዋ፤ "በኹሉም የምርጫ ጣቢያዎች ከአስፈፃሚዎች ጋር ተያይዞ የቀረበ ችግር የለም።" ሲሉ ገልጸዋል።ቦርዱ ምርጫውን ለምታዘቡ ለ2 የአገር ውስጥ ተቋማትና ለ206 ታዛቢዎች እውቅና በመስጠት ከእነዚህ ውስጥ 168 ታዛቢዎችን በዞኑ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ማሰማራቱን ገልጸዋል።
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን 7 የሰብዓዊ መብት ተከታታዮችን ማሰማራቱም ተገልጿል።ሰብሳቢዋ መራጮች ለ6 ወር በአካባቢው መቆየታቸውን የማያሳይ መታወቂያ ይዘው መገኘታቸው፣ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ መራጮች መታወቂያ ይዘው መገኘታቸው፣ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ድልቦአውጥሮ 1 የምርጫ ጣቢያ ላይ አንድ ግለሰብ ባዶ መታወቂያ ከቀበሌ አውጥቶ ሲሞላ እጅ ከፍንጅ መያዙን ገልጸዋል።
በተጨማሪም፤ በሁምቦ ምርጫ ጣቢያ አስፈፃሚ ሳይሆን የሌላ ሰው ባጅ አንጠልጥሎ በክትትል መያዙን እና በገሱባ ምርጫ ጣቢያ ላይ ስርዝ ድል ያለበት መታወቂያ ይዞ የተገኘ ግለሰብ መኖራቸው በሕዝበ ውሳኔው የምርጫ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውንም አብራርተዋል።
ከመታወቂያ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ችግሮችን በምስክርና ተጨማሪ ሰነድ እንዲያቀርቡ በማድረግ ችግሩ ተፈትቶ ድምፅ መስጠታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ እጅ ከፍንጅ የተያዙ አካላት ደግሞ ወደ ፖሊስ መተላለፋቸውን ገልጸዋል።እስከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ 514 ሺሕ 620 መራጮች መሳተፋቸውንም ሰብሳቢዋ በመግለጫቸው ማስታወቃቸውን ደሬቴድ ዘግቧል።
በጣቢያዎቹ የሚከናወነው የድምጽ ቆጠራ እንደተጠናቀቀም በየምርጫ ጣቢያው ጊዜያዊ ውጤት የሚለጠፍ ሲሆን፤ በመቀጠልም የድምፅ መስጫ ወረቀቶቹ ወደ ዞን ማስተባበሪያ ቢሮ ተሰብስበው የውጤት ማዳመር ተሰርቶ ጊዜያዊ ውጤት በዞን ደረጃ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።ቦርዱ ሰኔ 19 ላይ አጠቃላይ ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ የገለጹት ሰብሳቢዋ፤ ከተቻለም ከተገለጸው ቀን ቀደም ብሎ ውጤት ለመግለፅ ጥረት እንደሚደረግም ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

❤1
የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ስርጭት በሃምሌ ወር እንደሚጀምር ገለጸ!
ድርጅቱ በትግራይ ክልል በግንቦት ወር በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ደግሞ በሰኔ ወር የእርዳታ እህል ስርቆት ተበራክቷል በሚል የምግብ ድጋፉን ማቋረጡ ይታወሳል።አሜሪካም እንዲሁ የሰብአዊ ድጋፍ ከተቸገሩ ዜጎችን እየተነጠቀ መሆኑን በመጥቀስ ድጋፏን ማቆሟ አይዘነጋም።
የአለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታው የሚደርሳቸው ሰዎች የሚለዩበት መንገድ እንዲስተካከል ያሳሰበ ሲሆን፥ ተረጂዎችን በመለየቱ ሂደት ከፍተኛ ድርሻ ሊኖረኝ ይገባል ብሏል።በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች የሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ ሲሆን፥ የአለም ምግብ ፕሮግራም ለ6 ሚሊየን ሰዎች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ሬውተርስን ጠቅሶ አል አይን ዘግቧል።

ለሽረ ዕደስላሴ አዋሳኝ በሆኑት በሽራሮ እና ማይፀብሪ አካባቢዎች በኤርትራ ሰራዊት ተደጋጋሚ ትንኮሳ እየደረሰ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
የኤርትራ ሰራዊት ከሽራሮ 17 ኪሎ ሜትር ድረስ ተቆጣጥሮ በመያዝ በርካታ ግፎችን በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገልፃል፡፡የሽረ እዳስላሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተፈሪ ሀይለመለኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣የኤርትራ ሰራዊት ከፍተኛ ትንኮሳ በየቀኑ እንደደሚፈፅማባቸው አስታውቀዋል፡፡
የኤርትራ ሰራዊት በባድመ፣ገምሀሎ እና በሽራሮ በኩል 17 ኪሎ ሜትር ድረስ በመዝለቅ ከብቶች የመዝረፍ፣ የመግደል እና ለእርሻ የተሰማሩ ሰዎች የመግድል እንቅስቃሴ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ገልፀውልናል፡፡
በማይፀበሪም በተለያዩ አከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ትንኮሳ እየደረሰበት እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ በዚህ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ የተማረረ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባው፣ አሁንም ድረስ በሚድርስበት ጥቃት ክፉኛ እንደተጎዳ ተናግረዋል፡የክልሉ መንግስት በሰላም ስምምነቱ ላይ ባለው አመኔታ ነገሮችን በትዕግስት እያለፈ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
[Ethio FM]

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ባለሀብቶች ወደ እንግሊዝ ሀገር ከታሪፍ ነፃ ገበያ ምርቶቻቸውን ሊያቀርቡ ነው!
የታዳጊ ሀገራት አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ ምርቶቻቸውን ከታሪፍ ነፃ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የመክፈቻ መርሃ ግብር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስቴር ናይጄል ሀድልስተን የታዳጊ ሀገራት ነፃ የንግድ ፕሮግራም በ65 የዓለም ሀገራትና በ37 የአፍሪካ ሀገራት የሚጀመር መሆኑን ገልፀው በኢትዮጵያ በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም በሌሎች የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ምርት የተሰማሩ አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ ላይ ምርቶቻቸውን በነፃ እንዲያቀርቡ ያግዛል ብለዋል።
Via EPA

በቦረና ዞን በድርቅ ለተጠቁ ሰዎች ሲደርስ የነበረው ሰብዓዊ ድጋፍ መቋረጡ ተገለጸ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ሲቀርብ የነበረው ሰብዓዊ ድጋፍ መሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መቋረጡን የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የድርቁ አስከፊነት በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ከተሰማ በኋላ ሲደረግ የነበረው ሰብዓዊ ድጋፍ መልካም እንደነበረ የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪው ነገር ግን ለአምስት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ተቋርጦ የነበረው ዝናብ መዝነብ ከጀመረ በኋላ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ መቋረጡን አስረድተዋል፡፡አሁን ላይ መጠነኛ ድጋፍ እየተደረገ ያለው መንግሥታዊ ባልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ብቻ መሆኑን አስታውሰው በሌሎች አካላት ሲደረግ የነበረው ሰብዓዊ ድጋፍ ግን ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን አክለው ተናግረዋል፡፡
ከተረጂዎቹ ቁጥር ብዛት አንጻር በአንድ ብቻ መንግሥታዊ ያልሆን ድርጅት የሚደረገው ድጋፍ እጅግ አነስተኛ ነው ያሉት አቶ ዋሪዮ በዚህም ምክንያት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተረጂዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውንም ነው የገለጹት፡፡በቦረና ዞን የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በብዛት አርብቶ አደር በመሆናቸው እና በድርቁ ምክንያት ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጉዳት የደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን መልሶ ለማቋቋም እጅግ ፈታኝ መሆኑ በተደጋጋሚ ጊዜ መገለጹ ይታወሳል።
[አሐዱ]

የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ!
የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ “ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ደርሰንበታል” ብሏል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑንም አስታውሷል:: በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

👍1
👉 _ አስደሳች ዜና
በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።
መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉 _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና ::
👉 _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
👉 _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
👉 _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር እና በሌሎች ነገሮች።
_ 👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
👉 _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
👉_ ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
👉 _ አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ ንግድ -ግብርና ወይም በትምህርት ዙሪያ
👉 _ በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
👉_ በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
👉_ ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
👉_ ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
👉 _ እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
👉 _ ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ
የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
☎️ 0912718883
0917040506

TikTok
TikTok - Make Your Day
TikTok - trends start here. On a device or on the web, viewers can watch and discover millions of personalized short videos. Download the app to get started.
👍1👎1
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
👍1
#ADVERTISEMENT
👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ
📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠
💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ
ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ
📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠
💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ
ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
👍1
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው
Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy
Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL
Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel

በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈውን “እመጓ” የተሰኘውን መፅሐፍ ቱባ መተግበሪያ ላይ ያንብቡ!
“እመጓ”ን እና ሌሎች በርካታ ተወዳጅ መፃሕፍትን በማንኛውም ጊዜና ቦታ በኢቡክ እና በትረካ መልክ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማንበብ ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ።
Download Tuba: https://tuba.et
@tuba_books @tuba_books

#የቻናል_ጥቆማ❗️
🏗በ እትዮጵያ ብቸኛ ቡዙ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው የconstruction ዘርፍ መረጃዎችን ትምህርቶችን ምታገኙበት channel 👇
https://tttttt.me/ethioengineers1
~ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት👇
https://tttttt.me/ethioengineers1
~ የኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭና ገዢ የሚገናኙበት ምርጥ ቻናል ለማገኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን👇
©️Telegram 👇

Telegram
Ethio Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ሕጻናት የነገ ተስፋ ለአዲስ አበባ" በሚል መሪ የቀዳማይ ልጅነት ልማት የንቅናቄ ሳምንት አስጀመሩ
ሰኔ 14/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ሕጻናት የነገ ተስፋ ለአዲስ አበባ" በሚል መሪ ቃል የቀዳማይ ልጅነት ልማት የንቅናቄ ሳምንት አስጀመሩ፡፡
ከንቲባዋ ከጽንስ እስከ ስድስት ዓመት ዕድሜ ያሉ ሕጻናት በአዕምሮና በአካል እንዲበለጽጉ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው ዛሬ ባስጀመርነው ንቅናቄ እናቶች አሳዳጊዎች እና ባለድርሻ አካላት በሕጻናት አስተዳደግ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይሰራል ብለዋል::
ለዚህም እንዲያመች በዛሬው ዕለት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትን ለማሸጋገር የሚያስችል በጥናት እና ምርምር ላይ የተደገፈ ስራ ለመስራት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመናል ያሉት ከንቲባ አዳነች 1400 በሕጻናት እንክብካቤ የሰለጠኑ ባለሙያዎች መመረቃቸውንም ገልጸዋል::
ከተማ አስተዳደሩ በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የቀዳማይ ልጅነት ፍኖተ ካርታ አጽድቆ ስራ መጀመሩን ገልጸው በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የህጻናት ማቆያና ተንከባካቢ ባለሙያዎች ይመደባሉ ብለዋል::
በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 12 ሺሕ የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎች ለማዘጋጀት እየሰራ ያለው ከተማ አስተዳደሩ 59 የሚሆኑትን ዘንድሮ ማጠናቀቁን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በቀዳማይ ልጅነት ሳምንት በሕጻናት አስተዳደግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የሚሰሩ ይሆናልም ነው የተባለው::
@Yenetube @Fikerassefa

በጎፋ ዞን ከታራሚዎች ማምለጥ ጋር በተያያዘ በ18 የፖሊስ አባላት ላይ ውሳኔ ተላለፈ
በጎፋ ዞን በነፍስ ግድያ ፣ አስገድዶ መድፈር ፣ ወንብድና እንዲሁም ዝርፊያ ወንጀል ተከሶ በተላለፈበት ውሳኔ በሣውላ ማረሚያ ተቋም የሕግ ታራሚ የሆነን ኤልያስ ማናዬ ማራ እና ሌሎች ታራሚዎች ከማረሚያ ቤት ማምለጥ ጋር በተያያዘ 18 የፖሊስ አባላት በወንጀል ተከሰው በህግ እንዲጠየቁ መደረጉ ተነግሯል ።የሕግ ታራሚ ኤልያስ ማናዬ ግብረአበሮቹ ተብለው ተከሰው ውሳኔ የተላለፈባቸውን ጨምሮ 8 የሚሆኑ የሕግ ታራሚዎችን በማስተባበር ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ በሣውላ ከተማ የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በማድረግ በር ሰብረው የማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸውን እና በዕለቱ በተደረገው ክትትል 7 የሕግ ታራሚዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ኤልያስ ማናዬ ማምለጡን ተነግሯል ።
የሣውላ ማረሚያ ተቋም ፣ የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያና የዛላ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት የወንጀል ምርመራና ክትትልና ቡድን ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ርብርብ ከ5 ቀናት ፍለጋ በኋላ የሕግ ታራሚ ኤልያስ ማናዬን በሕይወት ለመያዝ ከፍተኛ ጥረትና ሙከራ መደረጉን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሸብር ሲንሳ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ። ነገር ግን የፖሊስ አባላት የሕግ ታራሚውን በሠላማዊ መንገድ ለመያዝ ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካና ታራሚው እጅ ከመስጠት ይልቅ በሁለት እጁ ጦርና ገጀራ በመያዝ በአንድ የፖሊስ አባል ላይ ጦር በመወርወር ለመግደል ሙከራ በማድረጉ የፖሊስ አባሉ ሕይወቱን ለማዳን ሲል በወሰደው እርምጃ በጥይት እግሩ ተመትቶ ወደ ሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢገባም በደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል።
ውሳኔ የተላለፈባቸው የፖሊስ አባላት ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም የሕግ ታራሚው በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ጥቂት የተቋሙ ፖሊስ አባላት ወደ ሣውላ ከተማ በሚገቡበት ወቅት ያለተቋሙ እውቅና ጥይት ያለአግባብ በመተኮስ የሕዝቡን ሠላምና ደህነት በማናጋት ከፖሊስ አባል የማይጠበቅ የስነ-ምግባር ጥሰት ፈፅመዋል። ስለሆነም ከታራሚዎች ማምለጥ ጋር በተያያዘ እና ያመለጠ ታራሚ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተፈፀመ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፖሊስ አባላቱ በወንጀል ተከሰው በህግ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፏል ። በዚህ መሰረት ሁለት የፖሊስ አባላት ከታራሚዎች ማምለጥ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ከስራ እንድሰናበቱ ተወስኗል ። ሦስት የፖሊስ አባላት በበኩላቸው የህግ ታራሚን በእንዝላልነት እንድያመልጥ በማድረግ ወንጀል ተከሰው በህግ እንዲጠየቁ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ።ሌሎች 13 የፖሊስ አባላት ያለአግባብ ከትዕዛዝ ውጭ ጥይት ከተማ ውስጥ በመተኮስ የህዝቡን ሰላም ያናጉ በመሆናቸው በከባድ ዲስፒልን ተከሰው እንዲቀጡ እና የተኮሱትን የጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ ውሳኔ መተላለፉን ዋና ኢንስፔክተር አሸብር ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።
[ዳጉ ጆርናል]

በትግራይ ክልል በጦርነት ለተጎዱ ባለሀብቶች የዕዳ ስረዛ እንዲደረግ ተጠየቀ!
መነሻውን በትግራይ ክልል ያደረገው፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ ከፍተኛ ጉዳት ላደረሰባቸው የትግራይ ክልል ባለሀብቶች፥ ዕዳ እንዲሰረዝ፣ የክልሉ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ፕሬዚዳንት ጥሪ አቀረቡ።ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት፣ ክልሉ፣ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት በሚል፣ በመቐለ ከተማ በተዘጋጀ ውይይት ላይ ነው። የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነርም፣ ለባለሀብቶች ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ፣ በውይይቱ ወቅት አሳስበዋል።
Via VoA

ቅዴፓ "የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ከ1 ሺህ 500 በላይ የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጆች ህይወት አልፏል" አለ።
የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ቅዴፓ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ፓርቲው በመግለጫው በተለይም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በብሔረሰቡ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ባለው ግድያና እስር ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 334 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ንብረት ወድሟል ብሏል።
አሁንም ድረስ በማረሚያ ቤቶች ያለ ፍርድ እየተሰቃዩ የሚገኙ የብሄረሰቡ ተወላጆች መኖራቸውም አመልክቷል።
ጥያቄያችን ብሔረሰቡ የሚኖርበትን ቦታ የብሔሩ ተወላጆች ያስተዳድሩት፤ ቋንቋውም ይደግ ነው ነገር ግን በክልሉ መንግስት የሚሰጠው ምላሽ ተገቢ አለመሆኑን የፓርቲው አመራሮች አንስተዋል።
እኛ የማንም ተላላኪ አይደለንም ያለው ፓርቲው ጥያቄያችን ህገመንግስታዊ ነው ሲሉም አክለዋል።
[Asham]

የቀድሞዋ አፈጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም መረጃ በማጥፋታቸው የራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ እንዲጓተት ምክንያት ሆኗል ተባለ
የራያ አላማጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ እልባት እንዲሰጠው በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የላከው ደብዳቤ በቀድሞ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም አማካኝነት እንዲጠፋ ተደርጓል ተብሏል።
የአላማጣ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሞገስ እያሱ፤ የራያ አላማጣ የማንነት እና የበጀት ጥያቄ ከ2011 ጀምሮ ለፌደሬሽን ምክርቤት ሲቀርብ እንደነበር ገልጸው፤ “የወቅቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኬሪያ ኢብራሂም የማንነት ጥያቄውን ለማዳፈን በማሰብ ለምክር ቤቱ የገባው መረጃ እንዲጠፋ አድርገዋል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
በዚህም ለምክር ቤቱ የገባው መረጃ እንዲጠፋ መደረጉ፤ የራያ አላማጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ መፍትሄ ሳያገኝ ለአራት ዓመታት እንዲጓተት ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት።
“አፈጉባኤዋ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ በገባው ደብዳቤ መሰረት የማንነት ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ስንጠይቅ፤ መረጃው መጥፋቱ ስለተነገረን ቅጂውን በድጋሜ ለማስገባት ተገደናል፡፡” ሲሉ ጠቁመዋል።
ባሳለፍነው ሰኞ ሰኔ 12/2015 የራያ አላማጣ እና ባላ አካባቢዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ከ150 ሺሕ በላይ የሕዝብ ፊርማ ተሰብስቦ ለፌደሬሽን ምክር ቤት መግባቱን የጠቀሱት ኃላፊው፤ “ዋና ዓላማውም የማንነት ጥያቄያችን ተፈቶ ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን እንድንካተትና በጀቱ በትግራይ ክልል ሳይሆን በአማራ ክልል በኩል እንዲለቀቅልን ነው፡፡” ብለዋል።
አክለውም፤ በተለይ የፌደራል ተቋማት በአካባቢው የተሟላ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆኑ፣ ከባንክ፣ ከኤሌክትሪክና ከኢንተርኔት ጋር ያለው አገልግሎት በቶሎ ምላሽ ሊስጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ለዚህም አራት ዓመታትን ያስቆጠረው የራያ አላማጣ የማንነት እና የበጀት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ኮሚቴ ተቋቁሞ፤ ሰኞ ሰኔ 12/2015 ለፌድሬሽን ምክር ቤት መግባቱ ነው የተገለጸው።
ሕወሓት ለራያ እና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መድቧል በሚል የሚነሳውን ጉዳይ በተመለከተም መድቧል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ አምስት አመራሮችን የቀያየረ መሆኑን ጠቁመው፤ “ወደ ራያ እና አላማጣ ግን ሊመጡ አይችሉም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።
ራያ አላማጣ ለኹለት ዓመታት ያለ በጀት መቆየቱን የገለጹት ኃላፊው፤ የማንነት ጥያቄው እና ለኹለት ዓመት የተቋረጠው በጀት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው ህዝቡ በተደጋጋሚ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ከፌደሬሽን ምክር ቤት ፅሕፈት ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል።
በተያያዘም፤ በዛሬው ዕለት የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ''መንግሥት የማንነት ጥያቄቸውን ሕጋዊ እንዲያደርግላቸው'' በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ ሲሆን፤ ነዋሪዎቹ በሰላማዊ ሰልፉ “አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም”፣ “የፌደራል መንግሥት ተቋማት ዲስትሪክት ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ይዛወሩልን”ና ሌሎች የተለያዩ መፈክሮችን ማሰማታቸውን የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሱሳ ከሰኔ 21 ቀን 2023 ጀምሮ ከስራ አስፈፃሚነታቸው ተነሱ።
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት ትምህርትት ቤቶች በቀጣይ ዓመት በሚያደርጉት የክፍያ ጭማሪ ላይ ከወላጆች ጋር መግባባት ባለመቻላቸዉ ምዝገባ እንዳያከናዉኑ ታገዱ!
በአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቅዱስ ሚካኤል ት/ቤቶች እና ብራስ ዩዝ አካዳሚ የተሰኘ ትምህርት ቤቶች በቀጣይ ዓመት የተማሪዎች ምዝገባ እንዳያከናውኑ ማገዱን አስታዉቋል።ባለስልጣኑ ፤ ማንኛዉም ት/ት ቤት በቀጣይ አመት ለሚያደርገዉ የወርሃዊ ክፍያ ጭማሪ ከተማሪ ወላጆች ጋር ከስምምነት ደርሶ መሆን አለበት ቢልም ፤ ት/ት ቤቶቹ እና ወላጆች ከፍ በሚደረገዉ የክፍያ መጠን ላይ መስማማት አልቻሉም።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ፤ ብራስ ዩዝ አካዳሚ ለቀጣዩ የ 2016 አመት የ 40 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ ቢያቅድም ከወላጆች ጋር በተደረገው ዉይይት ተቀባይነት አላገኘም። በአንጻሩ ወላጆች ለቅድመ መደበኛ የ 25 በመቶ እና ለመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የ 30 በመቶ ለሚደረግባቸዉ ጭማሪ እሺታቸዉን ሰጥተዉ ነበር።
ሆኖም ትምህርት ቤቱ በወላጆች በኩል የቀረበዉን ሀሳብ ዉድቅ አድርጎታል። በዚህም መሰረት የአዲስአበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሁለቱን አካላት ለማስማማት ጥረት አድርጎ ነበር። በዚህም የ 30 በመቶ የጭማሪ ሀሳብ በባለስልጣኑ ቀርቦ ወላጆችም ከስምምነት ደርሰዉ የነበረ ቢሆንም ትምህርት ቤቱ ሳይቀበለዉ ቀርቷል።
በተመሳሳይ ቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ ዓመት ከ100 እጥፍ በላይ ጭማሪ ለማድረግ ቢያቅድም ከወላጆች ጋር በተደረገዉ ዉይይት 80 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ ወስኗል። ሆኖም ወላጆች ከ 50 በመቶ በላይ ጭማሪ ለማድረግ ፈቃደኞች አልሆኑም። ባለስልጣኑ ሁለቱን አካላት በ 60 በመቶ ጭማሪ ለማስማማት ቢሞክርም በተመሳሳይ ትምህትት ቤቱ ዉድቅ አድርጎታል።
በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ በወላጆችና በት/ት ቤቶቹ መካከል ስምምነት አለመደረሱን ተከትሎ ሁለቱም ት/ት ቤቶች ለሚቀጥለዉ አመት የተማሪዎች ምዝገባ እንዳያከናዉኑ ጊዜያዊ እግድ የተጣለባቸው መሆኑን ገልጸዋል።በዚህ ሳምንት ሁለቱም ት/ት ቤቶች ምላሻቸዉን ያሳዉቃሉ ብለዉ እንደሚጠብቁ የተናገሩት ወ/ሮ ፍቅርተ ፤ ከወላጆች ጋር ከስምምነት ይደርሳሉ ብለዉ ተስፋ እንደሚያደርጉ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
[Bisrat FM]

ሕገ-ወጥ የማዕድን አምራቾችን ስርዓት ለማስያዝ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ አሻድሊ ሀሰን
መንግስት ሕገ-ወጥ የማዕድን አዘዋዋሪዎችን እና አምራቾችን ስርዓት ለማስያዝ የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ቁጥጥር ኮማንድ ፖስት ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ ሥራዎችን በዘርፉ የተሠማሩ ባለሃብቶች በተገኙበት ገምግሟል፡፡
በመድረኩ አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ በመከላከያ ሠራዊት የ404ኛ ኮር አዛዥ ጄነራል ሰይፈ አንጌን ጨምሮ የጸጥታ እና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን÷ በማዕድን ዘርፉ ላይ የሚስተዋለው ህገ-ወጥ ተግባር ሀገርን ወደ ኢኮኖሚ ስብራት ለማስገባት ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡