YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የግብርና ሚኒስቴር የአትክልት ማሳዎች ወደ ስንዴ ማሳነት ተቀይረዋል የሚለውን መረጃ ሀሰት ነው ሲል አስተባበለ፡፡

ከሰሞኑ ከሽንኩርትና ቲማቲም ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ አትክልት ነጋዴዎች የዋጋ ንረቱ የተከሰተዉ ማሳዎቹ ስንዴ እንዲመረትባቸዉ መደረጉ ነዉ ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሃላፊ ደረጄ አበበ ለአሻም በሰጧት ምላሽ መረጃው ሀሰት ነው፤ የህገወጥ ደላሎች ሴራ ነዉ ሲሉ ጉዳዩን አስተባብለዋል፡፡

አሻም በአዲስ አበባ ከተማ የቄራ አትክልት ተራ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባልን አነጋግራ በሰራችዉ ዘገባ የሽንኩርትና ቲማቲም ዋጋ አልቀመስ ለማለቱ የአትክልት ማሳዎቹ መንግስት በያዘዉ አቅጣጫ ማሳዎቹ ስንዴ እንዲመረትባቸዉ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ማህበሩ ሽንኩርት ከመቀሌ፣ከሱዳንና ከጅጅጋ እያስመጣ እንደሚገኝ ለአሻም መጥቀሳቸው አይዘነጋም፡፡በሽንኩርትና ቲማቲም ምርት የሚታወቁት ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙት የኦሮሚያ አካባቢዎች አርሶአደሮቻቸዉ በስንዴ ምርት ላይ እንዲጠመዱ መደረጉ ለአትክልት እጥረትና ዋጋ ንረቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ሃላፊው ደረጄ አበበ የስንዴ ምርትም ሆነ የአትክልት ምርቶች ሁለቱም የኛው ናቸዉ ይላሉ፡፡ ‹ የሽንኩርትና የቲማቲም ማሳዎች ወደ ስንዴ ምርትነት ገቡ › ፤ ‹ ሽንኩርት ከመቀሌ እያስመጣን ነው › ሲሉ የሚያስወሩት የሕገወጥ ደላሎች ስራ እንጂ እውነተኛ መረጃ አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል፡፡የአትክልት አምራች አካባቢዎች ወደ ስንዴ ምርትነት እንዲቀየሩ ተደርጓዋል መባሉም ትክክኛ መረጃ አለመሆኑን ጠቅሰው አስተባብለዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
አል ሸባብ በኢትዮጵያና ሶማሊያ ወታደሮች የጦር ግቢ ላይ ጥቃት ፈጸመ!

አል ሻባብ በሶማሊያ የሚገኝ አንድ ወታደራዊ ሰፈርን ዛሬ ማጥቃቱን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።ሁለት የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታዎች የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ወታደሮች በሚገኙበትና ባርዴር በተሰኘችው ደቡባዊ ከተማ ባለ ወታደራዊ ሰፈር መፈጸሙን ምንጮች ተናግረዋል።ወዲያውም የከባድ መሣሪያ ተኩስ ተሰምቷል።

ጥቃቱ የተከሰተው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮችን መቀነስ መጀመሩን ባስታወቀበት ወቅት ነው።አል ሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን በወሰደበት ጥቃት ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ወዲያውኑ ማወቅ እንዳልተቻለ ዘገባው አመልክቷል።

የመጀመሪያው ፍንዳታ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ የሶማሊያ ወታደሮችን በሚያሰለጥኑበት ግቢ መግቢያ በር ላይ እንደነበር የአካባቢው የፖሊስ አባል የሆነው አብዲ ባሬ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግሯል።ሁለተኛውም ፍንዳታ ከ5 ደቂቃ ቆይታ በኋላ እንደተስማና ተጎጂዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን ዝርዝር መረጃ እንደሌለ የፖሊስ አባሉ ጨምሮ ገልጿል። ከመጀመሪያው ፍንዳታ በኋላ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደነበር ጨምሮ ተናግሯል።

ጥቃቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት እስከአሁን ያለው ነገር የለም።ባለፈው ወር የአልሸባብ ተዋጊዎች የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ላይ ባደረሱት ጥቃት 54 የኡጋንዳ ወታደሮች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱን በተመለከተ የሚናፈው የፈጠራ ዜና ከዕውነታ የራቀ እና መሠረተ-ቢስ ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ!

“የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት (ካርጎ እና ሎጂስቲክስ) ክፍል ወደሌላ ሀገር በሽያጭ ሊተላለፍ ወይም ለብድር መያዣነት ሊውል ነው” በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው የፈጠራ ዜና ከዕውነታ የራቀ እና መሠረተ-ቢስ ነው ሲል አየር መንገዱ አስታወቀ።

አየር መንገዱ ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ “ድርጅታችን በጥቂት የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ እየተናፈሰ ያለውን ‘የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት (ካርጎ እና ሎጂስቲክስ) ክፍል ወደሌላ ሀገር በሽያጭ ሊተላለፍ ወይም ለብድር መያዣነት ሊውል ነው’ የሚል የፈጠራ ዜና ተመልክቷል፤ ዜናው ፍጹም ከዕውነታ የራቀ እና መሠረተ-ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያረጋግጣል” ብሏል።

“ይህ ከእውነት የራቀ ወሬ የብሔራዊ አየር መንገዳችንን ስም እና ገፅታ የሚጎዳ ስለሆነ ወሬውን የሚያሰራጩ ወገኖችን ይህንን ከማድረግ እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን” ሲልም አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
#ADVERTISEMENT

👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ

📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠

💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ

ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!

የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!

Download Tuba: https://tuba.et

@tuba_books    @tuba_books
#የቻናል_ጥቆማ❗️

🏗በ እትዮጵያ ብቸኛ ቡዙ ተከታዮችን  ማፍራት የቻለው የconstruction ዘርፍ መረጃዎችን ትምህርቶችን ምታገኙበት channel 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

~ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች  እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

~ የኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭና ገዢ የሚገናኙበት ምርጥ ቻናል ለማገኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን👇

©️Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
ለአምስት የውጭ አገር ባንኮች ፈቃድ ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ!

አምስት የውጭ አገር ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማትን ከማጠናከር ጎን ለጎን የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የባንኩ የገንዘብ ተቋማት ዘርፍ ምክትል ገዥ ሠለሞን ደስታ ለኢፕድ ገልጸዋል።

‹‹ሥራውን አሁን እያጠናቀቅን ነው፡፡ አዋጁን የመከለስ ሥራውንም እያጠናቀቅን ነው:: ከለጋሾች አንዳንድ ግብዓቶችን እየጠየቅን ነው:: በወራት ዕድሜ ለህዝብ እንደራሴዎች ይቀርባል:: ስለዚህ ሥራው እየተፋጠነ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም የገለጹት ምክትል ገዥው፤ የውጭ ባንኮች የአገር ውስጥ ባንኮችን ከገበያ እንዳያስወጧቸው የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት አቅም ግንባታ ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ለዚህም የተቀመጠ አሰራር መኖሩን አመልክተዋል::

ተቋማቱ ከመደበኛ በጀታቸው ኹለት ከመቶ የሚሆነውን ለአቅም ግንባታ እንዲያውሉትና፤ ይህም ለባንኮች ከረጅም ዓመታት በፊት የተላለፈ መሆኑን በመግለጽ፤ አሁንም ድረስ በዚሁ አግባብ ክትትል እንደሚደረግ ሠለሞን ጨምረው አስረድተዋል::

@YeneTube @FikerAssefa
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደ ቀድሞ መጠሪያው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሊቀይር ነው፡፡

የ98 አመቱ አንጋፋው የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ፣የአሁኑ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል።የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ በላይ ከፋለ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፣ታሪካዊ ስሙን ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብልዋል።

የትምህርት ቤቱ የቀድሞው ምሩቃን ኮሚቴ አዋቅረው፣ኮሌጁ በቀድሞው ስሙ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እንዲጠራ እየጠየቁ መሆኑን አቶ በላይ ተናግረዋል።ከሁለት ዓመት በኋላ አንድ ክፍለ ዘመን የሚሞላው ይህ አንጋፋ የትምህርት ተቋም መቶኛ ዓመቱን ሲያከብር በቀድሞው ስሙ እንደሚሆን ተገልጿል።

የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በ1917 ዓ.ም የተመሠረተና በደርግ ዘመነ መንግስት ወደ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደተቀየረም ምክትል ዲኑ አስታውሰዋል።አሁን ያለው ስያሜ የተቋሙን ታሪክና ቦታ የማይወክል በመሆኑ የቀድሞው ስሙ እንዲመለስለት ተጠይቋል።

ኮሌጁ አሁን ላይ 11 የትምህርት መስኮችና ከ 40 በላይ ስልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፍ ተቋም መሆኑንም አቶ በላይ ተናግረዋል።ኮሌጁ ከሁለት ዓመት በኋላ መቶኛ ዓመቱን በድምቀት ለማክበር ከወዲሁ ዝግጅት መጀመሩም ተገልጿል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ማምረት ጀመረ!

በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ወደማምረት ስራ ተሸጋገረ።ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ ሚድባስ እና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰጠኝ እንግዳው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 መኪኖችን ለመገጣጠም አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፈረንሳይ ፓሪስ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ፈረንሳይ መግባታቸው ይታወሳል።

በጉባዔው ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ ልዑል አልጋወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሰዴን ሶዶ የወረዳ አመራር ተገድለው መገኘታቸው ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከኹለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተገለጸ።የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው መገኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሃይሉ አብዶ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል።

ኃላፊው፤ "በቀለ ቃቻ በአዳማ ከተማ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ባለፈው ቅዳሜ ወደ ቤተሰብ ተመለሱ፤ በዕለቱ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ከቤታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።ቅዳሜ ምሽት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት የወረዳው አስተዳዳሪ ላለፉት ኹለት ቀናት የት እንዳሉ ሳይታወቅ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ተገድለው ተገኝተዋል ሲሉም ገልጸዋል።

የአስተዳዳሪው አስክሬን በቶሌ ወረዳ፣ ኢሉ ወረዳ እና በበቾ ወረዳ መካከል በጸጥታ ኃይሎች አሰሳ መገኘቱም ተመላክቷል።በቀለ፤ የወረዳው አስተዳዳሪ በመሆን ለኹለት ዓመታት ማገልገላቸው፤ ከዚያ በፊት በትውልድ አካባቢያቸው በዳዎ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ማገልገላቸውን ኃይሉ ገልጸዋል።

ኃይሉ፤ ለግድያው ተጠያቂው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት "ኦነግ - ሸኔ" የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሃይል መሆኑን ጠቅሰዋል።"አዎ፣ እንደ ሕዝብ ጥቆማ እንደዛ የሚባል ነገር አለ። በተግባር ከወረዳችን ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎች እየታገቱ ነው። የሚያግተው ይኸው አካል ነው። አንዳንድ ጠቆማዎችም አሉ፣ ታግተው የተለቀቁ ሰዎችም አሉ፡፡" ሲሉም ተናግረዋል።

መንግሥት 'ኦነግ ሸኔ' የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ስለ ውንጀላው እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።በመንግሥት ባለስልጣናት እና በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከት ግን ታጣቂ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ነበር።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከቤታቸው ከታገቱ ከአንድ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ በቀለ ቃቻ እንዲለቀቁ “10 ሚሊየን ብር” መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ፤ “ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ለወረዳው አስተዳዳሪ ቀደም ብለው የሰጡት ማስጠንቀቂያ / ዛቻ አለ? ወይንም በግላቸው ደውለውላቸው የጠየቁት ገንዘብ አለ? ተብለው የተጠየቁት ኃይሉ፤ የአስተዳዳሪው ስልክ በታጣቂዎቹ እጅ ስለገባ ይሄን ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል። "ዛቻ ወይም ማስጠቀቂያ እየተነዛበት እንደሆነ ሪፖርት ቀርቦ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ " ሲሉም አክለዋል።

ታጣቂዎቹ የወረዳውን አስተዳዳሪ ከእገታ ለማስለቀቅ የጠየቁት ገንዘብ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ግልፅ የሆነ ነገር ባይኖርም የተገደሉት "የጠየቁት ገንዘብ ስላልተሰጠ" ነው የሚል ግምት መኖሩንም ተመላክቷል።ኃይሉ ግን "ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ነገር ግን በቀጣይ ምርመራ ይታወቃል፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በኹለት ቀናት ውስጥ የጸጥታ ሃይሎች አስተዳደሪውን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል።የተገደሉት አስተዳዳሪ ከ30ዎቹ - 40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ባለትዳር እና የልጆች አባት ነበሩ።

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊው ኃይሉ፤ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነን የሚሉ የታጠቁ ሃይሎች (መንግሥት ኦነግ - ሸኔ የሚላቸው) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን እያገቱ ብዙ ገንዘብ እየጠየቁ በማሰቃየትና በመግደል ላይ ናቸው፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።"ፖለቲካ የማያውቁ እና ማንም ነገር ውስጥ የማይገቡ ገበሬዎችን በየቀኑ እያፈኑ፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እየተጠየቀ ነው።" ያሉት አቶ ኃይሉ፤ " ገንዘብ የሌለው ግለሰብ ኹለት መቶ ሺሕ ፣ ሦስት መቶ ሺሕ፣ አምስት መቶ ሺሕ ብር ዘመዶቹ እየሰበሰቡ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡" ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፤ ልጆቻቸውን የማገትና በአሰቃቂ ሁኔታ የመግደል ሁኔታ መጨመሩንም አስረድተዋል።የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኃይሉ አብዶ፤ "መፍትሄው እርስ በእርስ ከመገዳደል ፤ አንድ ቋንቋ እየተናገርን ከመጨራረስ ይልቅ በውይይት መፍታት ነው፡፡" ሲሉም ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ኹለት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ የወረዳ አስተዳዳሪ ሲገደል ይህ ለኹለተኛ ጊዜ ሺኆን፤ ሰኔ 1 ቀን በምዕራብ ሸዋ ዞን የአዳ ባርጋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አብዲሳ ቀነኒ በበካቴ ከተማ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በታጣቂዎች ተገድለዋል።በተያዘው ዓመት በመጋቢት ወር ላይ የነቀምት ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ ደሳለኝ በኮንጃ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች መገደላቸውም ይታወሳል፡፡

[BBC/Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ቢገለጽም አሁንም ችግሩ እንዳልተፈታ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑን ይታወሳል::

ይህንኑ እውነታ መነሻ በማድረግ በተለይ ከጣራና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ የቤት ክራይ ጭማሪ በነዋሪው ላይ እየተደረገ መሆኑን አንስቶ አሐዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የንብረት ግብር ማስተግበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ አስማማው ሙሉጌታ አነጋግሯል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ማረጋገጡን የገለጹት አቶ አስማማው ችግሩን ለማስወገድ እና በተከራዮች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ በተለያዩ ጊዜያቶች ከተማ አስተዳደሩ ህግ እያወጣ ቁጥጥር ለማድረግ እየጣረ መሆኑን አስታውሰው በተፈጻሚነቱ ላይ ካቢኔው ጠንካራ የሆነ አቋም መያዙንም ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ኩራዝ ቴክኖሎጂስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና የሚያዘጋጁ ኮርሶችን የያዘ አገልግሎት በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።

የኦንላንይን መማሪያዎችን የያዘዉ በኩራዝ ቴክኖሎጂ የበለፀገዉ የስልክ መተግበሪያ የተለያዩ የመማሪያ መፅሀፍትን ከእንላይን ኮርስ ጋር የያዘና ከየትኛውም ቦታ ሆኖ በቀላሉ ማግኘት የሚቻል ነው።

ኮሮሶቹን እንዲያዘጋጁ የተደረጉት  ከዚህ ቀድም የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተናን ወስደው 600 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች መሆናቸውን የኩራዝ ቴክኖሎጂስ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ብስራት ሀይሉ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን በስልክ እና ከዌብሳይቶች ላይ ማግኘት እንደሚቻል የገለፁት አቶ ብስራት ክፍያውንም በቴሌ ብር መፈጸም እንደሚቻል ገልፀዋል።ፕላትፎርሙን ለመጠቀም ለአንድ ኮርስ 150 ብር ክፍያን ይጠይቃል ተብሏል።

ይህንን ክፍያ በዲጂታል በማንኛዉም የዲጅታል መክፈያ አማራጭ መፈፀም እንደሚቻልም ተገልጿል።አዲሱ አገልግሎት "ኩራዝቴክ" ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲዘጋጁበት ከማስቻሉም ባሻገር ደራሲያን መጻህፎቻቸውን ለአንባቢያን በቀላሉ ተደራሽ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ተብሏል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ኢትዮጵያ ዘንድሮ ሕዳሴ ግድብን ለአራተኛ ጊዜ በውሃ ለመሙላት ዝግጅት ላይ መኾኗን ዛሬ በድንበር ዘለል ወንዞች አጠቃቀም ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ በመከረው የቀጠናው ከፍተኛ የሚንስትሮች ስብሰባ ላይ መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ደመቀ፣ “ሕዳሴ ግድብ የአገራት የጋራ ሃብት የኾነውን ወንዝ ለብቻቸው መጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎችን አሉታዊ ትርክት በመቋቋም፣ ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ እየተቃረበ" መኾኑን ገልጸዋል ተብሏል። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ፣ ደመቀ "ሕዳሴ ግድብ የፍትሃዊና ምክንያታዊ ውሃ አጠቃቀም ተምሳሌት ነው" በማለት መናገራቸውን በትዊተር ገጹ ገልጧል። በስብሰባው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ተገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
1
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
👍2
#ADVERTISEMENT

👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ

📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠

💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ

ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel