YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቢዮንሴ በስዊዲን ያዘጋጀችዉ ኮንሰርት በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ

የስዊድን የዋጋ ግሽበት በግንቦት ወር ከ10 በመቶ በታች ማሽቆልቆሉን አሀዛዊ መረጃዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡ ነገር ግን በተወሰኑ እቃዎች እና የአገልግሎት ዋጋ ወጪዎች በድንገት ጨምሯል፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ቢዮንሴ ወደ ስዊዲን በመምጣቷ የተነሳ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በግንቦት ወር የሸማቾች የምርት ዋጋ በ9.7 በመቶ ጨምሯል፣ በሚያዝያ ወር ከነበረው 10.5 በመቶ ቀንሷል፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ከስድስት ወራት በኃላ ከ10 በመቶ በታች ደርሷል።"የቀጠለው የኤሌትሪክ እና የምግብ ዋጋ መቀነስ በግንቦት ወር ዝቅተኛ የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ አድርጓል" ሲሉ የስታስቲክስ ስዊድን የስታስቲክስ ባለሙያ የሆኑት ሚካኤል ኖርዲን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ሆኖም ግን የአንዳንድ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ወጪዎች ጨምረዋል፣ “ለአብነት የሆቴልና ሬስቶራንት ጉብኝቶች፣ የመዝናኛ አገልግሎቶች እና አልባሳት” ላይ ጭማሪ መታየቱን የስታስቲክስ ኤጀንሲው ገልጿል።በዳንስኬ ባንክ የስዊድን ዋና ኢኮኖሚስት ማይክል ግራህን እንዳሉት “ቢዮንሴ በስዊድን የዓለም የሙዚቃ ስራዎቿን የማቅረብ ጉዞ በግንቦት ወር የጀመረች ሲሆን ግሽበትን አስከትሏል ፣ ምን ያህል ለሚለዉ እርግጠኛ አይደለንም” ብለዋል።

በግንቦት ብዙ የተነገረላቸው ኮንሰርቶች በሆቴሎች እና በሬስቶራንቶች የዋጋ ግሽበት አስከትለዋል፡፡በሰባት አመታት ውስጥ የመጀመሪያውን የሙዚቃ ጉዞ የጀመረችው ድምጻዊቷ ሁለቱን ኮንሰርቶች ለማየት በግንቦት ወር አጋማሽ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ስቶክሆልም ከተማ ጎርፈዋል።


ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @fikerassefa
አየር መንገዱ 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 13 ነጥብ 7 ሚሊየን መንገደኞች ማጓጓዙን ተናግረዋል፡፡

በኮቪድ-19 ወቅት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎችን ከመመለስ በተጨማሪ ወደ ሰባት አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩንም አንስተዋል፡፡

የአውሮፕላን ቁጥርን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 12 አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡በአየር መንገዱ የጥገና እና ምህንድስና ማዕከል ከመንገደኛ ወደ ጭነት አገልግሎት ሰጪነት የተቀየሩ ሁለት አውሮፕላኖች የካርጎ ስራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰማኮ በደሞዝ ማሻሻያ ጉዳይ ላይ ባነሳቸው ጥያቄዎች የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ጠርቶ እስኪያነጋግራቸው እየጠበቁ መሆናቸው ተገለጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ዳግም የደሞዝ ማሻሺያን እና ዝቅተኛ የደሞዝ እርከን እንዲወጣ የሚሉ ጥያቄዎችን በላባዳሮች ቀን አከባበር ላይ በሰለማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንቅስቃሴ ከተደረገ በኃላ ሰልፉ መከልከሉ የሚታወስ ነው ፣ ታዳይ አሁን ላይ ጥያቄያችሁ ከምን ደረሰ ሲል አሐዱ ኢሰማኮን ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው አህመድ ለአሐዱ እንደገለጹት በወቅቱ ከነበረው የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር የአዲስ አበባ ፀጥታ ቢሮ ሰልፉን ማድረግ ቢከለከልም በሰልፉ ላይ ልንጠይቃቸው በነበሩ ሁሉም ጥያቄዎች ላይ እንዲያነጋግሩን በኮንፈዴሬሽኑ ስር በሴክተር ከተደራጁ ሌሎች 9 የኢንዱስትሪ ፌደሬሽኖች ጋር በጋራ በመሆን ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ደብዳቤ አስገብተናል ብለዋል፡፡

ከደሞዝ የሚቆረጥ ታክስን መቀነስ በተመለከተ ደግሞ ጥያቄያችንን ለገንዘብ ሚኒስቴር አስገብተናል ብለዋል፡፡በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ላይ የተደነገጉ አሰሪ ፣ ሰራተኛ እና መንግስት እንደዚህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት የሶስትዮሽ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ ይደነግግጋል ፡፡በዚህም መሰረት ደብዳቤ አስገብተን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ውይይቱን በማዋቀር ላይ ፣ በቅርቡ ይጠሩናል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በጊዜያዊነት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታገደ!

በቻይና ሀገር የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በቻይና ሀገር ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ የሚገኘው ቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሕጋዊ የሆነ ፈቃድ አለመኖሩን የጀርመኑ ኩባንያ በኤንባሲው በኩል በደብዳቤ ለሚኒስቴሩ ማሳወቁ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በቻይና ሀገር የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከኩባንያው ሕጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስከሚረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል በማድረግና የሕጋዊነት ማረጋገጫ መረጃዎችን የማጥራት ስራም በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሠራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲመረቱ፣ እንዲገጣጠሙና ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ለይቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ ለማስቀየር እየተንቀሳቀስኩ ነው አለ!

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን ለማስቀየር ዲፕሎማስያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ሕጋዊነት ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ፣ የሰላም ስምምነቱን የሚጎዳ ነው ሲል ፓርቲው ገልጿል።በሌላ በኩል ህወሓት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው ወደ ፍርድቤት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረመው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት አስቀድሞ ተሰርዞ የነበረው ሕጋዊ ሰውነቱ ለማስመለስ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማስያዊ ጥረት ማድረጉ እንደሚቀጥል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በትላንትናው የህወሓት መግለጫ እና በህወሓት እና የምርጫ ቦርድ ውዝግብ ዙርያ አስተያየታቸው ያጋሩን የሕግ ምሁሩ ሙስጠፋ ዓብዱ፣ ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ለመቀልበስ እንደሚፈልግ ማሳያ ብለውታል።

ምርጫ ቦርድ በህወሓት የሕጋዊ ሰውነት ዙርያ ያስተላለፈው ውሳኔ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ የሚገልፁት የሕግ ሙሁሩ ሙስጠፋ ዓብዱ፥ በመሰረቱም ጉዳዮ የአንድ ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ ውዝግብ አድርጎ መመልከት እንደማይገባ፣ ሊያስከትለው የሚችል ችግርም ታሳቢ በማድረግ ተገቢ ምላሽ ልያገኝ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ።

ከዚህ ውጭ ህወሓት በትላንትናው መግለጫው የፌደራሉ መንግስት የትግራይ ሕገመንግስታዊ ግዛት እንዲያስከብር፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የበኩሉ እንዲወጣ የጠየቀ ሲሆን ወደ ትግራይ የተቋረጠው ሰብአዊ እርዳታም እንዲቀጥል ጥሪ ከቅርቧል። ህወሓት በመግለጫው መጨረሻ 'ያለንበት ምዕራፍ የተወሳሰበ ነው' ያለ ሲሆን፣ ህወሓትን ለማፍረስ እንቅስቃሴ መኖሩንም በመግለጫው አስታውቋል። ይህም በላቀ ጥበብ እንደሚታገለው ገልጿል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሓት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም የቀረበ የቅድመ እውቅና ጥያቄ አለመቀበሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ዕለት ባሰራጨው ደብዳቤ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ ብሎ ባሰራጨው ደብዳቤ በህወሓት ስም ለረዥም ግዜ የሚታወቅ ፓርቲ በመኖሩ ይህም በህዝብ ዘንድ መደናገር የሚፈጥር በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ አለመቀበሉ አስረድቷል። ጥያቄው ያቀረቡ አካላት የቦርዱ ውሳኔ ይቃወማሉ። ጥያቄው ካቀረቡት መካከል ከሆኑት አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ " እኛ ከታሪክ ጋር መያያዝ የለብንም። እኛ መብታችን ነው የጠየቅነው።ህወሓት የሚባል ፓርቲ ደግሞ የለም ተሰርዟል። ምርጫ ቦርድ ራሱ ነው የሰረዘው። ከተሰረዘ ስሙ ነፃ ነው" የሚሉ ሲሆን፣ መደናገር ይፈጥራል ለሚለው ደግሞ "ለህዝቡ ማስረዳት የኛ ስራ ነው፣ ምርጫ ቦርድ አይመለከተውም" ሲሉ አክለዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ገብረሚካኤል በቀጣይ ጉዳዮን ወደ ፍርድቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል።

[ዶቼ ቬለ]
@YeneTube @FikerAssefa
1
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
#የቻናል_ጥቆማ

🔔 የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
🔔 በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

🔥 እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ
     ቻናል እንጠቁመዎት 👇👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

📚 በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
👉 የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
👉 በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

Join us on Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
https://tttttt.me/ethioengineers1
ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!

የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!

Download Tuba: https://tuba.et

@tuba_books @tuba_books
በሃዋሳ ከተማ በተፈጸመው ከተማሪ ሜላት መሃመድ ጠለፋ ጋር በተገናኘ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ተማሪ ሜላት መሃመድ ከትምህርት ቤት ተመልሳ ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት በሁለት ተሽከርካሪ መጠለፏን ቤተሰቦቿ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ከዚህ የጠለፋ ድርጊት ጋር በተገናኘ 8 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንና እየተደረገ በሚገኘው ክትትልም ጠላፊውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዘን ይፋ እናደርጋለን ሲሉ የተናገሩት የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ናቸው፡፡

በቅርቡ ተጠልፋ የነበረችውና ከቀናቶች በኃላ ነጻ የሆነችው ጸጋ በላቸውም ይሁን በተማሪ ሜላት መሃመድ ላይ የተፈጸሙት ጠለፋዎች በምርመራ በተረጋገጠው መሰረት ከዚህ በፊት በነበሩ ትውውቆች ላይ የተመሰረቱ እንጂ በማያውቁት ሰው የተፈጸመ እገታ አይደለምም ብለዋል፡፡

በከተማው በግለሰብ ደረጃ ከሚያጋጥሙ ጥቃቅን ወንጀሎች በስተቀር በክልሉ በሚነገረው ልክ የዝርፊያ እና እገታ ወንጀሎች እየተፈጸሙ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ችግሮችም ለዜጎች የመኖር ዋስትናን ሊያሳጡ የሚችሉ ጉዳዮች አይደሉም ሲሉ ነዉ ሃሳባቸዉን የገለጹት፡፡

መንግስት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ግዴታው በመሆኑ የክልሉ የጸጥታ ሃይል አስፈላጊውን ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ህወሓት በጦርነቱ ለማገዳቸው ታጣቂዎች ሰብዓዊ እርዳታዎችን አሳልፎ በመስጠት የራሱን ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያስጠብቅ ለማድረጉ ዋነኛ ተጠያቂው የፌደራል መንግሥት ነዉ ሲል ኢዜማ ከሰሰ

👉🏼ኢዜማ ፤ ብልጽግና ሰብዓዊ እርዳታዎችን ለፖለቲካዊ ትርፍ ይጠቀምበታል
ብሏል

ኢዜማ ፤ ከሰሞኑ የመንግስት የሞራል ማጣት ልጓም እጅጉኑ በመክፋቱ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የሚያቀርቧቸው ሰብዓዊ ዕርዳታዎች በመንግሥት ኃይሎች እየተዘረፉ ለችግሩ ተጠቂዎች ከመድረሳቸዉ ይልቅ ለሌላ ዓላማ እየዋሉ መኾኑን ጠቅሰው ፤ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የዕርዳታ መርኃ ግብር ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል ብሏል።

መንግሥት በቂ የሆነ ምርት እንዲኖር የማስቻል ስራውን በተገቢው ሁኔታ አለመወጣቱ ሃገሪቱን ለእርዳታ መዳረጉ እና በዜጎች ላይ የተረጂነት እና ጥገኝነት መንፈስ እንዲሰፍን ማድረጉ ሳያንስ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ህይወታቸውን ማቆያ የሚሆንን የእርዳታ እህል መዝረፍ እና እንደ ሃገር መከላከያ ያሉ ተቋማትን ስም በሚያጠለሽ ሁኔታ እንዲነሳ ማድረጉ የመንግሥት የሞራል ዝቅጠትን ጥግ ያሳያል ሲል ኮንኗል።

ይህ የተረጂነት መንፈስ የሚፈጥረው የመንፈስ ስብራት እንዳለ ሆኖ በባሰ መልኩ ለዜጎች መዋል የነበረበትን ፍጆታ ለግል ጥቅም ማዋል ባስ ሲልም በአደባባይ ለሽያጭ ማቅረብ፣ የተጋነነ የተረጂዎችን ቁጥር በማቅረብ በሌሉ ሰዎች ስም እርዳታን መቀበል እና የእርዳታው ተጠቃሚዎችን ከተተመነላቸው ድጋፍ በታች በመስጠት ትርፍን መውሰድ አይነት አሳፋሪ ተግባሮች ሲፈጸሙ ይስተዋላል ሲል ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡

ሌላኛው በተደጋጋሚ እንደታዘብነው መንግሥታዊ ተቋማት ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እና ድጋፎችን እርዳታ የሚደረሳቸውን ዜጎች ነፃነት በሚነጥቅ ሁኔታ  ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ አድርገው ይጠቀሙበታል ያለዉ ኢዜማ ፤ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚኾነው ብልፅግና ፓርቲ ከኢሕአዴግ በወረሰው መጥፎ ጠባይ ፤ ባለፈው ሃገራዊ ምርጫ የገጠር እና የከተማ ሴፍቲኔት መርኃግብሮችን ለምርጫ ድምፅ መግዣ አድርጎ በስፋት ተጠቅሞበታል ሲል ከሷል፡፡ “ብልፅግናን ካልመረጣችሁ የሴፍቲኔት ድጋፉን እናቋርጣለን” በሚል ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማስፈራሪያ እንዲሁም ለሴፍቲኔት ፕግራም የተመደቡ በጀቶችን ለምርጫ ቅስቀሳ ጥቅም ላይ የማዋል ተግባራት ሲፈጸሙ እንደነበር የአደባባይ ሀቅየ ነው ብሏል፡፡

በምጽዋት የሚሰጥን ፍጆታ ከዜጎች ጉሮሮ የመንጠቅ ሞራል ካለው ሃገሪቱ የምታመርታቸውን ምርቶች ዋጋ ሆነ ብሎ እንዲያጋሽብ የማያደርግበት፣ ፍጆታዎች ሆነ ተብለው በየማከማቸው የማይደበቁበት፣ ለአርሷደሮች የሚመጣ ማዳበሪያ ሆነ ተብሎ እንዲነፈግ የማይደረግበት እና በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ በየትኛውም መልኩ የሚፈጠር ትርምስ አትራፊ ያደርገኛል ብሎ ካመነ ምንም አይነት ነገር ከማድረግ እንደማያቆም ማሳያ ግልጽ ተግባር ነው ሲል ጠንከር ያለ መግለጫ አዉጥቷል።

እንዲህ አይነት መልካም አስተዳደር የጎደለበት ሥርዓት በምጽዋት የሚሰጥን ፍጆታ ከዜጎች ጉሮሮ የመንጠቅ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ዝቅጠት እና ወንጀል የማኅበረሠባችንን እሴት እጅጉን የሚፈታተን አፀያፊ ተግባር እንደሆነ ሊታወቅ ይገባልም ብሏል።

መንግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ የፌደራል መንግሥቱ ሊኖረው የሚገባውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው  ለህወሓት ያልተገደበ ነፃነት ሰጥቶ ትንፋሽ እንዲዘራ እና ትግራይ ክልልን መልሶ እንዲቆጣጠር በማድረጉ ምክንያት ከአንድ ወር በፊት በክልሉ ሰብዓዊ ዕርዳታዎች ላልተገባ ዓላማ እየዋሉ መኾኑን በመጥቀስ የዕርዳታ ድርጅቶች ድጋፋቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡ የትግራይ ህዝብ አሁንም ተመልሶ ለከፋ ርሃብና እጦት ሲጋለጥና ህወሓት በተመቻቸለት ነፍስ የመዝራት ዕድል ተጠቅሞ ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እየደረሱበት ያሉ ተቃውሞዎችን ለመከላከል  በጦርነቱ ለማገዳቸው ታጣቂዎች አሳልፎ በመስጠት የራሱን ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያስጠብቅ ለማድረጉ ዋነኛ ተጠያቂው የፌደራል መንግሥት መኾኑ ሊሰመርበት ይገባል ብሏል፡፡

በመኾኑም፤ መንግሥት በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚቀርብ ድጋፍን ከብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ እንዲያከናውን የተጣለበትን ግዴታን እንዲሁም በረዥም ጊዜ ሂደት ሃገሪቱን ከተመጽዋችነት የምትላቀቅበትን ምርታማነትን የማሳደግ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጠይቋል፡፡ በየትኛውም ደረጃ የሚደረግን ሰብዓዊ ዕርዳታ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለምርጫ ቅስቀሳ እና ለገፅታ ግንባታ የመጠቀም አባዜም በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስቧል፡፡

ዓለምአቀፍ የተራድዖ ድርጅቶችም በስግብግብ መንታፊ መንግሥታዊ አሠራር ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን የሚጎዳ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተገንዝበው ከመንግሥት ጋር በጋራ የጀመሩትን እነዚህን ወንጀለኞች ሕግ ፊት የማቅረብ ጥረት ማጠናከር እና የእርዳታው ተደራሽነት ላይ ቀደም ካለው ጊዜ በበለጠ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ከእርዛት እና መከራ እንዲያወጡ ሲል ጠይቋል።

መንግሥት ይህን አሳፋሪ እና አፀያፊ ተግባር  ከዚህ ቀደም ተድበስብሰው እንደቀሩ ሌብነቶች በአንድ ሰሞን ግርግር እንዳያልፍ ይልቁንም  ከምንም ነገር አስቀድሞ መንግሥት በይፋ ወጥቶ ይህንን ቆሻሻ ተግባር ከማመን በተጨማሪ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ የድርጊቱ ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ገለልተኛ አካል ታክሎበት እንዲታይ፣ ሂደቱም በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን እና በመጨረሻም ፍትህ ሲሰፍን በግልጽ ሊያሳይ ይገባል ሲል ፓርቲዉ ባወጣዉ መግለጫ አሳስቧል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ኮምፒውተሮች እና ንብረቶች እየገዙ በቅናሽ የሚሸጡ ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ!

ግምታቸው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ኮምፒውተሮች ከአራት ተጠርጣዎች ጋር መያዙንና በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ግለሰቦቹ ህጋዊ የንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቁ ንብረቶችን እየገዙ በቅናሽ ሲሸጡ መያዛቸውን የጠቀሰው ፖሊስ የተሰረቁ እቃዎች በሚገዙ ግለሰቦች ላይ እያደረገ ያለውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ወረዳ ስምንት ይርጋ ኃይሌ ህንፃ ውስጥ የተሰረቁ እቃዎችን እየገዙ በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ባደረገው ክትትል ከተለያዩ ቦታዎች የተሰረቁ ግምታቸው 1 ሚሊዮን 210 ሺሕ ብር የሚያወጡ 42 ላፕቶ፣ 12 የዴስክ ቶፕ ሞኒተሮችንና አንድ ኪቦርድ በኤግዚቢትነት መያዙን ገልጿል፡፡

ህጋዊ የንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድግ የተሰረቁ እቃዎችን ገዝተው በቅናሽ ዋጋ የሚሸጡ ግለሰቦች ህጋዊ መንገድን ተከትለው በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ከሚያሳድሩት ጫና ባሻገር ለወንጀል መስፋፋት ምክንያት በመሆናቸው ችግሩን ለመከላከል ተግባራት ህጋዊ ነጋዴዎች ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከዚህ ቀደም ላፕቶፕና የዴስክ ቶፕ ኮፒውተሮችና ሞኒተሮች የጠፋባቸው ግለሰቦች አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከማስረጃ ጋር በመቅረብ ንብረቶቻቸውን መለየት እና መረከብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከቀድሞ ምሩቃኖቹ ጋር በአዲስ አበባ ሊመክር ነው!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታው ጀምሮ አስተምሮ ያስመረቃቸውን ተማሪዎች በማሰባሰብ ዩኒቨርሲቲውን ለመደገፍ በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ሊወያይ መሆኑን የተቋሙ አልሙናይ ጉዳዮች ጽ/ቤት አሳውቋል።

በዚህ 4ኛው ልዩ የአልሙናይ መድረክ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃንም ተከታዩን ሊንክ https://docs.google.com/.../1dDKoiPTCpctmpoZNnFEM2ZA.../edit በመጠቀም የመመዝገቢያ ቅጹን እንዲሞሉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ/ኢባትሎ በሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች የቀየራት ግዙፏ ሁለገብ የጭነት መርከብ በመጪው ሰኔ 17 ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የወደብ ማእከል፣ ጅቡቲ መህልቋን እንደምትጥል ተገለፀ።

አባይ 2 የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች መርከብ ድርጅቱ በ60 አመት ታሪኩ አስተዳድሮ የማያውቀው ግዙፍ መርከብ ነች። የመጫን አቅሟ 65ሺ ቶን የሆነችው አባይ 2 (በመጫን አቅሟ በዘርፉ አልትራማክስ የሚል መጠሪያ ትታወቃለች) በወቅቱ የሎጅስቲክ ዘርፍ እንቅስቃሴ በጣም አዋጭ ሆና በመገኘቷ ነው በለውጥ የተወሰደችው።

በአንፃሩ ከተገዙ 11 አመት የሆናቸው ሁለት የነደጅ ጫኝ መርከቦች ያለበቂ ጥናት የተገዙ እንደነበር ሲገለፅ ቆይቷል። በመሆኑም ከተገዙ በኋላ ለበርካታ ወራት በጅቡቲ ወደብ ቆመው ከቆዩ በኋላ የወቅቱ የድርጅቱ አመራር በሌላ ኩባንያ እንዲተዳደሩ አድርጎ ነበር። ሆኖም ለድርጅቱ አትረሰፊ እንዳልነበሩ ነው የሚታወቀው።በመሆኑም ድርጅቱ መርከቦቹን ለመሸጥ አልያም በአዋጭ መርከብ ለመቀየር ሲንቀሳቀስ ከአመት በላይ በርካታ ሂደቶችን አልፎ ባለፈው መጋቢት የመርከብ ቅያሬ ድርድሩ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቅ ችሏል።

ድርጅቱ መሰል አልትራማክስ ግዙፍ መርከቦችን ከሌሎች የመርከብ ድርጅቶች በመከራየት ማዳበሪያ፣ የከሰል ድንጋይ፣ እህል፣ ስኳር እና ስንዴ ወደ ኢትዮጵያ ሲያጓጉዝ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአባይ ሁለት መምጣት ይህን የመርከብ ኪራይ እንደሚቀንስለት ኩባንያው መግለጹ ይታወሳል፡፡በመተሳሳይ ኩባንያው በሌሎች ወደቦች ጭነት በማድረስ በውጭ ምንዛሬ የሚገኘውን ገቢ በይበልጥ እንደሚሳድግለት ነው የተናገረው፡፡ በተለይ የግዙፍ መርከቦች ባለቤት መሆን እራቅ ላሉ የወደብ መዳረሻዎች እቃ እንዲያጓጉዙ እድል የሚፈጥር በመሆኑ አዋጭነታቸው ከፍ የሚል መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ከኢትዮጵያ ጭነቶች በተጨማሪ የሌሎች አገራት ጭነትን በማጓጓዝ/ክሮስ ትሬድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያገኘ መሆኑ ይታወቃል፡፡የመሰል ግዙፍ መርከቦች ባለቤት እየሆነ መምጣቱ ደግሞ ይህን ስራውን በይበልጥ እንደሚያሰፋለት ነው ያስታወቀው፡፡

ወደ ስራ ከገባች የ 7 አመት እድሜ ያላት እና በማርሻል አይላንድስ ተመዝግባ በጀርመን የመርከብ አንቀሳቃሽ ድርጅት ስራ ላይ የነበረችው አባይ 2 በኢባትሎ ባለቤትነት እና ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ከቻይና ሻንሃይ ወደብ ተነስታ ወደ ስራ ከገባች ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ የተለያዩ ጭነቶችን በመያዝ ወደ ኮርያ እና ቬትናም ያደረሰች ሲሆን አሁን ላይ ከፍተኛ የብረት ጭነት ይዛ ወደ ሰሜን አውሮፓ፣ ባልቲክ ባህር እያመራች ነው።

በተመሳሳይ ኢባትሎ ሌሎች ሁለት 65 ሺ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው አልትራማክስ መርከቦችን ለማስገንባት ከቻይና የመርከብ ገንቢ ጋር ድርድር የጨረሰ ሲሆን በቅርቡ ውል እንደሚያስር ይጠበቃል፡፡ ግንባታው ከተጀመረ በኋላም ለመረከብ ሁለት አመት እንደሚፈጅ የሚገመት ሲሆን የመርከቦቹ መምጣት የድርጅቱን የማጓጓዝ እንቅስቃሴ እና የውጭ ምንዛሬ ገቢውን በይበልጥ እንደሚያሰፋለት ተስፋ ተጥሏል፡፡

ዛሬ ላይ ከአባይ 2 በተጨማሪ ኢባትሎ 9 ሁለገብ መርከቦች ያሉት ሲሆን የመጫን አቅማቸው በዘርፉ ሃንዲሳይዝ በመባል የሚታወቁ እና በአነስተኛ ደረጃ ወይም የመጫን አቅማቸው ከ28 ሺ ቶን የማይበልጥ ነው፡፡ይህም መርከቦቹ በመካከለኛ የርቀት መዳረሻ ላይ ብቻ እንዲተኩሩ አድርጓቸዋል፡፡በመንግስት ስር ከሚተዳደሩ ግዙፍ እና አትራፊ የልማት ድርጅቶች መካከል ኢባትሎ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደብ ነው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ውስጥ ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ውስጥ ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ታጣቂዎቹ ንብረት ላይም ጉዳት ማድረሳቸውን እና የቁም እንስሳት መዝረፋቸውንም ያነጋገርናቸው የኪረሙ ወረዳ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ የምስራቅ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ለሜሳ ደሬሳ በኪረሙ ወረዳ ጽንፈኛ ያሏቸው ሀይሎች ጉዳት ማድረሳቸውን በስልክ ተናግረዋል፡፡ የኪረሙ ወረዳ ኮሙኒኬሽን በማህራዊ መገናኛ ዜደው እንደጠቀሰው በደረሰው ጥቃት የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 13 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ መድረሱን አመልክተዋል፡፡

የጸጥታ ችግር በተደጋጋሚ በተከሰተባቸው የምስራቅ ወለጋ ዞን እና የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ በተለያየ ስም በሚንቀሰቃሴ ታጣቂዎች የሚደርሰው ጥቃት ትኩረት እንደሚሻ ከዚህ ቀደም የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ዋስት በተባለች አንድ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ትናንት የታጣቁ ሐይሎች በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውም ተገልጸዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁም እንስሳት መዝረፋቸውን አቶ ኦሊ ጃርሶ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ ትናንት ማለዳ 12፡00 ሰዓት ገደማ በተለያዩ አቅጣጫ ወደ መንደር በመግባት ጥቃት በማድረስ ዝርፍያ መፈጸማቸውን አብራርተዋል፡፡

" በሶስት አቅጣጫ በማለዳ 12 ሰዓት ላይ ተኩስ ሲከፍቱ በአካባቢው ያሉት የታጠቁ ሚሊሻዎችና ህዝቡ ራሳቸውን ለመከላከል ሞከሩ ሌሎች ደግሞ ሸሹ፡፡ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፈዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ቆስለዋል፣ ከብቶችም ተወስደዋል፡፡ በበአባይ በረሃና በዋስት ቀበሌ አዋሳኝ ቦታዎች ጥቃት እየደረሰ ነው፡፡ የጸጥታው ሁኔታ በጣም አስጊ ነው፡፡ "

ትናንት በኪረሙ በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ያልታጠቁ እና በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ሰዎች እንደሆኑ ሌላው ነዋሪ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ 15 በሚደርሱ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱንና የጠፉ ሰዎችም እየተፈለጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ወደ ጊዳ አያና ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ጤና ጣቢያ ለህክምና መላካቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የምስራቅ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና ጸጥታ ጽ/ቤት በበኩሉ በኪረሙ ወረዳ የታጠቁ ጽንፈኛ ሀይሎች ጉዳት ማድረሳቸውን አመልክተዋል፡፡ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ኮሎኔል ለሜሳ ደሬሳ በኪረሙ ወረዳ ዋስቲ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ የመንግስት ጸጥታ ሐይሎች ወደ ስፋራው መሰማራታቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል፡፡ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ያረጋገጡ ሲሆን የጉዳት መጠኑ ወደ ስፍራው የተሰማራው የጸጥታ ሐይል በኩል ተመዝግቦ ሲጠናቀቅ እንደሚገልጹ አመልክተዋል፡፡

"በኪረሙ ወረዳ በረሃ ዋስቲ በሚባል ቀበሌ ውስጥ የታጣቁ ጽንፈኛ ሀይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፍታቸውና ጉዳት መድረሱን ሪፖርት አለን፡፡በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን እየተጣራ ነው፡፡ ከብት መዝረፍና መንዳት አልፎ አልፎ ይስተዋል ነበር፡፡ አሁን ግን በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ ጉዳት መድረሱን መረጃ ደርሶናል፡፡ "

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ የተባሉ ወረዳዎች ውስጥ ለረጅም ጊዜ በቆየው የጸጥታ ችግር ሳቢያ የሰው ህይወት መጥፋትን ጨምሮ ከ63ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው ቆይተዋል፡፡በኪረሙ ወረዳ አጎራባች በሆነው አሙሩ ወረዳ በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እና ሐሙስ በታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት ወደ አምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተዘግበዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
#የቻናል_ጥቆማ

🔔 የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
🔔 በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

🔥 እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ
     ቻናል እንጠቁመዎት 👇👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

📚 በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
👉 የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
👉 በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

Join us on Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
https://tttttt.me/ethioengineers1
ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!

የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!

Download Tuba: https://tuba.et

@tuba_books @tuba_books
በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የወለዱ እናቶች፥ በአሳሳቢ የምግብ፣ የሕክምና እና የመጠለያ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተናገሩ፡፡

ወይዘሮ ለምለም ወንዳፍራሽ፣ ከምሥራቅ ወለጋ ዞን ሲቡስሬ ከተባለ አካባቢ፣ የስድስት፣ የ10 እና የ14 ዓመት ዕድሜ ካላቸው ሦስት ልጆቻቸው ጋራ ተፈናቅለው፣ ደብረ ብርሃን የደረሱት ፣ በያዝነው ዓመት ኅዳር ወር ላይ ነው፡፡የአራት ወር ነፍሰ ጡር ኾነው ከቀዬአቸው የወጡት ወይዘሮ ለምለም፣ አራተኛ ልጃቸውን በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ውስጥ ከወለዱ፣ ገና ሁለት ወራቸው ነው፡፡ለመውለድ ምቹ ባልኾነ መጠለያ ውስጥ፣ በቂ የምግብ አቅርቦት ሳያገኙ አራስ መኾን ከባድ እንደኾነ፤ ይናገራሉ፡፡ወደ ደብረ ብርሃን ከመምጣታቸው በፊት፣ ሦስት ልጆቻቸውን ሲወልዱ፣ የአራስ ወጉ እንዳልተጓደለባቸው የሚናገሩት ወሮ. ለምለም፣ አሁን ግን ሁሉም ነገር እንደከበደባቸው አልደበቁም፡፡

የሦስት ልጆቻቸው አባት፣ ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በተቀሰቀሰው የጸጥታ ችግር፣ በሰው እጅ ሕይወታቸውን እንዳጡ የሚናገሩት ወሮ. ለምለም፣ የአራተኛ ልጃቸው አባትም፣ መፈናቀሉ ባስከተለባቸው ፈተና ተማርረው፣ ወደማያውቁት ቦታ ጥለዋቸው እንደሔዱ ገልጸዋል፡፡ ይህም፣ የመፈናቀል እንግልት፣ ካደረሰባቸው አካላዊ ጉስቁልና ባሻገር፣ ለሥነ ልቡና ጫና እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡የወሮ. ለምለም ቅርብ ቤተሰብ እንደኾኑ የሚናገሩት ሚኪያስ ጉርባው፣ ወላዷ፥ በእርግዝናቸው ወቅትም ኾነ ከወለዱ በኋላ፣ አስቸጋሪ ጊዜያትን ማሳለፋቸውን አውስተዋል፡፡

መፈናቀል፣ ለፍቺ ምክንያት እየኾነ እንደመጣ አቶ ሚኪያስ ጠቁመው፣ በዚኽም ዋና ተጎጅዎቹ፣ ሴቶች እና ሕፃናት ናቸው፤ ብለዋል፡፡

ከምሥራቅ ወለጋ ዞን ዋዩ ጡቃ ወረዳ ልዩ ስሙ መኮፋ ከሚባለው አካባቢ የመጡት ካሳነሽ ሐሰን ደግሞ፣ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በሽሽት ላይ ባሉበት መንገድ ላይ መውለዳቸውን ይናገራሉ፡፡እናቶቹ፣ በቂ ምግብ እና መጠለያ አለማግኘታቸው፣ በሕፃናቱ እድገትም ኾነ በእነርሱ ጤና ላይ ተጽእኖ እንዳይፈጥር ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ወ/ሮ ለምለምም ኾኑ አቶ ሚኪያስ፣ በዚኽ ኹኔታ እስከ መቼ ይዘለቃል፤ የሚል ጥያቄም ያነሣሉ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(UN-OCHA)፣ ከአንድ ቀን በፊት ባወጣው ወቅታዊ ሪፖርቱ፣ በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ፣ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እና የሕክምና ቁሳቁስ አቅርቦት የሚያስፈልጋቸው፣ የሚያጠቡ እና ነፍሰ ጡር እናቶች፣ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የኾኑ ሕፃናት ቁጥር ጨምሯል፡፡ በዚኽም የምግብ ድጋፉ አስፈላጊነት፣ አንገብጋቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ብሏል፡፡

በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ውስጥ፣ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡት የጤና ባለሞያው በለጠ ዓለማየሁ፣ ከሳምንታት በፊት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ለሕክምና ከሚመጡት አብዛኞቹ፣ የምግብ እጥረት ያለባቸው ሕፃናት እና እናቶች እንደኾኑ ተናግረው ነበር፡፡ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ልዩ ዞኖች የመጡ፣ 30ሺሕ የሚደርሱ ተፈናቃዮች፣ በደብረ ብርሃን ውስጥ ባሉ ስድስት መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa