YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ምርጫ ቦርድ "ሕወሃት" በሚል ስያሜ ትግራይ ውስጥ አዲስ ክልላዊ ፓርቲ ለማቋቋም ያሰቡ ግለሰቦች ያቀረቡን የፓርቲ ቅድመ እውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ዛሬ አስታውቋል።

ቦርዱ፣ የትግራይ ክልል ነዋሪ የኾኑ ሦስት ግለሰቦች የ120 የፓርቲ መስራቾችን ስም ዝርዝር በማያያዝ፣ ቦርዱ ለአዲሱ ፓርቲ የቅድመ እውቅና ፍቃድ እንዲሰጥላቸው ማመልከቻ ማቅረባቸውን ገልጧል። ኾኖም አዲስ የሚቋቋም ማንኛውም ፓርቲ የሚይዘው ስያሜ በምርጫም ኾነ ከምርጫ ውጭ በዜጎች ዘንድ መምታታትና ግርታ የማይፈጥር መኾን እንዳለበት በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ላይ እንደተደነገገ ቦርዱ ጠቅሷል። ከሕጉ አንጻር አዲሱ ፓርቲ ስያሜ ለበርካታ ዓመታት በትግራይና ከትግራይ ውጭ "ሕወሃት" በሚል ሥያሜ ከሚታወቀው ፓርቲ ጋር አንድ ዓይነት መኾኑን የገለጠው ቦርዱ፣ ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው ለጥያቄው አቅራቢዎች በጻፈው ደብዳቤ ገልጧል።

@YebeTube @FikerAssefa
በደንበጫ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች ተቃውሞ ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ ትላንትና እና ከትላንት በስቲያ በነበረ የተኩስ ልውውጥ፣ የሦስት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የደንበጫ እና ፍኖተ ሰላም ሆስፒታሎች ሥራ አስኪያጆች ገለጹ፡፡የየአካባቢው ነዋሪዎች፣ ዛሬ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ በሁለቱ ከተሞች፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት፣ የተገደሉ እና የቆሰሉ ሰዎችን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ትላንት፣ ከዐዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደው ዋናው መንገድ በመዘጋቱ፣ ትራንስፖርት ተስትጓጉሎ እንደነበርና ዛሬ መከፈቱን፣ እንዲሁም በፍኖተ ሰላም ከተማ ሰልፍ ወጥተው በነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አንድ ሆቴል መውደሙን፣ ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በበኩሉ፣ ካለፈው እሑድ ምሽት ጀምሮ፣ በዞኑ ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ ተከሥቶ የነበረው አለመረጋጋት፣ ዛሬ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን አስታውቋል፡፡

ባለፈው እሑድ እና ትላንት ሰኞ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን በደንበጫ እና በፍኖተ ሰላም ከተሞች በነበሩ ግጭቶች፣ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን፣ የደንበጫ እና የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሥራ አስኪያጆች፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።የደንበጫ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዐዲሱ ፍቅሬ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ ማታ፣ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ሰዎች፣ ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውንና በደረሰባቸው ጉዳት የተነሣ፣ ሰዎች ለኅልፈት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በደንበጫ ከተማ፣ መናኸሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ አመሻሽ በሥፍራው ነበርኹ፤ ያሉ፣ ስማቸውን በምሥጢር እንድንይዝ የጠየቁን አንድ ነዋሪ፣ በዕለቱ የነበረውን ኹኔታ ለአሜሪካ ድምፅ እንዲህ አብራርተዋል።ትላንት ሰኞ ከቀትር በኋላ፣ በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች እንደነበሩና ከእነዚኽም መካከል አንድ ሰው እንደ ሞተ የገለጹልን ደግሞ፣ የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ አቶ ማናየ ጤናው ናቸው፡፡

የከተማው ነዋሪዎች፥ መንግሥት፣ በአካባቢው የሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም የሚጠይቅ ሰልፍ ተደርጎ እንደነበርና በሰልፉ ላይ ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡በሰልፉ ወቅት የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የገለጹት እኚኹ የከተማው ነዋሪ የኾኑ አስተያየት ሰጪ፣ ልውውጡ በማንና በእነማን መካከል እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሓላፊ አቶ ዘመኑ ታደለ በበኩሉ፣ ካለፈው እሑድ ምሽት ጀምሮ፣ በዞኑ ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ ተከሥቶ የነበረው አለመረጋጋት፣ ዛሬ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ገልጸዋል፡፡የክልሉ መንግሥት የሰላም እና ጸጥታ ቢሮም፣ በሚያዝያ ወር ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ ማስከበር ርምጃው፣ አጥፊዎች ለሕግ እስኪቀርቡ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ማለቱ ይታወቃል።

በሌላ በኩል፣ በዐማራ ክልል ምክር ቤት፣ የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ተመራጭ የኾኑ 13 የሕዝብ እንደራሴዎች፣ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት፣ ያለክልሉ ምክር ቤት የእገዛ ጥያቄ በሕግ ማስከበር ስም ወደ ዐማራ ክልል ያስገባውን፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ እንዲያስወጣ ጠይቀዋል።ምንም እንኳን መንግሥት፣ በክልሉ እየሰወደ ያለው ርምጃ፣ ሕግ የማስከበር እንደኾነ ቢገልጽም፣ የዐማራ ክልል ምክር ቤት አባል የኾኑ የአብን ተመራጮች ግን፣ ርምጃው፥ ሕግን የተከተለ አይደለም፤ ሲሉ ተቃውመዋል። የፌደራል መንግሥት፣ የመከላከያ ሠራዊቱን ወደ ክልሉ ያስገባው፣ የዐማራ ክልል ምክር ቤት፣ እገዛውን ሳይጠይቅ በመኾኑ፣ ይህም፣ ርምጃውን ሕገ ወጥ እንደሚያደርገው አስረድተዋል፡፡ ይልቁንም፣ እየተወሰደ ያለው ርምጃ፥ በክልሉ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፤ ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
Forwarded from YeneTube
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
መቀለ ፣ አዲግራትና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች በመጪዉ መስከረም ስራ ይጀምራሉ ተባለ!

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው መስከረም ወር 2016 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢፕድ ዘግቧል።

የሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት የምግብ ፣ የመኝታና የህክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን ገልጸው ራያ ዩኒቨርሲቲም ይህንን አሟልቶ በትናንትናው ዕለት የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን ጠቁመዋል።

መቀሌና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በቀጣዮቹ ወራት ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር እንደሚጨርሱና ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነቱ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ እንደሚችልም ገልጸዋል።

አራቱ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከጦርነቱ በፊት 45 ሺሕ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ እንደነበር አስታውሰው ከእነዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት 22 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲወጡና በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ዪኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል ብለዋል።

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችም አሁን ላይ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ 20 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎችን ይሆናል ተብሏል።

በመጪው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ የቆዩ መሆኑን የገለጹት መሪ ስራ አስፈጻሚው ፤ አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹም ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በሱሉልታ ከተማ በታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል በሚል እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በቅርቡ በተዋቀረው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መንግስት ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የሚገልጹ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ሲዘዋወሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የተወሰዱት ሰዎችም ያሉበት እንደማይታወቅ እና አጋቾችም ይህን ያህል ብር አምጡና እንለቃቸዋለን በማለት እየተደራደሩ እንደሚገኙ መዘገቡም ይታወቃል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን ነባራዊ እውነታ እንዲያብራሩ አሃዱ ያነጋገራቸው የሸገር ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ናስር ሁሴን  ከተማ አስተዳድሩ መረጃው ከወጣ በኋላ የማጣራት ስራዎችን እንደሰራ አንስተው ሆኖም በከተማ መስተዳድሩ ውስጥ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ታፍነው የተወሰዱ ዜጎች አለመኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየወጡ ያሉት ዘገባዎች ከእውነት የራቁ እና ተአማኒነት የሌላቸው መሆናቸውን በመግለጽ ህብረተሰቡን በተሳሳቱ ዘገባዎች ማደናገር ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ቀይ ሽንኩርት በአንድ ሳምንት ውስጥ የ40 ብር የዋጋ ጭማሪ አሳየ!

 - በኪሎ ከ 70 እስከ 80 ብር እየተሸጠ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የቀይ ሽንኩርት ዋጋ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ሸማቾች ቅሬታቸዉን ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡ሽንኩርት በኪሎ ከ70 እስከ 80 ብር እየተሸጠ መሆኑን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተለይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የ40 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰአት ገቢያቸው እና ኑሮው እየተመጣጠነ አለመሆኑ እና የሚፈልጉትን ሸምተው መኖር አለመቻላቸው ኑሮአቸውን  እንዳከበደውም ነዋሪዎች አክለዋል ።ብስራት ሬዲዮ በተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ተዘዋውሮ ለማየት እንደሞከረው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ከመኖሩ ባሻገር አቅርቦቱ ከእለት እለት እየቀነሰ መሆኑን ሃሳባቸውን ለጣቢያችን ከገለጹ ነጋዴዎች ለመገንዘብ ችለናል ።

ብስራት ሬዲዮ ጉዳዩን በተመለከተ ምክንያቱ ከምን የመጣ ነዉ የሚለዉን ለማጣራት የከተማዉ ንግድ ቢሮ የሚመለከታቸውን አካለት ለማናገር በተደጋጋሚ የስልጥ ጥሪ ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያለ አግባብ የእስር እና አስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲፈጸም አድርገዋል የተባሉ 5 ተከሳሾች ከአንዱ በቀር ሌሎቹ ነፃ ተባሉ!

በአርቲስት አረጋኸኝ ወራሽ በተሰጣት ውክልና ከውጭ የገባ የሙዚቃ መሳሪያ እንድትመልስ በማስፈራራት የግል ተበዳይ እንድትታሰርና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲፈጸምባት አድርገዋል ተብለው የተከሰሱ ግለሰቦች ነጻ ተባሉ።በዚሁ መዝገብ ላይ የግል ተበዳይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በታሰረችበት ወቅት የዕለቱ ተረኛ ጥበቃ ወታደር የነበረው 5ኛ ተከሳሽ የመድፈር ወንጀል መፈፀሙ በማስረጃ በመረጋገጡ በቀረበበት ክስ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።በቀረበባቸው የወንጀል ክስ ላይ በዛሬው ቀጠሮ ሙሉ በሙሉ ነጻ የተባሉት ተከሳሾች 1ኛ- ተከሳሽ በአዲስ አበባ ፖሊስ የአየር መንገድ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር መንግስቱ ገብረሚካኤል፣ 2ኛ- ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ዋና ሳጅን ቦሴ ለምለሙ ሙልዬ፣ 3ኛ- የቀድሞ የመከላከያ አባል ሻለቃ ዮሐንስ አበበ ፣ 4ኛ- በግል ስራ ላይ ይተዳደራል የተባለው አደም ሰይድ መሀመድ ናቸው።

የዐቃቤ ህግ ክስ በተከሳሾቹ ላይ አቅርቦት በነበረው ክስ የግል ተበዳይ የሙዚቃ መሳሪያዎች ከውጪ ለማስገባትና ጉዳይ ለማስፈጸም ከአርቲስት አረጋኸኝ ወራሽ ሚያዚያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ውክልና መሰረት እቃዎችን ከውጭ ማስገባቷን አመላክቷል።ነገር ግን 4ኛ ተከሳሽ የአርቲስት አረጋኸኝ ወራሽ ውክልና ስላለኝ ንብረቱን መልሺልኝ በማለት በጠየቀበት ጊዜ የግል ተበዳይም እቃውን ከውጭ ለማስገባት ለቀረጥና ለጉምሩክ ሰራተኞች የከፈለችውን አጠቃላይ 3 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር በቅድሚያ እንዲከፍላት ትጠይቃለች፡፡

ይህን ተከትሎም 4ኛ ተከሳሽ ጉዳዩን በሕጋዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር ወደ መኖሪያ ቤቷ በመሄድ ንብረቱን እንድትመልስ በማስፈራራት፣ በመዛት፣ ያለአግባብ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፖሊስ ጣቢያ እንድትታሰር እና በዕለቱ ጥበቃ እንድትደፈር አድርገዋል በሚል ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።ተከሳሶቹ በአጠቃላይ በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸው 3 ክስ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አልፈፀምንም በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ህግ አርቲስት አረጋኸኝ ወራሽን እና የግል ተበዳይን ጨምሮ አጠቃላይ ስምንት ምስክሮች እና የለተያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱ የምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ዛሬ በዋለው ችሎት ከ1 እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በክሱ ላይ የተጠቀሰባቸውን የወንጀል ድርጊት አጠቃላይ ስለመፈጸማቸው በሰውም ሆነ በሰነድ ማስረጃ አለመረጋገጡ ተገልጿል።በተለይም 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የሙዚቃ መሳሪያው እንዲመለስለት 4ኛ ተከሳሽ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በህግ የተሰጣቸው ኃላፊነትን በመጠቀም በመኖሪያ ቤት ብርበራ እና ምርመራ እንዲደረግ ከማድረግ ባሻገር ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር አለመፈጸማቸው ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የግል ተበዳይ የአስገድዶ መድፈር ተፈጸመብኝ ብላ በተናገረችበት ወቅት በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ ህክምና ተቋም እንደወሰዷት በጉዳዩም ማዘናቸውን በግል ተበዳይ በምስክርነት ቃል መሰጠቱንም ችሎቱ አረጋግጧል።በዚህም መሰረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ሁሉም ተከሳሾች በነጻ እንዲሰናበቱ በሙሉ ድምጽ ተወስኗል።በዚሁ መዝገብ ላይ በ5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰው 5ኛ ተከሳሽን በሚመለከት የግል ተበዳይን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያለአግባብ በታሰረችበት ወቅት የዕለቱ ተረኛ ጥበቃ በግሉ ሀሳብና ተነሳሽነት አስገድዶ ስለመድፈሩ በማስረጃ በመረጋገጡ በሌለበት የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።በተከሳሹ ላይ በዐቃቢ ህግ የሚቀርበውን የቅጣት አስተያየት ለመመልከት ለሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፈው እሁድ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ በተከሰተ አለመግባባትና ግጭት ሰላማዊ ሰዎችና የመከላከያ ሠራዊት አባላት መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት፣ የህክምና ምንጮችና ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

የደንበጫ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ላቀ ወንድይፍራው በደንበጫ 5 ሰዎች ከሁለቱም ወገን መገደላቸውን አረጋግጠዋል፡፡ሶስቱ ሰላማዊ ሰዎች ሁለቱ ደግሞ የመከላከያ አባላት መሆናቸውን የገለጹት አዛዡ በግጭቱ የቆሰሉትን ቁጥር የሚመለከት መረጃ እንደሌላቸው ነው የተናገሩት።አንድ የደንበጫ ሆሰፒታል የህክምና ባለሞያ 2 ሰዎች እንደሞቱ ና 18 እንደ ቆሰሉና ጠቁመው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 4 ሰዎች ወደ ከፍተኛ ህክምና መላካቸውን ተናግረዋል።

አንድ የደምበጫ ከተማ ነዋሪ የወጣቶቹ ጥያቄ «እኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረግን ፣መከላከያዎች ለምን ወደ ከተማ ገቡ? የሚል እንደነበርና በመካከሉ በተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት ተኩስ መከፈቱን ወጣቱ ሆ ብሎ በየአቅጣጫው የሚመጡ መኪናዎችን እንዳይተላለፉ መንገዶችን መዝጋቱን እና የፀጥታ ኅይሎች ወሰዱ ባሉት «ተመጣጣኝ ያልሆነ ርምጃ« ከሰላማዊ ሰዎች ሶስት  መገደላቸውን ተናግረዋል።

ግጭቱ ወደ አጎራባች ጂጋና ፍኖተሰላም ከተሞች በመስፋፋት ጉዳቶች መድረሳቸውን አንድ የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።ነዋሪው በፍኖተ ሰላም ወጣቱ ኅብረተሰቡ በሰላማዊ መንገድ አስፋልት ላይ ቅሬታውን እየገለጸ አንድ ፖሊስ ተኩስ ከከፈተ በኋላ አንድ ሰው መገደሉን ከ10 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን አይቻለሁ ብለዋል።የምዕረብ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘመኑ ታደለ ዝርዝር ጉዳዮች ገና በምርመራ ላይ ቢሆኑም ግጭት በነበረባቸው የዞኑ ከተሞች የሞቱት ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር በአጠቃላይ ከ3 እንደማይበልጥ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ ተናግረዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
"ሰላምና ደኅንነትን የማስጠበቅ እንቅስቃሴዎች ሰብዓዊ መብቶችን እንዳይጥሱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል!" ኢሰመጉ

ሰላምና ደኅንነትን የማስጠበቅ እንቅስቃሴዎች ሰብዓዊ መብቶችን እንዳይጥሱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ።ኢሰመጉ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ የከተማዋን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚል መንግሥት ከአዲስ አበባና ከፌደራል ፖሊስ የተዋቀረ የጋራ ግብረ ሃይል በማቋቋም ደኅንነት የማስከበር ሥራዎችን እንደሚሰራ ማስታወቁን አስታውሷል።

እነዚህ ሰላምና ደኅንነትን ለማስከበር ተብለው በመንግሥት የሚሰሩ ሥራዎችና የሚከተሏቸው ስነ-ዘዴዎች አንዳንድ ጊዜ የሕግ ሥነ ስርዓትን ያልተከተሉ እና የሰዎች ሰብዓዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚጥሉ ሆነው እንደሚገኙም ገልጿል።አምስት አካላትን የያዘው የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፤ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ በመግለጽ፤ በአዲስ አበባ ውስጥ ተከታታይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ሊያካሄድ መሆኑን ባወጣው መግለጫ መግለጹን ያስታወሰው ኢሰመጉ፤ ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱ አግባብ መሆኑን ገልጿል።

ነገር ግን "የእዚህን አይነት ይዘት ያላቸው ለሕግ አስፈጻሚው አካል ከፍ ያለ ስልጣን የሚሰጡ እርምጃዎች በሕግ ከተደነገገው ውጪ በሚፈጸሙበት ወቅት በሂደቱ የሚሳተፉ አካላት የሕግ ሥነ ስርዓትን ያልተከተሉ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና ሰዎች ሕጋዊ፣ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲገደቡባቸው ሲያደርጉ የሚስተዋል በመሆኑ፤ ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ሂደቱ ላይ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ህግና ስርአትን የተከተለ አሰራር እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡" ሲልም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አሳስቧል።ኦፕሬሽኑን ተከትሎ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ በጸጥታ አካላት የሕግን ሥነ ስርዓት ያልተከተሉ የመንገድ ላይ ፍተሻዎች፣ እስሮች፣ ማዋከቦች እና እንግልቶች በሰዎች ላይ እየተፈጸሙ መሆኑን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉንም ገልጿል፡፡

ይህ የጋራ ግብረ ኃይል መደበኛውን የሕግ ሥነ ስርዓት በመከተል ሊንቀሳቀስ የሚገባው ቢሆንም፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ከመደበኛው የሕግ ሥነ ስርዓት ከፍ ያለ ስልጣን እንዳለው በማሰብ ስልጣንን አላግባብ የመጠቀም ሁኔታዎች መስታዋላቸውን አመላክቷል፡፡በዚህም መሠረት፤ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል በአዲስ አበባ ውስጥ እያካሄደ ያለው ተከታታይና የተቀናጀ ኦፕሬሽን የታሰበለትን ሰላምና ደሕንነት ማስከበር እንዲችል የሕግ ሥነ ስርዓትን የተከተለ እንዲሆን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም የጸጥታ አካላት ይህንን ኦፕሬሽን በሚፈጽሙበት ወቅት የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች አላግባብ እንዳይገድቡ እና እንዳይጥሱ ተገቢውን የሕግ ሥነ ስርዓት እንዲከተሉና ያልተመጣጠነ እና አላስፈላጊ የሆኑ ኃይሎችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡም ጠይቋል።እንዲሁም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል በሚያካሄደው ኦፕሬሽን ስልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ በሂደቱ የሚሳተፉ አካላትን የሚቆጣጠርበት እና በሕግ ተጠያቂ የሚያደርግበትን ስርዓት እንዲዘረጋ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ተፈጽሟል የተባለዉን የሰብዓዊ እርዳታ ስርቆት በብዛት የፌደራል ሀይሎች የፈጸሙት ነዉ ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ!

በትግራይ የሰብአዊ ርዳታ ስርቆትን እንዲያጣራ በክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር የተመራው የትግራይ ግብረ ሃይል ኮሚቴ እስካሁን የሰብአዊ እርዳታ ማጭበርበርን የሚያሳዩ ግኝቶችን እና ተጠርጣሪዎችን ማግኘቱን የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ (ማንጁስ) ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

እንደ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዉ ገለጻ በሰብአዊ እርዳታው ስርቆት እና ምዝበራ ላይ የተሳተፉት አምስት ዋና ዋና ተዋናዮች ነበሩ ብለዋል። እኚህም የትግራይ ክልል መዋቅር ፣ የኤርትራ ሰራዊት ፣ የፌደራል መንግስት መዋቅር እና የተፈናቃዮች አስተባባሪዎች እና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።በምርመራው ውጤት መሰረት በደቡብ ትግራይ ፣ ደቡብ ምስራቅ ፣ ምስራቅ ፣ መካከለኛ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች 186 ተጠርጣሪዎች ተለይተው በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

የተመዘበሩ የሰብዓዊ ድጋፎችን በሚመለከትም በፌዴራል ሀይሎች እና በኤርትራ ስራዊት ከፍተኛዉን ድርሻ ይይዛሉ ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በክልሉ መዋቅር ዉስጥ ባሉ ሰዎች ስርቆት መፈጸሙን ተናግረዋል።በዚህም መሰረት በትግራይ መንግስት መዋቅር ስር ባሉ ግለሰቦች14 ሺህ 317 ኩንታል ስንዴ ፣ 42 ሺህ 759 ሊትር ዘይት እና 1ሺህ 424 ኩንታል ኦቾሎኒ (አልሚ ምግብ) ላይ ስርቆት መፈጸሙን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ፌዴራል መዋቅር ባሉ ሰዎች 43 ሺህ 196 ኩንታል ስንዴ ፣129 ሺህ 585  ሊትር ዘይት እና 4ሺህ 184 ኩንታል ኦቾሎኒ መሰረቁን በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል። ይህም በጊዜያዊ መስተዳድሩ ምርመራ መሰረት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል።እስካሁን በክልሉ ጊዜያዊ በተደረገው ምርመራ በኤርትራ ጦር  28 ሺህ 880 ኩንታል ስንዴ ፣ 43 ሺህ200 ሊትር ዘይት እና1 ሺህ 440 ኩንታል ኦቾሎኒ ላይ ስርቆት መፈጸሙን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከረድኤት ድርጅቶች የተላከው ሰብዓዊ እርዳታ መጥፋቱንም ነግረዉኛል ሲል የቴሌቪዥን ጣቢያዉ ዘግቧል።ሌ/ጀነራል ፍስሃ ማንጁስ ግብረ ሀይሉ የማጣራት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የምርመራ ውጤቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። የእርዳታ ድርጅቶች ለትግራይ ህዝብ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ችግር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ የማይሰጥባቸው ት/ቤቶች እንዳሉ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ችግር ባሉባቸው የገጠር አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች፣ ትምህርት ካቋረጡ ከሦስት ዓመታት በላይ እንደኾናቸው፣ የቤተሰቦቻቸው አባላት ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በክልል ደረጃ፣ በቅርቡ የሚሰጠውን የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱትም፣ በከተማ እና በወረዳ ከተሞች ውስጥ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች እንደኾኑና እነርሱን እንደማያካትት፣ እነኚኹ የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ገልጸዋል።የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሓላፊ ዶክተር ቡልቶሳ ሂርኮ፣ በሁሉም ወረዳዎች፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱንና ከ400ሺሕ በላይ ተማሪዎች፣ በዘንድሮው ዓመት በሚሰጠው የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

በኦሮሚያ ክልል፣ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪ እና የተማሪ ወላጅ እንደኾኑ ጠቅሰው፣ ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ፣ “ቀደም ሲል በወረዳችን፣ ብዙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ፥ ጎደጃባ፣ ሻካኬ፣ ቃሬ ቶከ፣ ኛኣ እና ቶሌንና አልዴራ የሚባሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይጠቀሳሉ፡፡ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ግን፣ በእነዚኽ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጧል።” በማለት በወረዳቸው ያለውን የመማር ማስተማር ሒደት አስመልክቶ አስተያየት ሰጥተዋል።

አክለውም፤ “ከሦስት ዓመት በፊት፣ ስምንተኛ ክፍል ደርሰው የነበሩ፣ አሁንም እዚያው ስምንተኛ ናቸው፡፡ ከአንድ እስከ ስምንት የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች፣ ባሉበት ነው ያሉት። በተለይ፣ በቆላማ አካባቢው በሚገኙ 10 ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች፣ ምንም የመማር ዕድል አላገኙም። ምክንያቱም፣ በጸጥታ ችግር ትምህርት ቤቶቹ ሥራ በማቆማቸው ነው። በመኾኑም፣ በዘንድሮው የስምንተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡት፣ በወረዳው ከተማ ያሉ ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለወደፊቱ፣ የልጆቻችን ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ ነው።” ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በዋናነት የጸጥታ ችግር የተፈጠረው በክልሉ በሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎችና በመንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ባለው ግጭችት ምክኒያት ሲኾን፤ ነዋሪዎቹ ሌሎች መደበኛ ያልኾኑ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሳሉ በሚሉበት አካባቢም በስጋት ምክኒያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን መማር እንደተሳናቸው ያነጋገርናቸው ቤተሰቦች ገልፀዋል።በሌላ በኩል የያያ ጉለሌ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በወረዳው፥ 400 ተማሪዎች፣ በስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ ይቀመጣሉ።

የአሙሩ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዓለማየሁ ዋቅጅራ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በወረዳቸው፥ ዘጠኝ የሚደርሱ የአንደኛ ትምህርት ቤቶች፣ በጸጥታው ምክንያት የመማር ማስተማር ሒደቱን መቋረጡን፤ ገለፀው “በ21 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 640 ወንድ ተማሪዎችንና 635 ሴት ተማሪዎችን፣ በአጠቃላይ 1ሺሕ275 ተማሪዎችን፣ በኦቦራ እና አገምሳ ክላስተር ላይ ለመፈተን ተዘጋጅተናል። በወረዳችን ዘጠኝ ትምህርት ቤቶች፣ በጸጥታ ችግር ሳቢያ ትምህርት እየተሰጠባቸው አልነበረም። በተቻለ መጠን፣ ተማሪዎች፥ ወደ ወረዳው ከተማ ተቃርበው እንዲማሩ ተደርጓል። አሁንም፣ ለፈተናው የሚቀመጡት እነርሱ ናቸው።” ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፣ በሁሉም ወረዳዎች፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ፣ የተናገሩት የቢሮው ምክትል ሓላፊ ዶክተር ቡልቶሳ ህርኮ፣ “ፈተናውን፣ በሁሉም ወረዳዎች እንሰጣለን። ከጸጥታው ችግር ጋራ በተያያዘ፣ የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጦ በቆየባቸው ትምህርት ቤቶች ግን፣ ፈተና አይሰጡም። ቁጥራቸውን ለመግለጽ አሁን ዳታቸው የለኝም። በዚኽ ዓመት ለመፈተን ካቀድናቸው ተማሪዎች መካከል፣ 97ነጥብ2 የሚኾኑቱ ናቸው ለፈተናው የሚቀመጡት። ቀሪዎቹ፣ በጸጥታው ምክንያት እና በሌሎችም ችግሮች፣ ለፈተናው አይቀመጡም።” ብለዋል።

አሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው፣ የአንዳንድ ተማሪዎች ወላጆች፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ ትምህርት መቋረጡን፤ ሲገልጹ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ትምህርት ስለተቋረጠባቸው አካባቢዎች በአሀዝ አስደግፎ ከመግለጽ ተቆጥቧል።በኦሮሚያ ክልል በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ ከትምህርት በተጨማሪ ሌሎች የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እንደተሳናቸው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ሲገልጹ ቆይተዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ!

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ።በኢትዮጵያ በተለይም የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው በተለያየ መልኩ ሲገለጹ ቆይቷል።የባንክ ደንበኞችም ለአገልግሎት ባመሩባቸው የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ሲጠይቁ እንዳልሰጧቸው በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተሰተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል።የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት "በኢትዮጵያ በግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል እሚባለው መረጃ ሀሰት ነው" ብለዋል።

የጥሬ ገንዘብ እትረት ገጥሟቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ናቸው መባሉን ሰምተናል ፣ "ነገር ግን በሶስት ባንኮች ላይ የተወሰነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞ ነበር፣ ብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በወሰዷቸው ማስተካከያዎች አሁን ላይ ከአንድ ባንክ በስተቀር የጥሬ ገንዘብ እጥረት ያጋጠመው ባንክ የለም" ሲሉም ምክትል ገዢው አክለዋል።

በኢትዮጵያ የገንዘብ አቅርቦቱ እና ፍላጎቱ የተጣጣመ አይደለም ያሉት አቶ ሰለሞን አሁን ያጋጠመው ክስተትም ጦርነት ውስጥ በነበርንበት የቆመው የፋይናንስ እንቅስቃሴ አሁን የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የፋይናንስ ፍላጎቱ በመጨመሩ ብቻ የተፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎቶችን ለዓለም አቀፍ ተቋማት በሯን ክፍት ማድረጓን ተከትሎ ይህ ሂደት የት ደረሰ? በሚል ለምክትል ገዢው ለቀረበላቸው ጥያቄም " ስራው ሰፊ ዝግጅቶችን የሚጠይቅ ነው፣ ከዓለም ባንክ ጋርም አብረን እየሰራን ነው በአንድ ዓመት ውስጥም ስራውን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

" የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱን ተከትሎ የአገር ውስጥ ባንኮች ራሳቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ውህደት ለመፈጸም በሂደት ላይ ያሉ ባንኮች አሉ" ያሉት አቶ ሰለሞን የኢትዮጵያ ባንኮች በቴክኖሎጂ ፣ ፋይናንስ አቅም እና ሰው ሀይል የበለጠ እንዲዘጋጁም ጥሪ አቅርበዋል።

ስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው ይህ ትኩረቱን በካፒታል ማርኬት ላይ ያደረገ ሲሆን የየፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶች እና ውይይቶች እየተደረጉበት ይገኛል።በጉባኤው ላይ የባንክ ስራ አስኪያጆች፣ ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች ተሳትፈውበታል።

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
#የቻናል_ጥቆማ

🔔 የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
🔔 በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

🔥 እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ
     ቻናል እንጠቁመዎት 👇👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

📚 በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
👉 የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
👉 በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

Join us on Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
https://tttttt.me/ethioengineers1