YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
Forwarded from YeneTube
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
የቤት ግብር ማሻሻያው የተደረገው መንግስት ላይ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች በመኖራቸው ነው ተብሏል፡፡

በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የቤት ግብር ማሻሻያ አስመልክቶ በርካታ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡ከነዚህም መካከል በአሁኑ ወቅት በዜጎች ላይ ከሚታየው ምጣኔ ሃብታዊ ጫና አንጻር ማሻሻያው ወቅታዊ አይደለም የሚሉ ሃሳቦች ሲነሱ ይደመጣል፡፡

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ አሃዱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የንብረት ግብር ማስተግበርያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ አስማማው ሙሉጌታን አነጋግሯል፡የያዝነው ዓመት ብዙ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች የተነሱበት እንደነበር ጠቅሰው እነዚህን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመፍታት ደግሞ ግብር መክፈል ዋነኛ መፍትሄ በመሆኑ ከዚህ በፊት ለረጅም ጊዜ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ነባር አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የንብረት ባለቤቶች አንጻራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ የመክፈል አቅም አላቸው ያሉ ሲሆን ባለቤቶቹ እንደንብረታቸው መጠን እንዲከፍሉ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡የመክፈል አቅምና ገቢ የሌላቸው ከሆኑ በየወረዳው እየተገመገመና እየቀረበ ነጻ የሚሆኑበት ወይም ምህረት የሚደረግበት አሰራር እንዳለም በአዋጁ ተቀምጧል ብለዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
👎1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በ14ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለ ሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መንግሥታት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገብተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጎደሬ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ የፖሊስ አዛዥ ተገደለ!

ከደቡብ  ምዕራብ ክልል ሚዛን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት  ጥቃት የአንድ ፖሊስ አዛዥ ተገድሏል። በጥቃቱ አንድ የፖሊስ  አባል ላይ ጉዳት መድረሱን በጋምቤላ ክልል የጎደሬ ወረዳ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳኜ ወርቅነህ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡብ ምዕራብ ክልል የኪ ወረዳ  ልዩ ስሙ ባያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  ነው። ጥቃቱ በትላንትናው እለት ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም  ከምሽቱ 1 ሰዓት 30 ደቂቃ አካባቢ ተፈፅሟል።

ግድያው የተፈጸመው የፖሊስ  አባላቱ ከደቡብ ምዕራብ ክልል ሚዛን ከተማ ስልጠናቸውን ጨርሰው ወደ ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ ነው ብለዋል።ጥቃቱንም የጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ፈፅመውታል።

በጥቃቱ የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ አብዮት ሮኬት ህይወታቸው አልፏል። በሌላ አንድ የፖሊስ አባል ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በቴፒ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ሲሉ አቶ ዳኜ ወርቅነህ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ድርጊቱን በፅኑ የሚያወግዝ መሆኑን እና አጥፊዎቹም ለህግ እንዲቀርቡ ከፍትህ አካላትና ከሚመለከታቸው ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞዉ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርሉስኮኒ በ 86 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በርሉስኮኒ ከሳንባ ኢንፌክሽን ጋር በተያያዘ በሚላን በሚገኝ ራፋኢል ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ነበር፡፡

ቢሊዮነሩ በርሉስኮኒ ጣሊያንን ከፈረንጆቹ 1994 እስከ 2011 በጠቅላይ ሚንስትርነት አገልግለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ!

ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄን በመተካት የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዮናስ ብርሃነ መዋ ከእስር ተለቀቀ!

ባሳለፍነው አርብ ሰኔ 2/2015 ምሽት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው የፊልም ባለሙያ እና የጉማ የፊልም ሽልማት አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ መዋ ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መፈታቱ ታውቋል።

ዮናስ አርብ ምሽት ከጉማ የፊልም ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በኋላ ሲቪል በለበሱ የመንግሥት ደኅንነት ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።

በማግስቱ ቅዳሜ ጠዋት ፍርድ ቤት የቀረበው ዮናስ በአምስት ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ በፍርድ ቤት ቢወሰንለትም፤ በተመለዶ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ወደሚጠራው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መዘዋወሩም ተገልጾ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሆነ!

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በግጭት በተጎዱ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች በተገኙበት ይፋ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሲደረግ በግጭቱ 28.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመትና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ውድመቱን መልሶ ለመገንባት 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራሙ ይፋ በተደረገበት ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ መንግስት ለፕሮግራሙ ውጤታማነት ከሚያደርገው ሰብአዊ ድጋፍ በተጨማሪ በጀት መድቦ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ተግባር በመንግስት አቅም ብቻ የሚከናወን ተግባር ባለመሆኑ ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋሮች ለፕሮግራሙ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ አተገባበር ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው የፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮችና በግጭት የተጎዱ ክልሎች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎችና የልማት አጋሮች ኃላፊዎች በፕሮግራሙ አተገባበር ላይ ሰፊ ውይይት አድረገው የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ታገዱ!

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ማገዱን አሰታወቀ።ከጥቅምት 14/2015 እስከ ታህሳስ 30/ 2015 ዓ.ም ድረስ 15 ኤጀንሲዎች ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ሪፖርት አለማድረጋቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ በላይ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡በህግ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዜጎችን ለሥራ ስምምነት ወደተደረሰባቸው መዳረሻ ሀገራት ለመላክ ፍቃድ በመውሰድ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችም በአዋጅ ቁጥር 923/08 እና በማስፈፀሚያ መመሪያ መሰረት ሊያሟሉ የሚገባቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡በአዋጅ ቁጥር 923/08 መሰረት ድርጊቱ የሥራ ፈቃድ ስረዛ የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሶ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አልቻሉም፡፡

ስለሆነም ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎ ከድርጊታቸው መማር እንዲችሉ ከግንቦት 11ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለመጨረሻ ጊዜ ለሦስት ወራት ታግደዋል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
👍1
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በአዲስ አበባ ከተማ ወንዝ ዉስጥ የገባው የ45 ዓመት ሰዉ አስከሬን ከ2 ሰዓታት ፍለጋ በኃላ ተገኘ!

-
በሌላ የአደጋ ዜና አንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች ተቃጥለዋል

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ሰኔ 5 ቀን  በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ ተባበር በርታ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 45 ዓመት የተገመተ ሰዉ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ከሁለት ሰዓት ፍለጋ በኋላ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።በሌላ በኩል በዚያዉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች ተቃጥለዋል።የእሳት አደጋዉ ያጋጠመዉ የአንበሳ አዉቶቢስ የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥና የነዳጅ  መቅጃ ማዕከል ላይ ሲሆን የተቃጠሉት አዉቶቢሶች ከቅጥር ጊቢ ዉጭ ቆመዉ  የነበሩ አውቶቡሶች መሆናቸውን አቶ ንጋቱ ማሞ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ እና ሰላሳ አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል።የእሳት አደጋዉ ወደ ነዳጅ ታንከርና ጋራዡ  ላይ ተሳፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል።የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የጠየቀ ሲሆን በሰዉ ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በሞስኮ በአደገኛ የዕፅ ንግድ ተጠርጥሮ የተያዘው አሜሪካዊ ፍ/ቤት ቀረበ!

በሞስኮ፣ በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ተይዞ የተከሠሠው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሙዚቀኛ እና የቀድሞ አየር ወለድ አባል የነበረ አሜሪካዊ፣ ፍርድ ቤት መቅረቡን፣ ሮይተርስ ዘገበ፡፡በመንግሥት ቴሌቪዥን እንደታየው፣ አሜሪካዊው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት፣ የብረት እጥር በኾነ የተከሣሽ መቆሚያ ውስጥ እንዳለ መታየቱ ተዘግቧል፡፡

የሩሲያ ፍርድ ቤት፣ የ51 ዓመቱ አሜሪካዊ ማይክል ትራቪስ ሊክ፣ በማለት የገለጸው ተከሣሹ፣ ቀደም ሲል በሩሲያ “ሎቪ ኖች” ተብሎ በሚጠራው የሮክ ባንድ፣ ሙዚቀኛ እና የዜማ ደራሲ እንደነበር ተወስቷል፡፡“ሩሲያ 24” የተባለው ቴሌቪዥን፣ ባለፈው ቅዳሜ፣ የተከሣሹን ምስል ያሳየው፣ ተከሣሹ፥ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ከተያዘ በኋላ እንደኾነ ተነግሯል፡፡

ወጣቶችን ባሳተፈ የአደገኛ ዕፅ ዝውውር እና ንግድ የተከሠሠው ሊክ፣ እ.አ.አ እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2023 ድረስ በእስር እንደሚቆይ፣ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡ሊክ፣ ጠበቃ ያለው ስለመኾኑ ግልጽ አይደለም፤ ያለው የሮይተርስ ዘገባ፣ በሩሲያውያን ቁጥጥር ሥር ያለውን የተከሣሹን አስተያየት ለማግኘት አለመቻሉን አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ “በቅርቡ ሞስኮ ውስጥ፣ አንድ አሜሪካዊ በቁጥጥር ሥር ስለ መዋሉ የወጡትን ዘገባዎች እናውቃለን፤” ብለዋል፡፡ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ሚኒስቴሩ፥ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ፣ በውጭ አገር በታሰረ ጊዜ፣ ወዲያኑ፣ የዚያን አገር ቆንስል አግኝቶበማነጋገር፣ የሚያስፈልገውን ርዳታ ሁሉ ያገኝ ዘንድ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ይኹን እንጂ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ የቆንስሉ ርዳታ፣ እስከ አሁን ለተከሣሹ ሊክ መስጠት ስለመቻላቸው፣ ቃል አቀባዩ የገለጹት ነገር የለም፡፡የዩክሬኑ ጦርነት ከተጀመረ ካለፈው ዓመት የካቲት አንሥቶ፣ ሩሲያ ውስጥ ሊደርስባቸውን የሚችለውን የዘፈቀደ እስር እና እንግልት ለማስወገድ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች፥ ሩሲያን ለቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ስታሳስብ መቆየቷ ተመልክቷል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
"መንግስት ስልጣን የሰጣቸው የአብን አመራሮች ፓርቲው የተመሰረተበትን ዓላማ በመተው የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል" - የአብን ጽ/ቤት ሃላፊ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የጽህፈት ቤት ሃላፊ ቴዎድሮስ ሀይለማርያም (ዶ/ር) "መንግስት ስልጣን የሰጣቸው የአብን አመራሮች ፓርቲው የተመሰረተበትን ዓላማ በመተው የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል" ሲሉ ለአሻም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል መንግስትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል እየተደረጉ ያሉ ግንኙነቶችን አስመልክቶ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራሮች ለሁለት መከፈላቸውን ሃላፊው ይፋ አድርገዋል።

ሀላፊው እንደሚሉት የሁለቱ አካላት ግንኙነት ሰላም እስካመጣ ድረስ መልካም ነው የሚሉ አመራሮች አሉ በአንፃሩ  ደግሞ ተጠያቂነት ሳይኖር ጦርነቱን በበላይነት ሲመሩ የነበሩ አካላት የሚያደርጉት ውይይት አግባብ አይደለም የሚሉ መኖራቸውን ነግረውናል፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለፅ "ይህ መከፋፈል የመጣውም በመንግስት ሹመት ተደልለው የመንግስት ስራ አስፈፃሚ የሆኑ የንቅናቄው አመራሮች በመኖራቸው ነው፡፡" ሲሉ ተችተዋል።

ግማሹ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በመንግስት ካቢኔ ውስጥ ተቀምጠው የአማራ ህዝብን ሳይሆን የገዢውን ብልፅግና ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል የሚሉት ቴዎድሮስ "በአማራ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምበት ንቅናቄው ከተመሰረተበት ዓላማ ውጭ የመንግስትን ጉዳይ በማስፈፀም የአማራ ህዝብን የሚታገል ድርጅት ሆኗል" ሲሉም አክለዋል።

ሃላፊው  መፍትሔ ብለው በማስቀመጡት ሃሳብም "አብን ይህን ጉዳይ አስታርቆ  ሊቀጥል የሚችለው በመንግስት ስልጣን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከስልጣናቸው ሲለቁ አልያም ፓርቲውን መልቀቅ ሲችሉ ብቻ ነው" ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ሀላፊው አክለውም "ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ እያሉ ለሕዝቡ ጠላት የሆነው መንግስትም አካል ነኝ ማለት ሊሆን አይችልም፤ ምን አልባትም ድርጅቱ ጉባኤውን ካካሄደ እነዚህን ሰዎች ምርጫቸውን ይሰጣቸዋል" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን የማጣራት ስራ መጀመሩን ተከትሎ 67 መምህራን ስራ ጥለው ጠፉ!

በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የማጣራት ስራ ተጀምሮ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ፍተሻ ተደርጓል። ይህንኑ ተከትሎ የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘባቸው የተወሰኑ መምህራን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 67 መምህራን ስራ ጥለው መጥፋታቸው ተነግሯል ።

በተያዘው በጀት ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ 4ሺ 4 መቶ 74 የትምህርት ማስረጃዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልከው በተደረገ የማጣራት ስራ የ82 መምህራን ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱን የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ  አ/ቶ ሽኩራል አወል ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ። ከነዚህ መምህራን መካከል 28 ቱ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ቀሪዎቹ መጥፋታቸው ተገልጿል ። 

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በ15 መምህራን ላይ የፍርድ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን ቀሪ መምህራን በገንዘብ ዋስ ከወጡ በኋላ መጥፋታቸውን አክለዋል። የ67ቱ መምህራን ስራቸውን ጥለው መጥፋት በአንድ ወረዳ ብቻ የ23 መምህራን የትምህርት ማስረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል ። ሀሰተኛ ማስረጃው በተራቀቀ መንገድ የተሰራ መሆኑንና በምርመራ ወቅት ማወቅ እንደተቻለው ደላሎችን ጨምሮ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በዚሁ ተግባር ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ መምህራኑ ተናግረዋል ።

እንዲህ ዓይነት ችግሮች ዳግመኛ እንዳይከሰቱና ለመከላከል እንዲቻል የሚመለከተው አካል ሁሉ በጉዳዩ ዙሪያ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አ/ቶ ሽኩራል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ!

የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ፍፁም ብርሀን እንዳስታወቁት÷ በአክሱም ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለቱሪስቶች ክፍት ተደርገዋል።

ቅርሶቹ ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆኑ ኅብረተሰቡ በጉልበቱ፣ በገንዘቡ እና በሙያው ያደረገው ተሳትፎ የላቀ እንደነበረም ተናግረዋል።

የቱሪዝሙን ዘርፍ ወደነበረበት ለመመለስ እና ኅብረተሰቡ ለቱሪስቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ለፎቶ አንሺዎች፣ አስተርጓሚዎች፣ ለባህላዊ ጌጣጌጦች እና ቅርፃቅርፅ ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለ ሆቴሎች ሥልጠና መሰጠቱን አሰረድተዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa