YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከሀዋሳከአዳማከሻሸመኔ አስቸኳይ ፓስታ ወደ አዲስ አበባ ያሉበት ድረስ በ 300 ብር ብቻ።

እንዲሁም

Online የገዙትን ልብስ፣ጫማ የተለያዩ እቃዎችን ከአዲስ አበባ እቃው ያለበት ድረስ በመምጣጥ እንቀበሎታለን። እንዲሁም ሀዋሳ ፣ አዳማ ፣ ሻሸመኔ ፣ያሉበት ድረስ እናደርሳለን።

የግል ድርጅት ያላችሁ አብራችሁን መስራት የምትፈልጉ በ0980526262 ወይም በ0962627762 ላይ ይደውሉልን።

የየኔቲዩብ እህት ድርጅት አዲስ ኤክሰረስ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ 25% ቅናሽ ያግኙ
T.me/addisexpressdelivery
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
👍1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
👍1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በሥራ ላይ እያለ በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወቱ ማለፉ ተነገረ!

በትላንናው ዕለት እሁድ ግንቦት 20/2015 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ዓለም ባንክ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በኤሌክትሪክ አደጋ የአንድ ሰዉ ሕይወቱ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋዉ ያጋጠመዉ ወጣት እድሜዉ 28 ዓመት የሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ ሲሆን፤ ባለገመድ የስልክ መስመር በመዘርጋት ላይ እያለ ከከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ጋር ተገናኝቶ የሞት አደጋ መድረሱን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን አዉርደዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውንም ንጋቱ ጨምረው ገልጸዋል።በተመሳሳይ ዓርብ ግንቦት 18/2015 በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፖርክ ሰራተኛ በሥራ ላይ እንዳለ በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ!

ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

በባለሥልጣኑ የተሽከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በድሉ ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መንግሥት ሕገወጥነትን ለመከላከል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ አንዱ ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎችን የመለየት ሥራ አንዱ ነው። ይህም ከተጀመረ አንድ ወር ሆኖታል።

‹‹ባለሥልጣኑ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ጥናት በባለሥልጣኑ የሚመዘገበው የገንዘብ መጠን እና ለገቢዎች ቢሮ የሚቆረጠው ደረሰኝ ተመሳሳይ ያለመሆን ሁኔታዎች አሉ። በዚህም በተለይ የአዲስ ተሽከርካሪዎች ዋጋ የሚቆረጥበት ደረሰኝና ገዢዎች ለመኪናው የሚከፍሉት ዋጋ ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡›› ብለዋል።

በዚህም መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ግዥና ሽያጭ ማግኘት የሚገባውን የታክስ ገቢ እያገኘ አለመሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህንን እና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎችን የመለየት ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።

‹‹ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት ኹለት አይነት ሕገወጥ ተግባራት ይገጥሙታል›› ያሉት ኃላፊው፤ እነሱም ከክልል በዝውውር የሚመጡ መኪናዎች ላይ እና በተጭበረበረ ሰነድ የተመዘገቡ መኪናዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ይህንን ለመከላከል የሚያግዝ ዘመናዊ ሥርዓት የመኪናዎቹን ሕጋዊነት የማጣራት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

‹‹ይህም የማጣራት ሥራው የሚሠራው ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ ነው፡፡›› ያሉት በድሉ፤ ከዚህ በፊት አንድ የመኪና ሻጭ በሥሙ የነበረውን መኪና ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ የማጣራት ሥራ እንዳልተሠራ በመግለጽ፤ ‹‹በዚህም መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ታክስ አላገኘም። አሁን ግን ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን አዲስ ሥርዓት መዘርጋት ተችሏል፡፡›› ብለዋል።

‹‹ሥርዓቱም መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ማግኘት የሚገባውን ታክስ እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ መኪና ገዢዎች እንዳይጭበረበሩ እና መንግሥት ሕገወጥነትን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት የሚያጠናክር ነው። በሂደቱም በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎች የሚወረሱ ይሆናል፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፤ ‹‹የአዲስ መኪና ገዢዎች የሚከፍሉት ዋጋ በደረሰኙ ላይ መጠቀሱን በማረጋገጥ ሊገዙ ይገባል። ይህንን ማድረግ ለገዢው በርካታ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ከመሆኑ ባለፈ የሚሰበሰበው ገቢ ለከተማዋ መሠረተ ልማት የሚውል በመሆኑ በኃላፊነት ሊታይ ይገባል›› ሲሉም ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ቀድሞ ይፋ ባልተደረገ ጉብኝት ኬንያ ገብተዋል።

የሞስኮ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሚኒስትሩን ሰኞ ንጋት ላይ ናይሮቢ መግባት ይፋ ያደረገ ቢሆንም ለምን እንደመጡ ግን ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጠም።በናይሮቢ የሩሲያ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ “ፍሬያማ የሁለትዯች ግንኙነት ለሩሲያና ኬንያ” የሚል መልዕክት አስፍሯል።የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ ሰኞ የናይጄሪያው አዲሱ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በዓለ ሲመት ጉዟቸውን በላቭሮቭ ጉብኝት ምክንያት ሳይሆን አይቀርም፣ ሰርዘዋል።

ላቭሮቭ ወደ ኬንያ የመጡት የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲመትሪ ኩሌባ አዲስ አበባን ጨምሮ በአፍሪካ አገራት ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።ላቭሮቭ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ወደ አፍሪካ ሲመጡ ይህ የመጀመርያቸው አይደለም።በፈረንጆች በሐምሌ ወር 2022፣ ግብጽን የጎበኙት ላቭሮቭ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል አቅንተው ከዚያ ኢትዮጵያን እና ኡጋንዳን ጎብኝተው ነበር።በጥር ወር 2023 ዓ/ም ደግሞ ኤርትራን መጎብኘታቸውና ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር መምከራቸው አይዘነጋም።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
1
የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ላይ የሚፈጠሩ መስተጓጎሎችን ተከትሎ የጥቁር ገበያ የነዳጅ ግብይት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል መገበያያ መንገዶች ብቻ እንዲሆን መደረጉ የሚታወቅ ቢሆንም በዚሁ ምክንያት የተፈጠሩ መስተጓጎሎችን ተከትሎ በህገ ወጥ መንገድ የጥቁር ገበያ መስፋፋቱን የትራንስፖርት ሚንስቴር የነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪው አቶ ሰልማን መሃመድ ገልጸዋል፡፡

በተለይ በክልሎች ላይ ለአርሶ አደሮች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት በጀሪካን እና በበርሜል እንዲገዙ ፈቃድ የሚሠጥ ሲሆን በዲጂታል ግብይት አጀማመር ላይ የነበረውን መስተጓጎል እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የጥቁር ገበያ የነዳጅ ግብይት እንዲስፋፋ ማድረጉን ነው የገለፁት።

ይህንንም ለመቆጣጠር ከክልል የንግድ ቢሮዎች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ የክትትል ስርአት በመዘርጋት አስፈላጊው ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አክለውም እየተሠሩ ባሉት የቁጥጥር እና የእርምጃ ስራዎች በጥቁር ገበያ የሚካሄደው የነዳጅ ግብይት መቀነስ እንደተቻለ ገልፀው ይህን ህገ ወጥ ግብይት ሙሉ ለሙሉ ማስቆም እስከሚቻልበት ጊዜ ድረስ የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1😭1
#ScamAlert

"በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለንም"--- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አማካኝነት የብድር አገልግሎት እየሰጠ ነው በሚል የሀሰት መረጃ ስርቆት ለመፈፀም የሚሞክሩ አጭበርባሪ መልእክቶች እየተሰራጩ እንደሚገኙ ዛሬ አስታውቋል።ባንኩ እንዳለው እነዚህ የማጭበርበርያ መልዕክቶች ደንበኞች ብድር ለማግኘት እንዲጠቀሙበት ባስቀመጡት ሀሰተኛ ኮዶች አማካኝነት ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ገንዘብ ለመስረቅ እየሞከሩ ነው፡፡

"ነገር ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለም። በመሆኑም ደንበኞች ከንደዚህ ዓይነት አጭበርባሪዎች እራሳችሁን እየጠበቃችሁ ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃ ማግኘት ያለባችሁም ከግለሰቦች ሳይሆን ከባንኩ ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ከባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ መሆን እንዳለበት እንገልጻለን" ብሏል።

Via Commercial Bank of Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከ24 ሰዓት ውስጥ 16ቱን ሰዓት አገልግሎት መስጠት ጀምሬበታለሁ አለ፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የነዋሪውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት የአገልግሎት ሰዓቱ ላይ ማስተካከያ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡

ቀላል ባቡሩ ቀደም ሲል ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ማለትም በየቀኑ ለ14 ሰዓታት የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ማለትም ከግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰዓቱን እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በማራዘም በየቀኑ ለ16 ሰዓታት ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በዛሬው እለት በተከሰተ የእሳት አደጋ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደረሰ!

በዛሬ  እለት ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በአንድ ንግድ ቤትና በአንድ መኖሪያ ቤት ባጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።በእሳት አደጋዉ አንድ  የተሽከርካሪ ጌጣጌጥ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በታፒሴሪዉ ለአገልግሎት ቆመዉ የነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል።

የእሳት አደጋዉ ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደረጉ ከነበሩ ነዋሪዎች መካከል በአምስቱ ላይ ቀላል ላይ ጉዳት ደርሷል።የእሳት አደጋዉ ወደተሽከርካሪዎቹ በመዛመቱ በቀላሉ ሊስፋፋ ችሏል።የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 7 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ የተሰማራ ሲሆኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ ተዛምቶ ከዚህ የከፋ አደጋ ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ በጋምቤላ ክልል ባንድ የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ግንቦት 12 ቀን ባደረሱት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።

ጥቃቱ 11 ሰዓት ገደማ የተፈጸመው፣ በምዕራብ ጋምቤላ ቤተል ሲኖዶስ አገልግሎት ክልል "ማታራ" በተባለ ቀበሌ ውስጥ መኾኑን መግለጫው አመልክቷል። ከ2 ሺህ 700 በላይ የመንፈሳዊ ጉባዔው ተሳታፊ ወጣት ሴቶች፣ እናቶችና ሕጻናት የዕለቱን መንፈሳዊ መርሃ ግብር አጠናቀው ለእራት በተቀመጡበት ወቅት፣ ድንገት የደረሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሕጻናትን አፍነው ለመውሰድ በሞከሩበት ወቅት በተፈጠረ ግብግብ፣ መንፈሳዊያኑ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ ቤተክርስቲያኗ ጨምራ ገልጣለች። ከተገደሉት መካከል አንዲት ሕጻን እንደምትገኝበትና፣ በጥቃቱ የቆሰሉ በርካታ ምዕመናን ጋምቤላ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና ላይ እንደኾኑም በመግለጫው ላይ ተገልጧል።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa