YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ የጣሱ 8 የነዳጅ ቦቴዎችን ወረሰ!

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ስምንት የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታወቀ፡፡ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ ስምንት የነዳጅ ካምፓኒዎች ቦቴዎች በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ ተወርሰዋል፡፡

የተወረሰው ነዳጅም በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቀዋል።የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ÷ ሕግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቪዲዮ፦ ከፍተኛ ፉክክር ያስተናገደው የኢዜማ የመሪነት ምርጫ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና በእርሳቸው ስብስብ ስር ባሉ አመራሮች የበላይነት ተጠናቅቋል። በምርጫው ከተሳተፉ የኢዜማ ጉባኤተኞች ውስጥ 62.74 በመቶ ድምጽ ያገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ደጋፊዎቻቸው ደስታቸውን በጭፈራ መግለጽ የጀመሩት የምርጫው ውጤት በይፋ ከመነገሩ አስቀድሞ ነበር። የደስታው ስሜት ምን ይመስል እንደነበር ከታች የተያያዘውን ቪዲዮ ተጭነው ይመልከቱ።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 አመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጠት ጀመረ!

የአዲስ አባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተናን በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች በአጠቃላይ 71 ሺህ 832 ለሚደርሱ ተማሪዎች በየፈተና ጣቢያዎቹ ፈተናውን መስጠት ጀምሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከሀምሌ ወር አጋማሽ በኋላ ለተከታታይ ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊዘንብ ይችላል ተባለ!

በመደበኛ ሁኔታ በሀምሌ ወር የክረምት ዝናብ በሁለም የሀገሪቱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ እየተስፋፋ እና እየተጠናከረ እንደሚሄድ እና በአንዳንድ ቦታዎች ሊይ ነጎድጋዳማ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

በመጪው የሀምሌ ወር ከደቡብ ንፍቀ ክበብ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ያለዉ እርጥበት አዘል አየር እየተጠናከረ ሊሄድ እንደሚችልና ከዚህም ጋር ተያይዝ ቀደም ሲል ወቅታዊውን ዝናብ በመደበኛ ሁኔታ ማግኘት የጀመሩትን የምዕራብ አጋማሽና የመካከለኛዉ የኢትዮጵያ ክፍሎችን ጨምሮ የሰሜን ምሥራቅ እና የምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎችን የሸፈነ ዝናብ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረዉ ይጠበቃል ብላል፡፡

በተለይም ከወሩ አጋማሽ በኋላ ለተከታታይ ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል እንዲሁም በዉስን ሰዓት ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዝ በአንዳንድ ተዳፋትና በወንዞች አካባቢ ለጎርፍ መከሰት መንስኤ ሊሆን ስለሚችል ማህበረሰባችንና የሚመለከተዉ ሁለ ከወዲሁ አስፈላጊዉን ክትትልና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን፡፡

በአጠቃላይ በሚቀጥለው ወር በኦሮሚያ ጅማ ኢለአባቦራ፣ ሁለም የሸዋ ዞኖች፣ በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም፣ የሰሜን፣ የደቡብ፣ መካከለኛዉና ምዕራብ ጎንደር፣ የባህርዳር ዘሪያ፣ አዊ ዞን፣ የዋግህምራ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ የሰሜን ሸዋ በተጨማሪም የሰሜንና የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የጋምቤላና ከቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የከፊ፣ የቤንች ማጂ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ የዲውሮ ልዩ ወረዳን ጨምሮ፣ ከደቡብ ብሄር ብሄረ ሰቦችና ህዜቦች ክልል የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የሀዲያ፣ የሀላባ ጠምባሮ፣ ከምባታ፣ የወላይታ፣ የጋሞና ጎፊ በአብዛኛው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

በተጨማር ከኦሮሚያ ክልል በቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ እና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ የአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች የሲዲማ ሁለም ዞኖች እና ከሱማሌ ክልል ደግሞ የሲቲና ፊፈን ዞኖች በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ያገኛል።በሌላ በኩል ቀሪዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች መጠነኛ የደመና ሽፋንና ደረቅ ሆነዉ ይቆያለ ተብላል፡፡

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 15 ብር የነበረውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ወጪ በራሱ ፈቃድ ወደ 34 ብር አሳድጎ ተገኘ!

አሶሳ ዩኒቨርስቲ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀመጠውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ዋጋ በሕግ ከተፈቀደለት ውጪ በአንድ ተማሪ ላይ በቀን 19 ብር ጨምሮ ለአንድ ተማሪ በቀን 34 ብር ተመን ሲመግብ እንደነበር በኦዲት መረጋገጡ ተሰምቷል።

ዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስቀመጠውን እለታዊ የተማሪ ምገባ ወጪ ተመን ማለትም 15 ብር የነበረውን፣ ወደ 34 ብር ከፍ በማድረግ በፈቃዱ በማኔጅመንት አጽድቆ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አረጋግጫለሁ ብሏል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ብይን ተሰጠ!

የ“ፍትሕ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ የ100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ብይኑን በአብላጫ ድምጽ ያስተላለፈው በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ነው። ተከሳሽ በቀረበበት ክስ ላይ የሚያቀርበውን የክስ መቃወሚያ ለመስማትም ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 11፤ 2014 ቀጠሮ ሰጥቷል።

የጋዜጠኛ ተመስገንን የወንጀል ክስ በመመልከት ላይ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስትና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ ሰኞ ሰኔ 27፤ 2014 ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፤ ተከሳሽ በጠበቃው አማካኝነት ያቀረበውን የዋስትና ጥያቄ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነበር። የተመስገን ጠበቃ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ የዋስትና ጥያቄውን ያቀረቡት ባለፈው ረቡዕ ሰኔ 22 በዋለው ችሎት ነበር።

ጠበቃ ሄኖክ በወቅቱ ባቀረቡት ማመልከቻ፤ ደንበኛቸው የተከሰሱባቸው ሶስት የወንጀል አይነቶች የዋስትና መብት የማያስከለክሉ በመሆናቸው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ጥያቄ አቅርበው ነበር። የፌደራል ዐቃቤ ህግ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ያቀረባቸው ሶስት ክሶች፤ “ወታደራዊ ሚስጥሮችን ላልተፈቀደለት ሰው ወይም ለህዝብ ገልጿል”፣ “የሀሰት ወይም የሚያደናግር መረጃ አሰራጭቷል”፣ “መገፋፋት እና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ወንጀሎችን ፈጽሟል” የሚል ነው።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ተርኪዬ "የተሰረቀ" የዩክሬን እህል የጫነችውን የሩሲያ መርከብ በቁጥጥር ስር አዋለች!

ተርኪዬ ከዩክሬን ተሰርቋል ያለችውን እህል የጫነችውን የሩሲያ ጭነት መርከብ በቁጥጥር ስር ማዋሏን በአንካራ የኪቭ አምባሳደር አስታወቁ።አምባሳደር ቫሲል ቦድናር በትናንትነው እለት በዩክሬን ብሄራዊ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከተርኪዬ ጋር “ሙሉ ትብብር አለን” ሲሉ ተደምጠዋል።"መርከቧ በአሁኑ ጊዜ በተርኪዬ የጉምሩክ ባለስልጣኖች ተይዛ ወደብ መግቢያ ላይ ቆሟለችም ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

ተርኪዬ የሩሲያ ባንዲራ የያዘችውን ዚቤክ- ዞሊ የጭነት መርከብ የያዘችው ቀደም ሲል ከዩክሬን በቀረበ ጥያቄ መሰረት ነው፡፡በካራሱ ወደብ አቅራቢያ ከባህር ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው መርከቧ፤ እስካሁን ምንም አይነት ግልጽ የእንቅስቃሴ ምልክቶች እንዳልታዩባይትም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የ7ሺ 146 ቶን ክብደት የምትመዝነው መርከብ እጣ ፈንታ የሚወሰነው ፤ መርማሪዎች በዛሬው እለት ተገናኝተው በሚሰጡት ውሳኔ ነው ተብሏል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
እናት ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ለመቋጨት በሚደረገው ድርድር ” የጦርነቱ ግምባር ቀደም ገፈት ቀማሾቹ” የአፋርና አማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት እንዲሆኑ ሲል ጠየቀ፡፡

እናት ”ድርድሩ የሚደገፍ ቢሆንም በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይደረግ!” ሲል ሰይሞ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ”ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት በደስታ የምመለከተው ነው” ብሏል፡፡”ጦርነቱን የተቀሰቀሰው በብልፅግናና ህወሓት የስልጣን ሹኩቻ ነው” የሚለው እናት ” የተዋጋውና ዳፋው የተረፈው ግን ህዝብና መንግስት በመሆኑ ወደአንድ ፓርቲ ለመጎተት የሚደረገው ጥረት አዋጭ እንዳልሆነ ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡” ሲል አሳስቧል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው ” ፓርላማው ሕወሓትን አሸባሪ በሚል ፈርጇል፡፡ምንም እንኳን እንዳለመታደል ሆኖ የአንድ ፓርቲ ውቅርም ቢሆን ድርድሩን መፍቀድ፣ ከሽብርተኝነት መሰረዝ፣ የድርድር ነጥቦችን ማውጣት፣ ብቁና ወካይ ተደራዳሪዎችን መሰየም፣ ሂደቱን በየጊዜው መከታተል፣ ውጤቱንም ማጽደቅ ያለበት ፓርላማው ሆኖ ሳለ የፓርቲ ውሳኔ እንደመንግስት ውሳኔ ተቆጥሮ ዘሎ የማለፍ አዝማሚያ አደገኛ ውጤት ያለው ነው” ብዬ አምናለሁ ብሏል፡፡

ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን በሚል ስድስት ነጥቦችን የዘረዘረው ፓርቲው ” በፌደራል መንግስት ከሚወከሉት በተጨማሪ የጦርነቱ ግምባር ቀደም ገፈት ቀማሾች አፋርና አማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት እንዲሆኑ” ጠይቋል፡፡”የትግራይ ህዝብንም ስሜት በትክክል የሚያንፀባርቁ አካላት እንዲወክሉት” ጥሪ አቅርቧል፡፡”ድርድሩ እንደመንግስት እንዲመራና ፓርላማው ሙሉ ሂደቱን እንዲመራው፣ ውጤቱም ተግባራዊ የሚሆነው በፓርላማው ሲፀድቅ ብቻ እንዲሆን፣ ተደራዳሪዎቹም ከአንድ ፓርቲ ሳይሆን የፓርቲ ውክልና የሌላቸውም ጭምር እንዲካተቱበት” አበክሬ እጠይቃለሁ ብሏል፡፡

እናት ፓርቲ በመግለጫው የዘረዘራቸውን ነጥቦች በተመለከተ መንግስት እንዴት ይመለከታቸዋል በሚለው ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጽህፈት ቤት የስራ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ጥረት ቢደረግም ሊሳካ ባለመቻሉ የመንግስትን ሀሳብ ማካተት አልተቻለም፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት የፍትሕ ሚኒስትሩና የገዢው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ከብልፅግና ስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች በኋላ ”የሰላም ንግግር” እንደሚጀመርና ለዚህም የሚሆኑ አባላት የተዋቀሩበት ቡድን መቋቋሙን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ገዢው ፓርቲ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ድርድሩ እንዲመራ ሀሳብ ሲያቀርብ በእንደራሴው ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ደግሞ የኬንያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታን በአማራጭነት ማቅረቡ እየተዘገበ ነው፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
ከመጪዉ ሀምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለለት የነዳጅ ድጎማ ላይ አሰራሩን ዘመናዊ የሚያደርግ ስርዓት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ማዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በዛሬዉ እለት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ባደረገዉ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ እንደተገለጸው የነዳጅ ድጎማዉ ተጠቃሚ የሚሆኑ 164 ሺህ 343 ተሽከርካሪዎችን የልየታ ስራ መስራቱን ገልጿል። ስርዓቱ ተሽከርካሪዎቹ የሚያገኙትን የነዳጅ ድጎማ ከዘመናዊ ስርዓት ጋር በማስተሳሰር አገልግሎቱን በቀላሉ በቴሌብር እንዲያገኙ ያስችላልም ተብሏል።

በትራንፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ እንደተናገሩት የድጎማዉ ተጠቃሚ የሆኑ ተሽከርካሪች በተሰጣቸው ልዩ የሚስጥር ቁጥር በመጠቀም ድጎማዉን ማግኘት ይችላሉ ብለዋል። ለዚህም አገልግሎት የሚሰጡ 860 ነዳጅ ማደያዎችን ከስርዓቱ ጋር ማስተሳሰር መቻሉም ገልጸዋል።

እስካሁንም በተዘረጋዉ ስርዓት ተጠቃሚ ለመሆን ከ 140 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች በቴሌብር በኩል መመዝገባቸዉም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታዉቀዋል። አዲስ የሚዘረጋዉ ስርዓት በአዲስአበባ ፣ በአዳማ ፣ በባህርዳር ፣ በወላይታ ሶዶ እና በሀዋሳ ከተሞች ተሞክሮ የሚፈለገዉን ዉጤት አይተናልም ብለዋል። የሞባይል መተግበሪያዉ በአማርኛ ፣እንግሊዝኛ ፣ ትግረኛ እና በሶማሊኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

ተሽከርካሪዎች በአመት በአማካይ የሚጓዙት ኪ.ሜ ፣ ተሽከርካሪዎቹ ያስቆጠሩት እድሜ እና ያላቸዉ አቅም ፣ የሚጠቀሙት የነዳጅ አይነት ፣ የነዳጅ ኢኮኖሚዉ እና የሚጓዙበት የመንገድ ሁኔታ ፤ ከግምት ዉስጥ ተደርጎ ድጎማዉ ተግባራዊ እንደሚደረግም ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ዘመናዊ ስርዓቱ ባይዘረጋ ከሚባክነዉ ግዜ በተጨማሪም በወረቀት ስራዎች ተግባራዊ ቢደረግ በየጊዜዉ እስከ ስድስት ሚሊዮን ኮፒዎች ያስፈልግ እንደነበርም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ታጠቅ ነጋሽ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ነዳጅ አከፋፋዮች የሚያገኙትን ነዳጅ ወደ ትግራይ እና ሱዳን ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል ተባለ!

ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያመላልሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የነዳጅ ቦቴ መኪኖች፣ በጥቁር ገበያ ወደ ትግራይ እና ሱዳን ነዳጅ ሲያከፋፍሉ መገኘታቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር ሰሀረላ አብዱላሂ ነግረውኛል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ።ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ከጅቡቲ ተነስተው መድረሻቸውን ሱዳን እና ትግራይ የሚያደርጉ የነዳጅ ቦቴዎች እየበዙ መምጣታቸውን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ማሳወቁን ዘገባው አስነብቧል።

የክልል መንግስታት የሚረከቡትን ነዳጅ በትክክል አለማስመዝገባቸው ችግሩን እንዲሰፋ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን ከሰኔ 24፣ 2014 ጀምሮ የአማራ ክልል ብቻ በትክክል ሲያዝመዘግብ እንደነበረ ተጠቅሷል።ከሰኔ 8 እስከ 19 ድረስ 83 የነዳጅ ማመላለሻ መኪናዎች ከጅቡቲ ተጭነው አማራ ክልል ውስጥ ሊከፋፈሉ ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ በሪፖርቱ መሰረት ከ83ቱ መካከል 33ቱ ብቻ መድረሳቸው ተነግሯል።

[Reporter/Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
“በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ እየገባ ነው”፦ የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ነዳጅ ለመቅዳት በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።በአቅርቦት በኩል ክፍተት እንዳይኖርም ቀድሞ በቀን ይቀርብ ከነበረው 9 ሚሊዮን ሊትር ወደ 10 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ማሳደጉን የባለስልጣኑ የነዳጅ ስታንዳርድ ጥራት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል።

ነዳጅ የጫኑ ቦቴ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ መዘግየት እንዳይፈጠር እና ስርጭቱ ላይ ችግር እንዳይኖር ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።ባለፈው ሳምንት እንደሀገር 200 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ከጂቡቲ ተነስተው 18ቱ ሞጆ ወደብ መድረሳቸውን እና የተቀሩት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው አቶ ለሜሳ ገልጸዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
እገታን በተመለከተ በመንግስት በኩል ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ አለመሆኑ ወንጀሉን አባብሶታል ሲል ኢሰመጉ አስታወቀ!

የህግ ስርዓትን ያልተከተለ እስር እና አስገድዶ መሰወር ወይም እገታን በተመለከተ መንግስት ውትወታ ቢደርሰውም የሚታይ እርምጃ አለመወሰዱ ወንጀሉ እንዲባባስ በር ከፍቷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኞች፣ ተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰቦች ላይ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እስር እየተፈፀመ መሆኑንም ጉባኤው አሳስቧል።

ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከእስር በዋስ የተለቀቀው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱ ቢሰማም ቤተሰቦቹ እና ጠበቃው እስካሁን ያለበትን ማወቅ አልቻሉም ብሏል። በተጨማሪም የደረሰበት ሳይታወቅ አንድ ሳምንት የሞላው ገጣሚ እና የማህበረሰብ አንቂ በላይ በቀለ ወያም እስካሁንምያለበት አለመታወቁን ኢሰመጉ አረጋግጧል።አሁንም የቀጠሉት እገታና ህግን ያልተከተለ እስር ለሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመቻቹ በመሆናቸው መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram 👇🏻

https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
🔵 0991203033 🔵 Fabulous mart
💥የወንዶች እና የሴቶች ፀጉር ማሳደጊያ
📌የወንዶች ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ
👉Imported from 🇺🇸USA🇺🇸
💎የ 1 ወር ዋጋ 999ብር
💎የ 3 ወር ዋጋ 2800ብር
💎የ 6 ወር ዋጋ 4900ብር
📌 ለሴቶች የቆዳ ውበትና የፀጉር ቁመት የሚጨምር
🇺🇸 BIOTIN 🇺🇸 💎2499 ብር
📌Neo hair lotion 💎2950 ብር
📌DERMAROLLER
👉 የቆዳን ቀዳዳ በመክፈት የፀጉርን ሴል የሚያነቃቃ
👉ለተሸበሸበ ቆዳ ጥርት ያለ ገፅታን የሚሰጥ
price💎950 birr 🚛free delivery 🚛🚛
☎️+251991203033 & 0904132709
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ

እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።

እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883

https://tttttt.me/meritibe

👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
ኡጋንዳ ለህወሓት ኃይሎች ሥልጠና እና ድጋፍ ትሰጣለች የሚለውን ክስ አስተባበለች!

ከአንድ ዓመት በፊት አንስቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ጋር ጦርነት ውስጥ የገባውን ህወሓትን የኡጋንዳ ሠራዊት ሥልጠና እና ሌሎች ድጋፎችን እየሰጠ ነው የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው ምላሹ የወጣው።ይህ ኡጋንዳ ለህወሓት ድጋፍ እያደረገች ነው የሚለው ዘገባ በኢትዮጵያውያን የበይነ መረብ ገጾች ላይ ካለፈው ግንቦት ወር ወዲህ በመውጣት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

የኡጋንዳ ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ብርጋዲየር ፌሌክስ ኩላዬጊዬ እሁድ ዕለት በሠራዊታቸው ላይ የቀረበውን ክስ በማስመልከት በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ ኡጋንዳ የኢትዮጵያን ሰላም ለማናጋት ጥረት እያደረገች ነው የሚለው ክስ ፍጽም ፈጠራ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።ይህንን ክስ የተመለከተው ዝርዝር ጽሁፉ መቀመጫው ኒውዚላንድ በሆነ የበይነ መረብ ገጽ ላይ ባለፈው የወጣ ሲሆን፣ ጽሁፉ ህወሓትን በተመለከተ የሚካሄደውን ሥራ የሚያስተባብሩ ናቸው የተባሉ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና ሌሎች የደኅንነት ኃይሎች አባላትን ስም ዝርዝር ይዟል።

ሥልጠናውም በማዕከላዊ ኡጋንዳ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ማሳካ ወረዳ ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጾ ነበር።የወጣው ሰነድ ጨምሮ እንደሚያመለክተው ከ4,000 በላይ የህወሓት ተዋጊዎች ኡጋንዳ ውስጥ በሚገኙ በአራት የማሰልጠኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለወታደራዊ ሥልጠና መግባታቸውን አመልክቷል።ከዚህ ባሻገር ይህ ሥልጠና ኡጋንዳ ውስጥ ይካሄድ እንጂ በአሜሪካ እና በግብፅ የሚደገፍ መሆኑንም በሰነዱ ላይ ተገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.bbc.com/amharic/articles/cld2g41ygyzo
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ጋር ባለፉት አራት ወራት ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ሥራዎች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።በዚህም መንግሥት ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ለኮሚሽኑ አባላት አረጋግጠውላቸዋል።ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ባለፉት 4 ወራት የሰራቸውን አጠቃላይ ስራዎች ማብራሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አሠጣጥን አስመልክቶ መግለጫ ሠጥቷል።የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሙላው አበበ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ገልጸው ፈተናውም ከሰኔ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም ይሠጣል ብለዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በግል የስምንተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ከ359 ሺሕ በላይ ተማሪዎች በ5 ሺሕ 395 ትምህርት ቤቶች ላይ ክልላዊ ፈተና እንደሚወስዱም ገልጸዋል።ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ከ10 ሺሕ በላይ መምህራን እንደሚሳተፉና የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት የጸጥታ አካላት ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ተማሪዎች ፈተናውን በተረጋጋ እና ሥነምግባር በተሞላበት ሁኔታ እንዲፈተኑ መምህራን፣ ወላጆች እና የጸጥታ አካላት ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል። በፈተና ወቅት ኩረጃ ሊያስከትል የሚችለውን ቅጣት በተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ አብሮ የወረደ በመሆኑ ተማሪዎች ወደ ቅጣት እንዳይገቡ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት፡፡የወላጅ መምህር ኅብረት አባላት ፈተናው ታሽጎ ፈተና ጣቢያው ላይ መድረሱን እና በተማሪዎች ፊት መከፈቱን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማሳሰቡን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
"የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው።

በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል።

በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን።"

Via:- ጠ/ም አብይ አህመድ
@Yenetube @Fikerassefa
ሸዋሮቢት ላይ ሰዎች መገደላቸው

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ ውስጥ የመንግሥት ኃይሎች የወለጋውን ጭፍጨፋ በተቃወሙ ዜጎች ላይ በወሰዱት እርምጃ ከስምንት እስከ 12 የሚገመቱ ንጹሐን ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬሌ ተናገሩ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በበኩሉ ከሰልፉ ጋር በተያያዘ አባላቱ መታሰራቸውን አመልክቷል።

Via DW
@Yenetube @Fikerassefa